nebsie wrote:በመጀመሪያ የብሄራዊ ቡድናችን ለአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ ስለበቃ ከፍተኛ ደስታችን ሆኖ ሰንብቷል;; አሁን ደግሞ ከብሄራዊ ቡድናችን ጋር አብሮ የሚሄዱት ከሁሉም ዘርፍ የተውጣጡ ግለሰቦችንና ቡድኖችን እንጠቅሳለን;; ኤርፖርቱን ማለፍ ስለማይችል ተብሎ ስለታሰበ እዛው ሳውዝ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ለብሄራዊ ቡድናችን ከሚያቀርቡት ነገር አንዱ በተሰላፊ ተጨዋቾቻችን ገምባሌ ውስጥ ሻጥ የምትደረግ ጩቤ በተለይ ለአጥቂዎቻችን የሚያገለግል እነዛ የሰማይ ስባሪ የሚያካክሉ የተቃራኒ ተጫዋች ተከላካዮችን አስፈራርቶ ለማለፍና ጎል ማስቆጠር እንዲችሉ እንዲረዳ ተብሎ ነው;; ሌላው ደግሞ ከቡድናችን ጋር ከሚሄዱት ግለሰቦች ውስጥ ከጎጃም ከወሎ እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢ የተውጣጡ አሉ የተባሉ ያፍዝ ያደንግዝ መስራት የሚችሉ ሰዎች አብረው እንደሚግዋዙ የታወቀ ሲሆን ይህም የሚረዳው አጥቂዎቻችን ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል መድረስ ካልቻሉ ያቺን ያፍዝ ያደንግዝ ተቃራኒ ቡድን ተከላካይ እጁን ነካ ወይም ቀባ በማድረግ እንዲያፈዝላቸው ታስቦ ነው;; ከዚሁ ጋር በተያያዘ ደግሞ አብሮ የተዘጋጀው የተቃራኒ ቡድን አጥቂዎች በጣም ጎል ለማግባት አስጨናቂ የሆነ ተደጋጋሚ ሙከራ ካደረጉ ወይም ካጣደፉን ፋታ ካሳጡን ያቺን እግራቸውን ቄጤማ የምታደርገውን ነገር ክዋሱ ላይ ቀባ ማድረግ ነው;; ሌላውን በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን;; ቸር ይግጠመን
ጌታ wrote:ክቡሻ - ነብሴ ማለት አንተ ዋርካ ላይ ሳትጸነስ የዋርካ አድባር የነበረ ልጅ ነበር:: ያኔ - በድንጋይ ዳቦ ዘመን ማለቴ ነው::
ነብሴ እንኳን በደህና ከች አልክ - አሪፍ ዘገባ ነው::
ጌታ wrote:ክቡሻ
ቀልድ መሆኑ ገብቶኛል ግን እግረመንገዴን ነብሴ ዋዛ ዋርከኛ እንዳልሆነ ግንዛቤ ላስጨብጥህ ብዬ ነው:: አንተ ግን በ2013 ከተለያዩ መንፈሶች ጋር ውጊያ የገጠምክ ትመስላለህ:: በቆረጣ ስታይል ድል እንደምትመታቸው እርግጠኛ ነኝ::
Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት
Users browsing this forum: No registered users and 1 guest