የነቀምት ምንቸት ግባ የአጋዚ ምንቸት ውጣ ብሏል የደሴ ኳስ አፍቃሪ! የዘረኝነት መርዝ ዘሪውን ሲበላ!
ቋጠሮ-December 9, 2017
በደሴ ከተማ ሃሙስ ህዳር 28/2010 ከደሴ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ጨዋታውን ለማካሄድ ደሴ የገባውን የለቀምት ከነማ እግር ኳስ ክለብን ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምተገኘው ኮምቦልቻ ፎነተኒና ድረስ በመሄድ በሞተር አሽከርካሪዎች በመታጀብ በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
አቀባበሉ ላይ ህዝቡ አንድ ነን፣ አንለያይም፣ እንኳን ደህና መጣችሁ! ስፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለወዳጅነት፣ መሆኑን እያበሰሩ የፍቅር የጥበብና የውበት አምባ በሆነችው ደሴ ላይ ቆይታቸው ምቹና የተሳካ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ የደሴ ከነማና የለቀምት ከነማ እሁድ ታህሳስ 1/2010 በሆጤ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፤ መልካም እድል!