የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Sat Nov 11, 2017 8:03 pm

ሰላም ዋርካ ፡እንዴት ሰነበታችሁ ?
እስቲ እንቀጥል
የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ትንተና በዚህ ብቻ የሚቀር ወይም የሚቆም ነገር አይደለም፡፡ ጊዜ ሲኖር ሳይካትሪስቱ ቆቁ አንድ በአንድ ይመለስበታል
የዛሬው ጥያቄ
እንዴ አድርጎ ከነዚህ ግለሰቦች ጋር መኖር ይቻላል የሚለው ይሆናል፡፡
የናርዚስት ዲሶርደር ያለባቸው ግለሰቦች
በፖለቲካው መድረክ ዋና ዋና ቦታ ሲኖራቸው
በሐይማኖት ድርጅት መዋቅርም ዋና ዋና ቦታ ይዘው ይገኛሉ
ንብረት ወይም በሆነ ነገር ተሰጥዎ ያላቸው ግለሰቦች ሊሆኑ ይችላሉ
ዝነኛ የኩዋስ ተጨዋቾች ወይም ዝነኛ ዘፋኖች ወይም ዝነኛ የሆነ ነገር ሊሆኑ ይችላሉ
በጠቅላላው እብረውን የሚኖሩ ግለሰቦች ናቸው ፡፡
በሐገራችን በኢትዮጵያ ሁኔታውን ለመግለጥ እስቸጋሪ ብሆንም በአሜሪካ እና በእውሮፓ ግን ከልጅነት ጀምሮ የዚህን ዲሶርደር ሁኔታ ለመተንተን እያዳግትም በጣም ቀላል ነው ፡፡ልዩነቱ ለማሳየት ይህንን ያህል የሚያዳግት አይሆንም፡፡
በአውሮፓና በአሜሪካ ሁኔታውን ለመተንተን ከልጅነት ጀምሮ ማጥናት ሲያስፈልግ ፡፡ በሐገራችን ግን በተቃራኒው የግለሰቡን ሁኔታ ካለበት ሁኔታ ወደ ልጅነት ታሪኩ በማጥናት ይሆናል፡፡
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Fri Jun 29, 2018 5:09 pm

እስቲ እንመልስ ወደዚህ ዓለም ወደ ዋርካ ጄኔራል፡፡
የፐርሶናሊቲ ዲሶርደርን አስመልክተን ወደ ሐገራችን ስንመለስ ከልጅነት ጀምሮ በማጥናት ሳይሆን ከትልቅነት ወደ ልጅነት ወደ ሁዋላ ተመልሶ በማጥናት ነው የሚታወቀው ብሎ ነበር ሳይካትሪስቱ ቆቁ ፡፡

አደናጋሪ ቃላትን መወርወር ፡

በሐገራችን በነበረው የፖለቲካ መድረክ አያሌ ፖለቲከኞች መነሳታቸው ግልጽና ፍርጥርጥ ያለ እውነታ ነው ፡፡

ብዙዎቹ ፖለቲከኞች ከፖለቲካው ሳይንስ በመመረቅ ወይም በሶሺያል ሳይንስ ውስጥ በማለፍ ሳይሆን ከወታደሩም ከአስተማሪውም፡ ከሰራተኛዉም ከተማሪውም ከዛም ከዚህም የተውጣጡ እንደነበረ መጥቀስ አያስቸግርም ፡፡

ከፖለቲካ ሳይንስ የወጡትም ቢሆን በወቅቱ የፖለቲካ መስመር ( እይዲኦሎጂ ) ውስጥ ስለተነከሩ ስለኢትዮጵያ ባህላዊ ሕዝባዊ ችግር መፍትሄ ከመሆን ይልቅ ችግር ሆነው ነው ያለፉት ፡፡
ሰላምና ዲሞክራሲ እንፈጥራለን ብለው ብጥብጥና እምባጉዋሮ ችግር ነው የፈጠሩት

እንደውም በመቃብሮች ላይ አበቦች እንደሚያብቡ ለማስረዳትም የሞከሩበትም ጊዜ ነበር( ሌላው አደናጋሪ መፈክር )

የኛ ፖለቲከኞች ከቀዳማዊ ሐይለስላሴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሚገልጹዋቸው ቃላቶች ለሰሚ የሚገርሙ እና የሚያደናብሩ ናቸው፡፡

በነዚህ በኛ ፖለቲከኞች ብዙ ጊዜ የሚሰነዘሩ ቃላቶች ይህንን የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር እንዴት እንደሚገልጹ ወደፊት በዚህ ዓምድ ላይ እንመለከታለን፡፡
(የተሰባሰበ የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ግሩፕ)

በፖለቲካው ዓለም የተጀቦኑ ቃላቶች ማለትም አጠቃላይ የሆኑ ቃላቶች በትርጉማቸው የሚያደናብሩ ፡ ዝም ብሎ ተቀብሎ ሆ ብቻ የሚባልባቸው ቃላቶች ነበር የሚሰነዘሩት ፡፡
ዳቦ አይፈጥሩ ፡ እንጀራ አይፈጥሩ በአጠቃላይ ስራ የማይፈጥሩ ሰገራ የሆኑ ቃላቶች ነበሩ ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡

አንዳንድ ቃላቶች የኢትዮጵያን ተማሪ ጦርነት ውስጥ እንደከተቱት ታሪክ ያስረዳል ፡፡
ለምሳሌ
በወዝ አደርና በላብ አደር መካከል ያለው የቃላት ልዩነት ሁለት በዛን ጊዜ የነበሩትን እንጋፋ የፖለቲካ ድርጅቶችን ጥይት ሊያማዝዝ በቅቶአል

ይህንን ስንመለከት በእውነት ወዛደርና ላባደር የሚሉት ቃላቶች ጦርነት የሚያስነሱ ቃላቶች ናቸው ?

በነዚህ ቃላቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር ፡ድህነት፡ ስራ አጥነት፡ የመሳሰሉት ወይም በጠቅላላው ባህላዊ እና ሕዝባዊች ችግሮች ይ ፈቱ ነበር ? በማለት ሳይካትሪስቱ ቆቁ ያልፍና

እስቲ ቃላቶችን አንድ በአንድ እንመርምር ይላል በዚህ ጽሁፉ
ምሳሌ 1 -----------------" አብዮቱ ያሸንፋል "
ምን ማለት ነው አብዮቱ ያሸንፋል ማለት ?
ይህ ቃል ከየት መጣ ?
የተኮረጀ ቃል?
እነማን ናቸው ይህንን ቃል የፈለሰፉት ?
አብዮት ማለት ሕዝብ ማለት ነው ?
አብዮቱ ማንነው የሚያሸንፈው ?
ለማን ነው ይህ መፈክር የሚፈከረው ? ለኢትዮጵያ ሕዝብ ? ወይስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ?
እንደዚህ ያለ የተጀቦነ ቃል ፡ ውዥንብር የሚነዛ ቃል የሚያደነባብር ቃል እንዴት ሊፈጠር ቻለ?


ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ????
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Mon Jul 02, 2018 6:14 pm

ምሳሌ 2 ኦርቶዶክስን ሰባበርነው
Our governor is Jesus Christ... And our flag that of Ethiopia. Our religion is that of Yohannes IV. People of Tigray, follow the motto of Weyane.
ይህ ከላይ የምታዩት ጽሁፍ ከዊኪፒዲያ ላይ የተጠቀሰ ጽሁፍ ነው
ቀዳማይ ወያኔ በሐይለስላሴ ዘመነ መንግስት የመጨረሻው ዓላማ እና ውሳኔው ከላይ በተገለጸው ጽሁፍ ይገለጻል ፡፡

ገዢያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ እምነታችን የዮሓንስ አምነት ነው

ከዛስ የተከተለው ምን ይላል ?

ነገር ግን በአንድ ወቅት " ኦሮቶድክስን ሰባበርነው " የሚል ቃል በአንድ ጉብኤ ተሰምቶአል

የሚያስደነግጥ አባባል ነው
ግራ የሚያጋባ ክርስቲያኑን ብቻ ሳይሆን እስላሙንም ጨምሮ ማለት ነው

ምን ማለት ነው ኦርቶዶክስን ሰባበርነው ማለት ?

ለምን ኦርቶዶክስን ሰባበርነው ማለት አስፈለገ ?

ይህንን የተናገረው ግለሰብ እምነቱ ምንድነው ነው ?

በየት ሐገር ነው ጸረ ኦርቶዶክስ እምነት የተከሰተው?
የራሺያ ኦርቶዶክስን?
የምስራቅ ኦርቶዶክስን?
የኮፕቲክ ክርስትናን ?
ምን ለማለት ነው እንደዚህ ያለ አደናጋሪ ፡ የተጀቦነ እና ትርጉም የሌለው ቃል የተነዛው

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ???
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Sat Jul 07, 2018 1:46 pm

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብ ለስልጣን ፍለጋ ፡ ከሁሉም በላይ ሆኖ መገኘትን የሚመርጥ ግለሰብ ነው፡፡

የተናገረውን መቃወም ፡ ወይም ማሻሻል አይቻልም እንደዚህ ያለ ሙከራ ከተደረገ ነገሩ አለቀ ደቀቀ ማለት ይሆናል ፡፡

-ውሸት እና እውነት ድምበራቸው የት እንደሆነ መግለጽ የማይችል ግለሰብ ነው ፡

- ሲርቁት እንደ ማግኔት ለመሳብ ሲጠጉት እንደሾህ የሚወጋ ግለሰብ ነው ፡፡

-ሰውን ከማጥመድ ስራ ሌላ ስራ የለውም የሚያጠምደውን ሰው ደግሞ ማጥመድ ብቻ ሳይሆን የማሽመድመድ ችሎታ ያለው ግለሰብ ነው ፡፡

በዚህ የፐርስናሊቲ ዲሶርደር ግለሰብ ስር ሌሎች ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር ያለባቸው ግለሰቦች ከተሰለፉ ነገሩ ሁላ የተዘበራረቀ፤ ለሌላው ሕዝብ ጤና የማይሆን ችግር ተወለደ ማለት ይሆናል ፡፡

እንደዚህ ያለ ችግር የሚወለደው በስራ ቦታ የስራው ማናጀር በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የተበላሸ ከሆነ እና በስሩ ያሉት ምክትል ማናጀሮች እና የመሳሰሉት በዚህ በፐርሰናሊቲ ዲሶርደር ተበላሽተው የዋናው ማናጀር ጥገኛ ከሆኑ ድርጅቱ ሁላ በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ግለሰቦች የሚመራ ይሆንና መላ ሰራተኛውን ለአማኑኤል የሚዳርግ መርዝ ይሆናል ማለት ነው ፡፡

በፖለቲካው ዓለም ከሆነ ደግሞ ከመሪው በስተጀርባ ወይም በመሪው ስር የሚገኙት ረዳት ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለባቸው ይደማመሩና የፖለቲካው ይዘት በሙሉ መላውን ሕዝብ ራስ የሚያዞር ከጥይት እና ከዱላ እንዲሁም በእስርቤት ከማጎር በስተቀር መፍትሄ የሌለበት ስርዓት ይሆናል ማለት ነው ፡፡ ምንክንያቱም ሰውን ማመን የሚባል ነገር በፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ለተለከፈ ሰው ዱብእዳና እንግዳ ነገር ስለሆነ ፡ ሰውን ማመን የማይዋጥ ነገር በዚህ በሽታ ለተለከፈ ሰው ማለት ነው፡፡

በነ ኢዛና ሐገር
በነ ካሌብ ሐገር
በነ እቡነ እረጋዊ ሐገር
በዘጠኙ ቅዱሳን ሐገር
በነ ዮሃነስ ሐገር
ኦሮቶድክስን ሰባበርነው ሲባል
ኢዛና ምን ይል ነበር ፡
ካሌብ ምን ይል ነበር ፡
አቡነ አረጋዊ ምን ይሉ ነበር
ዮሐንስ ምን ይል ነበር ብለን ለማለፍ እንችላለን ምክንያቱም እነሱ የሉምና ነገር ግን ይህንን የሰሙ ክርስቲያኖች ፡ እስላሞች አብረው ያጨበጨቡ ግለሰቦችን ምን ብለን እንለፋቸው ?
????
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Sun Jul 08, 2018 3:33 pm

የነ ፡ዓጺ ገብረ ፡መስቀል፡ ሐገር ፡፡

የነ ፡ቅዱስ፡ ያሬድ ፡ሐገር ፡

ዜማው ፡ቅዳሴው፡ ዘፈኑ ሁላ ፡ የያሬድ የቅዱሱ ያሬድ ሐገር በሆነባት ኢትዮጵያ ፡ አክሱም ኢትዮጵያ እንዴት ኦርቶዶክስን ሰባበርነው የሚል ቃል ሊወጣባት ቻለ ?

ይህ ቃል ሲወጣ እንዴት የቅዱስ ያሬድ ዝርያዎች የገብረመስቀል ዝርያዎች ፡ የነ ካሌብ ዝርያዎች ፡የነ ኢዛና ዝርያዎች ፡ዝም ብለው፡
አጨብጭበው አለፉ ?

ግራ የሚያጋባ ለሰሚው የሚከብድ አባባል !!!

እውነት ኦሮቶዶክስ ተሰባበረ ?

በእውነት ቅዱስ ያሬድ ተሰባበረ ?
በእውነት ኢዛና ተሰባበረ ፡?
በእውነት ካሌብ ተሰባበረ?
በእውነት ፍሬምናጦስ ተሰባበረ ? በእውነት አቡነ አረጋዊ ተሰባበሩ ?

የሚገርም የሚያስደነግጥ አባባል ነው ነው ፡
ለመስማት የሚያዳግት ፡ ????

በሚቀጥለው
ምሳሌ ሶስት
" ዝምብም አልገደልኩም"
" ባንዲራ ጨርቅ "ነው
እንዲሁም ሌሎች .... አነጋገሮች ለፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ምሳሌ ይጠቀሳሉ

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Postby ቆቁ » Fri Jul 13, 2018 5:20 pm

ይህ ዓምድ የተከፈተው የፐርሶናሊቲ ዲሶርደርን ለማሳየት ነበር
ሆኖም በአጋጣሚ ነገሮች ስለተገጣጠሙ ሁኔታዎችን ለመግለጽ ወደ ፖለቲካው ዓለም ዘው ማለት የግድ ይሆናል

ባንዲራ ጨርቅ ነው

በእውነት ባንዲራ ከጨርቅ መሰራቱን የማያውቅ ፍጡር በዚህ ዓለም ይኖር ይሆን ?
ወይስ ውዥንብር እና ግራ ማጋባትን ለመፍጠር ?
ውዥብር ማደናገር ለመፈጠሩ በአሁኑ ሰዓት ስለ ባንዲራ ያለውን አመለካከት መከታተል በቂ ነው ፡፡

ባንዲራ ጨርቅ ነው አዎ ጨርቅ ነው ፡
ባንዲራ ብረት ነበር እንዴ ወይስ ባንዲራ እንጨት ነበር እንዴ እያልን ብንጠይቅ በነገሩ መርቅነን፡ በሐሳብ ሰክረን መደፋታችን ይሆናል
የተደናገር ግለሰብ ባንዲራው ከጨርቅ ለመሰራቱ እንደገና መመልከት መዳሰስ ሊኖርበት ነው

ነገር ግን የዚህ ባንዲራ ጨርቅ ነው የሚለው አባባል ለምን አስፈለገ ?

የየክልሉ ብሄረ ሰብ ባንዲራ እንዲያውለበልብ ተደርጉዋል በየክልሉ ባንዲራ ብቻ ነው የሚታየው
የኢትዮጵያ የእሜሪካ የእስርኤል የእልጄሪያ የናይጀሪያ የመላው ዓለም ሐገሮች ባንዲራ ሁላ ጨርቅ ነው ብረት አይደለም
ታዲያ ይህ እንደዚህ ሆኖ ለምን ባንዲራ ጨርቅ ነው ለማለት አስፈለገ ?ዛሬ ጊዜው ተገላበጠና የባንዲራ ጥያቄ ያንገበግብ ያንሰፈስፍ ጀመር

ባንዲራ በኢትዮጵያ ምድር ይውለበለብ ጀመር
የሚውለበለበው ያ ጨርቅ የተባለው ባንዲራ ነው ፡

ባንዲራ በባንዲራ ሆነች ሐገራችን ለዛውም በኪሎሜትር ርዝመት

ባንዲራ ጨርቅ አልነበረም እንዴ ዛሬ ምን ነካው ባንዲራ ?

እንደውም ከዛ እልፎ ባንዲራው ይህ አይደለም ባንዲራው ይህ ነው የሚል እምባጉዋሮ የተጀመረ ይመስላል

አንደኛው ሕገ መንግስቱን ይጻረራል የአሁኑ ባንዲራ ሲል ሌላኛውም እንደዚሁ በእሁኑ ሰዓት የሚውለበለበው ባንዲራ ትክክለኛ ባንዲራ አይደለም በማለት ሊያስረዳን ሊተነትልን ይሚክራል

ባንዲራ ጨርቅ ነው ሲባል የት ነበሩ እነዚህ ተከራካሪዎች?

እንደ እስስት መለዋወጥ ?

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር???

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4067
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests