ብራዚል 2014 የአለም ዋንጫ

ስፖርት - Sport related topics

Postby ገልብጤ » Mon Jun 16, 2014 11:08 pm

ጌታ wrote:ገልቤው -

አንዱ አርኪቴክት ስፔን ውስጥ ኔዘርላንድ ስፔንን 5-1 ያሸንፋል ብሎ በመገመቱ የዓመት ነጻ ነዳጅ አሸነፈ አሉ:: እንዳንተ ዓይነቱ ደግሞ እዚህ በነጻ በትክክል ይገምታል :lol: :lol: :lol:

ቅቅቅቅቅ
እንኳን አርክቴክቱ ታዋቂ ቆማሪወችም ስፔን ላይ 5 ይገባል ብለው አልተወራረዱም ..የሆነ ክስተት ነው
ሜሲ
ሮናልዶ
የነሱ ጊዜ እያበቃ ነው
አይ ዲጎኔ ዋርካን ሚስቶ አደረገው ..ቦጠሊቃ እና ስፖርት እየቀላቀለ
ይህ ሰውዬ ስለስፖርት ካላወራ እዚህ ቤት ድርሽ እንዳይል..ዋ ብያለሁ ዶጎኔ
ከኔ ከሰማይ ሰባሪው ጋር መሳፈጥ ይቅርብህ ...ዋ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ጌታ » Tue Jun 17, 2014 7:25 pm

ቤልጅጎች ተሟሙተው 3 ነጥብ ይዘው ወጡ:: ጨዋታውን ባልከታተልም ስታቲስቲክሱ እንደሚያሳየው ቤልጅግ 67% ኳሷን ተቆጣጥረው ውለዋል:: ማሸነፍ ሲያንሳቸው ነው::

ሜኺኮ ኸብራዚል ይቀውጡታል! ልገምትና ሜኺኮ ብራዚልን 3 ለ 1 ይሸከሽከዋል ልበላ! ግፋ ቢል መሳሳት ነው ምን ይመጣል?
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዲጎኔ » Tue Jun 17, 2014 8:31 pm

ሰላም ለሁላችን
የዋርካው ጌታ ይህ በኩዋሱ አለም ያልተለመደ ቃል ነው:: እንኩዋን በድሮው ጨዋው ካታንጋ ደደቢቶች በተቆጠጠሩት ሜዳም አልተሰማ::ወይስ ከእንትን የዋለች እንትን ተማረች ሆኖብህ እናትህ ት...ወይም እናትህ በእንጨት ት...የሚለው ጥሩ ሰው ያልከው ገልብጤ/ሙዝ አጋባብህ ቅቅቅ
ወደጨዋታው ስመጣ ካሜሮን ከሜክሲኮ ሲጫወት ብቻ ነው ከላቲኖዎች ጋር እየተፎካከርን በስሜት ያየሁት ሌላው ግን ለስፖርት ብቻ ፋታ ሲኖረኝ ሄጄ አያለሁ እንጂ ብዙም አይጥመኝ::የእናንተን እንጃ ለለኔ ማንነቴን አፍሪካዊነቴን የሚያለመልም ብቻ ነው ማየትና መደገፍ የምወደው::
ገልቤ/ሙዝ ምን ትፎክራለህ?ምን ስድብ ቀረህ? የመጨርሻ ክፉ ስድብ በቤ/ክርስቲያን በተመሰለች እናት ላይ የሚደረግ ስለሆነ ምን ብትስድበኝ ከዚያ የበለጠ አይኖርምና አባው ይውጣልህ ተሳፈጥ/ ተሳደብ ቅቅቅ

ጌታ wrote:... 3 ለ 1 ይሸከሽከዋል ልበላ!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጌታ » Thu Jun 19, 2014 3:59 pm

ዲጎኔ ወንድማችን -

መሸክሸክ የሚለውን ቃል በዋነኝነት የማውቀው በገብስ ሲሆን በተወራሽ ትርጉም መደብደብ እንደማለት ነው:: አንተ የምታውቃቸው ሰዎች ደግሞ ለወሲብ ድርጊት ይጠቀሙበታል:: እዚህ ጋር ስለኳስ ሳወራ 'መሸክሸክ' በደንብ አድርጎ ማሸነፍን ለመግለጽ እንጂ ለፍተወት ሥጋ መግለጫነት አላሰብኩትም::

ስለኳስ እያወራን እናትን ስለመስደቢያ ብልግና ቃላት መጠምዘዙ አስፈላጊ አልነበረም::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዲጎኔ » Thu Jun 19, 2014 5:24 pm

ሰላም ለሁላችን
የዋርካ ጌታ ስለማብራሪያ አመሰግናለሁ ቁዋንቁዋ የሚያድግ ነው::ይህ ቃል ለኩዋስ ይቻላል ካልክና ተቃዋሚ እስከሌለ ትርጉሙ እቀበላለሁ::ባለፈው እናትህ ት..ከዚያም እናትህ በእንጨት ት.. ያለ ወዳጅህ ያ ሳያንሰው ሲዝትብኝ ማጋለጥ ላንተ መጠምዘዝ ከሆነ ይሁንልህ::እኔና መሰሎቼ ግን ኩዋስ ሆነ ባህል በሀይማኖትና ፖለቲካ እናት ሰዳቢ ወያኔ መጋለጥ አለበት!ፔሌ ጋሽ ይድነቃቸው ያደነቀው መጥፎ አመለካከት እንዳለው ባውቅም ዛሬ ኩዋስ ሜዳ ባገኘውና ያን ቢደግም እናትህ ት...አልለውም ክፉ አባባሉን ብጠቅስ ግን ቅን ብራዚላዊያንና ስፖርት ተመልካች መጠምዘዝ አይሉኝም::

ጌታ wrote:ዲጎኔ ወንድማችን -
መሸክሸክ የሚለውን ቃል በዋነኝነት የማውቀው በገብስ ሲሆን በተወራሽ ትርጉም መደብደብ እንደማለት ነው:: አንተ የምታውቃቸው ሰዎች ደግሞ ለወሲብ ድርጊት ይጠቀሙበታል:: እዚህ ጋር ስለኳስ ሳወራ 'መሸክሸክ' በደንብ አድርጎ ማሸነፍን ለመግለጽ እንጂ ለፍተወት ሥጋ መግለጫነት አላሰብኩትም::

ስለኳስ እያወራን እናትን ስለመስደቢያ ብልግና ቃላት መጠምዘዙ አስፈላጊ አልነበረም::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጌታ » Thu Jun 19, 2014 6:44 pm

ዲጎንሻ

እኔ እኮ የገልብጤንም ሆነ የማንንም ስድብ ደግፌ አላውቅም:: ሜክሲኮ ብራዚልን ይሸከሽካል ማለት እንዴት ከእናት ስድብ ጋር ይመሳሰላል አልኩ እንጂ::

ለነገሩ በኛ ባህል/ቋንቋ ማንኛውም ግስ ወደ ወሲብ ይጠመዘዛል:: መብላት/ማድረግ/ማውጣት/መሄድ/እንትን ማለት/ማለት እራሱ/መደሸቅ/መለጥለጥ/..........ልቀጥል?

እናም ቃላትን በኮንቴክስት ብናያቸው የተሻለ እንግባባለን እላለሁ:: የብልግና ቃል በኔ ዕድሜ አያምርም :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Fri Jun 20, 2014 11:42 am

ሳልዋሻቹ..እስካሁን ካየዋቸው አለምዋንጫዎች..እንደዘንድሮው ያስመረቀነኝ የለም...እሚገርሙ ውጤቶች..እሚገርሙ ጎሎች..እሚገርሙ መሳጭ ጨዋታዎች..ፓፓፓፓፓ ብያለሁ!

ያለጥርጥር..የስካሁኑ ምርጥ ቡድን...ቺሊ!! እንዴ? ሰዎቹ ምን በልተው ነው የመጡት?.... ሳልወድ በግድ የነሱ ደጋፊ ሆኛለሁ.... በመቀጠል ደሞ..ሆላንድ...

ቅቅቅቅቅ...እንግሊዝ....በሳቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ.....ጉራ ብቻ.... ፕሪምየርሊጋቸውም እድሜ ለውጭ ተጭዋቾች ሞቅ ሞቅ ያረጉላችዋል..እንጂማ..የቱ የረባ ተጭዋቻቸው ነው ደሞ?

ሽዋሬዝ...ከ 4 ሳምንት በፊት ግራ ጉልበቱን ቀዶ ጥገና አርጎ... ምናልባትም 50% የጨዋታ ብቁ ሆኖ ባለበት..ያሳየን ጭሎታው..ዋው ዋው! እሚገርም ተጭዋች ነው.....ሪልማድሪድ ሊሄድ ነው ይባላል... የአለማችን ምርጥ አጥቂ ነው ግን.!

ጋሽ ዲጎኔ....ኤርሚያስ የመድኑን እኔም ደርሼበታለሁ...አሪፍ ተጭዋች ነበር...እሱ...ሀሰን በሽር...አብዲ...ፋሲል አብርሀ...አሪፍ ቡድን ነበር..ያኔ መድን...
መብራትና ..መድን በጭዋታቸው ያስደሰቱኝ ቲሞች ነበሩ... ቡና ግን ሁሌ ኳስ አሪፍ አንቸው ይባላሉ..አንድም ቀን ሳያረኩኝ ነው አገር የለቀኩት..ስም ብቻ!! ሳንጆርጅ..ኢትዮጵያዊ..ማንቼ..በዚም በዛም ብሎ ማንጫ ያስተማምናል...ቅቅቅቅ

ገልቤው...ሆላንድ በቀደም ካውስትራልያ..ብዙም አላስደሰቱኝም...ጥያቄ ምልክት አርጌባቸዋለሁ...

በሉ..ሞቅ አርጉት..ግምቱን ውይይቱን.... እነ ጌታ..ክቡራን..ዲጎኔ... ገልቤው... ምን ታዘባቹ? እስካሁንስ ያረካቹ ጨዋታ የቱ ነው?...

ለኔ...

ጣልያን ከ እንግሊዝ

ሆላንድ ከ ስፔን

ቺሊ ከስፔን

እንግሊዝ ከ ዩራጋይ

አንኳር ጨዋታዎች ሆነው አልፈዋል!!
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ዲጎኔ » Mon Jun 23, 2014 7:49 pm

ሰላም ዘጌው
ትዝታህ ድንቅ ነው!የማይረሱ ትምህርትኮሚሽን ህሩይና የመድን ኤርሚያስ ሲሆኑ ወንድማገኝ ከርቸሌኮሌጅ አብረን ነበርን::ከከርቸሌ የምደግፍ ነጸብራቅ ነበር በኢሀፓ ይታማ ነበር ታጋይ ታስሮም አይተኛ!
የመድህን አሰልጣኝ ስዩም አባተ ብዙ ሲደክም እንደተመኝ አልሆነለትም::ልክነህ ቡናዎች ዝም ብሎ ቅልብ ነበሩ አይ ዘመን!ኩዋሱ ብዙ ደሞዝ ሲያስገኝ ሀገር የሚያስጠራ ሩጫ ትንሽ ደሞዝ ነበር::የሀገሪቱን ስፖርት መስመር ለማስያዝ የጣሩ እንደይድነቃቸው ተሰማ ያሉ ዛሬም ያስፈልጉናል:: አለም ዋንጫ መጀምሪያ ዙር እንኩዋ ያላለፈች ሀገራችንን ፈጣሪ ያንሳት::ነጸረ ገብረአብ ስፖርት ፌዴረሽን ባልደረባ አጼውን ከእርስዎ አመራር የይድነቃቸው ይሻላል ብሎ አርባ ተገርፏል::ከነጸረ ወንድም ጋር አብረን እንሰራ ነበር ወያኔ የገባ ሰሞን ላውንቸር ገደለው::በስፖርትም ለፍትህ መተንፈስ የግድ ነው!ሰሞኑን ቺሌን እየደገፍኩ ነው ድሮ በህዝቦች ትግል ጁንታው ፒኖቼ ያደረሰባቸው ትዝ ይለኛል በአለምአቀፍ ትግል ከሁሉም ጋር አብረን እንቆማለን!

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:ጋሽ ዲጎኔ....ኤርሚያስ የመድኑን እኔም ደርሼበታለሁ...አሪፍ ተጭዋች ነበር...እሱ...ሀሰን በሽር...አብዲ...ፋሲል አብርሀ...አሪፍ ቡድን ነበር..ያኔ መድን...
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sat Jun 28, 2014 10:59 am

ሰላም ዲጎኔ.... አንተ ጥሩ ጥሩ ትዝታዎች አለክ...
እኔም ስሰማ ጋሽ ይድነቃቸው ዘመን ሀገራችን በእግርኳሱ አለም ትልቅ አክብሮት እንደነበራትና የሳቸውም ቅጽል ስም..የጂብራልታሩ አለት..ይባል እንደነበር ነው... አሁን ግን ከአመራርሩም ከተጫዋቹም አልሆንም..ዝም ብሎ ነገር ነን መሰለኝ....

በተረፈ...ይህ አለም ዋንጫ..ዘ ቤስት አለምዋንጫ ሳይሆን እንደማይቀር እየተነገረለት ነው... የጎል ውርጅብኝ...ኮንትሮቨርሲው....እሚያስመረቅኑ አሪፍ ጨዋታዎች....ያልታሰቡ ታላልቅ ቡድኖች ገና በጥዋቱ መገንደስ....ያልታሰቡ አነስተኛ ቡድኖች አስደሳች አጨዋወታቸውን ማሳየት..እንደ ቺሊ እና ኮስታሪካ የመሳሰሉት.... በጣም ነው የጣመኝ!!
ዛሬ...ጥሎ ማለፍ ይጀመራል...ብራዚል ከቺሊ.. ከባድ ጨዋታ ነው... ኡራጋይ ከ ኮሎምቢያ ..ካለሽዋሬዝ ትገጥማለች...

ለዋንጫ ማን ከማን ይደርሳል?

በኔ ግምት... ብራዚል ከ ኔዘርላንድ(ሆላንድ) ብዬ ካሁኑ ገምቻለሁ!!

የናንተስ?
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ገልብጤ » Sat Jun 28, 2014 2:17 pm

በኔ ግምት ... ብራዚል ከ ኔዘርላንድ (ሆላንድ ) ብዬ ካሁኑ ገምቻለሁ !

ከምላሴ ጸጉር ይነጫል ብራዚል ለዋንጫ አትደርስም
የኔ ግምት
ሆላንድ Vs ቺሊ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ጌታ » Mon Jun 30, 2014 3:44 pm

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:
ለዋንጫ ማን ከማን ይደርሳል?

በኔ ግምት... ብራዚል ከ ኔዘርላንድ(ሆላንድ) ብዬ ካሁኑ ገምቻለሁ!!

የናንተስ?


ዘጌው

ይህ ያለም ዋንጫ እኮ አንዳንዴ ችሎታ ብቻ ሳይሆን ጥቃቅን አጋጣሚዎችና ስህተቶች ሲወስኑት ታያለህ እናም እገሌ ያሸንፋል ለማለት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል:: አንተ ለዋንጫ ያጨሃቸው ብራዚልና ሆላንድ በመርፌ ቀዳዳ ሾልከው ሩብ ፍጻሜ ደረሱ:: ስፔን ላይ እንደዛ የፈነጩት ኦሬንጆች ጎል ብርቅ ሆኖባቸው ዋሉ:: ብራዚሎች ደግሞ ፔናልቲ አመታት ከኮስታሪካ እና ከግሪክ ይማሩ..........

እስካሁን ጨዋታቸውን የማየት ዕድል ባይገጥመኝም ውጤታቸውን በማየት ብቻ ፈረንሳዮች የሚያሸንፉ ይመስለኛል:: ጀርመንም የዋዛ ቡድን አይደለም::

ይልቅ ዛሬ በሕልሜ ፈረንሳይ ናይጄሪያን 6-1 አሸንፎ አየሁ:: አብሮኝ ለሚሰራው ኢቦኒዊ ብነግረው ፍቺው ተቃራኒ ነው አለኝ :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ወንበዴው » Tue Jul 01, 2014 6:14 pm

ሜዳ ላይ እርስ በርስ የተደባደቡት የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከአቛማሪዎች ጋር በመመሳጠርና 'ከችሎታ በታች' በመጫወት ተጠርጥረው ምርመራ ላይ ናቸው>>>
http://www.cbc.ca/sports/soccer/brazil2014/cameroon-soccer-federation-probes-match-fixing-claims-1.2692759
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 342
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Postby ምክክር » Sun Jul 06, 2014 11:04 am

ለዋንጫው 'ሚፎካከሩት ሁለቱ ቡድኖች የአርጀንቲና ና የብራዚል ብሔራዊ ቡድኖች ናቸው ብያችሁ አላመናችሁኝም ነበር አይደል....የ2014 ዋንጫ ወደ ደቡብ አሜሪካ እንደሚገባ አትጠራጠሩ:: ለግማሽ ማጣሪያ ያለፉት ሁለት የደቡብ አሜሪካና ሁለት የኤሮፕ ቡድኖች ሆነዋል::

አይ የዘንድሮው ኳስ....በዓይናችን ተጫወቱበት::

የዘንድሮው ዓለም ዋንጫ ፉክክር በሕይወቴ ከተከታተልኩት ሁሉ የመጨረሻው አስጠሊታ ሆነብኝ:: አላስደስተኝም:: የታለ የኳስ ጥበብ....ፍልሚያ....ኩመካ.....ቅብብል.....ጎል::
ብራዚሊያውያኑ ጋ የጋለ የማሸነፍ ፍላጎት አለ::
አንዱ ምክንያት አስተናጋጅ መሆናቸው ነው::
አርጀንቲና ዋንጫዉን ቢነጥቃቸው ምን ያህል እንደሚቃጠሉ ገምታለሁ:: ብራዚሊያውያን የአርጀንቲናን ተፎካካሪ ነበር የሚደግፉት::

በ2014 የኳስ ጥበብ ና ዉበት አልታየም::
ጠንካራዎቹ ጀርመናውያኑ ቀዝቅዘዋል::
የሪያል ማድሪዱ ኖናልዲኖ ብሔራዊ ቡድን ኢን አል ዲኖ እያለ ነበር 'ሚጫወተው::
ኔይማር ብቻዉን ይለፋል:: የቡድን ጨዋታ ግን አላሰየም::
መሲ ይሻላል ልበል? መሲ ኳስ ሲይዝ ሕዝበ ክርስትያን ሁሉ ይርበደበዳል:: መሲ እስካለ አርጀንቲናን እንደምንም እናጣጥማቸዋለን::
ጥሩ ጨዋታ ያየሁት የቺሊ ና የስፔን:
የአርጀንቲና ና የናይጄሪያ:
የብራዚልና የኮሎምብያ
እንዲሁም የጀርመን ና የአልጄሪያን ነው::

ናይጄሪያዎቹ ከአርጀንቲና ጋር ያሳዩት ፉክክር ቀላል አልነበረም:: ክቡራን ግን ምን ነክቶት ነው ይህን ጨዋታ ካየ በኋላ እንኳን ተሸነፍን ....እንኳን ያልተሰለፍን ያለው?
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 452
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ክቡራን » Sun Jul 06, 2014 12:54 pm

ምክሩ አንተ ሾካካ!! :D እየነካካህ ታናግረኛለህ..አይደል..አንተ የምትፈልገው በሰንበት ክፉ ተናግሬ ሀጢያት እንድገባልህ ነው እይደለም?? !! እኔ ደሞ ዝም!! እንኴን ቡድናችን አልተሰለፈ አልልም:: :lol: በነገራችን ላይ ያለምን ዋንጫ ጀርመን ያነሳል:: አላህ ገለጸልኝ:: ክቡራን ምን አለ በል ..! ጀርመኖች የኴስ ጥበብ ወይም እኛ ድሮ ሜዳ ላይ እንደምናደርገው አብዶ የላቸውም:: አብዶ መስራት ለቲፎዞ ወይም ለተመልካች እንጂ ለቡድን የሚያመጣው ቡዙም አስተዋጾኦ የለውም:: ሜሲ አብዶ ያበዛል:: ግን ሲለው ፍትፍት የሆነ ኴስ እየፈተፈተም ያቀባላል:: እኔ በስድስት ቦታ አንዳንዴም በዘጠኝ ቦታ ሆኘ ሳከፋፍል የነበረውን ትዝታዬን ይቀሰስቅስብኛል ይሄ ሜሲ!! ዔጭ! :lol: ግን እኔ በቀኝ እንጂ በግራ እግሬ እንደሱ መጫወት አልችልም:: ቡዙ ተጫዋች ወይም ተከላካይ በቀኝ እግሩ ስለሚጫወት በቀኝ በኩል ባለው አእምሮው የሚያስብ ይመስለኛል ለዚህ ነው እንደ ሜሲ ያሉ አጥቂዎች ለተከለካይ የሚያቃጥል ሚጥሚጣ የሆኑት:: በግራ ኴስ ይዞ ለሚመጣባቸው አእምሯቸው ዝግጁ አይደለም::
... እንዳልኩት ጀርመኖች ጋ አብዶ የለም...ለውጤት የሚያበቃ ከብረት የጠነከረ የኴስ ዲሲፕሊን ግን እነሆ ጀርመኖች ጋ አለ....

ክቡራን ነኝ:: ከፍቅሩ ኪዳኔ የስፖርት ዘገባ ስር ሆኜ የብራዚልን ሜዳ ከሚቃኙ ወገኖች ተርታ..ከሀሳዊ መሲሁ ጋዜጠኛው ዲጎኔ ወዲያ ማዶ:: :lol:

መልካም ሮመዳን ይሁንልህ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9240
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ምክክር » Mon Jul 07, 2014 10:58 am

ክቡራን wrote:ምክሩ አንተ ሾካካ!! :D እየነካካህ ታናግረኛለህ..አይደል..አንተ የምትፈልገው በሰንበት ክፉ ተናግሬ ሀጢያት እንድገባልህ ነው እይደለም?? !! እኔ ደሞ ዝም!! እንኴን ቡድናችን አልተሰለፈ አልልም:: :lol: በነገራችን ላይ ያለምን ዋንጫ ጀርመን ያነሳል:: አላህ ገለጸልኝ:: ክቡራን ምን አለ በል ..! ጀርመኖች የኴስ ጥበብ ወይም እኛ ድሮ ሜዳ ላይ እንደምናደርገው አብዶ የላቸውም:: አብዶ መስራት ለቲፎዞ ወይም ለተመልካች እንጂ ለቡድን የሚያመጣው ቡዙም አስተዋጾኦ የለውም:: ሜሲ አብዶ ያበዛል:: ግን ሲለው ፍትፍት የሆነ ኴስ እየፈተፈተም ያቀባላል:: እኔ በስድስት ቦታ አንዳንዴም በዘጠኝ ቦታ ሆኘ ሳከፋፍል የነበረውን ትዝታዬን ይቀሰስቅስብኛል ይሄ ሜሲ!! ዔጭ! :lol: ግን እኔ በቀኝ እንጂ በግራ እግሬ እንደሱ መጫወት አልችልም:: ቡዙ ተጫዋች ወይም ተከላካይ በቀኝ እግሩ ስለሚጫወት በቀኝ በኩል ባለው አእምሮው የሚያስብ ይመስለኛል ለዚህ ነው እንደ ሜሲ ያሉ አጥቂዎች ለተከለካይ የሚያቃጥል ሚጥሚጣ የሆኑት:: በግራ ኴስ ይዞ ለሚመጣባቸው አእምሯቸው ዝግጁ አይደለም::
... እንዳልኩት ጀርመኖች ጋ አብዶ የለም...ለውጤት የሚያበቃ ከብረት የጠነከረ የኴስ ዲሲፕሊን ግን እነሆ ጀርመኖች ጋ አለ....

ክቡራን ነኝ:: ከፍቅሩ ኪዳኔ የስፖርት ዘገባ ስር ሆኜ የብራዚልን ሜዳ ከሚቃኙ ወገኖች ተርታ..ከሀሳዊ መሲሁ ጋዜጠኛው ዲጎኔ ወዲያ ማዶ:: :lol:

መልካም ሮመዳን ይሁንልህ::


ክቡሻ ሮመዳን እግር ጥሎህ እንግዳዬ ብትሆን የፈጥርን ሥርዓት በተምርና ሳምቡሳ በሾርባና ሸፉት ታጣጥመው ነበር:: ሙክክ ያለ የኢስላም ሥጋ: በሽትኒ: በዝግኒ ...ሁለተኛ ቴረሪስት የሚባል ነገር ካፍህ ሲወጣ ትን እንዲልህ አድርጌ :D :D :D

ዋንጫዉን ጀርመን አይወስድም:: ከአርጀንቲና ና ብራዚል አንዱ ያነሳል:: ጀርመኖች ለመጨረሻው ማጣሪያ በመድረስ ሪከርድ የሚስተካከላቸው የለም:: ዘንድሮ ግን አልታዩኝም እልሃለው::

እኔ ምልህ ቂቂቂ ስድስትና ዘጠኝ ቁጥር ነበርክ እንዴ? ክቡሻ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፎቶግራፍህ ላይ የለበስከው ማልያ ሁለት ቁጥር ቁልጭ ብሎ ይታያል:: ምንድነውሱ? ወይስ ፎቶግራፈሩ አድሃሪ ነበር ልትል ነው? :D :D :D .....ሠላም ሁን::
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 452
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

PreviousNext

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests