የክቡራን መገለጥ እውን ሆነ

ስፖርት - Sport related topics

የክቡራን መገለጥ እውን ሆነ

Postby ሻቬዝ-x » Sun Nov 03, 2013 9:17 am

የመልሱን ጨዋታ መጠበቅ አያስፈልግም


1 ኮት ዲ'ቮዋር
2 ጋና
3 አልጄሪያ
4 ካምሩን
እና
5 ናይጄርያ


ናቸው
Last edited by ሻቬዝ-x on Mon Jul 14, 2014 7:03 am, edited 4 times in total.
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ቃላት » Sun Nov 03, 2013 3:53 pm

ሻቬዝ

ክለቦች አይደሉም ብሄራዊ ቡድኖች ናቸው:

የኔ ግምት ደግሞ:

ኮትዲቯር
ጋና
ቡርኪናፋሶ
ካሜሮን እና
ኢትዮጵያ

ይመስሉኛል
ቃላት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 84
Joined: Sun Apr 23, 2006 1:46 pm

Postby ቀዳማይ » Sun Nov 03, 2013 10:59 pm

የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ጨዋታ መቼ ነው?
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ሻቬዝ-x » Mon Nov 04, 2013 7:05 am

ቃላት wrote:ሻቬዝ

ክለቦች አይደሉም ብሄራዊ ቡድኖች ናቸው:

የኔ ግምት ደግሞ:

ኮትዲቯር
ጋና
ቡርኪናፋሶ
ካሜሮን እና
ኢትዮጵያ

ይመስሉኛል


ሰላም ቃላት

ለእርማቱ አመሰግናለው

የኢትዮጵያ ቡድን ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ቀርብዋል በዚህ ይደነቃል ሆኖም ኢትዮጵያ አገሩ ላይ የተሸነፈ ብቸኛ ቡድን ነው የመልሱ ጨዋታ አ አበባ ላይ ቢሆን ከደጋፊ ጩኸት ጋር አንድ ነገር እንጠብቅ ነበር ሆኖም የመልሱ ጨዋታ ናይጄርያ ላይ ነው ናይጄርያ ደግሞ አገሩ ላይ የምታሸንፈው አይነት ቡድን አይደለም ስለዚህ ሪያሊስቲክ ግምት ይወሰድ ከተባለ ናይጀርያን አገሩ ላይ ያሸንፈዋል ብሎ መተንበይ ይከብዳል ተአምር ካተፈጠረ

የኢቶጵያ እና የናይጀርያ ቡድን ጨዋታ በ ቅዳሜ ኖቨምበር 16 በናይጀርያ ካላባር ላይ በ16:00 GMT ይደረጋል ለማንኛውም መልካሙ እንመኝለታለን !
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Re: ብራዚል የሚሄዱት 5 የአፍሪካ ክለቦች ታወቁ

Postby TAዛBI » Wed Nov 06, 2013 7:16 am

ሻቬዝ-x wrote:የመልሱን ጨዋታ መጠበቅ አያስፈልግም


1 ኮት ዲ'ቮዋር
2 ጋና
3 አልጄሪያ
4 ካምሩን
እና
5 ናይጄርያ


ናቸው


ሰላም ሻቬዝ የመልሱ ጨዋታማ በጣም ተጠባቂ ነው
እስካሁን ማለፉን አረጋግጥዋል ሊባልለት የሚችለው በመጀመርያው ዙር ጨዋታ ግብጽን 6-1 የሸከሸከው የጋና ቡድን ብቻ ነው ይህን ጨዋታ ባየው ደስ ይለኝ ነበር ( ግብጾችን እንዲህ አናታቸውን ሲባሉ ደስ ይለኛል :P )
በተረፈ ሴኔጋል አገሩ ላይ አይቮሪኮስትን 2-0 ማሸነፍ ከቻለ አላፊ ነው
ቡርኪናፋሶ ከአልጄርያ ጋር እኩል መውጣት ከቻለ አላፊ ነው
ቱኒዝያ ከካሜሩን ጋር 1-1 መውጣት ከቻለ ያልፋል
ኢትዮጵያም እንግዲህ ናይጄርያን 2-0 ማሸነፍ ከቻለ.....ማን ያውቃል ...
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Re: ብራዚል የሚሄዱት 5 የአፍሪካ ክለቦች ታወቁ

Postby ሻቬዝ-x » Tue Nov 19, 2013 2:04 pm

ሻቬዝ-x wrote:የመልሱን ጨዋታ መጠበቅ አያስፈልግም


1 ኮት ዲ'ቮዋር
2 ጋና
3 አልጄሪያ
4 ካምሩን
እና
5 ናይጄርያ


ናቸው


እንደታሰበው 3 ቡድኖች

ኮት ዲቮዋር ከሴነጋል 1-1 በመውጣት
ካመሩን ቱኒዝያን 4-1 በመርታት
ናይጄርያ ኢትዮጵያን 2-0 በመርታት

ማለፋቸውን አረጋግጠዋል !

ከተወሰኑ ሰአታት በህዋላ ደግሞ ጋና ከግብጽ እንዲሁም አልጄርያ ከቡርኪናፋሶ ጋር ይገጥማሉ

ግብጽ በመጀመርያው ዙር 6/1 ስለተከናነበ አሁን ውጠቱን የሚቀለብስበት ሁኔታ የለም !

አልጄርያ ደግሞ ምንም እንክዋን በመጀመርያው ጨዋታ 3-2 በቡርኪናፋሶ ቢሸነፍም አሁን በሜዳው ከ 1:0 በላይ በሆነ ውጤት የማሸነፍ ብቃት አለው

ስለዚህም ቀሪዎቹ አላፊዎች ጋና እና አልጄርያ በመሆን ዛሬ ይለያሉ
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ጌታ » Wed Nov 20, 2013 7:10 pm

ሻቬዝ ግምትህ ይዞልሃል:: አሁን ደግሞ ዋንጫውን ማን እንደሚያነሳ ንገረነ

http://www.fifa.com/worldcup/preliminaries/index.html

Qualified Teams
AlgeriaAlgeria (ALG)19-11-2013CameroonCameroon (CMR)17-11-2013Côte d'IvoireCôte d'Ivoire (CIV)16-11-2013GhanaGhana (GHA)19-11-2013NigeriaNigeria (NGA)16-11-2013
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሻቬዝ-x » Sat Nov 23, 2013 11:18 am

ጌታ wrote:ሻቬዝ ግምትህ ይዞልሃል:: አሁን ደግሞ ዋንጫውን ማን እንደሚያነሳ ንገረነ

http://www.fifa.com/worldcup/preliminaries/index.html

Qualified Teams
AlgeriaAlgeria (ALG)19-11-2013CameroonCameroon (CMR)17-11-2013Côte d'IvoireCôte d'Ivoire (CIV)16-11-2013GhanaGhana (GHA)19-11-2013NigeriaNigeria (NGA)16-11-2013


ጌታ ሰላም ነው

በ2010 የአለም ዋንጫም ማጣርያውን አልፈው አፍሪካን የወከሉት እኒሁ አምስት አገራት ነበሩ

ዋንጫውን ግን ብራዚል አገሩ ላይ ለሌላ አሳልፎ ይሰጣል ትላለህ ??

ሆኖም ለመገመት የመጀመርያውን ዙር ውድድር እንኳን ማየት ግድ ይላል (ፐርፎርማንሳቸውን ለማየት) :D
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ሻቬዝ-x » Sat Dec 07, 2013 9:33 am

የአለም ዋንጫ ድልድል እጣ ትላንት በወጣው መሰረት እንደሚከተለው ሆኗል

Group A: Brazil, Croatia, Mexico, Cameroon.

Group B: Spain, Netherlands, Chile, Australia.

Group C: Colombia, Greece, Ivory Coast, Japan.

Group D: Uruguay, Costa Rica, England, Italy.

Group E : Switzerland, Ecuador, France, Honduras.

Group F: Argentina, Bosnia-Hercegovina, Iran, Nigeria.

Group G: Germany, Portugal, Ghana, USA.

Group H: Belgium, Algeria, Russia, South Korea.በዚህ መሰረት ካመሩን አሰቃቂዎቹን ብራዚልን ሜክሲኮንና ክሮኤሽያ በየተራ ይገጣል

ኮት ዲ'ቮዋር ወደ ሁለተኛ ዙር የማለፍ ጥሩ እድል አለው

ለገምተኛው ናይጄርያ ኢራንንም የሚያሸንፍ አይመስለኝም

ጋናም ከጀርመንና ከፖርቱጋል ጋር ይጋፈጣል

በመጀመርያው ዙር ብዙ ተጠባቂ ጭዋታዎች አሉ
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ጌታ » Mon Dec 09, 2013 8:09 pm

ሻቬዝ ወንድማችን

ስለቅሪላ ብዙም ባላውቅም ኳስ ድቡልቡል መሆኗን ነፍስ ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ የተከታተልኳቸው 14 የዓለም ዋንጫ ተሞክሮዬ ይነግረኛል::

ትናንት አንድ እንግሊዛዊ ተንታኝ ብራዚል ባገሯ ስለምትጫወት ዋንጫውን ለማንም አሳልፋ አትሰጥም እያለ ሲቀባጥር ነበር ብሎ የሚተረጉምልኝ ልጅ ነገረኝ:: አሜሪካኖቹ ደግሞ ሰሞኑን ከጀርመንና ፖርቱጋል ጋር የሞት ምድብ ደረሰን እያሉ እያለቃቀሱ ነው:: ጋናን ንቀናታል ቢሉም ባለፉት አንድ ይሁን ሁለት ዋንጫ ካለም ዋንጫ ውድድር ያስፈነጠረቻቸው ጋና መሆኗን አልረሱትም::

ለአፍሪካ ተሳታፊዎች መልካሙን እየተመኘሁ ከታሪክ ልምዴ በመነሳት አርጀንቲና ብራዚል ጥልያን ፈረንሳይ ስፔን እና ጀርመን ወደፊት ገስግሰው አንዳቸው ዋንጫ ያነሳሉ ብዬ እገምታለሁ:: እንግሊዝ የመጀመሪያውን ዙር ካለፈች ይበቃታል::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሻቬዝ-x » Wed Dec 11, 2013 1:31 pm

ጌታ wrote:ሻቬዝ ወንድማችን

ስለቅሪላ ብዙም ባላውቅም ኳስ ድቡልቡል መሆኗን ነፍስ ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ የተከታተልኳቸው 14 የዓለም ዋንጫ ተሞክሮዬ ይነግረኛል::

ትናንት አንድ እንግሊዛዊ ተንታኝ ብራዚል ባገሯ ስለምትጫወት ዋንጫውን ለማንም አሳልፋ አትሰጥም እያለ ሲቀባጥር ነበር ብሎ የሚተረጉምልኝ ልጅ ነገረኝ:: አሜሪካኖቹ ደግሞ ሰሞኑን ከጀርመንና ፖርቱጋል ጋር የሞት ምድብ ደረሰን እያሉ እያለቃቀሱ ነው:: ጋናን ንቀናታል ቢሉም ባለፉት አንድ ይሁን ሁለት ዋንጫ ካለም ዋንጫ ውድድር ያስፈነጠረቻቸው ጋና መሆኗን አልረሱትም::

ለአፍሪካ ተሳታፊዎች መልካሙን እየተመኘሁ ከታሪክ ልምዴ በመነሳት አርጀንቲና ብራዚል ጥልያን ፈረንሳይ ስፔን እና ጀርመን ወደፊት ገስግሰው አንዳቸው ዋንጫ ያነሳሉ ብዬ እገምታለሁ:: እንግሊዝ የመጀመሪያውን ዙር ካለፈች ይበቃታል::


ሰላም ጌታ

እኔም አለም ዋንጫን በፍቅር ነው የምከታተለው

በልጅነቴ ያየህዋቸው የነፕላቲኒ የነቲጋና የነሶክራተስ የቫን ባስተን የማራዶና ቀጥሎ የመጡት እነ ዚዳን 8) ፊጎ ...ትዝታቸው አሁንም አለ የአሁኖቹ እነሜሲ ሮናልዶ ምናምን የዛን ዘመኖቹን ያህል የሚያረኩኝ አይመስለኝም

ብራዚል አስደንባሪ ቡድን ይዞ እንደሚቀርብ ተስፋ አደርጋለው

ከአፍሪካ ኮት ዲቮዋር ከደረሰው ምድብ አንጻር ጥሩ አድቫንስ ያደርጋል ብዬ አስባለው

ሮናልዶ ላገሩ የመሟሟት ባህሪ ስላለው ፖርቱጋልም የማይናቅ ተፎካካሪ ነው

ጀርመን ጠንካራ ቡድን ነው

ሜሲ ጥሩ ቲም ሜቶች ካገኘ ባሁኑ አገሩን ይክስ ይሆናል

ጣልያን መሰሪ ቡድን ነው (ጨዋታን እንዴት ማሸነፍ እንዳለባቸው ያውቃሉ )

እንግሊዝ እንዳለከው አለም አቀፍ ጨዋታ ላይ ምን እንደሚያልፈሰፍሳቸው አላውቅም (የሚያስደነግጥ ቲም አይቼባቸው አላውቅም ) የአሁኑን እንጃ

ኢራንና አሜሪካ የሚጋጠሙበት አጋጣሚ ቢፈጠር ደስ ይለኛል (ኳስና ፖለቲካ አብረን እንድናይ )

እነ ግሪክም አይናቁም የአውሮፓ ዋንጫ መውሰድ የቻሉ ናቸው

ለሎቹም ቀላል የሚመስሉት ክለቦች ሀይለኛ እንደሚሆኑ አምናለው

ብራዚል ዉስጥ የሚደረግ ጨዋታ መሆኑ በራሱ ክላሲክ ያደርገዋል ስለዚህ ተጠባቂ የአለም ዋንጫ ነው !
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ወርቅነች » Mon Dec 30, 2013 5:49 pm

እነደልማዷ ለዋርካው ምድራዊ ጥቁሩ ጌታ እጅ ትነሳለች ጀሚላ የችርችል ጎዳናዋ :lol:

ከታሪክ ልምዴ በመነሳት አርጀንቲና ብራዚል ጥልያን ፈረንሳይ ስፔን እና ጀርመን ወደፊት ገስግሰው አንዳቸው ዋንጫ ያነሳሉ ብዬ እገምታለሁ :: እንግሊዝ የመጀመሪያውን ዙር ካለፈች ይበቃታል ::


እንወራረድ... ከብራዚል ሌላ ምናልንባትም እንሊዝ የጠቀሰካቸው ሁሉ አርጀንቲና ጣልያን ፈረንሳይ ሰፔን እና ጀርመን ዋንጫዋን ንክች አያደርጎዋትም ትላለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና :lol: :lol: :lol:


ጌታ wrote:ሻቬዝ ወንድማችን

ስለቅሪላ ብዙም ባላውቅም ኳስ ድቡልቡል መሆኗን ነፍስ ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ የተከታተልኳቸው 14 የዓለም ዋንጫ ተሞክሮዬ ይነግረኛል::

ትናንት አንድ እንግሊዛዊ ተንታኝ ብራዚል ባገሯ ስለምትጫወት ዋንጫውን ለማንም አሳልፋ አትሰጥም እያለ ሲቀባጥር ነበር ብሎ የሚተረጉምልኝ ልጅ ነገረኝ:: አሜሪካኖቹ ደግሞ ሰሞኑን ከጀርመንና ፖርቱጋል ጋር የሞት ምድብ ደረሰን እያሉ እያለቃቀሱ ነው:: ጋናን ንቀናታል ቢሉም ባለፉት አንድ ይሁን ሁለት ዋንጫ ካለም ዋንጫ ውድድር ያስፈነጠረቻቸው ጋና መሆኗን አልረሱትም::

ለአፍሪካ ተሳታፊዎች መልካሙን እየተመኘሁ ከታሪክ ልምዴ በመነሳት አርጀንቲና ብራዚል ጥልያን ፈረንሳይ ስፔን እና ጀርመን ወደፊት ገስግሰው አንዳቸው ዋንጫ ያነሳሉ ብዬ እገምታለሁ:: እንግሊዝ የመጀመሪያውን ዙር ካለፈች ይበቃታል::
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ሻቬዝ-x » Thu Jun 19, 2014 6:11 am

አለም ዋንጫን እንዲህ ባየናቸው ጫወታዎች ገመገምነው

1.ብራዚል :-የማይረባ ቡድን ይዞ ነው የቀረበው ይህችን ዙር እንደምንም ቢያልፍም በጥሎ ማለፉ የሚገጥመው ሆላንድን ወይንም ቺሊን ስለሆነ በሁለቱም የመሸነፍ እድሉ ከፍተኛ ነው

2:- ስፔን አይ ስፔን በ2010 የደስታን ጣራ አይተዋት ነበረ አሁን ደግሞ ተቃራኒውን ማጣጣም ነበረባቸው መሰል ::ይዘውት የመጡት ከባባድ ስሞችን ነበር የቡድኑ ተጫዋቾች ጠቃላላ ዋጋ ቢሰላ ከ600 ሚልየን ዶላር በላይ እንደሆነ ነው የሰማሁት ሆኖም ያደረጉት እንቅስቃሴ የአዋሳ ጨርቃጨርቅ ቡድን ነው ያስመሰላቸው መሀል ሜዳ ላይ ጠቅ ጠቅ ብቻ ቲካ ቲካ ምንም ውጤታማ ያልሆነ አጨዋወት ነው ባሁኑ ግዜ የሚፈለገው ፍጥነት እና ጥንካሬ የሚታይበት ጨዋታ ነው ልክ እንደሆላንድና ጀርመን

3;- እንግሊዝ ;- የተለመደው ልፍስፍስ አጨዋወታቸውን ይዝው ነው የመጡት እንደስፔን በመጀመርያው ዙር የመሰናበታቸው እድል ከፍ ያለ ነው በዛሬ ጨዋታቸው ቢያሸንፉ ግን ደስ ይለኛል መናጢ ቢሆኑም ለምን እንደሆነ አንጀቴን ይበሉኛል :D

4; ጀርመን the best team ፖርቱጋልን 4-0 ማሸነፍ የቻለ ቡድን ማን እንደሚያቆማቸው አይታወቅም

5:- ፈረንሳይ :- ዘንድሮ ጥሩ ቲም ይዘው መጥተዋል በነቲጋና እና ፕላቲኒ ዘመን የነበረውን ማራኪ ጨዋታ የሚደግሙ ይመስላሉ

6;- ቺሊ :- ያልተጠበቀ በጣም ጠንካራ ቡድን ለሁሉም ክለቦች አደጋ ሊሆን እንደሚችል ከስፔን ጋር ባደረገው ጨዋታ አስመስክርዋል ከላቲን አሜሪካ አገሮች ጥሩ ፕርግረስ ያደርጋል የምለው ቡድን ነው

7:- አርጀንቲና :- ደህና ቡድን ያገኘው እለት ይፈተናል አስፈሪ ክለብ መሆኑ ግን አክትምዋል በቅርቡ የነስፔን እጣ ይደርሰዋል

8;- ጣልያን ;- ምናልባት የተወሰነ መንገድ ሊግዋዙ ይችላሉ

9 ;አፍሪካውያን ዋጋ የላቸውም ከኮት ዲቮዋር በቀር እሱም በሚቀጥለው ዙር የመሰናበት እድሉ ሰፊ ነው

10 ኤስያውያን ዋጋ የላቸውም

11 ሆላንድ my favorite የቫን ፐርሲ እና የሩበን ጎሎች እጅግ ምርጥ ነበሩ ብራዚልን ልክ እንደባለፈው ያለም ዋንጫ ዘንድሮም አገሩ ላይም የሚቀጡት ይመስለኛል ..
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ጌታ » Thu Jun 19, 2014 9:23 pm

ሻቬዝ-x wrote:3;- እንግሊዝ ;- የተለመደው ልፍስፍስ አጨዋወታቸውን ይዝው ነው የመጡት እንደስፔን በመጀመርያው ዙር የመሰናበታቸው እድል ከፍ ያለ ነው በዛሬ ጨዋታቸው ቢያሸንፉ ግን ደስ ይለኛል መናጢ ቢሆኑም ለምን እንደሆነ አንጀቴን ይበሉኛል :D


እነዚህ መናጢዎች በገዛ ጓደኛቸው በመጀመሪያው ዙር ሊሰናበቱልህ ነው:: ሱዋሬዝ ከህመሙ አገግሞ አንድ ብሏቸዋል!!

እኔም የሚገርመኝ ነገር ጉራቸውን እንዲህ ሲያስተነፍሷቸው ጥሩ እንደሆነ እያወቅሁ ለነሱ ማዘኔ ነው:: ገና ጡጧችንን ሳንጥል የነሱን ኳስ እያየን ስላደግን አይፈረድብንም::

ትንሽ የሚያሳዝነኝ ትንሹ እስተርሊንግ ነው::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ክቡራን » Fri Jun 20, 2014 3:24 am

እባካች ሁን የስፖርት ቤተስቦች ኡጎ ቫቬዝ (ተሳስቼ በድብቅ የምታጠቃበትን ስም ልጠራው ነበር ) :lol: ወይም ጌታ እስኪ አንዳንዴ ምርጥ ምርጥ የሆኑ ግቦችን የሚያሳዩ ሊንኮችን ስታገኙ ለጥፉልን ስል በስራና ባንዳንድ ምክንያት ጨዋታው ባመለጣቸው ስም በትህትና እጠይቃለሁ::
አክባሪያቹ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests