የኢትይጵያ ብሄራዊ ቡድንን ልምምድ እና የወዳጅነት ጨዋታ በአካለ የማየት እድል አጋጥሞኝ ነበር በርግጥ ልጆቹ እንደፈራህዋቸው ሳይሆን የማይናቅ እና ጥሩ ኳስ የሚጫወቱ ናቸው
ሁለት ችግር ግን አለባቸው
1 የበረኛ :- እርግጥ ጥሩ ተከላካዮች ቢኖሩም እነሱ ታልፈው በረኛው ደህና ሙከራ ከተሞከረበት ግብ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው
2 ፊዚክሊ ከዛምብያ ተጫዋቾች የሚመጠኑ አይደሉም
በነዚህ እና የዛምብያን ቡድን ጥንካሬ ግምት ውስጥ በማስገባት በዛሬው ጨዋታ 3-1 ይሸነፋሉ ብዬ እገምታለው
እርግጥ ልጆቹ ጥሩ ኢንቱሲያዝም እና የማሸነፍ ፍላጎት እና ወኔ ያላቸው ናቸው
ይህ ጥሩ ጎናቸው ነው