አትሌቲኮ ወይንስ ባርሣ? ...ማን ይበላዋል?

ስፖርት - Sport related topics

አትሌቲኮ ወይንስ ባርሣ? ...ማን ይበላዋል?

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sat May 17, 2014 4:24 pm

30 ደቂቃ ቀርቶታል... አባ
ትንቅንቅ ነው ዛሬሬሬ....
አያ ሆ ሆ ማታ ነው ድሌ...ድሌ ማታ ነው ድሌ....አያሆሆ!!

እኔ አትሌቲኮ ማድሪድ እንዲበላ እፈልጋለው.... እስኪ ሙያዊ የስፖርት ክፍል ሰዎች ኑና አስተያየት ስጡበት.

ሜሲ ጉድ ፈላበት!!
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ገልብጤ » Sat May 17, 2014 7:57 pm

ዘጌ-ዘጋምባው...እኔም
አትሌቲኮ እንዲበላ ነበር ምኞቴ..ተሳክቷል አይ ሜሲንማ ተወው..ዋንጫ ሰልችቶታል ሜዳው ላይ ርሱ ሜሲ የሌለ ነው የሚመስለው
አርስናልም በላ...ቂቂቂቅ ድንቄም :roll: :roll: አለች ዌንገር

አሁን ደግሞ የባየርን እና የዶርትሞንድን እየተከታተልኩ ነው...ትንሽ በረድ ይላል..እጄን ቺኬ ጭን ወስጥ ገብቴ እያሟሟኩ ነው
ናብ ይበላል የጀርመኑን ዋንጫ
ዶርትሞንድ ቢበላ አርፊ ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Mon May 19, 2014 9:17 pm

ገልቤው...የገለምሶው...ማለቴ ገለምሶ የቃመም ገለምሶ የኖረም ገለምሶ የተወለደም..ያው ነው ብዬ ነው..የገለምሶው ያልኩሽ ...ከቃሙት ጎራ ነሽና...

ስማ እንጂ?...እንዴ.. ድሮ ከሀገሬ ስወጣ እርግፍ አርጌ የተውኩትን አርሴ ማንቼ ምናምን ቅሪላ... እንደአሰላ ብርድ ከሆዴ አልወጣም ለካስ...አገርሽቶብኝ አሁን እኔ ነኝ ያለ የፉትቦል ተከታታይ ሆኜልካለው...
በአትሌቲኮ ባለድልነት ደስታችኝ አንድ በመሆኑም እንኳን አብጺእኩም ብዬካለው!! ያ አሸዋ ግርፍ ፊቱ ኮስታ ተጎድቶ ሲወጣ ሽምቅቅ እንዳልኩ ወድያው ደሞ ጢሞ አርዳ ቱራንን... ያ ሾካካ ፊት ፋብሪጋስ ደንደሱን ብሎ ከጥቅም ውጭ ሲያረገው... በቃ አትሌቲኮ ላይ ግራ ቆለጥ እንደተያዘባቸው ደመደምኩልክ... በነገራችን ላይ የእሱን ልጅ ጉዳት ቪድዮውን ዩዌፋ ድጋሚ ሊመረምረው ይገባል... ይቺ ደቃቃ ፋብሪጋስ በጩቤ ብትወጋው ነው እንጂ በምናባትዋ አቅምዋ ነው ሰው ጎድታ የምታስወጣው... ብቻ ለማንኛውም ነገረኛዎቹ እንግሊዞች የስፔንን ሊግ ምን ብለው እንደሚተርቡት ሰማክ? " ጸሀያማዋ ስኮትላንድ" !! .....ለምን እንደዛ እንዳልዋቸው ካልገባሽ በሚቀጥለው ሙሉ ማብራርያ እስከነ ግርጌ ማስታወሻው እለቅብሻለው.... :lol:

.... ማንቼም ያን በግ አይን ሞዬስን አባራ.. በ ጊግስ አለሳልሳ ....ትቢተኛውን አሰልጣን ቫንጋልን ዛሬ ሾመች.... በፊትም ተሳስተዋል..ሞዬስ እኮ ቡድኑን እብድ የያዘው በሶ አስመስሎት ዋለ... ( ቂቂቂቂ..ይቺ የበሶዋ ነገር ከሰሞኑ የናንተ ፖለቲክስ ውይይት የቀለብኳት አባባል ናት) .....


ብቻ እልካለው...የፉትቦል ነገር አገርሽቶዋልና... ከሰሞኑ ስለ ቻምየንሊግ ፋይናል...አትሌቲኮ ከ ሪያል ጋር..ይቀደዳል... ያው እንደተለመደው የአትሌቲኮ ነኝ እኔ.... ማድሪድ በጣም የምጠላው ቲም ነው.... ለኔ ሪልማድሪድ ማለት./..ቆንጆ ገርልፍሬንድክን ይዘክ ልትዝናና ክለብ ስትሄድ ከሚድናይት በውሀላ በፌራሪ መኪናው ከ አንትራዡ ጋ..ከች ብሎ ቪአይፒ ዱቅ ብሎ በውድ መጠጥ እየተዝናና አካብዶ ( አንተ ኮሮናክን እየመጠመጥክ)...የፈራከው አልቀረም ክለቡ ሳይዘጋ ገርልክን ይዞ የሚሸብለለ ሀብታም ጋይ ነው.... ስለዚ 3-0 አትሌቲኮ!! ቫሞኖስ

ስለአለም ዋንጫም እንቀባጥራለን....
የአለም ዋንጫ ስቱርዮ ፓናሊስቶችን ልማስተዋወቅ ያክል....

1. እኔ (መድረክ መሪ)
2. ዲጎኔ ( ድሮ ውቤ በረሀ አብሮ የተዝናናቸው ታዋቂ ተጭዋቾችን ታሪክ ከነ ክርስትያኖ ሮናልዶ ጋ እያመሳከረ አስተያየት ይሰጣል)
3.ወርቅሰው (ሰማይ ቤት ያሉት የቀድሞ አለማቀፍ ፉትቦል ስታሮችን ኢንተርቪው እያደረገ ያቀርብልናል)
4. ተጋባዥ ልዩ እንግዳ ( እንደወቅቱ አጀንዳ)


የዛ ሰው ይበለን...
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ገልብጤ » Tue May 20, 2014 8:42 pm

ዘጌ-ዘጋምባው
ገለምሶ ያከሳው
ሰላም አባ ..እንዴት ነክ ባያሌው
ገልቤው ...የገለምሶው ...ማለቴ ገለምሶ የቃመም ገለምሶ የኖረም ገለምሶ የተወለደም ..ያው ነው ብዬ ነው ..የገለምሶው ያልኩሽ ...ከቃሙት ጎራ ነሽና ...

ቅቅቅቅቅ...ባይገርምህ ከአገር ስወጣ ገለምሶ እንዳይወደድ ብዬ ከቤታችን ጐሮ የገለምሶ ችግኝ ተክዬ አብቦልኝ ስመለስ ቀምበጥ ቀምበጡን እቅመዋለሁ ብዬ ..ገና በንጭጩ ጓሯችን ለልማት ብሎ ሲፈርስ ገለምሶወም አብሮ ፈረሰ እልሀለሁ
ስማ እንጂ ?...እንዴ .. ድሮ ከሀገሬ ስወጣ እርግፍ አርጌ የተውኩትን አርሴ ማንቼ ምናምን ቅሪላ ... እንደአሰላ ብርድ ከሆዴ አልወጣም ለካስ ...አገርሽቶብኝ አሁን እኔ ነኝ ያለ የፉትቦል ተከታታይ ሆኜልካለው

አበሻ ከአገር ሲወጣ ይዞት የወጣው ኮተት መች የዋዛ ይለቀዋል ብለክ ነው ያው ለትዝታ ይሆንሀል
በአትሌቲኮ ባለድልነት ደስታችኝ አንድ በመሆኑም እንኳን አብጺእኩም ብዬካለው

ቅቅቅቅቅ
ያ አሸዋ ግርፍ ፊቱ

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ያ አሸዋ ግርፍ ፊቱ ኮስታ ተጎድቶ ሲወጣ ሽምቅቅ እንዳልኩ ወድያው ደሞ ጢሞ አርዳ ቱራንን ያ ሾካካ ፊት ፋብሪጋስ ደንደሱን ብሎ ከጥቅም ውጭ ሲያረገው ... በቃ አትሌቲኮ ላይ ግራ ቆለጥ እንደተያዘባቸው ደመደምኩልክ ...

እኔም ገርሞኛል ያው ተስፋ ወደመቁረጥ ብዬ ነበር..አስደግመውባቸው ይሆን ብዬ ነዋ
በነገራችን ላይ የእሱን ልጅ ጉዳት ቪድዮውን ዩዌፋ ድጋሚ ሊመረምረው ይገባል ... ይቺ ደቃቃ ፋብሪጋስ በጩቤ ብትወጋው ነው እንጂ በምናባትዋ አቅምዋ ነው ሰው ጎድታ የምታስወጣው ..

ድግምት ነው ባክክ
Code: Select all
 ( ቂቂቂቂ ..ይቺ የበሶዋ ነገር ከሰሞኑ የናንተ ፖለቲክስ ውይይት የቀለብኳት አባባል ናት )

የፖለቲካ ቤት ማልያሽ ቁጥር ይነገረና
ብቻ እልካለው ...የፉትቦል ነገር አገርሽቶዋልና ... ከሰሞኑ ስለ ቻምየንሊግ ፋይናል ...አትሌቲኮ ከ ሪያል ጋር ..ይቀደዳል ... ያው እንደተለመደው የአትሌቲኮ ነኝ እኔ

ያው እነኮስታ ከጉዳት ከተመለሱ ድሉ የአትሌቲኮ ነው
ስለአለም ዋንጫም እንቀባጥራለን ....
የአለም ዋንጫ ስቱርዮ ፓናሊስቶችን ልማስተዋወቅ ያክል ....

23 ቀን ቀረው ይቀባጠራል እንደጉድ
1. እኔ (መድረክ መሪ )

ጀምረህዋል እኮ አሁንም
2. ዲጎኔ ( ድሮ ውቤ በረሀ አብሮ የተዝናናቸው ታዋቂ ተጭዋቾችን ታሪክ ከነ ክርስትያኖ ሮናልዶ ጋ እያመሳከረ አስተያየት ይሰጣል )

የዲጎኔን መልስ እንጠብቃለን..ያው ጌታ የመንፈስ ታይቶኝ ነው ስራ ካላበዛበት
ባይገርምክ እሱ ምን ያልገባበት ቤት አለ ብለክ ነው...ከስባተኛ እስከ ይገባዋል ቤት
3.ወርቅሰው (ሰማይ ቤት ያሉት የቀድሞ አለማቀፍ ፉትቦል ስታሮችን ኢንተርቪው እያደረገ ያቀርብልናል )

እዚህ ላይ እኔ የለሁበትም .... ነብስህ አትማርም
4. ተጋባዥ ልዩ እንግዳ ( እንደወቅቱ አጀንዳ )

የዋርካው ጌታ ካሜራ ማን
እስኪ እስካዚያው ቸር እንሰንብት
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests