ካዲሱ የዋይኒ ሩኒ መጽሀፍ በጥቂቱ::

ስፖርት - Sport related topics

ካዲሱ የዋይኒ ሩኒ መጽሀፍ በጥቂቱ::

Postby ክቡራን » Mon Oct 08, 2012 4:56 pm

ሩኒ በቅርቡ ‹‹My decade in the premier league›› በሚል ርዕስ ያለፉትን 10 የእግር ስ ህይወቱን የሚያስቃኝ አዲስ መፅሀፍ በቅርቡ ለንባብ አብቅቶ ይገኛል፡፡ ከዚህ ውስጥ የተወሰነውን ያንብቡት፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶን በተመለከተ
በ2006 የአለም ዋንጫ(የፖርቹጋልና እንግሊዝ ጨዋታ) ላይ በተፈጠረው አጋጣሚ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር አብረን መጫወት እንደማንችል ጋዜጦች ወሰኑ፡፡ በዚያ የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ላይ በተከላካያቸው ሪካርዶ ካርቫልሆ ጋር አለመግባባት ተፈጠረና ጥፋት ፈፀምኩበት፡፡ መጥፎ ቢመስልም አጋጣሚ ነበር፡፡ ጥፋተኛ አለመሆኔን ለአልቢትሩ ለመግለፅ ስሞክር ሮኒ(ሮናልዶ) ካርድ እንደሚገባኝ ለዳኛው በምልክት ይገልፅ ጀመር፡፡ አልቢትሩም ካርዳቸውን መዘዙብኝና ከሜዳ ተሰናበትኩ፡፡

በቃ! ውድድሩ ለእኔ ተፈፀመ፡፡ ወደመልበሻ ቤት ሳመራ ለውሳኔው ሮናልዶን መውቀስ እንደሌለብኝ ተረድቼ ነበር፡፡ ሃገሩ ጨዋታውን እንድታሸንፍ ጥረት በማድረጉ ወቀሳ አይገባውም፡፡ ከዕረፍት በፊት አስመስሎ በመውደቁ ቢጫ ካርድ እንዲመለከት ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ ሲለዚህ እኔም እንደርሱ ሁሉ መጥፎ ሆኙ ነበር፡፡ ካርዱን ከተመለከትኩ በኃላ ግን ሮናልዶ ወደሜዳው ጠርዝ ዞሮ ጨዋታውን በቴሌቪዥን ለሚመለከተው ህዝብ የዓይን ጥቅሻ አሳየ፡፡ ይህ መጥፎ ድርጊት ነበር፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ እቺን ይጫኑ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7963
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest

cron