የክቡራን መገለጥ እውን ሆነ

ስፖርት - Sport related topics

Postby ሻቬዝ-x » Fri Jun 20, 2014 8:52 am

ጌታ wrote:
ሻቬዝ-x wrote:3;- እንግሊዝ ;- የተለመደው ልፍስፍስ አጨዋወታቸውን ይዝው ነው የመጡት እንደስፔን በመጀመርያው ዙር የመሰናበታቸው እድል ከፍ ያለ ነው በዛሬ ጨዋታቸው ቢያሸንፉ ግን ደስ ይለኛል መናጢ ቢሆኑም ለምን እንደሆነ አንጀቴን ይበሉኛል :D

እነዚህ መናጢዎች በገዛ ጓደኛቸው በመጀመሪያው ዙር ሊሰናበቱልህ ነው:: ሱዋሬዝ ከህመሙ አገግሞ አንድ ብሏቸዋል!!

እኔም የሚገርመኝ ነገር ጉራቸውን እንዲህ ሲያስተነፍሷቸው ጥሩ እንደሆነ እያወቅሁ ለነሱ ማዘኔ ነው:: ገና ጡጧችንን ሳንጥል የነሱን ኳስ እያየን ስላደግን አይፈረድብንም::

ትንሽ የሚያሳዝነኝ ትንሹ እስተርሊንግ ነው::

ሰላም ጌታ
እንዳልከው ድሮ BIG LEAGUE SOCCER ስናይ ከነበረበት ግዜ አንስቶ እነ ኢያን ራሽ, ጋሪ ሊኒከር, ጆን ባርነስ በፕረሚየር ሊጉም እነካንቶና ዴቪድ ቤካም ..ከፓወርፉሉ የእንግሊዝ ሚድያ ጋር ተደምሮ እንግሊዝን የእግር ኳስ ፈጣሪ (inventor) አድርገን እንድናምን ተደርገናል ስለዚህ አለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር አንድ ነገር ከነሱ የመጠበቅ አባዜ ይይዘናል ልክ እንዳሁኑ የትም እንደማይደርሱ ልባችን ቢያውቅም :)

አሁንም በስማቸው ብቻ ለኳሱ እንደጌጥ ስለነበሩ ትንሽ ቢገፉ ተመኝቼላቸው ነበር ግና ዝና ሌላ ችሎታ ሌላ ሆነና በግዜ ደህና ክረሙ ብለውን ሄደዋል
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ሻቬዝ-x » Fri Jun 20, 2014 9:12 am

ክቡራን wrote:እባካች ሁን የስፖርት ቤተስቦች ኡጎ ቫቬዝ (ተሳስቼ በድብቅ የምታጠቃበትን ስም ልጠራው ነበር ) :lol: ወይም ጌታ እስኪ አንዳንዴ ምርጥ ምርጥ የሆኑ ግቦችን የሚያሳዩ ሊንኮችን ስታገኙ ለጥፉልን ስል በስራና ባንዳንድ ምክንያት ጨዋታው ባመለጣቸው ስም በትህትና እጠይቃለሁ::
አክባሪያቹ:: :D

ወዳጄ ክቡራን ቀልቤን መግፈፍ ስራየ ብለህ ያዝከው አይደል ሆኖም ያኛውን ስሜ ቀርቶ ይህንን ስሜን እንክዋን በትክክል አልጠራኸውም ኡጎ ሳይሆን ሁጎ ነው :D

ለማንኛውም በአሁኑ አገሩ ስላልተካፈለች በዚህ የአለም ዋንጫ ላይ ባናየውም በግሌ ከሜሲ እና ከሮናልዶ ይበልጣል ብዬ የማምንበትን የዝላታን ኢብራሂሞቪች ምርጥ ግቦችን እንድትኮመኩም ወዲህም ችሎታውን እንድታይልኝ እጋብዝሀለው http://www.youtube.com/watch?v=XYan94S8slU
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ጌታ » Fri Jun 20, 2014 10:14 pm

ሻቬዝ-x wrote:ሰላም ጌታ
እንዳልከው ድሮ BIG LEAGUE SOCCER ስናይ ከነበረበት ግዜ አንስቶ እነ ኢያን ራሽ, ጋሪ ሊኒከር, ጆን ባርነስ በፕረሚየር ሊጉም እነካንቶና ዴቪድ ቤካም ..

ይኸውልህ የሊቨርፑል ደጋፊ የሆንኩት በነ ኢያን ረሽ እና ባርነስ ምክንያት ነው:: እንደኔው ሽሜ ነሽ ማለት ነው ቂቂቂቂ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሻቬዝ-x » Sat Jun 21, 2014 7:25 am

ጌታ wrote:
ሻቬዝ-x wrote:ሰላም ጌታ
እንዳልከው ድሮ BIG LEAGUE SOCCER ስናይ ከነበረበት ግዜ አንስቶ እነ ኢያን ራሽ, ጋሪ ሊኒከር, ጆን ባርነስ በፕረሚየር ሊጉም እነካንቶና ዴቪድ ቤካም ..

ይኸውልህ የሊቨርፑል ደጋፊ የሆንኩት በነ ኢያን ረሽ እና ባርነስ ምክንያት ነው:: እንደኔው ሽሜ ነሽ ማለት ነው ቂቂቂቂ

ሰላም ጌች

ባለፈው የሰይፉ ፋንታሁን ፕሮግራም ሳይ "ወመሽ" ነኝ ሲል ሰምሁት ወጣት መሳይ ሽማግሌ ማለት ነው አሉ እኔ እንክዋን የት እንደምመደብ አላውቅም እድሜዬ ባንተና በገልብጤ እድሜ ማሀል ነው ገልብጤ 24 አመቱ ነው አሉ :) እንግዲህ የገልብጤን እና ያንተን እድሜ ደምረህ ለሁለት ማካፈል ነው እኔ ኳስ ማየት የጀመርኩት በ1982 የስፔን አለም ዋንጫ ጀምሮ ነው ፓውሎ ሮሲ ሀትሪክ ሰርቶ የነሶክራተስ የነዚኮ እና ፋልካዎን ብራዚል ሲያሸንፍ በደንብ አስታውሳለው በዛን ዘመን የነበረው ምርጥ የፈረንሳይ ቡድንም ትዝ ይለኛል ያኔ የፈረንሳይ ደጋፊ ነበርኩ (ያሁኑ የፈረንሳይ ቡድንም የዛን ዘመኑን ፈረንሳይ እያስታወሰኝ ነው ) ከዛ ወዲህ እንግዲህ 32 አመታት አልፈዋል ያኔ ግን በጣም ትንሽ ልጅ ነበርኩ እንግሊዝኛ ዘፈን መስማት የጀመርኩትም በማይክል ጃክሰን ትሪለር በነሊዮነል ሪቺ ሴይ ዮ ሴይ ሚ ዘመን ነው ያኔ ትንሽ ልጅ ነበርኩ አሁን ግን ጸጉሬ ገብስማ መሆን ጀምርዋል ግርማ ሞገስ ሆኖልኛል አሁንም ጂንሴን በፖሎ ሸርት ስለብስ ገልብጤን ማከል እችላለው :lol: ሱፌን በካራቫት ስለብስ ደግሞ አንቱ ተብዬም መስተናገድ እችላለው ፍሌክሰብል እድሜ ላይ ነኝ ማለት ነው : ንዋይ ደበበ በርግጠኝነት ቢያንስ ከ10 አመታት በላይ ይበልጠኛል እንደምታየው እሱ ግን አሁንም 'ወመሽ' ነው :D

ወአለም ዋንጫችን ስንመጣ እንዴት ነው ካየነው ፐርፎርማንስ አንጻር ፈረንሳይ እና ጀርመን all the way የሚሄዱ አይመስልህም ?
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ክቡራን » Mon Jun 23, 2014 6:50 am

ወዳጄ ሁጎ ምስጋናየ ይድረስህ....የኢብራሂሞቪችን ጨዋታዎችንና ግቦች አየኌቸው.. ድንቅ የኴስ ችሎታ አለው:: አንደኛው በመቀስ ምት ተገልብጦ ያገባትን ግብ ሳይ በልጅነት ለሰፈራችን ቡድን ስጫወት ያገባሁትን ግብ አስታወሰኝና ትንሽ አስተከዝከኝ:: ጥሩ አላደርክም ቫቬዝ ነፍሴ .. ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ:: እስኪ ሌላ ጨምርልኝና ካሰኝ:: :D

ሁጎ ሻቬዝ-x wrote:
ክቡራን wrote:እባካች ሁን የስፖርት ቤተስቦች ኡጎ ቫቬዝ (ተሳስቼ በድብቅ የምታጠቃበትን ስም ልጠራው ነበር ) :lol: ወይም ጌታ እስኪ አንዳንዴ ምርጥ ምርጥ የሆኑ ግቦችን የሚያሳዩ ሊንኮችን ስታገኙ ለጥፉልን ስል በስራና ባንዳንድ ምክንያት ጨዋታው ባመለጣቸው ስም በትህትና እጠይቃለሁ::
አክባሪያቹ:: :D

ወዳጄ ክቡራን ቀልቤን መግፈፍ ስራየ ብለህ ያዝከው አይደል ሆኖም ያኛውን ስሜ ቀርቶ ይህንን ስሜን እንክዋን በትክክል አልጠራኸውም ኡጎ ሳይሆን ሁጎ ነው :D

ለማንኛውም በአሁኑ አገሩ ስላልተካፈለች በዚህ የአለም ዋንጫ ላይ ባናየውም በግሌ ከሜሲ እና ከሮናልዶ ይበልጣል ብዬ የማምንበትን የዝላታን ኢብራሂሞቪች ምርጥ ግቦችን እንድትኮመኩም ወዲህም ችሎታውን እንድታይልኝ እጋብዝሀለው http://www.youtube.com/watch?v=XYan94S8slU
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ጌታ » Mon Jun 23, 2014 3:01 pm

ሁጎ - በኔና በገልብጤ መካከል ከሆንሽማ 44 ነሽ ማለት ነው :lol: :lol: :lol: ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነሻ :wink:

ፓ ፓ ፓ ፓ ፓ አብራሞቪች እውነትም የቅሪላ ጂኒየስ ነው:: እዚ ዓለም ዋንጫ ላይ እኔ ደካማው የማልስተውን ጎል የሚ'ስቱት ያፍሪካ ሸፋፎች ይህን ቪዲዮ ቢያሳይዋቸው ጥሩ ነበር::

ሶል - ትዝ ይለኛል ድሮ ሰፈር ውስጥ በጨርቅ ኳስ ያብራሞቪችን የመሳሰሉ ጎሎች ስታገባ ቂቂቂቂ አንተ እኮ አውሮፓ ተወልደህ ቢሆን በብዙ ነገር የት በደረስክ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሻቬዝ-x » Wed Jun 25, 2014 12:27 pm

ክቡራን wrote:ወዳጄ ሁጎ ምስጋናየ ይድረስህ....የኢብራሂሞቪችን ጨዋታዎችንና ግቦች አየኌቸው.. ድንቅ የኴስ ችሎታ አለው:: አንደኛው በመቀስ ምት ተገልብጦ ያገባትን ግብ ሳይ በልጅነት ለሰፈራችን ቡድን ስጫወት ያገባሁትን ግብ አስታወሰኝና ትንሽ አስተከዝከኝ:: ጥሩ አላደርክም ቫቬዝ ነፍሴ .. ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ:: እስኪ ሌላ ጨምርልኝና ካሰኝ:: :D

ሁጎ ሻቬዝ-x wrote:
ክቡራን wrote:እባካች ሁን የስፖርት ቤተስቦች ኡጎ ቫቬዝ (ተሳስቼ በድብቅ የምታጠቃበትን ስም ልጠራው ነበር ) :lol: ወይም ጌታ እስኪ አንዳንዴ ምርጥ ምርጥ የሆኑ ግቦችን የሚያሳዩ ሊንኮችን ስታገኙ ለጥፉልን ስል በስራና ባንዳንድ ምክንያት ጨዋታው ባመለጣቸው ስም በትህትና እጠይቃለሁ::
አክባሪያቹ:: :D

ወዳጄ ክቡራን ቀልቤን መግፈፍ ስራየ ብለህ ያዝከው አይደል ሆኖም ያኛውን ስሜ ቀርቶ ይህንን ስሜን እንክዋን በትክክል አልጠራኸውም ኡጎ ሳይሆን ሁጎ ነው :D

ለማንኛውም በአሁኑ አገሩ ስላልተካፈለች በዚህ የአለም ዋንጫ ላይ ባናየውም በግሌ ከሜሲ እና ከሮናልዶ ይበልጣል ብዬ የማምንበትን የዝላታን ኢብራሂሞቪች ምርጥ ግቦችን እንድትኮመኩም ወዲህም ችሎታውን እንድታይልኝ እጋብዝሀለው http://www.youtube.com/watch?v=XYan94S8slU

ወዳጄ ክቡ ኢብራሂሞቪች ትዝታህን ቀሰቀሰው አይደል ..ህይወት ግን ምን ጣእም አላት ብለህ ነው ስንቶቹ የተቀኙለት ትዝታ ባይኖር ... በርግጥ ልጁ የሚገርም ችሎታ አለው ጀርባውን ለጎሉ ሰጥቶ ባለበት ሁኔታ የሚያገባቸው ጎሎች ..በተረከዙ የሚያገባቸው ጎሎች 1.95 ሜትር ቁመት እያለው አክሮባቲክ ጎሎች ማግባት መቻሉ ፍጥነቱ ጉልበቱ እና ግምቱ ጥይት የሆኑት ሹቶቹ በጣም የሚገርሙ ናቸው ሜሲና ሮናልዶ በተደጋጋሚ የአለም ኮኮብ ተብለው ሲመረጡ እሱ አለመመረጡ ይገርመኛል በአሁኑ ሰአትም ፓሪስ ሴንት ጀርመን የፈረንሳይ ዋንጫ እንዲበላ ከማድረጉም በላይ በቻምፒየን ሊጉም ሀይለኛ ተፎካካሪ አድርጎት እንደነበረ ይታወቃል

እስቲ ደግሞ አንዳንዶቹን የሰፈር ትዝታዎች ከቀሰቀሰብህ የሮናልዲኖን ድሪብል እና ሰማይ ላይ ሲጠብቁት መሬት እየመታ የሚያገባቸውን የቅጣት ምቶች ታስተውልልኝ ዘንድ ልጋብዝህ

http://www.youtube.com/watch?v=1Arb7XPG-jw
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ሻቬዝ-x » Wed Jun 25, 2014 2:11 pm

ጌታ wrote:ሁጎ - በኔና በገልብጤ መካከል ከሆንሽማ 44 ነሽ ማለት ነው :lol: :lol: :lol: ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነሻ :wink:

ፓ ፓ ፓ ፓ ፓ አብራሞቪች እውነትም የቅሪላ ጂኒየስ ነው:: እዚ ዓለም ዋንጫ ላይ እኔ ደካማው የማልስተውን ጎል የሚ'ስቱት ያፍሪካ ሸፋፎች ይህን ቪዲዮ ቢያሳይዋቸው ጥሩ ነበር::

ሶል - ትዝ ይለኛል ድሮ ሰፈር ውስጥ በጨርቅ ኳስ ያብራሞቪችን የመሳሰሉ ጎሎች ስታገባ ቂቂቂቂ አንተ እኮ አውሮፓ ተወልደህ ቢሆን በብዙ ነገር የት በደረስክ

ሰላም ጌታ

እድሜዬን በጣም ደርሰህባታል አንድ አመት ብትጨምርልኝ ወይ ብትቀንስብኝ ነው ግዴለም :) ይገርማል ግን ዘመኑ ተቀይሮ ይህችም አንድ ፍሬ ልጅ ማስባልዋ :lol: ድሮ እኮ እናቶቻችን በ 12 አመታቸው እንዴት የበሰሉ ነበሩ አባቶቻችን በ 15 አመታቸው አዋቂዎች አምባ ነበር የሚውሉት የዘመኑ ሴት ግን በ 30 አመቷ እንደህጻን ስታስብ ታገኛታለህ በ 18 አመቷማ ገና ኑኑ ናት ጡጦ ያልጣለች በ40 አመት አባቶቻችን የልጅልጅ ይመክሩበት ነበር አሁን ግን የሊጅ እድሜ ሆነ 60 አመት እራሷ አሁን ጩጨ ሆነች እኮ ለወንዶች :D

ወደአፍሪካኖች ጨዋታ ስንመጣ እንዳልከው ሸፋፋ ነገር ስለነበሩ የትም አይደርሱም ብዬ ነበር ሆኖም ባለፈው ጋና ከጀርመን ያደረገውን ጨዋታ ተመልክቼ እጅግ ተደንቅያለው ጋና ብቃት ባለው አጨዋወት አይደፈሬ ይመስል የነበረውን ጀርመንን ኦልሞስት አሸንፎት ነበር ናይጄርያ ወደሚቀጥለው ዙር ለማለፍ እኩል መውጣት በቂው ነው አልጄርያና አይቮሪኮስትም ከፍልምያው አልወጡም ስፔን እንግሊዝና ጣልያን በተሰናበቱበት ሁኔታ ይህን ያህል መገተራቸው መልካም ነው ከንግዲህ ያሉት የአፍሪካውያን ጫወታዎች ወሳኝ ናቸው እዚ ደርሰው እንደማይንሻፈፉ ተስፋ እናድርግ :D

መልካም ውጤት እንመኛለን !
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ሻቬዝ-x » Thu Jun 26, 2014 9:39 am

እንግዲህ ወደ ፋይናል 16 ውስጥ እየተገባ ነው

1. ሆላንድ ሜክሲኮን ይገጥማል ሆላንድ ባለው ጥንካሬ በሩበን እና ቫን ፐርሲ ሜክሲኮን ያሸንፋል ብዬ እጠብቃለው

2; ብራዚል ከቺሊ :- ብራዚል አስፈሪ ክለብ መሆኑ ከነሮናልዲኖ ጋር አክትሞለታል አሁን ብራዚል እንደማንኛውም ተራ አገር ክለብ ሆንዋል ስለዚህም ቺሊ ያሸንፋል ብዬ እጠብቃለው

3. ናይጄርያ ከፍራንስ :- ናይጄርያ እዚህ መድረሳቸው መልካም ሆኖ ሳለ ፈረንሳይ ግን ይዞ የቀረበው ምርጥ ክለብ በመሆኑ ሊቋቋሙት አይችሉም ፈረንሳይ በጥራት ያሸንፋል
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ክቡራን » Thu Jun 26, 2014 8:04 pm

አሪፍ ነው ...ቫቬዝ ነፍሴ..እንደው እነዚህ ቪዲዮዎች ግን ከማስደሰትና ከማዝናናት ባሻገር ልቤን በትዝታ ወደ ኌላ እየመለሱት እያስተከዙኝ ነው:: ምን ይደረግ...!!!! በተለይ በረኛውን እያለፈ የሚያገባቸውን ጎሎች ሳይ የያን ጊዜ የሜዳ ውሎዬ ታየኝ:: አምስት አጥፌ አንዱን በላይለን ( በግሩ መሀል አሾልኬ) ያገባሁት ጎል እዚህ ላይ መጥቀሱ አስፈላጊ ባይሆንም ነገርን ነገር ያነሳዋልና ቢጠቀስ አይከፋም እላለሁ:: እኔ እንኴን ስለራሴ መናገር አልፈልግም ነበር...ግን ሆድ አስባስከኝ!! ችግሩ እኛ ስንጫወት ወንዳታ የሚል የቲፎዞ ጭብጭባ እንጂ የነበረው ቪድዮ ይዞ የሚቀርጸን አልነበረም:: አይ ድህነታችን!! ዛሬ ይሄ ሁሉ የምታየው የፈረንጅ ተጫዋች ሚሊየነር የሆነው ታሪኩ በቪዲዮ ስለተቀረጸለትም ይመስለኛል:: የኛ ታሪክ ጠላ ቤት ግድግዳ ላይ ተቀርጿል:: :D ወዳጄ ሁጎ ለማንኛውም እጊዚአብሄር ይስጥህ:: ሲመችህ ደሞ ካለም ዋንጫ ( የዚህን አመት ) ሀይላይት የተደረጉትን ካገኘህ ላክልኝ:: አመሰግናለሁ:: ያቺን ስምህን ብሞትም ለማንም አልናገርብህም:: :D

ሻቬዝ-x wrote:
ክቡራን wrote:ወዳጄ ሁጎ ምስጋናየ ይድረስህ....የኢብራሂሞቪችን ጨዋታዎችንና ግቦች አየኌቸው.. ድንቅ የኴስ ችሎታ አለው:: አንደኛው በመቀስ ምት ተገልብጦ ያገባትን ግብ ሳይ በልጅነት ለሰፈራችን ቡድን ስጫወት ያገባሁትን ግብ አስታወሰኝና ትንሽ አስተከዝከኝ:: ጥሩ አላደርክም ቫቬዝ ነፍሴ .. ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ:: እስኪ ሌላ ጨምርልኝና ካሰኝ:: :D

ሁጎ ሻቬዝ-x wrote:
ክቡራን wrote:እባካች ሁን የስፖርት ቤተስቦች ኡጎ ቫቬዝ (ተሳስቼ በድብቅ የምታጠቃበትን ስም ልጠራው ነበር ) :lol: ወይም ጌታ እስኪ አንዳንዴ ምርጥ ምርጥ የሆኑ ግቦችን የሚያሳዩ ሊንኮችን ስታገኙ ለጥፉልን ስል በስራና ባንዳንድ ምክንያት ጨዋታው ባመለጣቸው ስም በትህትና እጠይቃለሁ::
አክባሪያቹ:: :D

ወዳጄ ክቡራን ቀልቤን መግፈፍ ስራየ ብለህ ያዝከው አይደል ሆኖም ያኛውን ስሜ ቀርቶ ይህንን ስሜን እንክዋን በትክክል አልጠራኸውም ኡጎ ሳይሆን ሁጎ ነው :D

ለማንኛውም በአሁኑ አገሩ ስላልተካፈለች በዚህ የአለም ዋንጫ ላይ ባናየውም በግሌ ከሜሲ እና ከሮናልዶ ይበልጣል ብዬ የማምንበትን የዝላታን ኢብራሂሞቪች ምርጥ ግቦችን እንድትኮመኩም ወዲህም ችሎታውን እንድታይልኝ እጋብዝሀለው http://www.youtube.com/watch?v=XYan94S8slU

ወዳጄ ክቡ ኢብራሂሞቪች ትዝታህን ቀሰቀሰው አይደል ..ህይወት ግን ምን ጣእም አላት ብለህ ነው ስንቶቹ የተቀኙለት ትዝታ ባይኖር ... በርግጥ ልጁ የሚገርም ችሎታ አለው ጀርባውን ለጎሉ ሰጥቶ ባለበት ሁኔታ የሚያገባቸው ጎሎች ..በተረከዙ የሚያገባቸው ጎሎች 1.95 ሜትር ቁመት እያለው አክሮባቲክ ጎሎች ማግባት መቻሉ ፍጥነቱ ጉልበቱ እና ግምቱ ጥይት የሆኑት ሹቶቹ በጣም የሚገርሙ ናቸው ሜሲና ሮናልዶ በተደጋጋሚ የአለም ኮኮብ ተብለው ሲመረጡ እሱ አለመመረጡ ይገርመኛል በአሁኑ ሰአትም ፓሪስ ሴንት ጀርመን የፈረንሳይ ዋንጫ እንዲበላ ከማድረጉም በላይ በቻምፒየን ሊጉም ሀይለኛ ተፎካካሪ አድርጎት እንደነበረ ይታወቃል

እስቲ ደግሞ አንዳንዶቹን የሰፈር ትዝታዎች ከቀሰቀሰብህ የሮናልዲኖን ድሪብል እና ሰማይ ላይ ሲጠብቁት መሬት እየመታ የሚያገባቸውን የቅጣት ምቶች ታስተውልልኝ ዘንድ ልጋብዝህ

http://www.youtube.com/watch?v=1Arb7XPG-jw
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሻቬዝ-x » Sat Jun 28, 2014 7:41 am

ሰላም ክብራን እስካሁን እየቀለድክ ይመስለኝ ነበር አሁን ግን የሆነ እውነት ያዘለ ነገር ሊኖርህ እንደሚችል ገመትኩ

እኔም እንዳንተው ሰፈር ኳስ እጫወት ነበር እኔ እንኳን እንዳንተ የምኩራራበት ችሎታ አልነበረኝም አንድ ግዜ በደረቴ ያቅምኳት ኳስ አትረሳኝም :lol: ሆኖም ለስሜት እጫወት ነበር እንዳልኩህ ከባድ የኳስ ችሎታ ነበረኝ ባልልም በዛን ዘመን ቆንጆ የተባለ ኳስ ባለቤት ነበርኩ ስለዚህም በሰፈሩ ተፈላጊ ነበርኩ አሁን ኮንዶሚንየም ቤቶ የተሰሩበት ሰፊ ባዶ ሜዳ ስለነበረንም ቅዳሜና እሁድ ጥሩ መራገጫ ነበረን

እናም አሁን ትዝ የሚለኝና አንተ ያስታወከኝ ነገር በኳሷ አርት የሚሰሩ ምርጥ ምርጥ ልጆች እንደነበሩ ከነስማቸው በትክክል አስታውሳለው እነዚህ ልጆች በደንብ ቢያዙ እርግጠኛ ነኝ ከብራዚል ተጫዋቾች ከነሮናልዲኖ ከአርጀንቲናዎቹ ከነሜሲ የማይተናነስ ተጫዋች ይወጣቸው ነበር ...ግን የሀገራችን ነገር ሆነና የሚያያቸው ጠፍቶ ችሎታቸው እዛው ሰፈር ተቀብሮ ቀረና እድሚያቸውም አለፈ ሌሎችም ስንቶች እንደዚሁ ባክነው ቀርተዋል ..አንተም ከነዚህ የተፈጥሮ ችሎታ ከነበራቸው ልጆች አንዱ ከነበርክ እና የሚይዝህ ብታገኝ ይሄኔ ከነድርግባ የማትተናነስ የአለማችን ኮኮብ ትሆን ነበረ ..ውስጥህ ኳስ ተጫዋች ሆኖ ሳለ ሌላ ያንተ ያልሆነ ሞያ ላይ መስማራት ይህ በርግጥ ሊያስተክዝ እንደሚችል አሁን ተረዳሁልህ

የዛች ስሜን ነገር ነካክተህ ነካክተህ እሪ ብዬ እራሴን እንዳጋልጥ ፈልገህ ነው አይደል ? :lol:

የሆላንድን ጣፋጭ ብቀላ የቫን ፐርሲን እና የሩበንን ምርጥ ግብ እንድታይልኝ ይህችን ልጋብዝህ
http://www.youtube.com/watch?v=l2BawrOU31A

ክቡራን wrote:አሪፍ ነው ...ቫቬዝ ነፍሴ..እንደው እነዚህ ቪዲዮዎች ግን ከማስደሰትና ከማዝናናት ባሻገር ልቤን በትዝታ ወደ ኌላ እየመለሱት እያስተከዙኝ ነው:: ምን ይደረግ...!!!! በተለይ በረኛውን እያለፈ የሚያገባቸውን ጎሎች ሳይ የያን ጊዜ የሜዳ ውሎዬ ታየኝ:: አምስት አጥፌ አንዱን በላይለን ( በግሩ መሀል አሾልኬ) ያገባሁት ጎል እዚህ ላይ መጥቀሱ አስፈላጊ ባይሆንም ነገርን ነገር ያነሳዋልና ቢጠቀስ አይከፋም እላለሁ:: እኔ እንኴን ስለራሴ መናገር አልፈልግም ነበር...ግን ሆድ አስባስከኝ!! ችግሩ እኛ ስንጫወት ወንዳታ የሚል የቲፎዞ ጭብጭባ እንጂ የነበረው ቪድዮ ይዞ የሚቀርጸን አልነበረም:: አይ ድህነታችን!! ዛሬ ይሄ ሁሉ የምታየው የፈረንጅ ተጫዋች ሚሊየነር የሆነው ታሪኩ በቪዲዮ ስለተቀረጸለትም ይመስለኛል:: የኛ ታሪክ ጠላ ቤት ግድግዳ ላይ ተቀርጿል:: :D ወዳጄ ሁጎ ለማንኛውም እጊዚአብሄር ይስጥህ:: ሲመችህ ደሞ ካለም ዋንጫ ( የዚህን አመት ) ሀይላይት የተደረጉትን ካገኘህ ላክልኝ:: አመሰግናለሁ:: ያቺን ስምህን ብሞትም ለማንም አልናገርብህም:: :D

ሻቬዝ-x wrote:
ክቡራን wrote:ወዳጄ ሁጎ ምስጋናየ ይድረስህ....የኢብራሂሞቪችን ጨዋታዎችንና ግቦች አየኌቸው.. ድንቅ የኴስ ችሎታ አለው:: አንደኛው በመቀስ ምት ተገልብጦ ያገባትን ግብ ሳይ በልጅነት ለሰፈራችን ቡድን ስጫወት ያገባሁትን ግብ አስታወሰኝና ትንሽ አስተከዝከኝ:: ጥሩ አላደርክም ቫቬዝ ነፍሴ .. ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ:: እስኪ ሌላ ጨምርልኝና ካሰኝ:: :D

ሁጎ ሻቬዝ-x wrote:
ክቡራን wrote:እባካች ሁን የስፖርት ቤተስቦች ኡጎ ቫቬዝ (ተሳስቼ በድብቅ የምታጠቃበትን ስም ልጠራው ነበር ) :lol: ወይም ጌታ እስኪ አንዳንዴ ምርጥ ምርጥ የሆኑ ግቦችን የሚያሳዩ ሊንኮችን ስታገኙ ለጥፉልን ስል በስራና ባንዳንድ ምክንያት ጨዋታው ባመለጣቸው ስም በትህትና እጠይቃለሁ::
አክባሪያቹ:: :D

ወዳጄ ክቡራን ቀልቤን መግፈፍ ስራየ ብለህ ያዝከው አይደል ሆኖም ያኛውን ስሜ ቀርቶ ይህንን ስሜን እንክዋን በትክክል አልጠራኸውም ኡጎ ሳይሆን ሁጎ ነው :D

ለማንኛውም በአሁኑ አገሩ ስላልተካፈለች በዚህ የአለም ዋንጫ ላይ ባናየውም በግሌ ከሜሲ እና ከሮናልዶ ይበልጣል ብዬ የማምንበትን የዝላታን ኢብራሂሞቪች ምርጥ ግቦችን እንድትኮመኩም ወዲህም ችሎታውን እንድታይልኝ እጋብዝሀለው http://www.youtube.com/watch?v=XYan94S8slU

ወዳጄ ክቡ ኢብራሂሞቪች ትዝታህን ቀሰቀሰው አይደል ..ህይወት ግን ምን ጣእም አላት ብለህ ነው ስንቶቹ የተቀኙለት ትዝታ ባይኖር ... በርግጥ ልጁ የሚገርም ችሎታ አለው ጀርባውን ለጎሉ ሰጥቶ ባለበት ሁኔታ የሚያገባቸው ጎሎች ..በተረከዙ የሚያገባቸው ጎሎች 1.95 ሜትር ቁመት እያለው አክሮባቲክ ጎሎች ማግባት መቻሉ ፍጥነቱ ጉልበቱ እና ግምቱ ጥይት የሆኑት ሹቶቹ በጣም የሚገርሙ ናቸው ሜሲና ሮናልዶ በተደጋጋሚ የአለም ኮኮብ ተብለው ሲመረጡ እሱ አለመመረጡ ይገርመኛል በአሁኑ ሰአትም ፓሪስ ሴንት ጀርመን የፈረንሳይ ዋንጫ እንዲበላ ከማድረጉም በላይ በቻምፒየን ሊጉም ሀይለኛ ተፎካካሪ አድርጎት እንደነበረ ይታወቃል

እስቲ ደግሞ አንዳንዶቹን የሰፈር ትዝታዎች ከቀሰቀሰብህ የሮናልዲኖን ድሪብል እና ሰማይ ላይ ሲጠብቁት መሬት እየመታ የሚያገባቸውን የቅጣት ምቶች ታስተውልልኝ ዘንድ ልጋብዝህ

http://www.youtube.com/watch?v=1Arb7XPG-jw
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ሻቬዝ-x » Tue Jul 08, 2014 10:13 pm

አይ ብራዚል

በየአንዳንድ ደቂቃ ልዩነት ጎሎልችን አስተናግደው ገና በግማሹ 5-0 እየተመሩ ነው

ግቦቹ የገቡበት ፍጥነት በሪከርድነት ሳይመዘገብ አይቀርም በየ አንድ አንድ ደቂቃ ልዩነት :?: :shock:

በሁለተኛ ተጨማሪ ግቦች ይጠበቃሉ
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ክቡራን » Tue Jul 08, 2014 11:36 pm

ሰላም ሁጎ ነፍሴ...ባለፈው ይሄ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ለምክክር ነግሬው ነበር...ሰማይ የገለጸልኝ ሚስጥር ነበር:: ይሄን ዋንጫ ጀርመን ያነሳዋል ብዬ ነበር....!! ለምክክር የመለስኩለትን እዛኛው ልፍል ግባና አንብብ::ዋንጫውን ጀርመን ያነሳዋል:: ይሄ የዛሬው ውጤት ምስክር ይሁንህ:: ችግሩ ነቢይ ባገሩ አይከባበርም ሆነና ትንሽ እንደው አንከባበርም:: ትንሽ ብንከባበርና ለኛም የሚገባን ና የደንቡ ቢሰፈርልን መልካም መሰለኝ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሻቬዝ-x » Wed Jul 09, 2014 7:30 am

ክቡራን wrote:ሰላም ሁጎ ነፍሴ...ባለፈው ይሄ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ለምክክር ነግሬው ነበር...ሰማይ የገለጸልኝ ሚስጥር ነበር:: ይሄን ዋንጫ ጀርመን ያነሳዋል ብዬ ነበር....!! ለምክክር የመለስኩለትን እዛኛው ልፍል ግባና አንብብ::ዋንጫውን ጀርመን ያነሳዋል:: ይሄ የዛሬው ውጤት ምስክር ይሁንህ:: ችግሩ ነቢይ ባገሩ አይከባበርም ሆነና ትንሽ እንደው አንከባበርም:: ትንሽ ብንከባበርና ለኛም የሚገባን ና የደንቡ ቢሰፈርልን መልካም መሰለኝ:: :D

ሰላም ክቡ
የምክክርን ግምት አየሁት he has got it all wrong ! አንተ እስካሁን ሰማይ የገለጠልህ የያዘ ይመስላል እኔም ጀርመን ብራዚልን ያሸንፋል የሚል መገለጥ ነገር ነበረኝ መሰል ግን እንደው 1-0 ወይንም እስከ ፔናልቲ ሄደው ጀርመን ያሸንፋል አይነት ነገር መገለጥ እንጂ አልጄርያን በመከራ ያሸነፈው ጀርመን 7 ጎል ብራዚል ላይ ያርከፈክፋል የሚል ነገር ገላጩ አልገለጠልኝም ይህ ስኮር ላይን የተገለጠለት አንድም ተገላጭ ያለም አይመስለኝም

እኔ የምለው ግን እኔ እና አንተ የድሮ የሰፈር ከዋክብት ሰብሰብ ብለን ጀርመንን ብንገጥም እርግጥ 15 ለ 0 እንሸነፍ ይሆናል ነገር ግን በ5 ደቂቃ 4 ጎል ፈጽሞ አይገባብንም !ሊገለጥልኝ ያልቻለው የጎሉ ብዛት ሳይሆን በአጭር ደቂቃዎች የወረደባቸው የጎል ናዳ ነው የብራዚል ካፒቴኑ ቲያጎ ሲልቫ መቀጣት ቡድኑን ወና እንዳደረገው ታይትዋል

ስለዛሬው ጨዋታስ ሰማያዊ መገለጥ ምን ይልሀል ? :D እኔ የሆላንድ ደጋፊ ስለሆንኩ ሆላንድ ያሸንፋል እላልለው

በመጨረሻው መገለጥ ላይም እንለያያለን ጀርመን አስፈሪ ቡድን ቢመስልም ሆላንዶች እንዴት እንደሚያቆምዋቸው ያውቃሉ

መጨረሻው የዳቾች ነው
ሻቬዝ-x
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 232
Joined: Tue Nov 17, 2009 5:48 am

Postby ክቡራን » Wed Jul 09, 2014 5:13 pm

ሁጎ ነፍሴ እረ ያገርህ ልጆች ጨርቃቸውን ጥለው ማበዳቸው ነው...አረ አንድ በላችው.! :lol:
https://www.facebook.com/photo.php?v=83 ... =2&theater
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron