ክብዬ ደግሞ አንተ ከተወለድክ ጀምሮ ሰው አስቀህ እንጂ አበሳጭተህ ታውቃለህ እንዴ ?
በስም ብቻ ከሄድክማ ክቡዬ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አበበ በቀለ ከበደ አየለ
ትግራይም ከሆንክ ለምሳሌ አንተ አታክልቲ ወይ ሀድጉ ወይ ገረመድሂን ቺኮቹም ምጽላል ትብለጽ ለታይ..እየተባሉ መጠራት አለባቸው እኒ ዳንኤል ሳሙኤል ራሄል ሳራ እየተባሉ እንዴት ኢትዮጵያዊ ናቸው ይባላል
እስቲ እንግዲህ እንዳልከው የእሁዱ ከያዘልህ ምናባቱ አዲስ ስራ መፍጠር አለብህ ትንሽ ቤት ትከራይና ከፊት ለፊቱ በትልቅ ቦርድ ላይ ህልም እንፈታለን ...ሲኒም እናያለን.. ኮኮብ እንቆጥራለን..መዳፍ እናነባለን..ብለህ ታጽፍና ዘርፈ ብዙ የሆነ ድርጅት መክፈት ነው በዚች ያለም ዋንጫ ዝናህ ብቻ ደህና ደንበኛ ታፈራለህ ..
የኛ ሰው መቸም ምቀኛ ነው ከጎንህ ተመሳሳይ ቤት እስኪከፍቱ ጥሩ ሳትነጭባት አትቀርም ከፍትፍቱም ከዶሮውም አምጡ እያልክ ..ሌላ ጥያቄ አታብዛ እንጂ :)
ክቡራን wrote:ቫቬዝ ነፍሴ ትንሽ አበሳጨሁሽ እንዴ..? :D እኔ እኮ ያገርህ ልጆች ያልኩህ ስምህ የእነሱን ስለሆነ ነው... :lol: ሁጎ ቫቬዝ...ሆዜ ...ምናምን...ልቀጥል..? ዋናውን ልጥራው..? ልጻፈው..?? :lol: እንዳልኩህ እሁድ ለካ ክቡራን ነቢይ ነበር ትላለህ:: መቼም እንደተጻፈው ነቢይ ባገሩ አይከበርም:: ከእሁድ ጨዋታ በኌላ አንተም ሌሎችም ስለኔ ያላቹ አመለካከት ይቀየራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: የሚገባኝን እንግዲ ሳታጔድሉ ትሰፍራላቹ:: ሴቶች የሆናቹ ደሞ ምግብ ባገልግል ይዛችሁልኝ ስትመጡ ተነጋገሩ...አንድ አይነት ምግብ ሰርታቹ አትምጡ..ዛሬ የበግ ፍትፍት ከሆነ ነገ ዱለት ከነገ ወዲያ ደሞ ለጤና እንዲሆንኝ አዚፋ ደሞ ጾም ሲሆን በጥሩ ባለሙያ በሚጥሚጣ የታሸ የጎመን ክትፎ እየተነጋገራቹ ብቻ.... ለማንኛውም....እሁድ እንገናኝ....ሌላም የምጠይቀው ይኖረኛል :D
ሻቬዝ-x wrote:ማነው ያገሬ ልጅ ያረጋቸው ክቡዋ ?
የዛሬን አያርገውና ድሮ በነሶክራተስ ዘመን ብራዚል ሲሸነፍ እራሳቸውን የሚሰቅሉ ብዙ ነበሩ አሁንማ ሰልጥነው ንዴታቸውን የሚወጡት ሳምባ በመጨፈር ነው ....አሁንም ያረጉት ያንኑ ነው ሌሊቱን ሳምባ ሲሸከሽኩ አደሩ ንዴቱም በረደ ውጤቱንም ዋጡት በቃ አለቀ ! ለነገሩ የምትሞትለት ቡድንም አይደለም ተራ ቡድን ሆንዋል የጎሉ ቁጥር በዛ እንጂ መሸነፉ አይገርምም እንዳውም መሸነፍ የነበረበት በቺሊ ነበረ ...እሙዬንም የሚያስለቅስ ነገር የለም በላት አርፋ ሳምባዋን ታስነካ ...
በነገራችን ላይ ሆላንድም ተሸነፈ የኔ መገለጥም አከተመለት እንግዲህ እሁድ ያንተን መገለጥ መጨረሻ እናያለን