በሉ እዚ ክፍል የ 2014 አለምዋንጫን በተመለከተ አስተያየታቹን... መላምታቹን....ትንታኔያቹን...ትዝብታቹን... እርግማናቹን....ጥንቆላቹን...እምባቹን...በቃ የፈለጋቹትን የምትሉበት እንዲሆን እነሆ በረከት...
እሺ ብራዚል ከክሮሽያ?.... እንዴት ነው?
የባርሳው ኔይማር ከ ማድሪዱ ሞድሪች....ይፋጠጣሉ....
1950 ላይ ህዝበ ብራዚልን ያኮማሸሸ... ዋንጫ ከጉሮሮው ፈጥርቆ ያወጣው የኡራጋይ ቡድንም..ባዲሱ ትውልድ..ልዊስ ሽዋሬዝ እየተመራ መጣሁ ብሎዋል..ታሪክ ሊደግሙ..!! ስፔንስ? ቲኪታካ..እዚም ጠቅ እዛም ጠቅ..አፍዝ አደንግዝ ፉትቦላቸው ላይ በላይ ዋንጫን ያስገኝ ይሆን?....የመጀመርያ ጨዋታቸው የ 2010 ፍጻሜ ድጌ እንዲሉ..ከኔዘርላዶች ጋ ነው.... መቼ?አርብ የቀን ምርጥ ነዋ!... ሮበን ለካሲላስ ያሳቀፈውን ያንድ ለ አንድ ቻንስ እስካሁን እንቅልፍ እንደነሳው ነው....በዚ ጨዋታ..ሀገሩን ይክስ ይሆን?....ብዙ ጉድ እናያለን!! ..አፍሪካስ?....ጋና ብላክስታሮች የአፍሪካችን ምርጥ ተስፎች... ግማሽ ፍጻሜ ገብተው ታሪክ ይሰሩ ይሆን?..እንጃ...ምድባቸው ከአለት የጠነከረ ነው... በታለንት የተጨናነቀን ጀርመንንና የክሪስታኖ ሮናልዶውን ፖርቹጋል ገፍትረው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል.... ኮትዲቭዋርስ?....ወርቃማው ትውልድ የመጨረሻ ቻንሱ?...ድሮግባ 36 አመቱ ነው...ያያቱሬ..ጉዳት ላይ ይመስላል...ትሬኒንግ ማድረግ እንኳን አልቻለም... ወንድሙን ኮሎቱሬ ቢጫ ወባ ትጫወትበታለች..ቅቅቅቅ.... ብቻ ምናለፋን...አይቮሪኮስት ተይዛለች!..... እነ ጣልያንስ? እብዱ ባላቶሊ ሰከን ብሎ ታሪክ ያስመዘግብ ይሆን?.... እንደ ወይን እያደር ችሎታው እየጣም መጣው አንድሬታ ፒርሎስ በ 35 አመቱ ጣልያንን ተሸክሞ ለድል ያበቃ ይሆን?..አጠገቡ የሰው ነብሩ...ዳኒዬል ደሮሲ አለ::... አርጀንቲናን የረሳሁ ከመሰላቹ ተሳስታቹሀል...!!.....ምትሀታዊው ሜሲ ለሶስተኛ ግዜ አለምዋንጫ እድሉን ሊሞክር ወደብራዚል አቅንቷል...ያሁኑን የሚለየው የቡድኑ አንጋፋና መሪ ተቻዋች መሆኑ ነው....ከአጠገቡ...እጅግ የሚገርም የአጥቂ መስመርን እናገኛለን... አጉወሮ..ዲማርያ...እና ሂጋዋኢን... እውነትም እሚገርም! ማንስ ሊያቆማቸው? በአንድ ጨዋታ ከ 3 ጎል በታች ካገቡ እንደውድቀት እንው ምቆጥርባቸው...ቅቅቅቅቅቅ..... ኳስን ፈጠርኩ ባል የምትኮፈሰው እንግሊዝስ ምን ይዛ ይሆን?... ባለተለመደም መልኩ ወጠጤ ተጭዋቾችን እንደጉድ አካታለች... የዘንድሮ ሊቨርፑልን ምርጥ ፎርም ይደግሙልኛል ብላ ከሊቨርፑል አንድ ቁና ተጭዋቾችንም አካታለች....ሩኒስ? የስም ብቻ ተጭዋች?... 3 አለም ዋንጫ ተጫውቶ 1 ጎል ያላገባ የደከመ አጥቂ...ቅቅቅቅቅ... ቤልጀምንስ እንዴት ነው ምናያት? ሀዛርድ..ካምፓኒ...ፈላኒ...ደምቤሌ.. ቀውላላው...የአትሌቲኮ በረኛ...እረ ብዙ ናቸው! ያስፈራሉ!!
መልካም ውድድር ::