የኢትዮጵያ ቡድኖች ወንዱም ሴቱም 5 ለ 1 ተገረፉ

ስፖርት - Sport related topics

የኢትዮጵያ ቡድኖች ወንዱም ሴቱም 5 ለ 1 ተገረፉ

Postby ገንዳው » Tue Oct 30, 2012 5:15 am

Here we go again ! አለ ፈረንጅ ...... 3 ለ 0 አሸነፈ ተብሎ የተጨፈረለት የ ታዳጊው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቱኒዚያው አቻው 5 ጎል ቃመ:: እረ እንዲያው በስሜት ነው ወይ የአገራችን እግር ኳስ አደገ ሚባለው .... ባለፈው ሱዳን ላይም ትልቁ /ዋሊያ ቡድን 5 ተጠቅጥቆበት ነበር ዞሮ ዞሮ ዕድሜ ለአዲስ አበባ ሕዝብ ላንቃው እስኪቀደድ ባንድ ድምጽ ቢያቧዋርቅ ሱዳኖች ሽንታቸውን በቁምጣቸው አንጠባበጠቡ እንጂ ከ 2 በላይ ጎል አልለቀቅቁም ቅቅቅ አሁንም ሳውዝ አፍሪቃ ላይ ለሚደረገው ውድድር መንግሥት አንድ 500 የሚያህለውን ደህና የሚጮህ ከቢራና ከቡና ደጋፊዎች መልምሎ ካልወሰደ በቀር መሳቂያ እንደምንሆን አትጠራጠሩ:: :lol: ዛሬ ደግሞ <ሉሲዎቹ> <ሴት አናብስቶቹ> በአይቮሪኮስት ማጂክ ቁጥራቸውንያው አምስቷን ሳትቀነስ ቅመዋል::

እረ ባካችሁ እስቲ ሪለስቲክ እንሁን:: ያለን ዐለም አቀፍ ስታዲየም ጃንሆይ ያሰሩት ፓርኪንግ የለለው ዘሪያው በሕዝብ ሽንት ቤት የተከበበ አሳፋሪ ነው:: ይህ ራሱ ትልቅ ኢምፓክት አለው:: ዘመናት ተቆጠሩ ? እግር ኳስ ለማሳደግ ምን ተደረገ? ? ምንም ! እግዜር ይይላችሁ ......
ገንዳው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 334
Joined: Thu Dec 23, 2004 3:46 am
Location: united states

Re: የኢትዮጵያ ቡድኖች ወንዱም ሴቱም 5 ለ 1 ተገረፉ

Postby ሲምኖ » Tue Oct 30, 2012 2:05 pm

ለተቀማጭ አፉ ምላጭ ይባላል አንተ ምን ያህል የሞራል ብቃት ኖሮህ ነው ይህን አይነት እንዝላልነት የትሞላበት አስተያየት የምትሰጠው:: በመጀምሪያ ዋልያዎችም ሆን ቀይ ቀበሮዎች (The Red Jackal) 5 ለ 0 አልተሸነፉም: ዋልያዎች ሱዳን ላይ 5 ለ 3 እና ወጣቶቹ 5 ለ 1 ነው እነሱ ያስቆጠሩትን ጎል ማጣጣልህ ጤነኛ አስተያየት አይደለም:: ሉሲዎች ወርቅ የሆነ ጨዋታ ተጫውተው ሜዳው ለጨዋታ አመቺ ባለመሆኑ ኳስ ለመግፋት በጣም አስቸጋሪ እና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ ነበር ሆኖም ግን አገራቸውንና ህዝባቸውን ሊያኮሩ የቻሉትን አድርገዋል በዚህም ትልቅ ክብር ይገባቸዋል:: እኔ በበኩሌ በጣም ኮርቸባቸዋለሁ ሲያሸንፉ ልዘል ሲሸነፉ ልሰድባቸው እንዳንተ አይደለሁም:: ሁሉንም በፀጋ መቀበል ግድ ይላል እዚህ በሰለጠነው አለም ስታዲየም ኳስ ለማየት አጋጣሚውን ብታገኝ ደጋፊዎቹ ቡድናቸው ሲያሸንፍ ተደስተው ሲሸነፍ በማጨብጨብ እና በማበረታታት ተጫዋቾቹን ይሸኛሉ:: የሚሳደቡትም የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾችን ወይም ደጋፊዎችን ነው:: ተማር :!:

ገንዳው wrote:Here we go again ! አለ ፈረንጅ ...... 3 ለ 0 አሸነፈ ተብሎ የተጨፈረለት የ ታዳጊው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቱኒዚያው አቻው 5 ጎል ቃመ:: እረ እንዲያው በስሜት ነው ወይ የአገራችን እግር ኳስ አደገ ሚባለው .... ባለፈው ሱዳን ላይም ትልቁ /ዋሊያ ቡድን 5 ተጠቅጥቆበት ነበር ዞሮ ዞሮ ዕድሜ ለአዲስ አበባ ሕዝብ ላንቃው እስኪቀደድ ባንድ ድምጽ ቢያቧዋርቅ ሱዳኖች ሽንታቸውን በቁምጣቸው አንጠባበጠቡ እንጂ ከ 2 በላይ ጎል አልለቀቅቁም ቅቅቅ አሁንም ሳውዝ አፍሪቃ ላይ ለሚደረገው ውድድር መንግሥት አንድ 500 የሚያህለውን ደህና የሚጮህ ከቢራና ከቡና ደጋፊዎች መልምሎ ካልወሰደ በቀር መሳቂያ እንደምንሆን አትጠራጠሩ:: :lol: ዛሬ ደግሞ <ሉሲዎቹ> <ሴት አናብስቶቹ> በአይቮሪኮስት ማጂክ ቁጥራቸውንያው አምስቷን ሳትቀነስ ቅመዋል::

እረ ባካችሁ እስቲ ሪለስቲክ እንሁን:: ያለን ዐለም አቀፍ ስታዲየም ጃንሆይ ያሰሩት ፓርኪንግ የለለው ዘሪያው በሕዝብ ሽንት ቤት የተከበበ አሳፋሪ ነው:: ይህ ራሱ ትልቅ ኢምፓክት አለው:: ዘመናት ተቆጠሩ ? እግር ኳስ ለማሳደግ ምን ተደረገ? ? ምንም ! እግዜር ይይላችሁ ......
ሲምኖ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 124
Joined: Wed Oct 12, 2011 11:46 pm

Postby ገደል » Tue Oct 30, 2012 5:47 pm

ሲምኖ......ምክንያት ለመፍጠር ጊዜህን አታባክን:: እግር ኩዋስ በኢትዮጵያ የሞተ እስፖርት ነው::
እግር ኩዋስን ላማጠንከር መጀመርያ ብቃት ያለው ኢንስቲቲዩት አስፈላጊ ነው:: ከዚያ በሁዋላ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ብቃት ባላቸው ኮቾች እየሰለጠኑ በትምህርት ቤቶች መካከል በየደረጃው (ሰከንደሪ እና ኤለመንተሪ) ስታንዳርድ ግጥሚያ ማካሄድ አለባቸው:: የኮች እጥረት የለም::የቀድሞ የፕሪሚየም ሊግ እና የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለትምህርት ቤት ተጫዋቾች ኮች መሆን ይችላሉ::
በቀድሞ ጊዜ ማለት በ ሀይለስላሴ ጊዜ: የተደራጀ የትምህርት ቤት ግጥሚያዎች ነበሩ:: ለ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተሰለፉት ለምሳሌ መንግስቱ ወርቁ: ጌታቸው ወልዴ ግርማ ዘለቀ ሌሎችም ከትምህርት ቤት ግጥሚያዎች ተመልምለው በ ፕሪምየር ሊግ ተጫውተው ነው ለብሄራዊ ቡድን የበቁትና ያንን ለ 50 አመት ያልተደገም ውጠት ያስመዘገቡት::

ብሄራዊ ቡድን በህይሆይታ ግጥሚያ ሲደርስ ከያለበት የሚሰበሰብ ቡድን አይደለም:: ሙሽራ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ነገር::
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Re: የኢትዮጵያ ቡድኖች ወንዱም ሴቱም 5 ለ 1 ተገረፉ

Postby ገንዳው » Wed Oct 31, 2012 3:23 am

ሲምኖ wrote:. . . . ሉሲዎች . . . ሜዳው ለጨዋታ አመቺ ባለመሆኑ ኳስ ለመግፋት በጣም አስቸጋሪ እና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ ነበር

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ዐመት ከአምስት ቀንና ከአምስት ሰዐት ያስቃል:: :lol: :lol: :lol: የዐመቱ ኮሜዲ ብየዋለሁ ይሄንን ..... ፌስ ቡክ ላይ ፖስት አረገዋለሁ :idea:
ገንዳው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 334
Joined: Thu Dec 23, 2004 3:46 am
Location: united states

Postby ሲምኖ » Wed Oct 31, 2012 9:51 pm

ሰላም ገደል

በሀሳብህ እስማማለሁ የአገራችን ባለስልጣናት ለስፖርት ያላቸው አስተያየት በጣም ያነሰ ነው:: በልጅነታችን የኳስ ሜዳ ባለማግኘታችን ከመኪና ጋር እየተጋፋን ነበር የምንጫወተው ያሉትንም የኳስ ሜዳዎች ለተለያዩ ህንጻ መገንቢያ ውለዋል ብዙም ህጻናት እና ወጣቶች የሚዝናኑበት እና ስፖርት ሊሰሩበት የሚችሉበት ቦታ የለም:: ለዚህም ነው ከላይ እንዳልኩት ሞራሉ እንዴት ይኖረናል ያልኩት:: እነዚህ ሴቶች እህቶቻችን እንዲሁም የወንድ ብሄራዊ ቡድናችን ምንም አይነት ለስፖርቱ የተስተካከለ ነገር በሌለበት ሀገር በቅለው ማጣሪያውን አልፈው ለዚህ መብቃታቸዉ በራሱ የሚያስከብራቸው ነው እና በርቱ ልንላቸው ይገባል::

ገደል wrote:ሲምኖ......ምክንያት ለመፍጠር ጊዜህን አታባክን:: እግር ኩዋስ በኢትዮጵያ የሞተ እስፖርት ነው::
እግር ኩዋስን ላማጠንከር መጀመርያ ብቃት ያለው ኢንስቲቲዩት አስፈላጊ ነው:: ከዚያ በሁዋላ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ብቃት ባላቸው ኮቾች እየሰለጠኑ በትምህርት ቤቶች መካከል በየደረጃው (ሰከንደሪ እና ኤለመንተሪ) ስታንዳርድ ግጥሚያ ማካሄድ አለባቸው:: የኮች እጥረት የለም::የቀድሞ የፕሪሚየም ሊግ እና የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለትምህርት ቤት ተጫዋቾች ኮች መሆን ይችላሉ::
በቀድሞ ጊዜ ማለት በ ሀይለስላሴ ጊዜ: የተደራጀ የትምህርት ቤት ግጥሚያዎች ነበሩ:: ለ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተሰለፉት ለምሳሌ መንግስቱ ወርቁ: ጌታቸው ወልዴ ግርማ ዘለቀ ሌሎችም ከትምህርት ቤት ግጥሚያዎች ተመልምለው በ ፕሪምየር ሊግ ተጫውተው ነው ለብሄራዊ ቡድን የበቁትና ያንን ለ 50 አመት ያልተደገም ውጠት ያስመዘገቡት::

ብሄራዊ ቡድን በህይሆይታ ግጥሚያ ሲደርስ ከያለበት የሚሰበሰብ ቡድን አይደለም:: ሙሽራ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ነገር::
ሲምኖ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 124
Joined: Wed Oct 12, 2011 11:46 pm

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests