ብሄራዊ ቡድናችን!!

ስፖርት - Sport related topics

ብሄራዊ ቡድናችን!!

Postby ባርናባስ_23 » Tue Oct 09, 2012 3:43 pm

ሰላም ውድ ስፖርት አፍቃሪ ወገኖቼ!
እሁድ የእግር ኩዋስ ቡድናችን የሱዳን አቻውን አዲስ አበባ ላይ ይገጥማል
2-0 በላይ ካሽነፈ ለአፍሪካ ዋንጫ ክ30 አመት በሀላ ለመጀመሪያ ግዜ ያልፋል ማለት ነው::እኔ እሁድ በጣም ረዝሞብኛል :( ይህ በእንዲህ እናዳለ እኔን 2 ነገሮች አሳስቦኛል 1ኛ-ምድረ ሀብታም ካሽነፉ የብር ቁልል ቃል እየገባ በመሆኑ ልጆቹ ትክክለኛ ችሎታችውን በጭንቀት ሜዳ ሲገቡ ያጣሉ የሚል ሲሆን
2ኛው-ህዝቡ: ራዲዮ እና ጋዜጣው ሌላ ወሬ ትቶ ይህንን ሲያውጣ እና ሲያወርድ ነው ሚወለው ይህም ልጆቹ ላይ ጫና መፍጠሩን ከወደ ሽገር በስፊው እየተነገር ነው
እኔ በበኩሌ የቀረውን 4 ቀን ከፍተኛ የስነልቦና ባለሞያዎች
ቢመክሩዋቸው መልካም ነው እላለሁ::

መልካም እድል ለብሄራዊ ቡድናችን!!!!!
It always seems impossible until its done
ባርናባስ_23
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 305
Joined: Sun May 31, 2009 2:00 pm

Postby ራስብሩ » Thu Oct 11, 2012 11:38 am

ጤና ይስጥልኝ ወንድሜ ባርናባስ
እሁድ ረዝሞብኛል እንዳልከው እኔም ረዝሞብኛል:
ነገር ግን ለውጤቱ ያለህን ስጋት አስመልክተህ ከሰጠሀቸው ሁለት ምክንያቶች በተለይ የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ሀገራችን እጅግ ሊለመድና ሊበረታታ የሚገባው ጉዳይ ከመሆኑም በላይ ፉትቦሉን ከሚያሳድጉት ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ነው እላለሁ ::
ስለዚህ በዚያ በኩል ሊያሰጋህ አይገባም ምናልባት ውጤቱ ከችሎታ ብቃት ጋር ይጠበቃል ምክንያቱም
የሱዳንን ብሄራዊ ቡድን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ እንዳየነው ቀላል ግምት የምንሰጠው አይደለም::
ዋናው ነገር ግን ለተጫዋቾቻችን የሚገባላቸው ቃል ሞራላቸውን የሚያጠናክርና በጥሩ ጉልበት እንዲጫወቱ የሚረዳቸው ነው ብዬ አምናለሁ ::
በርግጥ አንተ የህዝቡ ትልቅ ግምትና የዜናው ጋጋታ ምክንያት የሀሳብ ጫና ይበዛባቸዋል እንዳልከው እኔ ደሞ ይሄ ደስ ሊያሰኛቸው እንጂ ሊያስጨንቃቸው አይችልም ነው የምለው::
ዛሬ የሁለቱም አሰልጣኞች አስተያየት ተሰምቷል ሁለቱም እናሸንፋለን ብለዋል : ዋልያዎቹ ያንን ለ31 ዓመታት ያልተደፈረ በር ዕሁድ ይከፍቱታል ብዬም አምናለሁ::
አስተያየቴ የተቃውሞ አለመሆኑን እንደምትረዳልኝ ተስፋ አለኝ ::
ድል ለዋልያዎች
አክባሪህ
ራስብሩ
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby geremew » Sat Oct 13, 2012 2:58 am

ሰላም ባርናባስ:
ልክ ነህ 2-0 ካሸነፍን እናልፋለን:: ስሌቱ በዛ ብቻ አያበቃም:: 3-1 እና 4-2 ውጤትም ያሳልፈናል:: ሱዳን ተከላክሎ እንደሚጫወት እያሰቡ አጥቅተን ነው የምንጫወተው በማለት ይናገራሉ:: ሱዳን እድሉን የሚያሰፋው ጎል ባገባ ቁጥር ስለሆነ ብዙ ይከላከላል ብዬ አላስብም:: ሀይላቸውን ቆጥበው በመልሶ ማጥቃት እንደሚጠቀሙ እሙን ነው::
ፌዴሬሽኑ የስነልቦና ጉዳይ ያሳሰበው ይመስላል:: ኮሜድያኖችን ተጠቅመው ዘና እንዲሉ እያደረጉ ነው:: በደጋፊው እርዳታ ጥሩ ውጤት እናያለን የሚል እምነት አለኝ::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Oct 13, 2012 4:09 am

ሰላም ባርናባስ_23 : ራስ ብሩ እና 'geremew' :-

'በወንዶች እግር ኳስ ላለፉት 31 ዓመታት ምንም ዓይነት የረባ ውጤት ለማስመዝገብ ያልተቻለበት ዋናው ሚሥጢር ለምን ይሆን?' ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው:: በእኔ በኩል ለውጤቱ መበላሸት ብዙ ችግሮች ነበሩ ብዬ አምናለሁ :- ከተጫዋቾች ተክለ ሰውነት ጀምሮ እስከ ስፖርት አመራሩ ድረስ :: እኒህ ችግሮች አሁንም አሉ :: ነገር ግን ካለፉት ጊዜያት በተለየ በአሁኑ ቡድን ውስጥ የምናየው አንድ መሻሻል አለ :- እርሱም ጎል ለማግባት ድፍረቱና ችሎታው ያላቸው አጥቂዎች አግኝተናል :: ሣላዲን ሰዒድ : ጌታነህ ከበደ : አዳነ ግርማ : ኡመድ ኡክሪ : ሌሎችም ... እኒህ ከአዲሱ ትውልድ የፈለቁ ጥሩ አጥቂዎች ናቸው :: ስለሆነም እንደድሮው ውጭ አገር ሄደው በጎል ክምር ተሸንፈው የሚመለሱ ሣይሆኑ ጎል ቢገባባቸውም እነርሱም ጎል አግብተው : ሲችሉ አሸንፈው : ቢሸነፉም በጠባብ የጎል ልዩነት ግጥሚያቸውን የሚጨርሱ ሆነዋል :: በዚህ ከቀጠሉ እንኳን ዝብርቅርቁ የወጣውን የሱዳንን ብሔራዊ ቡድን ይቅርና ለታሪካዊ ባላንጣችን ለግብፅ ቡድንም የሚመለሱ አይሆኑም ::

መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን :!: :!: :!:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ባርናባስ_23 » Sun Oct 14, 2012 12:03 pm

ሰላም ወግኖቼ!
ራስ ብሩ geremew ተድላ ሀይሉ እንደምን ሰነበታችሁ?
ጦርነቱ ሊጀምር 2 ስአት ነው የቀርው:: እኔ ዝምብዬ ስገምት 3-1 ምናሽንፍ ይመስለኛል:: እንደው ከምን ተነስትህ ?
ለሚለኝ ሰው እነሆ 1- ሳላዲን ከህመም አገግሞ እንደሚሰልፍ ሰማሁ እንድ በሉ
2-ታዳጊ ቡድናችን ቱኒስያን ሀገሩ ላይ 3-0 ማሽነፉ ትልቅ የሞራል ብርታት እንድሚሆን ጥርጥር የለውም
በመጨረሻም አርብ እለት ማታ በተደረገላቸው ልዩ ዝግጅት ልጆቹ ላይ ከፍተኛ ወኔ እና እልክ ተላብሰው እንዲጫወቱ ሚያስችሉ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደነበሩ ቦታው ከነበር ወዳጄ ስምቻለሁ :: ከነዚህ ዝግጅቶች በተለይ አባት አርብኞች ባንዲራ ለደጉ በሚያስርክቡበት ስነስረአት ልዩ ስሜት የፈጠረ እንደነበር እና ኢትዮፒያ የሚለው የጥላሁን ገሰሰ ዘፈን አብሮ ይሰማ በነበረበት ግዜ የእልክ እንባ አይናችው ላይ ይታይ ነበር::
ድል ለኢትዮፒያ ቡድን!!!!!!
It always seems impossible until its done
ባርናባስ_23
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 305
Joined: Sun May 31, 2009 2:00 pm

Postby geremew » Sun Oct 14, 2012 4:22 pm

ሰላም የስፖርት አፍቃርያን:
ዛሬ በቡድናችን ውጤት ከመጠን በላይ ተደስቻለሁ:: በዘመኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላየሁ ማለቴ ነው:: ይህ በቻይንኛ እድሜዬ 29 ነው ለማለትም ጭምር ነው::

ጨዋታው ባጭር ቃል ሲገመገም የሰራ (ያጠቃ) ያሸንፋል:: ሱዳንን ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ብቻ ሳይሆን ሱዳን እራሱም ነው:: 90 ደቂቃ ሙሉ ለመከላከል ወስነው ወደሜዳ ሲገቡ ኢትዮጵያ እንድታጠቃቸው ፈቅደው ነበር:: ከሁለቱ ጎሎች መቆጠር በኍላ ሱዳኖች ያሳዩት እንቅስቃሴ አስቀድመው ቢያሳዩ ኖሮ ውጤቱ ይቀየር እንደነበር መገመት ቀላል ነው:: ሊያልቅ ሲል ተሳቅቄ ስለነበር እስካሁን ያ ስሜት ውስጤ አለ:: ቡና ጠጥቼ ላስወጣው::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Oct 15, 2012 5:15 am

geremew wrote:ሰላም የስፖርት አፍቃርያን:
ዛሬ በቡድናችን ውጤት ከመጠን በላይ ተደስቻለሁ:: በዘመኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላየሁ ማለቴ ነው:: ይህ በቻይንኛ እድሜዬ 29 ነው ለማለትም ጭምር ነው::

ጨዋታው ባጭር ቃል ሲገመገም የሰራ (ያጠቃ) ያሸንፋል:: ሱዳንን ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ብቻ ሳይሆን ሱዳን እራሱም ነው:: 90 ደቂቃ ሙሉ ለመከላከል ወስነው ወደሜዳ ሲገቡ ኢትዮጵያ እንድታጠቃቸው ፈቅደው ነበር:: ከሁለቱ ጎሎች መቆጠር በኍላ ሱዳኖች ያሳዩት እንቅስቃሴ አስቀድመው ቢያሳዩ ኖሮ ውጤቱ ይቀየር እንደነበር መገመት ቀላል ነው:: ሊያልቅ ሲል ተሳቅቄ ስለነበር እስካሁን ያ ስሜት ውስጤ አለ:: ቡና ጠጥቼ ላስወጣው::


ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ሰላም 'geremew' :-

እንኳን ደስ ያለን :: ጨዋታውን በቀጥታ ለመከታተል ባልታደልም ውጤቱን ስሠማ ግን የተሠማኝ ደስታ በዝብርቅርቅ ስሜቶች የተሞላ ሆኖብኛል :: እስኪ እንደጀመሩት በዋንጫው ውድድርም ለፍሬ ያብቃቸው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Oct 15, 2012 6:32 am

በድጋሚ ሰላም :-

ለታሪካዊነቱ ... ኢትጵያ2 - ሱዳን 0

ምንጮች :-

1 ..... የመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ ::

2 ..... የሁለተኛው ግማሽ ጨዋታ ::


ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ገደል » Mon Oct 15, 2012 1:23 pm

ኢትዮጵያ ክ1972 (1968 በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ጀምሮ እራሱዋ ኢትዮጵያ ከጀመረቺው የአፍሪካ ዋንጫ ተለይታ ቆይታለች:: ይህም የሆነው 2 ጊዜ በመንግሥት አቅም እጦት ምክንያት ኢትዮጵያ ለማጣርያ ውድድር ባለመቅረቡዋ: አንድ ጊዜ ዲስኩዋሊፋይድ ሆና (2010) አራት ጊዜ ማጣርያውን ማለፍ ባለመቻሉዋ ነበር:: : አሁን ከ 31 አመት በሁዋላ ለዋንጫው ለመካፈል መብቃቱዋ እሰየው ነው::
ታድያ እንግዲህ ጥያቄው እንዚህ ልጆች አሁን የአፍሪካ እግር ኩዋስ ከደረሰበት ደረጃ ጋር ሲነጻጸሩ እንዴት ናቸው? በሰውነት ብቃት በቴክኒክ ብስለት በስነአእምሮ ዝግጅት ከደቡብና የምእራብ አፍሪካ ሀገሮችን ይቕቕማቸው ይሆን? ወይስ የጎል ቁዋት ሆነው ይመለሳሉ? ይህንን ሀገሪቱ ትኩረት ሰጣ የበሰለና ልምድ ያለው አስልጣኝ በማቅረብ: ልጆቹን ቀደም ብሎ ሰብስቦ በማዘጋጀት በርካታ የልምምድ ግጥሚያዎች በማድረግ: የስነአእምሮ ቴራፒ በመስጠት ሊያዘጋጁዋቸው ይገባል:: አለዚያ ውጠቱ አሳፋሪ ሊሆን ይችላል::
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Postby ዞብል2 » Tue Oct 16, 2012 1:13 am

1976(በኢትዮጵያ1968) ወይስ በገደልኛ የዘመን አቆጣጠር 1972(1968) የሚሆነው :?: :P

ዞብል ከአራዳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1997
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby geremew » Wed Oct 24, 2012 9:12 pm

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ : ናይጄርያ : እና : ከቡርኪና ፋሶ ጋር ተደልድልዋል:: ከሱዳን ጋር ሲተያይ ጠንካራ ውድድር እንደሚጠብቃቸው ግልጽ ነው:: ካሁኑ ጠንክረው ቢሰሩ የማያሳፍር ውጤት ያስመዘግባሉ:: በርቱ::
geremew
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 285
Joined: Tue Dec 28, 2004 8:43 pm
Location: united states

Postby ገደል » Mon Oct 29, 2012 5:12 pm

በእኔ ይሁንብህ ይህን ሰውነት እና ይህን ሞራል ይዘው የትም አይደርሱም:

geremew wrote:የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ : ናይጄርያ : እና : ከቡርኪና ፋሶ ጋር ተደልድልዋል:: ከሱዳን ጋር ሲተያይ ጠንካራ ውድድር እንደሚጠብቃቸው ግልጽ ነው:: ካሁኑ ጠንክረው ቢሰሩ የማያሳፍር ውጤት ያስመዘግባሉ:: በርቱ::
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests