ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ በዳላስ 2018

ስፖርት - Sport related topics

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ በዳላስ 2018

Postby እሰፋ ማሩ » Mon May 28, 2018 3:54 am

ለኢትዮጵያውያን የስፓርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ
የቦርድ አባላት

ጉዳዩ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ አሊን በዳላስ 2018 ዝግጅት ላይ መጋበዝን ይመለከታል።

ፌዴሬሽኑ ለ35 ዓመታት ኢትዮጵያውያንን በሰሜን አሜርካ በማቀራረብና የሀገራዊ አንድነትን መንፈስ በስፓርትና በባህል ፌስቲቫል በማክበር ያሳየው ታታሪነትና ጽናት በዲያስፓራ አሉ ከሚባሉ የኢትዮጵያውያን ተቋማት አንዱ አድርጎታል። በነዚህ 35 ዓመታት ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ያለፈው ፌደሬሽናችን የዲያስፓራ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ጭምር ትልቅ ኩራት ነው።

በሀገራችን ውስጥ ባለፉት ሶስት አመታት ወጣቶች ሲገደሉ ፣ ሲቆስሉ ፣ በሺዎች ሲታሰሩና ሲሰደዱ በብዙ ሀዘን ፡ ስጋትና ቁጭት ውስጥ ያላለፈ የዲያስፓራ ማህበረሰብ አባል የለም! በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያየናቸው በግፍ የተገደሉ ወጣቶች ፎቶግራፎችን በህሊናችን ላይ ታትሟል።

ወጣቱ በከፈለው ክቡር መስዋዕትነት ምክንያት ባለፉት ጥቂት ወራት በሀገራችን አንጻራዊ የሆነ የለውጥ ተስፋ አንሰራርቷል። በተለይም አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ አሊ የሰላም ፣ የዕርቅና የአገራዊ አንድነት ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስፕራ የምንኖር ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቧል።

የእነ ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ፣ አቶ አንዷለም አራጌ ፣ ኡስታዝ አመዲን ጀበል ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ፣ አቶ በቀለ ገርባ ፣ ወ/ት ንግስት ይርጋ ፣ እንዲሁም ይፈታሉ ተብሎ በመንግስት ሚዲያዎች የተነገረውና የሚጠበቀውን የታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ሌሎች በአስር በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈታት የጠ/ሚ ዓብይ አመራር ውጤት ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሰላም፣ የዕርቅና የአንድነት ጥሪና ተግባሮች ለማበረታታትና ኢትዮጵያውያንን መካከል የተፈጠረውን መራራቅና መከፋፈል ለማስወገድ ሲባል የፌደሬሽኑ ቦርድ ጠ/ሚ ዓብይን በ35ኛውን አመታዊ የስፓርትና የባህል ፌስቲቫል በዳላስ ቴክሳስ በእንግድነት እንዲጋብዝ በትህትና እጠይቃለሁ!

ልጅ ተክሌ ዘብሄረ ቡልጋ።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ በዳላስ 2018

Postby እሰፋ ማሩ » Wed May 30, 2018 1:37 pm

የዶር አብይ ጥያቄን እንዲቀበሉ ለያለንባቸው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ም/ቤት በመደወል በሰ/አሜሪካ ያሉ ይህን የሰላም የእርቅ ሃሳብ ደወለው ይነገሩ ዘንድ ይዝርዝራቸው ቀጥሎ ይገኛል :-

https://esfna.org/home-2/board-of-directors/
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests