ጀርመን ቡንደስሊጋ 2012/13

ስፖርት - Sport related topics

ጀርመን ቡንደስሊጋ 2012/13

Postby ቲኪ_ታካ » Tue Aug 21, 2012 9:39 pm

ሰላም እግርኳስ አፍቃርያን

ይህችን ገጽ ከጀርመን ፉትቦል ጋ የተያያዙ ጉዳዮችን እንድንወያይበት ከፍቻለሁ:; እንግዲህ ብቅ እያላቹ እንድጻተፉ እጋብዛለሁ::

የዘንድሮ ቡንደስሊጋ የፊታችን አርብ ይጀመራል:: በዚሁ በመክፈቻው ቀን የአምናው ባለጥንድ ድል ቦሩሽያ ዶርትመንድ በሜዳው ቬርደር ብረመንን ያስተናግዳል:: ይህ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል:: በአባቱ ኢትዮጵያዊ የሆነው ቴዎዶር ገብረስላሴን ለመመልከትም ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልናል:: ዶርመንድ ቁልፍ ተጭዋቹ ቺኒጂ ካጋዋን ለ ማንቸስተር ዩናይትድ ሸጦ በምትኩ የአምና የጀርመን ፉትቦል ኮከብ ተብሎ የተመረጠውን ማርክ ሮይስ ን አስፈርመዋል::

በተረፈ ቅዳሜ እለት ባየር ሙኒክ ከሜዳው ውጪ በመጓዝ ለመጀመርያ ግዜ በቡንደስሊጋው ለመሳተፍ የበቃውን spvgg greuther fürth የተሰኘ ቡድንን ይገጥማል:: ባየርኖች በታም ተርበዋል:: ለተከታታይ ሁለት አመት በከባድ ተቀናቃኛቸው ዶርትመንድ ክፉኛ የተዋረዱበት ሁኔታን ለመቀልበስ ዘንድሮ ሲዝንን ቆርጠው ተነስተዋል::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Tue Aug 28, 2012 5:55 pm

ቡንደስሊጋው እንደተጠቀሰው ባለፈው አርብ ሲጀመር ቦሩስያ ዶርትሙንድ በሜዳው ቬርደር ብሬመንን 2-1 አሸንፏል:: ለብሬመን አንዷን ጎል ያገባው ቴዎዶር ገብረሰላሴ ነበር:; እንግዲህ ገብረስላሴ ለአዲሱ ሲዝን የመጀመርያ ጎላቸውን ቀድሶላቸዋል:: ቡድኑም ጥሩ ቡድን መሆኑን ባሳዩት ፉክክር አስመስክረዋል:: በባየርንም በኩል የመክፈቻዋን ጎል ያገባላቸው አዲሱ ተጭዋቻቸው ማርኮ ሮይስ ነበር:: ሮይስ ዶርትሙንድ ተወልዶ ያደገ ከመሆኑም በላይ ባየርን ሙኒኮች ሲፈልጉት ጥያቅያቸውን ውድቅ አድርጎ ለአደገበት ከተማ ከለብና የባየርን ሙኒክ ቀንደኛ ተቀናቃኝ ቦሩሽያ ዶርትሙድ የፈረመበት ሁኔታ ትልቅ ዜና ሆኖ እንደነበር ትዝ ይለናል:: ምክንያቱም ካላቸው የኢኮኖሚ ጥንካሬ አንጻር ባየርኖች እየፈለጉት ለሌላ የጀርመን ክለብ መፈረም እምብዛም ያልተለመደ ነገር ነበርና ነው:: የሮይስ ማርዮ ጎትዘ እና ሎዋንዶውስኪ አክሲስ በዩሮፕ በጉጉት የሚጠበቅ አስፈሪ ኮምቢኔሽን ነው:: እንግዲህ ወደተግባር ይቀይሩታል ወይ ነው ጥያቄው::
ባየርን ሙኒክ furth የሚባልን ክለብ በቀላሉ 3-0 አሸንፏል:; ሰሞኑን ከክለቡ ጋ ተያይዞ ያለው ትልቁ ዜና ስፔናዊው ሀቪ ማርቲኔዝን ያስፈርሙታል ወይስ አያስፈርሙትም የሚለው ነው:: እንግዲ በጋው የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋ 2 ቀን ቀርቶታል የሚሆነውን እናያለን:: በተረፈ ስዊትዘርላንዳዊው ሻቂሪን ከባዝል ብራዚላዊው ዳንቴን ከ ሞንቻግላድባክ እና ክሮኤሽያዊው ማንድዙኪችን ከዎልፍዝበርግ አስፈርመዋል:: ማንድዙኪች በመክፈቻ ጨዋታቸው አንድ ጎል አስቆጥሮ የጎል አካውንቱን ከፍቷል:: የቡድኑ ስፖርቲግ ዳይሬክተር ዝነኛው የቀድሞ የጀርመን ተጭዋች ማቲያዝ ሳመር ነው:: ሳመር ባየርንን ባዲስ እያቀናጀና ቡድኑ ማራኪ ፉትቦል እንዲጫወት ጥርጊያ መንገዱን እያመቻቸው እንደሆነ ነው የሚሰማው::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests