ሰላም እግርኳስ አፍቃርያን
ይህችን ገጽ ከጀርመን ፉትቦል ጋ የተያያዙ ጉዳዮችን እንድንወያይበት ከፍቻለሁ:; እንግዲህ ብቅ እያላቹ እንድጻተፉ እጋብዛለሁ::
የዘንድሮ ቡንደስሊጋ የፊታችን አርብ ይጀመራል:: በዚሁ በመክፈቻው ቀን የአምናው ባለጥንድ ድል ቦሩሽያ ዶርትመንድ በሜዳው ቬርደር ብረመንን ያስተናግዳል:: ይህ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል:: በአባቱ ኢትዮጵያዊ የሆነው ቴዎዶር ገብረስላሴን ለመመልከትም ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልናል:: ዶርመንድ ቁልፍ ተጭዋቹ ቺኒጂ ካጋዋን ለ ማንቸስተር ዩናይትድ ሸጦ በምትኩ የአምና የጀርመን ፉትቦል ኮከብ ተብሎ የተመረጠውን ማርክ ሮይስ ን አስፈርመዋል::
በተረፈ ቅዳሜ እለት ባየር ሙኒክ ከሜዳው ውጪ በመጓዝ ለመጀመርያ ግዜ በቡንደስሊጋው ለመሳተፍ የበቃውን spvgg greuther fürth የተሰኘ ቡድንን ይገጥማል:: ባየርኖች በታም ተርበዋል:: ለተከታታይ ሁለት አመት በከባድ ተቀናቃኛቸው ዶርትመንድ ክፉኛ የተዋረዱበት ሁኔታን ለመቀልበስ ዘንድሮ ሲዝንን ቆርጠው ተነስተዋል::