Peace, love and harmony !!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Peace, love and harmony !!

Postby ምጥኔ » Mon Aug 22, 2005 4:16 am

ሰላም ለሁላችሁም

<<<REMEMBER THAT THIS IS HATE FREE ZONE>>>

<<<<-----LOVE PEACE AND HARMONY :!: ----->>>>

መልካሙን ሁሉ
Last edited by ምጥኔ on Sun Apr 02, 2006 11:13 am, edited 19 times in total.
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

Postby ምጥኔ » Wed Aug 24, 2005 12:17 pm

ሰላም ለሁላችሁም

1: Ethiopian Wood Collector

ምናልባት ያላያችሁት ካላችሁ እንድታዩት ነው ::

ሁሉንም ታሪኩን ለማንበብ just click the link below.
http://news.bbc.co.uk/1/shared/spl/hi/p ... html/1.stm

ከዚህ በተጨማሪ እዚሁ Picture Gallery ውስጥ በሌላ አርስት ስር ተጨማሪ ፎቶዎች ስላሉ ለማየት ከፈለጋችሁ እንድታዩት ለመጠቆም እፈልጋለሁ::
መልካሙን ሁሉ
Last edited by ምጥኔ on Sat Oct 15, 2005 12:00 am, edited 3 times in total.
ከክፋቱም:ከልፋቱም ሆነ ከውጣውረዱ ጋር ይህ አለም ግሩም ስፍራ ነው:: እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት:: ደስተኛ ለመሆን ተጣጣር:: :lol:
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

Postby ዶማው2005 » Wed Aug 24, 2005 9:36 pm

thanx fo sharing...
[/code][/quote]
ዶማው2005
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1650
Joined: Sat Jun 04, 2005 11:19 pm
Location: United States

...ለዶማው 2005

Postby ምጥኔ » Wed Aug 24, 2005 11:55 pm

ሰላም ላንተ

Sharing is happiness ! አይደል እንዴ የሚሉት??

መልካሙን ሁሉ
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

18 years ago in TIME

Postby ምጥኔ » Thu Aug 25, 2005 12:13 am

ሰላም ለሁሉም

2. 18 years ago in TIME Magazine,(from TIME Aug 15,2005)

August 15, 2005 TIME Magazine ገጽ 11 ላይ የወጣውን (ከ 10 ቀን በፊት ማለት ነው) ላላያችሁት ነው::
እንዲህ ብሎ ይጀምራል:
As with the current FAMINE in Niger, the humanitarian crises in Ethiopia two decades ago was a terrible sight to behold.

Image
Dec 21, 1987

ሁሉንም ለማንበብ ክፍያ አለው :shock: ......ግን ትንሽም ቢሆን እናነባለን ከተባለ here is the link
http://www.time.com/time/archive/previe ... 91,00.html

እንደው እስቲ የትኛውም አገር በተራበ ቁጥር ኢትዮጵያ ነች ምሳሌ መስጫ ማለት ነው :?: :?: መቼስ ስማችንን ሳይጠሩ አያስችላቸው...ውይ :arrow: :arrow:

መልካሙን ሁሉ
ብልጽግናም ለሀገራችን
አሜን
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

Postby ዶማው2005 » Thu Aug 25, 2005 9:51 pm

u just read ma mind, girl....why can't those moffos leaves alone? The story back in 198x; and they still refer us for any famine in da whole world... :twisted:
ዶማው2005
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1650
Joined: Sat Jun 04, 2005 11:19 pm
Location: United States

....ለዶማው

Postby ምጥኔ » Sun Aug 28, 2005 9:04 am

ዶማው2005 wrote:u just read ma mind, girl....why can't those moffos leaves alone? The story back in 198x; and they still refer us for any famine in da whole world... :twisted:

ሰላም ላንተ ዶማው
እኔም ያልኩት ይህንኑ አይደል? እስቲ ለትንሽ ግዜ እንኩዋን ቢረሱን ምን አለበት??? መቼም አይሆንላቸውም ባይሆን እንዲህ ብለው የጻፉት ይሻል ይሆን ?

Worries in Ethiopia
The Economist, Aug 11, 2005.
ALREADY at least 75m-strong, making it the second most populous country in Africa after 130m-strong Nigeria, Ethiopia could, by some estimates, be home to 140m people by 2030. :shock: :shock: It is not standing still: food production has more than doubled since 1993. :lol: :lol: Even so, by the government's own reckoning, 9m Ethiopians now depend on food aid and another 18m are malnourished.… :(
መልካሙን ሁሉ
ከክፋቱም:ከልፋቱም ሆነ ከውጣውረዱ ጋር ይህ አለም ግሩም ስፍራ ነው:: እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት:: ደስተኛ ለመሆን ተጣጣር:: :lol:
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

Hunger, intelligence and development

Postby ምጥኔ » Tue Aug 30, 2005 4:06 pm

ሰላም ለሁላችሁም

ስለአገራችን በ Western Magazine የተጻፉ ጽሁፎች በምንኖርበት አገር እውሮፓም ይሁን አሜሪካ ለሚኖረው ህብረተሰቡ ስለ አገራችንም ሆነ ስለኛ ያለውን አስተሳሰብ ምን ያህል affect ሊያረግ እንደሚችል ግልጽ ነው:: ስለ አገራችን በብዛት የሚጻፈው ረሀብና ከዚሁ ጋር የተገናኘ ነገር ብቻ ነው ለማለት ያስደፍራል:: ያው አትሌቶቻችን ሲያሸንፉ ካለው ዜና በስተቀር:: የምናውቀው ነው ምንም አዲስ ነገር የለውም ልትሉም ትችላላችሁ ግን ወደድንም ጠላንም እነዚህ ነገሮች ትንሽም ቢሆን ሳይረብሹን አይቀሩም:: በተለይ ይህንን ያነበበ የስራ ባልደርባችን በጠዋት ቡና ስንጠጣ አግኝቶ አየኸው/ አየችው ስለ ኢትዮጲያ የተጻፈውን ሲለን/ስትለን :: በአካባቢው የነበሩት ሰዎች ከተጨመሩማ..... :!: ወይ post-it ተለጥፎበት ለእከሌ/ሊት ይህንን ገጽ እየው/እይው ተብሎ ሰኞ ጠዋት ዴስኩ/ዋ ላይ ሲያገኘው/ታገኘው :roll: :roll:

ለማንኛውም ለዛሬ ሌላ ያየሁትን ላላየችሁት ልጠቁም ብዬ ነው :arrow: :arrow: :arrow: ሙሉን ግዜ እንዳገኘሁ እጽፈዋለሁ ::

እና እያንዳንዳችን በውጭ አገር ኑሯችንን ለማሸነፍ እና የተሻለ ነገር ለማግኘት በትምህርትም ሆነ በስራ አለም በተቻለን መጠን competitive ሆነን ለመገኘት የሚቻለንን ጥረት እያደረግንና የምናደርግ ይመስለኛል:: ነገር ግን አንድ ከዚህ በታች የተሳፈውን article ያነበበ Employer ከአንድ የአገራችን ሰው ውይም ከሌላ 3ኛው አለም ዜጋ የሚቀርብለትን የስራ ማመልከቻ እንዴት free from bias ሆኖ evaluate ሊያረገው ይችላል ???????

Hunger, intelligence and development
Jul 29th 2004
The Economist

PEOPLE in very poor countries are, on average, less intelligent than those in rich ones. Some readers may be shocked by this statement.

መልካሙን ሁሉ
ከክፋቱም:ከልፋቱም ሆነ ከውጣውረዱ ጋር ይህ አለም ግሩም ስፍራ ነው:: እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት:: ደስተኛ ለመሆን ተጣጣር:: :lol:
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

አፍሪካ የተማሩ ልጆቿን ማጣቷ

Postby ዘላለማዊ » Tue Aug 30, 2005 6:36 pm

ሰላም ያገር ልጆች

ኢኮኖሚስት መጽሄት ያቀረበው ዘገባ በእጅጉ አሳዛኝ ነው:: ሌላው የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ አፍሪካ በዓመት የተማሩ ልጆቿ በሀብታም አገሮች በመነጠቅ 700 ሚሊዮን ዶላር አሳልፋ ትሰጣለች:: ሐብታም አገሮች ለስልጠና የሚመድቡትን በጀት በየጊዜው እየቀነሱ የሚገኙበት አንደኛው ምክንያት አንዱ ከድሀዋ አፍሪካ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) በነጻ የሚያገኙት የሰው ኃይል መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ (በተለይ የዐለም ባንክ)::

በሌላኛው ዘርፍ ደግሞ "PEOPLE in very poor countries are, on average, less intelligent than those in rich ones' እንዲህ ይሉናል::

ቁምነገሩ ምን ይጠበቅብናል:: አገራችን ረሀብ መኖሩ ሀቅ ነው; ግን እስከመቼ እንዲህ እንጔዛለን? ማብቂያው የት ነው? ምንድን ነው የተሳሳትነው? የትጋ ነው ይህ የረሀብ ቀለበት የሚሰበረው? በምግብ እርዳታ የትም መድረስ አንችልም:: የምግብ እርዳታ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘን ነው:: በተለይ አገራችን ለዚህ ማስረጃ ናት:: የ30 ዐመት የምግብ ተረጂነቷ ረሀቡን ሊያጠፋ አይችልም::

ሲርበን ጆንያ ስንዴ አንጠልጥለው ከመምጣት ያለፈ የልማት ስራዎች ላይ ሳንቲም ለመስጠት እንደሚቸግራቸው ለጋሾቻችን ገልጠውታል:: ከሰሀራ በታች ካሉ አገሮች የመጨረሻውን ዝቅተኛ የልማት እርዳታ የምትቀበል አገራችን ናት; በድንገተኛ ጊዜ እርዳታ (በረሀብ) ግን በአለም ከፍተኛ እርዳታ ከሚቀበሉ አገሮች ተርታ ነች:: ምንድነው ወንጀላችን የልማት እርዳታ የተከለከልንበት?

አንድ የአለም ባንክ ጥናት ለሚቀጥሉት 20-30 አመታት ኢትዮጵያ ከረሀብ አትላቀቅም የሚል አንብቤ ልቤ ተሰበረ:: ምን ይሻለናል? እስኪ ያስተዋላችሁትን አካፍሉን? መውጫ መንገዱ ወዴት ነው?

ቁምነገር ብንነጋገርበት ፍሬ እናፈራ ይሆናልና; መተከዙን ትተን በዚህ አቅጣጫ ያለንን ለምን አንካፈልም?
ዘላለማዊ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Mon Aug 16, 2004 12:03 pm
Location: ethiopia

....

Postby ምጥኔ » Wed Aug 31, 2005 3:54 pm

ሰላም ላንተ ዘላለማዊ
በርግጥ እንደዚህ አይነት ስለአገራችንም ሆነ ስለ ሌሎች 3ኛው አለም አገሮች የተጻፉ articles ብናያቸው ስለኛ ምን እየተባለ እንደሆን ግንዛቤ ይሰጠናል የሚል ግምት ስላለኝ ነው አንዳንዶቹን ለመጻፍ የፈለኩት:: አንዳልከውም ልብ የሚሰብር ነው አንዳዱ አባባል:: ምን ይደርግ ?????
መልካሙን ሁሉ
ከክፋቱም:ከልፋቱም ሆነ ከውጣውረዱ ጋር ይህ አለም ግሩም ስፍራ ነው:: እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት:: ደስተኛ ለመሆን ተጣጣር:: :lol:
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

They said "we got the lowest IQ cvalues". Right?

Postby 4get.this » Wed Aug 31, 2005 7:30 pm

ሰላም ምጥኔ

ከአመት በፊት ይመስለኛል: ከአንድ ወዳጄ "ከሁሉም ኣናሳ I.Q. ያላቸው ኢትይዮጵያውያን ናቸው" የሚል "paper" ታትሞ እንደነበር ያጫወቱኝ ይመስለኛል። ኣይተሽው ይሆን? ምንጩን ልትጠቁሚኝ ከቻልሽ?

ኣክባሪሽ
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Re: They said "we got the lowest IQ cvalues". Right?

Postby ዶማው2005 » Wed Aug 31, 2005 9:17 pm

4get.this wrote:ሰላም ምጥኔ

ከአመት በፊት ይመስለኛል: ከአንድ ወዳጄ "ከሁሉም ኣናሳ I.Q. ያላቸው ኢትይዮጵያውያን ናቸው" የሚል "paper" ታትሞ እንደነበር ያጫወቱኝ ይመስለኛል። ኣይተሽው ይሆን? ምንጩን ልትጠቁሚኝ ከቻልሽ?

ኣክባሪሽ

እውነት እውነት ከተባለ American have da lowest IQ...they have no clue what'z goin on around....እነሱን ነበር ዶማ ማለት :) ...
there are still Americans (18+) who DO NOT know the name of Iraq's former leader...አይገርሙም?

Generally, the mothafuckas don't wanna say any good about 3rd World Countries
ዶማው2005
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1650
Joined: Sat Jun 04, 2005 11:19 pm
Location: United States

ረሀብና የአእምሮ ችሎታ

Postby ተፋለም » Wed Aug 31, 2005 11:09 pm

ትክክል ነው:: ረሀብ በበዛበት አካባቢ የህብረተሰብ የጋራ አእምሮ ችሎታ ይቀንሳል:: ይህ በምርምር የታወቀ ጉዳይ ነው:: ካለው የምግብ ማነስ የተነሳ አእምሮ ተፈላጊውን የምግብ ንጥረ ነገሮችን በበቂ መጠን ስለማያገኝ ነው::
ተፋለም
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Thu Aug 18, 2005 5:20 am
Location: united states

Re: ረሀብና የአእምሮ ችሎታ

Postby 4get.this » Thu Sep 01, 2005 11:39 am

ተፋለም wrote:ትክክል ነው:: ረሀብ በበዛበት አካባቢ የህብረተሰብ የጋራ አእምሮ ችሎታ ይቀንሳል:: ይህ በምርምር የታወቀ ጉዳይ ነው:: ካለው የምግብ ማነስ የተነሳ አእምሮ ተፈላጊውን የምግብ ንጥረ ነገሮችን በበቂ መጠን ስለማያገኝ ነው::

እጠራጠራለሁ:: እንዲያ ቢሆን ኖሮማ ... አሁን በምእራቡ አለም ያለው ትውልድ ከቀዳሚው ትውልድ በልጦ "ተአምር ፈጣሪ" በሆነ ነበር:: በትክክል እያየነው ያለነው ግን: ያው ባባቶቻቸው መሰረት ላይ ጥቂት ጥቂት እየሄዱ እንዳለ ብቻ ይመስለኛል:: በአገራችንም ብናይ: የገበሬ ብልሀት የተሻለ የተመጣጠነ ምግብ ከሚያገኘው ከከተሜ ሳይበልጥ ይቀራል :?:

ከሰላምታ ጋር
ተመለስኩ ማለት ነው? :-?
4get.this
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 505
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:37 pm
Location: escaped from nursing home

Postby ምጥኔ » Thu Sep 01, 2005 10:04 pm

ሰላም ለሁላችሁ

ዶማው.....ልክ ብለሀል..ባይገርምህ 'excuse me for my ignorance but where is Ethiopia?? or 'sorry I am not good at Geography where is Ethiopia' ብሎ የጠየቀኝ ጥቂት ፈረንጅ አይደለም::ከቤቴ አከራይ ጀምሮ :lol: በርግጥ አሁንም ረሀብ/ጦርነት አለ ብለው ስላልጠየቁኝ በጣም ደስ ያለኝ ቢሆንም ግን አለማወቃቸውን አውቀው መጠየቃቸው ደስ ብሎኛል ለማለት ነው::
በተለይ አንዳንድ ምእራባዊያን ጋዜጠኞች ሆን ብለው ይመስለኛል መጥፎ ነገር ፈለገው የሚያወሩት::በተለይ ዶክመንተሪ ፊልም አለማየት ነው:: አንድ ግዜ በናይሮቢ ዙሪያ ስለሚኖሩ ሰዎች ተብሎ የታየውን ካየሁ ጀምሮ ስለኢትዮጲያ ምን ይመጣ ይሆን እያልኩኝ እስካሁን አለሁ:: በጣም የሚዘገንን እስካሁን አልታየም ማለት ከረሀቡ ሌላ ማለት ነው::እሱም ቢሆን የተጋነነ አልነበረም ፊልሙ ሌላ ግዜ ከሚያሳዩት ማለት ነው ወሬው ግን አዎ::(ባለፈው በBBC ስለ ሀገራችን ተላለፈ ያሉትን እስካሁን አላየሁትም ግን ብዙ ተቃውሞ እንዳስከተለ አንብቤአለሁ)

4get.this--- የ IQ. ያልከውን ነገር እንኩዋን አላየሁትም:: ቢጻፍ ኖሮ እኔ እንኩዋን ባላየው ፈልጎ የሚያሳየኝ ብዙ ስለሆነ :lol: :lol: አያመልጠኝም ነበር :arrow: :arrow: specifically Ethiopia ተብሎ የተጻፈ አይሆን ይሆናል::

መልካሙን ሁሉ
ከክፋቱም:ከልፋቱም ሆነ ከውጣውረዱ ጋር ይህ አለም ግሩም ስፍራ ነው:: እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት:: ደስተኛ ለመሆን ተጣጣር:: :lol:
ምጥኔ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 461
Joined: Sun Jun 05, 2005 8:37 am

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests

cron