ብራዚል 2014 የአለም ዋንጫ

ስፖርት - Sport related topics

Postby ወንበዴው » Tue Jul 08, 2014 3:32 pm

የስፔንን አይነት- የባድመን ምሽግ የመሰለ ዲፌንስ ያለው ቡድንን- በቀላሉ 5-1 ያሰናበተው ሆላንድ ዋንጫ ይበላል__አርጀንቲናዎች እና ደጋፊዎቻቸው ለልቅሶ ተዘጋጁ :D
ወንበዴው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 342
Joined: Sun Aug 07, 2005 5:01 pm
Location: india

Postby ጌታ » Tue Jul 08, 2014 5:46 pm

ወንበዴው wrote:የስፔንን አይነት- የባድመን ምሽግ የመሰለ ዲፌንስ ያለው ቡድንን- በቀላሉ 5-1 ያሰናበተው ሆላንድ ዋንጫ ይበላል__አርጀንቲናዎች እና ደጋፊዎቻቸው ለልቅሶ ተዘጋጁ :D


ወሮበላው -

እኔ እንኳን በትንበያ ደረጃ ሳይሆን ፍጻሜ ግማሹን ብራዚልና ሆላንድ አሸንፈው ዋንጫውን ኦራንጆች እንዲያነሱት ነው ፍላጎቴ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Thu Jul 10, 2014 11:52 am

አይይይ...ይሄ ነገር/ ዋንጫ ዞሮ ዞሮ ጠንካሮቹና አይበገረዎቹ ጀርመኖች ጋ ሊገባ ይሆን?..... እንደለመዱት ከጭዋታ ጨዋታ እየጋሉ መተው ጭራሽ ብራዚልን ቅርጫት ኳስ ጨዋታ እስኪመስል ድረስ መሳለቅያ አረጉት.... ቅቅቅቅ... እነ ሮናልዶ ..ሮናልዲኖ ሪቫልዶ ሮማርዮ ቤቤቶ...ምናምን ባየንበት አይናችን...በጥፍሩ ኳስ የሚመታ ኦስካር... ማነው ደሞ ፖሊኖ የሚሉት ጎታታ... ያስ ደሞ ሆልክ የሚባል ክብደት አንሺ ይሁን ኳስ ተጭዋች ግራ የሚያጋባ እንጨት የዋጠ ግትር ተጭዋች...ቅቅቅቅ...ወይ ብራዚል ድሮ በቴክኒካቸው ልባችንን እንዳልሰወሩት በ 1 ነይማር ወፌ ቆመች ሲወዛወዙ እሱም ተጎድቶ ጉዳቸው ወጣ.... እንኳት ተለጠለጡ..ጎሽ!!

እኔም እንደጌታ የሆላንዶች እንዲበሉት ፈልጌ ነበር ..አልተሳካም.... አስጨናቅ 0-0 የ120 ደቂቃ ሙሉ ጭዋታ.... እድል ሁለቴ አይሳካምና አርጀንቲና ወደዋንጫው ጨዋታ አልፋለች...


እናሳ...ጀርመን ወይንስ አርጀንቲና? ማንን ታላላቹ...

?
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ጌታ » Fri Jul 11, 2014 5:18 pm

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:እኔም እንደጌታ የሆላንዶች እንዲበሉት ፈልጌ ነበር ..አልተሳካም.... አስጨናቅ 0-0 የ120 ደቂቃ ሙሉ ጭዋታ.... እድል ሁለቴ አይሳካምና አርጀንቲና ወደዋንጫው ጨዋታ አልፋለች...


እናሳ...ጀርመን ወይንስ አርጀንቲና? ማንን ታላላቹ...

?


ዘጌው-

በዚህ ያለም ዋንጫ እኔ የፈለኩት ብዙም አልሆነም:: እርግጥ ነው ሆላንዶች ኮስታ ሪካን ሲያሸንፉ ስለቴን አስገብቻለሁ::

ለጀርመንና አርጀንቲና ግድ ባይኖረኝም ጀርመን ያሸንፋል ብዬ ጥገት ላሜን አስይዣለሁ:: ይቅናህ በለኝ...
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3118
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Previous

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests