ኒጄርን 1 ለ 0 ከቱኒዚያ 1 ለ 1 ታንዛኒያን 2 ለ 1

ስፖርት - Sport related topics

ኒጄርን 1 ለ 0 ከቱኒዚያ 1 ለ 1 ታንዛኒያን 2 ለ 1

Postby ማካሮቭ » Fri Jan 11, 2013 7:10 pm

ለአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ላይ ያለው ብሔራዊ ቡድናችን እስካሁን ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ያለ ይመስላል:: ከሁሉም ኃይለኛ ከሚባሉት ከ ቱንዚያዎች ጋር ዶሀ ላይ ያደረገውን ጨዋታ በዩ ቱብ እንዳየሁት ቡድናችን ብዙ ግቦችን ስቶ በበላይነት ጨርሷል:: ቱኒዚያዎች አሉ የሚባሉ ፕሮፌሺናል ተጫዋቾቻቸውን እንዳሰለፉ ለማወቅ ተችሏል::

ከወደ አዲስ አበባ አከባቢ የሚናፈሰው ወሬ እንደሚያመለክተው ቡድናችን የግብ ጠባቂ ድርቅ እንደመታው ነው:: የጂማ ከነማ በረኛ በጣም ኃይለኛ እንደሆነ ቢነገርለትም የጂማ ከነማ 2ኛ ዲቪዢን ስለሚገኛ በሚል ሰበብ ለብሄራዊ ቡድናችን አለመመረጡ አነጋጋሪ ነው:: ሁላችንም እንዳየነው ሱዳን ላይ ከገቡብን አራቱ ግቦች ሶስቱ በበረኛ ስህተትና ችሎታ ማነስ እንደሆነና ይህ ባይሆን ውጤቱ በኛ ቡድን ድል እዚያው ካርቱም ላይ ይጠናቀቅ እንደነበር በቁጭት የሚናገረው የአዲስ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጋዜጠኛ ነው::
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests