ብራዚል 2014 የአለም ዋንጫ

ስፖርት - Sport related topics

ብራዚል 2014 የአለም ዋንጫ

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Tue Jun 10, 2014 3:21 pm

በሉ እዚ ክፍል የ 2014 አለምዋንጫን በተመለከተ አስተያየታቹን... መላምታቹን....ትንታኔያቹን...ትዝብታቹን... እርግማናቹን....ጥንቆላቹን...እምባቹን...በቃ የፈለጋቹትን የምትሉበት እንዲሆን እነሆ በረከት...

እሺ ብራዚል ከክሮሽያ?.... እንዴት ነው?
የባርሳው ኔይማር ከ ማድሪዱ ሞድሪች....ይፋጠጣሉ....
1950 ላይ ህዝበ ብራዚልን ያኮማሸሸ... ዋንጫ ከጉሮሮው ፈጥርቆ ያወጣው የኡራጋይ ቡድንም..ባዲሱ ትውልድ..ልዊስ ሽዋሬዝ እየተመራ መጣሁ ብሎዋል..ታሪክ ሊደግሙ..!! ስፔንስ? ቲኪታካ..እዚም ጠቅ እዛም ጠቅ..አፍዝ አደንግዝ ፉትቦላቸው ላይ በላይ ዋንጫን ያስገኝ ይሆን?....የመጀመርያ ጨዋታቸው የ 2010 ፍጻሜ ድጌ እንዲሉ..ከኔዘርላዶች ጋ ነው.... መቼ?አርብ የቀን ምርጥ ነዋ!... ሮበን ለካሲላስ ያሳቀፈውን ያንድ ለ አንድ ቻንስ እስካሁን እንቅልፍ እንደነሳው ነው....በዚ ጨዋታ..ሀገሩን ይክስ ይሆን?....ብዙ ጉድ እናያለን!! ..አፍሪካስ?....ጋና ብላክስታሮች የአፍሪካችን ምርጥ ተስፎች... ግማሽ ፍጻሜ ገብተው ታሪክ ይሰሩ ይሆን?..እንጃ...ምድባቸው ከአለት የጠነከረ ነው... በታለንት የተጨናነቀን ጀርመንንና የክሪስታኖ ሮናልዶውን ፖርቹጋል ገፍትረው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል.... ኮትዲቭዋርስ?....ወርቃማው ትውልድ የመጨረሻ ቻንሱ?...ድሮግባ 36 አመቱ ነው...ያያቱሬ..ጉዳት ላይ ይመስላል...ትሬኒንግ ማድረግ እንኳን አልቻለም... ወንድሙን ኮሎቱሬ ቢጫ ወባ ትጫወትበታለች..ቅቅቅቅ.... ብቻ ምናለፋን...አይቮሪኮስት ተይዛለች!..... እነ ጣልያንስ? እብዱ ባላቶሊ ሰከን ብሎ ታሪክ ያስመዘግብ ይሆን?.... እንደ ወይን እያደር ችሎታው እየጣም መጣው አንድሬታ ፒርሎስ በ 35 አመቱ ጣልያንን ተሸክሞ ለድል ያበቃ ይሆን?..አጠገቡ የሰው ነብሩ...ዳኒዬል ደሮሲ አለ::... አርጀንቲናን የረሳሁ ከመሰላቹ ተሳስታቹሀል...!!.....ምትሀታዊው ሜሲ ለሶስተኛ ግዜ አለምዋንጫ እድሉን ሊሞክር ወደብራዚል አቅንቷል...ያሁኑን የሚለየው የቡድኑ አንጋፋና መሪ ተቻዋች መሆኑ ነው....ከአጠገቡ...እጅግ የሚገርም የአጥቂ መስመርን እናገኛለን... አጉወሮ..ዲማርያ...እና ሂጋዋኢን... እውነትም እሚገርም! ማንስ ሊያቆማቸው? በአንድ ጨዋታ ከ 3 ጎል በታች ካገቡ እንደውድቀት እንው ምቆጥርባቸው...ቅቅቅቅቅቅ..... ኳስን ፈጠርኩ ባል የምትኮፈሰው እንግሊዝስ ምን ይዛ ይሆን?... ባለተለመደም መልኩ ወጠጤ ተጭዋቾችን እንደጉድ አካታለች... የዘንድሮ ሊቨርፑልን ምርጥ ፎርም ይደግሙልኛል ብላ ከሊቨርፑል አንድ ቁና ተጭዋቾችንም አካታለች....ሩኒስ? የስም ብቻ ተጭዋች?... 3 አለም ዋንጫ ተጫውቶ 1 ጎል ያላገባ የደከመ አጥቂ...ቅቅቅቅቅ... ቤልጀምንስ እንዴት ነው ምናያት? ሀዛርድ..ካምፓኒ...ፈላኒ...ደምቤሌ.. ቀውላላው...የአትሌቲኮ በረኛ...እረ ብዙ ናቸው! ያስፈራሉ!!

መልካም ውድድር ::
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ዲጎኔ » Tue Jun 10, 2014 7:17 pm

ሰላም ዘጌው
ኩዋስ ድሮ ካታንጋ ሚስማር ተራ መጀመሪያ የኤሌትሪክ ከዚያም የመድህንና የትምህርትኮሚሽን ቲፎዞ እያለን ቀረ!
ኩዋስ ሆነ ሩጫ ለእኔ ለህዝቦች ትግል ነው የምደግፈው::ያ የእግር ኩዋስ ንጉስ ያልነው ፔሌ ጥቁርነቱን የማይቀበል ጭራሽ ለጥቁር ከመቆም ተገዳዳሪ ነው የሚል በራሪ ወሬ ሰምቻለሁና ሀቁን ንገረኝ::
አንድ ጊዜ ቱኒሲያ ከቤልጂየም ሲጋጠም አይዞን የአፍሪካ ቡድን ስል ቱኒሲያዊው እኛ አረብ ነን ሲለኝ ቤልጂየምን ስደግፍ ውያለሁ ቅቅቅቅ
ዲጎኔ ሞረቴው ክብር ትሪቡን ከሀቀኛው ሰሜን አሜሪካ ኩዋስ ፌደሬሽን ከተለጣፊ ኢያያና ገ/መስቀል የአላሙዲ ቡችሎች ሩቅ ማዶ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Thu Jun 12, 2014 1:08 pm

እንደምነክ ጋሽ ዲጎኔ? .... ይገርምካል እኔም ባንድ ወቅት የመድን ድርጅት ደጋፊ ነበርኩ....የመሀል ሜዳ ቅመሙ አብዲ በሚጫወትበት ሰአት ማለት ነው....ከዛን ደሞ የኤሌክትሪክ ጽኑ ደጋፊ ሆንኩ...በጋሽ ሀጎስ አሰልጣኝነት በሚመሩበት ሰአት ማለት ነው....ከዛ ባለፈ..ሎያል ደጋፊ አይደለሁም..ጥሩ ለተጫወተ ቡድን ነው ድጋፌ ማለት ነው....

ፔሌ ትንሽ ራሱን እንደሚያመው አታውቅም እንዴ?...ሰውየው ሁሌ የሚሰጠው መግለጫና ኢንተርቪው የባጥ የቆጡን በማውራት..የተዛባ ግምት ..አልባሌ ነገሮችን በመናገር...አለም ሚድያ መሳለቅያ ነው.... ከቁምነገር አልቆጥረውም....
ቅቅቅቅ..የቤልጀም ከ ቱንዝያው የደረሰብክ አጋጣሚ.....እያሳቀ የሚያቆስል መራር እውነት ነው..... ግን እኛው ሀገርስ ....ባቅሚቲ ሬሲስት እየሆንን አይደለምን?..... ባለፈው ቀን የቡና ገበያ ጋምቤላዊ ተጭዋችን...በጦጣ ደምጽ ሲያንግዋጥጡ አልዋሉም?.... ይህን ክስተት በህይወቴ በጣም ካዘንኩባቸው አጋጣሚዎች ጎራ መድቤዋለሁ...

ብራዚል ከ ክሮሽያ.....ሊጀመር ነውውውውውውውው....

ግምታቹን ዱቅ ዱቅ አርጉ እንጂ..
ገለባብጤው.. ና ውጣ ከተደበክበት...
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ጌታ » Thu Jun 12, 2014 4:02 pm

ብራዚል 2 - ክሮኤሽያ 1
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ገልብጤ » Sat Jun 14, 2014 5:40 pm

የትምህርትኮሚሽን ቲፎዞ እያለን ቀረ
ገና ሳንጸነስ :roll: :roll: :roll: :roll: :roll: እንዲህም የሚባል ክለብ ነበር ለካ :roll: :roll:
ይህ መናፍቅ ጥምዝ ይዞራል ግን ..በየቦታው እየገባ ወደፊት ሲሉት ጥምዝ ወደኍላ ይዞራል ..ኤጭ :twisted: :twisted: :twisted:
ዘጌው አለው ሰላም ነክ ...በአለም ዋንጫ አይንክን እየሞራረድክ ነው ስሞናቱን ..የአለም ኮከቧ ስፔን ቲኪ ታካ ይዛ መታ ጉድ ሆነችልህ አይቀጡ ቅጣት ነው የቀጧት ..በረኝውንማ ሮበን ሲያንገላታው ...ቅቅቅቅቅ በቃ የሚያሳዝን ነገረ ሆነብኝ
እስኪ የዛሬውን የጣልያን እና የንጊሊዝ..ቅቅቅ
ጨዋታ ልገምት
ጣልያን 2-1 ንጊሊዝ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sun Jun 15, 2014 6:28 pm

የምጽፈው የ ኢኳዶር-ስዊዘርላንድን ጨዋታ እያየሁ ነው>>

ዘንድሮ አለም ዋንጫ ግን አልሬዲ ካለፈው ተሽሎ አግኝቼዋለሁ..... ምርጥ ጎል.. ምርጥፉክክር..ያልታሰቡ ውጤቶች...ካሁኑ እያስደሰቱን ነው አቦ.... የቫንፔርሲ ጎል እስካሁን እየገረመኝ ነው ያለው ..በጣም! ....

ቅቅቅቅ..የሩኒ ኮርና እንዴት አያቹት?.... :lol: ....ግን ለጎልዋ አሪፍ ክሮስ ነው ያረገው.... ፒርሎ ጣልያናዉው አርኪቴክት... አስደናቂ ችሎታውን አሳይቶናል...

ዛሬ ታላቁ ሜሲ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል....አርጀንቲና ከ ቦስኒያ..... ሀትትሪክ እንደሚሰራ...ይሰማኛል....እሱ ባይሰራ..አግወሮ...ይሰራል...ዲማርያ በራሪውስ? ...

ካሁኑ ስገምት ዋንጫው ከ ጀርመን እና አርጀንቲና አያልፍም....
የብራዚል ነገር ተከድኖ ይብሰል.... ስፔን..አቃቃቃቃቃቃ..... ያስቃሉ....

ቶሎ ኑና አስተያየት ጠብ ጠብ አርጉ
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ቱሉቦሎ » Sun Jun 15, 2014 9:12 pm

ትላንትና የአይቮሪኮስት በረኛ ሲያበሳጨኝ ነበር :: ምንም የማይቀሳቀስ ከረፈፍ በረኛ ነው :: መለወጥ አለበት
ደግነቱ አጥቂዎቹ በስተመጨረሻ ጥሩ ተንቀሳቅሰው ጃፓንን 2 ለ 1 በማሸነፋቸው ደስ ብሎኛል

ስዊዘርላንድ 30 ሰከንድ ሲቀረው ጎል አግብታ አሸንፋለች

ዘጌው እንዳልከው የብራዚል ኦሎምፒክ እግርኳስ ጨዋታ ጮማ ነው :: እየኮመኮምኩት ነኝ

የታዘብኩት ነገር
ብራዚል ግማሽ ያክል ህዝቡ ጥቁር ቢሆንም ተጫዋቾቹን አጅበው ከሚወጡት ህጻናት ጥቁር አላየሁም
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Postby ክቡራን » Sun Jun 15, 2014 10:52 pm

ትናናሽ ጭንቅላቶች ቀለምን ትላልቅ አእምሮዎች የኴሥ ጥበብን ያስተውላሉ:: ይጠበቡበታልም:: : መጽሀፈ ሲራክ እኮ ነው:: :lol: :D

ቱሉ-ፋራ wrote:
የታዘብኩት ነገር
ብራዚል ግማሽ ያክል ህዝቡ ጥቁር ቢሆንም ተጫዋቾቹን አጅበው ከሚወጡት ህጻናት ጥቁር አላየሁም
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Mon Jun 16, 2014 12:07 pm

ቱሉቦሎ ክቡራን እንክዋን መጣቹ!!

ቱሉቦሎ...የአይቮሪኮስት ጨዋታን አላየሁትም....ግን ለአፍሪካ ድል ስላስገኑድ እስ ብሎኛል....
አሪፍ ትዝብት ነው ...ብራዚል ከአፍሪካ ውጭ በጥቁር ህዝቦች ብዛት አንደኛ ናት ሲባል...ስታድየሙን የሞላው ምድረ ፖርቹጊዝና ጀርመን ድቃይ ሀብታም ነጭ ብቻ!!! ህምምምም... ደሀው ጥቁርማ በየ 'ፋቬላ' የደከመ ኑሮውን ይገፋል...
አርጀንቲና የሞትሞቱን 2-1 አሸነፈች...በዚ አያያዛቸው ዋንጫ መብላት ይከብዳቸዋል....እስካሁን ጣልያን እና ኔዘርላንድ ናቸው ጠንከር ያሉ ቲሞች ብዬ አስባለሁ...ዛሬ የጀርመን ከ ፖርቱጋል ጨዋታም በግጉት ይጠበቃል....
ሲ.አር.ሮናልዶ...በህመምም እያቃሰትኩ እጫወታለሁ ብሎዋል... የጀርመንን ማሽን ሊያቆም?

ገልቤው የገለምሶው...የማን ደጋፊ ነክ?? ዋንጫውንስ ማን ይበላል?
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ገልብጤ » Mon Jun 16, 2014 1:31 pm

ገልቤው የገለምሶው ...የማን ደጋፊ ነክ ?? ዋንጫውንስ ማን ይበላል

ደቾች / ሆላንድ/ ይበሉታል ብዬ አስባለሁ እስካሁን ካየሁት ቲም ያስመረቀኑኝ ሆላንዶች ብቻ ናቸው..አርጀንቲናማ በዚህ አያያዟ ቦሰንያን 2-1 የትም አትደርስም ብዬ ደምድሜያለሁ
እስኪ የዛሬውን እንይና ..በላ ልበልሀ እንበል
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ጌታ » Mon Jun 16, 2014 2:03 pm

ገልቤው -

አንዱ አርኪቴክት ስፔን ውስጥ ኔዘርላንድ ስፔንን 5-1 ያሸንፋል ብሎ በመገመቱ የዓመት ነጻ ነዳጅ አሸነፈ አሉ:: እንዳንተ ዓይነቱ ደግሞ እዚህ በነጻ በትክክል ይገምታል :lol: :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዲጎኔ » Mon Jun 16, 2014 2:23 pm

ሰላም ለሁላችን
ዘጌው ወደኩዋስ እየመለስከኝ ነው ቅቅ/ ት/ቤት የእኛ ልጆች ሲጫወቱ እንዲህ ነው ጨዋታ እያልኩ አልፎ አልፎ እሄድ ነበር::ድሮ ኤሌትሪክን የደገፍኩ ከኩራዝ ስለገላገለኝ ትምህርት ኮሚሽንን ደግሞ በተማሪነት ዘመኔ ቀጫጭኖቹ እነህሩይ ኩዋሱ እንደካልኩለስ ሲቀምሩነው::ቆይቶ መድህን የደገፍኩ በስራ ዋናው ደምበኛዬ ስለነበር ነው::የካምቦሎጁ ስድብ ብዙ አያምም እዚህ እናትህ ት.. ከሚል ቆየት ብሎ እናት በእንጨት ት..ካለ የወያኔ ቴክኖክራት ነን ባይ አይብስም::የመድህኑ ኤርሚያስን ወ/ሮ ኤርሚያስ ሲሉት ብቻ ያኔ ብበሳጭም የካታንጋና ሚስማር ተራ ማታ ነው ድሌ ዛሬ የዳላስና የዲሲ ይደገማል በጣም ያረኩኛል::በቀደም ሜክሲኮና ካሜሮን ሲጫወቱ አንዱ የኤልሳልቫዶር ፓስተር ሜክሲኮ ያቸንፋል እያለ ፊቱ ሲለወጥ እኔ ካሜሮን ስደገፍ መንፈሳዊ መሆናችን አንርሳ አልኩ::ኩዋስ የሰላም ፍልሚያ መድረክ ሲሆን የጋምቤላ ሰው የሰደቡት ብሄሮችን ወዳለሁ እያለ አሰስገሰስ ካለ መሪና ጀሌ ምን ይጠበቃል!ኤሌትሪክ ያኔ የማውቀው አሰልጣኝ ቢረጋ ነበር!

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:እንደምነክ ጋሽ ዲጎኔ? .... ይገርምካል እኔም ባንድ ወቅት የመድን ድርጅት ደጋፊ ነበርኩ....የመሀል ሜዳ ቅመሙ አብዲ በሚጫወትበት ሰአት ማለት ነው....ከዛን ደሞ የኤሌክትሪክ ጽኑ ደጋፊ ሆንኩ...በጋሽ ሀጎስ አሰልጣኝነት በሚመሩበት ሰአት ማለት ነው....ከዛ ባለፈ..ሎያል ደጋፊ አይደለሁም..ጥሩ ለተጫወተ ቡድን ነው ድጋፌ ማለት ነው....

ፔሌ ትንሽ ራሱን እንደሚያመው አታውቅም እንዴ?...ሰውየው ሁሌ የሚሰጠው መግለጫና ኢንተርቪው የባጥ የቆጡን በማውራት..የተዛባ ግምት ..አልባሌ ነገሮችን በመናገር...አለም ሚድያ መሳለቅያ ነው.... ከቁምነገር አልቆጥረውም....
ቅቅቅቅ..የቤልጀም ከ ቱንዝያው የደረሰብክ አጋጣሚ.....እያሳቀ የሚያቆስል መራር እውነት ነው..... ግን እኛው ሀገርስ ....ባቅሚቲ ሬሲስት እየሆንን አይደለምን?..... ባለፈው ቀን የቡና ገበያ ጋምቤላዊ ተጭዋችን...በጦጣ ደምጽ ሲያንግዋጥጡ አልዋሉም?.... ይህን ክስተት በህይወቴ በጣም ካዘንኩባቸው አጋጣሚዎች ጎራ መድቤዋለሁ...

ብራዚል ከ ክሮሽያ.....ሊጀመር ነውውውውውውውው....

ግምታቹን ዱቅ ዱቅ አርጉ እንጂ..
ገለባብጤው.. ና ውጣ ከተደበክበት...
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጌታ » Mon Jun 16, 2014 7:08 pm

ክቡራን wrote:ትናናሽ ጭንቅላቶች ቀለምን ትላልቅ አእምሮዎች የኴሥ ጥበብን ያስተውላሉ:: ይጠበቡበታልም:: : መጽሀፈ ሲራክ እኮ ነው:: :lol: :D

ቱሉ-ቦሎ wrote:
የታዘብኩት ነገር
ብራዚል ግማሽ ያክል ህዝቡ ጥቁር ቢሆንም ተጫዋቾቹን አጅበው ከሚወጡት ህጻናት ጥቁር አላየሁም


ክቡሻ

ቱሉቦሎ ያስተዋለው ጉዳይ እውነት ከሆነ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው:: ይህ የዓለም ዋንጫ እንደመሆኑ ሌሎች አጸያፊ ድርጊቶችን ኢግኖር አድርገን የኳስ ጥበብ ላይ ብቻ እናተኩር ማለቱ ተገቢ አይመስለኝም::

ድሮ ድሮ እንዳነበብኩት በዚች ፕላኔት እንደ አርጀንቲና እና ብራዚል ጥቁር ቀለም ያላቸው ሰዎች የሚገለሉበት አገር እንደሌለ ነው:: እና አሁን አንተ አቅምህ ፈቅዶ ጨዋታ ልትመለከት ብራዚል ሄደህ በቀለምህ አላግባብ አድሎ ቢደረግብህ ማዘንህ ይቀራል?

ዛሬ ጀርመን ሌላ የአውሮፓ ኃያል ቡድንን ገረሰሰ! እጅግ ሲወራለት የነበረው ሮናልዶ ተሸማቀቀ! አድነነ! ኢትዮጵያም ኳሊፋይ አድርጋ ቢሆን ከ5-1 የከፋ አይደርስባትም ነበር :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ክቡራን » Mon Jun 16, 2014 7:44 pm

እኔን አይመለክትም ወንድም ጌታ እኔ እኮ አማርኛ እችላለሁ እንጂ የባርባዱስ አገር ተወላጅ ነኝ :: ነጭ ህንድ ነኝ:: :lol: just kidding ቱሉ ቦሎን ትንሽ ላበሳጨው ብዬ ነው የጻፍኩት...ሀሳባችሁን እጋራለሁ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ጌታ » Mon Jun 16, 2014 8:43 pm

ክቡራን wrote:እኔን አይመለክትም ወንድም ጌታ እኔ እኮ አማርኛ እችላለሁ እንጂ የባርባዱስ አገር ተወላጅ ነኝ :: ነጭ ህንድ ነኝ:: :lol: just kidding ቱሉ ቦሎን ትንሽ ላበሳጨው ብዬ ነው የጻፍኩት...ሀሳባችሁን እጋራለሁ:: :D


እኔም እኮ ክቡሻ የአርጀንቲናውን ሜሲ ይመስላል እያልክ ለዲጎኔ ሳወራው ነበር:: :lol: :lol: :lol: :lol:

ይመችህ ሲኞር
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Next

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests