ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ሰላሙልኝ

Postby ባለሱቅ » Sun Sep 04, 2005 8:51 pm

ሀገርሽ የት ነው ቀዘባ
ተራራ ሜዳ ሀገር አንባ
አቤት ቁንጅና ውበቷ
የጀምጀም ላይጉጂ ልጅቷ
..
እንካ ብላ አልችኝ ደረቁን እንጀራ
እሷ በጣፈጠው በራሰው ልትበላ
ዲሲ ላይ ተኝቼ በልሜ የታየችኝ
የሲዳሞ ጉጂ አንጀቴን በላችኝ
....
እያለ ይዘፍን ነበር ገልቹ ኃይሉሸምቦ... ነፍሱን ይማረውና... በጊታሩ!...
በስራ ተወጥሬ ጠፋሁ አቦ!....
እንደምን አላቹ የወዩ ልጆች....
ሰላምታዬን በጉጂ ቱልቱማ ልጀምር ፈለኩና... ገና ጠጅ አልጠጣሁ... እረ ባፌ ወተትም አልዞረ...
አዮ... አሬራን ቀባ!
ሜ አስ ፊዲ!
ሜቃ!
ሱሙና ሰዲ!... ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ
ትንሽ ቀመስ ቀመስ....
ከቢራን ቀቡ?
አስ ፊዲ መሌ......
...
ሄ... ጉርባን ኩን ማሊፍ ጀዻ!
.........

በደበዳ ሀሬ... ኢልመን ሀጠሺ!....

ወዩን ከራ ሀገዽኡ....

ምናባት ጠፋብኝ እኮ.... አቤት ሲሰዳደቡ... አቤትትት ዋጋ ለመቀነስ የምከራከረው.... አቤትትትት ለቅምሻ እያልኩ የምጠጣው ወተት.... ስሙና-ሰዲ ሲጠፋ.... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንዴ የሰማሁት ነው..... የቅዳሜ ገበያ አልቆ... ጉጆቹ ጠጅ እየጠጡ ነበር.... ሰፈሩንና ነገሩን አልጥቀሰውና.. ብቻ አንዱ ጉጂ ጩኸቱን አቀለጠው... በር ላይ ወጥቶ.... ፖሊስ መጥቶ ምን እንደሆነ ሲጠይቀው ምን እንዳለ ታቃላቹ....
....
ይሄ እንትና... (ስሙን አልነግራቹም)....
ይሄ እንትና... ልጃገረዲቷን ሀሬዬን... ሰላብኝ.... .....
....
ቁመቱ እንዴት እንደደረሰለት ጌታ ይወቅ... ለነገሩ ልምድ ነበረው አሉኝ.... አሁን የት ይሆን ያለውውውውውውው...
.....
በተረፈ... እስኪ ትንሽ ፋታ ሳገኝ ብዙ ብዙ ትዝታዎች አሉኝ.. እዛች አገር ውስጥ.... እንዲሁ እንዲሁ እየተጨዋወትን ያንን ያልኳችሁን የመፃፉን ጉዳይም እንድንነጋገርበት እወዳለሁ....
የጌታ ፍቃድ ከሆነ በኦክቶበር አሜሪካ ሄጄ በማርች ወደ አዶላ ላቀና አስቤአለሁ.... የሚጠረቃቀም ነገር ካለ... መፃፍ መፃፍ መፃፍ... እስኪ ሁላችንም በያለንበት እንዘጋጅ... ከልብ .. በየዋህነት....
ማትሪክ ስፈተን አንዲትም መፃፍ ለማንበብ አልታደልኩም ነበር.... ጌታ ምስክሬ ነው.... ታናናሽ ወንድሞቻችንና ወገኖቻችን እኛ ያጣነውን ባያጡ... መልካም ምኞቴ ነውና...
በህብረታችን የድርሻችንንና የፍቅራችንን ለወዩ አንዲት ነገር እናኑር
አደራ በምድር በሰማይ...

ባለሱቅ ከትርፍ ሌላ ምንም አይቅም ብላቹ ወደ- "ትርፍ ካወጣች ኤርትራም ትሸጥ" ጎራ እንዳትመድቡኝ... አደራ
ያንፈራራው ሀጂ-ገሪገሪ የቢሉው ሼ-አሊፋሪስ... የ01ዱ ስላሴ የ04 ሚካኤል ከነደባሉ... መድሀኒአለምና ማርያም ይታዘቡኛል ... ብዋሽ...
.....
ወይ ጉድ ወሬኛ ሆንኩ"ኮ
ሆሆ
እስኪ ቸር ይግጠመን
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ቁጭ አድርጋችሁ አዋላችሁኝ እኮ

Postby ትትና » Mon Sep 05, 2005 12:14 am

ይቅርታ አድርጉልኝ ግን ሳልጠራ በመግባቴ:: ውይ ደስስስ ስትሉ እንዴት እንደምታስቀኑ!!! እግዚአብሄር ሀሳባችሁን ይሙላላችሁ:: በሉ እንግዲህ ለቁም ነገር አብቁት መሰባሰባችሁን::
እኔም አንድ ቀን የትውልድ መንደራችሁን ለማየት ያብቃኝ::

አክባሪያችሁ
ትትና
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

የጀምጀሙ ጉጂ የኒ ባለሱቅ

Postby የግልነስ » Mon Sep 05, 2005 2:45 am

ውይይይይ እንዲት ድስስስ ይላል የዛሪው ግጥምህ በተለይምም የጉጂ ጭውውትትህ ከምር ገበያ ክፍል ካለውው ትልቁ ገበያ መሀል ነው ያንቀዋለልከኝኝኝ ታውቃለህ ሁሊምም ያንተንን ጫወታ አልጠግበውምም ካወኩህ ጀምሮ ቅርንፍድድ ባክሽንን ሚሲጅሽንን እየጠበኩኝኝ ነውው ላኪልኝኝ እስቲ እናውራ እኒምም ቺካጎ ላሉት ወዩዎቸ መልክቲንን አስተላልፋያለውው በራስ ብሩ ተዛዝ መስረት በሉ እስቲ ለዛሪ ልስናበታቸውው የናተዋ የወዩዋ የግልልል ነኝኝኝ
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby ቅሩንፉድ » Mon Sep 05, 2005 11:26 am

ትህትናዬ ስለአድናቆትሽ አመስግንሻለው :!: ሲዳሞ ማለት በጣም የሚናፈቅ አገር ነው::እንደው በዝና ከሆነ የምታውቂው አንድ ቀን እንጋብዝሻለን መቼም ወረድ አላልሽ ይሆናል እንጂ ላንጋኖን ወንዶገነትን የምታውቂው ይመስለኛል::በዚያው መስመር ነው ይቺ ትንሽ ከተማችን የአዋራዋ ትዝታ ከፊት አይጠፋም::ስውም በጣም ሰለሚዋደድ ነው መሰለኝ ::
በይ ቸር ይግጠመን
ቅሩንፉድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 346
Joined: Fri Apr 15, 2005 9:07 pm
Location: germany

ለትትና

Postby ባለሱቅ » Tue Sep 06, 2005 11:53 am

ወተት ከናፈቀሽ... በቆራስማ ቅል
እሸቱን በቆሎ በገፉማ ሙልሙል
ባዶላ ወርቅ ጌጥ ካማረሽ መሽቀርቀር
ምጭና ተደሰች ጀምጀም ለሽርሽር::

በቦሬ ነጭ ማር በጀምጀሟ ቅቤ
በገብስማ ቆሎ በእንሰት ተከብቤ
እጠብቅሻለሁ ምርጥ አቀራርቤ::

ለጁስ አሬራችን ለኬክ ዳቦ-ሸዌ
ሀሪቲ ለሽታ ጤናዳም ለደዌ
ጠጁን ለመዝናኛ ቦርዴ ለቁርሳችን
ሁሉም ይዘጋጃል ነይ ነይ አዶላችን
እንጠብቅሻለን ዘርግተን እጃችን

ታዲያ እዛች ወዩ ዛፍ ላይ የሚንጠለጠል የስሙኒ ቅቤ ገዝተሽ መምጣት እንዳትረሺ.... አድባሯ ቅቤ ትወዳለችና

ሰላም ክረሚ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ሸጌ ነይነይ...................ላይ:

Postby ቀልቤለጌ » Tue Sep 06, 2005 3:09 pm

እንዴ............ሹፍ ቀልቤ የሞኬ ወንዲም...347..አታቁም.....ዬኛ ከፍቶች...ሹፍ..ወንዲሜ..ኢስቲ 1 ብሩ አምጣ......::
እኔ የራሴን ሳወራ ግዜ አጠፋሁ ወገኖቼ እንዴት ከረማችሁ! ተበራክታሁ የለም እንዴ:: (ትናንት ከሻለቃ ደስታ ጋር ነው ያደርኩት"ቢያስ......ንም ጮማ ይሻላል" አለች ብርሀኔ)ጊዜዬን ከናንተጋ ባጠፋ ና ሁሉም ቢቀርስ::የቀድሞ ክ/መንግስትን ሳስታውስ በተለይ አራዳ .አዲሴ-ሌቴ-ሲዴ-ጸጋዬ ሳንታ ሌሎችም በጣም ትዝ ይሉኛል::ጻዲቄ እና በጠሶቀጠሶንማ ሁኔታቸው ሁሉ አይረሳኝም::
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
ቀልቤለጌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 33
Joined: Wed Aug 31, 2005 1:08 pm
Location: UAE

ጉም ጉም

Postby አደቆርሳ » Tue Sep 06, 2005 4:43 pm

አካም ነጉማ ፈዩማ
አካም ነጉማ ፈዩማ...ኑ ነጋ ቀብና ጋሩማ
አካም ነጉማ ፈዩማ...
ይርጋለም አዋሳን ጌዴኦንም ዞሬ
ነጌሌ ቦረናን ክብረመንግሥት ዞሬ
ውብ ቆንጆ ፍለጋ ይርባ ላይ አድሬ
ከገብስ እሸት መሀል አገኘዃት ቦሬ::

መወለድ እንዳንቺ ሺሻ ገረምባው ሥር
ማደግስ እንዳንቺ አዋሳ ሀይቅ ዳር
መተኛት እንዳንቺ አንጥፎ አሹባ
መልበስስ እንዳንቺ ቆዳ ፍቆ ቱባ
ያለታ ብርቱካን የወንዶ አበባ
የአዶላ ቆንጆ ነይ የኔ ቀዘባ::

አላብዱና ማቲ ሆኩ ነው እድገቷ
ትዝ አለቺኝ አዮ ያንፈራራይቷ
ጉች ጉች ያለ ነው ጡቷ እንደደመና
ትናፍቀኛለች አጠገቤ ሆና !!!!እስቲ ማነሽ የግልነሽ ማነሽ ቅሩንፉድዬ እጣኑን ጨስጨስ አርጉት እንጂ::
አዎ እንዲያ ነው አቦ!................
ዝናዬ አሰጋኸኝ ባለህበት ሰላምታዬ ይድረስህ እነዚያ በርሲሳ ጋሎ የጻፍካቸው ግጥሞችህ ያቺን የጉጂ ባርኔጣ የደፋች ልጃገረድ ከነ ቡክቡካዋ ከተቆራሰመ የወተት ቡቄዋ ጋር እንዴት በግጥምህ እንደሳልካት:ትዝ አለና አቦ::አንድ የማውቀውን ልበላችሁ ግዜው አብዮት ነው:01ቀበሌ ፍ/ቤት ግቢ ውስጥ ስብሰባ ላይ:አብዮተኛ ሲናገር ሌላው አብዮተኛ (ብርሀኑ ደበላ)ወደኦሮምኛ ያስተረጉማል:በመሀል ተናጋሪው "የዛሩ መንግስት"ሲል አስተርጓሚው በኦሮምኛ ለመግለጽ ጥቂት ዝም ማለት: ሻምበል ባሻ ክፈለው ገዳ(ነፍሳቸውን ይማረውና) ጊዜም አልፈጀባቸው ወደ አስተርጓሚው ዞር ብለው "ሼጣና መንጊስቲ"ኢንጀቱ በማለት የሰለቸውን ህዝብ አዝናኑት:: ቸር ያቆየን::
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby ወቤ(ጃሎ) » Wed Sep 07, 2005 12:29 pm

በእውነቱ ስለ አዶላ(ክ/መ)በማንሳታችሁ በጣም ደስ ብሎኛል::የቦሬ ልጅ ብሆንም ክ/መን ከቦሬ ባልተናነሰ እወዳታለሁ: ራስ ብሩም በአንድ ወቅት 7ና8 ን ዉብሸት ምንድጌ የሚባል ዳይሪክተር በነበረበት ጊዜ ተምሬአለሁ::በጣም ብዙ ትዝታ አለኝ ሚ/ር ባክስቸር (አሜሪካዊ)አስተማሪ;ያሽልንግዬ ያሽልንግዬ ጉጂን ጉጂ ጂቤ ገብሬ መላጥዬ: --የሚለው መዝሙር;በዚያን ጊዜ የነበረ ኳስ (የመሰንጠቂያና ሌሎች ክለቦች) ወንድሙ ሳንታ;ሲሳይ ሳንታ;የወቅቱ አርቲስት አህመድ ሺፋ;እፍሬም ጎርፉ:ትዝ ይሉኛል::በተለይ 3ኛው ዙር መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሬጂ እብሮኝ ዘማች የነበረው ጓደኛዬ ወንደሰን ገድሌ ሁሌም አስታውሰዋለሁ::በተረፈ በርቱ እኔም ት/ቤቴን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ::እዚህ በምኖርበት እንግሊዝ ብዙ ልጆች እንዳሉ አውቃለሁ::ለማስተባበር በጀምጀም ወዩ ስም ቃል
ወቤ(ጃሎ)
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Wed Jul 28, 2004 6:57 pm

Postby ወቤ(ጃሎ) » Wed Sep 07, 2005 12:50 pm

ቃል እገባለሁ::በተለይ ትዝ የሚለኝ ሸዋ ሻይ ቤት በስሙኒ የስጋ ወጥ የምንበላው;የባላንበራስ መኮንን ሽንኮራ ;የአሮሬሳ ልጆች እነ ካሱ አለማየሁ ና ሌሎች የክ/መ አላዛር ጻዲቅ;ፍሰሀ;በተለይ በቀይ ሽብር የተገደለው እሱባለው ሳህሉ ጓደኛዬም ጎረቤቴም ነበር::የናንተው አብነት ጂሎ ኢጆሌ ቦሬ ከኢንግሊዝ
ወቤ(ጃሎ)
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Wed Jul 28, 2004 6:57 pm

Postby ቀልቤለጌ » Wed Sep 07, 2005 5:14 pm

አንተ ወቤጃሎ እንዴት ከረምክ ጃል!አደቆርሳ ያቺን አዮ ቦሬ ከገብሱ እሸት መሀል አገኘሁአት ሲል አምጣ የኔ ናት ለማለት ብቅ አልክ ብዬ........ ነበር:ዳሩ አንተም የራስብሩ ሆነህ በመምጣትህ ደስ ብሎናል::
ግን ከነዚያ የወቅቱ አርቲስት ካልካቸው ልጆች ውስጥ አህመድ ሺፋን አስታውሰህ ዘሜ ዓሊን መዘንጋትህ ገርሞኛል(የመጀመርያዋ ዳንሴሪ)ነበረቻ....:
ገሚሻ አሁንም ያው ነው:ደራርቱ የዘመዶቹን እርጎ እየጠጣ ነው::ከጠቀስካቸው ውስጥ ኤፍሬም ጎርፌና ወንድሙ ሳንታ አሁን በህይወት የሉም::በነገራችን ላይ የኢሀፓ እልቂት ሲጀመር በዚያው በጨምቤ በኩል እግሬ አውጪኝ ያሉ የወዩ ልጆች አሁን የት እንዳሉ የሚያውቅ አለ ???ተከስተ ሀብቴ ከረዥም ግዜ በሁዋላ ተመልሶ አሁን ያለው ክ/መ.ነው.እነ ሳህሉና ሀብቱ ኪዳኔ:ስለሺ ተስፋዬ.ከዚያ ደሞ እነ ተስፋዬ ሀ/ጊዮርጊስ(ጨጎና),አስቴር በተላ,የት ይሆኑ?እስቲ የሚያውቅ ካለ እጁን ያውጣ::
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
ቀልቤለጌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 33
Joined: Wed Aug 31, 2005 1:08 pm
Location: UAE

የወዩ ልጆች እንዴት ከረማቹሁ

Postby ቅሩንፉድ » Wed Sep 07, 2005 8:46 pm

ባለሱቅና አደቆርሳ በዚህች ግጥም እኔም የማይረሳ ትዝታ አለኝ:: በተለይ ከነዜማው ሲጫወተው ዝምነው:: እንዲያወም የወንድሜ ጎደኛ ስለነበረ እጣኑንም ስንት ቀን አጭሻለሁ መስለህ:: በነገራችን ላይ ራስ ብሩ የነስመኝን ሻይ ቤትን የሚያስታውስ የለም:: አቤት ብድር ደብተር ላይ የምናጽፈው:: ቀልቤለጌ ወፉንስ አታስታወስውም:: እንዲያውም የማልረሳው ሁልጊዜ ቡና ሲፈላ ጠዋት ጠዋት ቤታችን ይመጣል:: አቀማመጡ ራሱ ከፊቴ አይጠፋም :: ኩርምትምት ብሎ ተቀምጦ ላየው በሳቅ ነው የሚገድለው:: ሌላ ጊዜ እስቲ ስለሱ ጨምሬ እጽፋለሁ:: የምታውቁት ጨማምሩበት::
ቅሩንፉድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 346
Joined: Fri Apr 15, 2005 9:07 pm
Location: germany

ወፉ ????

Postby ቀልቤለጌ » Thu Sep 08, 2005 11:22 am

ሠላም ቅሩንፉድ በጽሁፍሽ የነስመኝ አለማየሁን ሻይቤት ስታስታውሽን ወይኔ....እረፍት ሆኖ እዚያ ለመሄድ.......በጣም እጅግ በጣም ትልቅ የልጅነት ትዝታ ቀሰቀስሽ አቦ !!!!! ወፉን በሚገባ አስታውሰዋለሁ እንጂ ....እንደውም ወፉን በጣም የሚወዱት ጋሽ ርዕሶም እና ጋሽ ከድሮ ስይድ ነበሩ::ጋሽ ከድሮ ሱቅ ሄዶ ያቺን ልብስ..?ብሎ ወፉ ከጠየቀው ያቺንው ነበር አውርዶ የሚሰጠው::ግን ከዚያች ቀን በላይ ወፉላይ የለችም::ጋሽ ርዕሶምም አንዳንዴ አመት በዓል ወይም (specialdays)ሲሆን ቂቅ አድርጎ አልብሶት እጁን ይዞ ወደከተማ ይወጣ ነበር::ወፉግን በአጠቃላይ ልብስ መልበስ አይወድም::""ያም ትመጣለህ""የሚለው የዘወትር አባባሉም አይረሳኝም:: መላጣውስ ?
ሌላው ቁምቢ ሮቢ እና ቢሆኔም ትዝ ይሉኛል::እነ ሀና ሀብቴ በረንዳ የሚያድረው አደፍርስም የኛ ሰፈር የካምቦ ልጅ ነበር::ስለ ወፉ ጨምራለሁ ባልሽው ላይ ሌላም ጨማምረሽ በትዝታ አዝናኚና አቦ !!
ወንዱ ጫካም ሌላውን ወፉ ሆኖ ነበርኮ!!!!!!
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
ቀልቤለጌ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 33
Joined: Wed Aug 31, 2005 1:08 pm
Location: UAE

Postby ወቤ(ጃሎ) » Thu Sep 08, 2005 1:06 pm

ወንድሜ ቀለቤለጌ በጣም የሚገርመው ትናንት የጻፍኩት በድንገት ነበር:ሆኖም ማታ ተኝቼ ሁሉም ነገር ፊቴ ላይ ተደቀነ:ዘሜ አሊን በታሪክ አልረሳትም ድንቅ ዳንሰኛ ነበረች:: ዛሬ ላነሳት ስል ቀደምከኝ::ሌላው,የሱማሌው የጃማ ሻይ ቤትእና ቆጪ አጠገብ ያለው ትልቅ ቤት የነበረ ሳምቡሳ ና ብስኩት ትዝ ይሉኛል::በአንድ ወቅት ገበያ ክፍል ኬላው አጠገብ ያለው ሀምሌ 19 (የግራዝማች ደመቀ) ሆቴል ነበር ባልሳሳት:የቦሬ ልጆች አልቤርጎዉን ተካራይተው (ለትምህርት መጥተው)ይኖሩ ነበር: አንድቀን እኔም ነበርኩ ከድር ከማል የተባለ ልጅ ወደጓሮ ሄዶ የተጣለች አሮጌ መኪና ስር የተኛች ትልቅ ሚዳቋ አይቶ ጠርቶን ይዘናት በማታ ከጆቫኒ መሰንጠቂያ ፊትለፊት ካለው ትልቅ ቤት ለሚኖረው አሜሪካዊ አስተማሪ ሚ/ር ባክስቸር በ14 ብር ሸጠን ያደረግነው ሰርግና ምላሽ አይረሳኝም::ሌላው የልጅነት ትዝታዬ ስለሆነ ና ያለፈ ታሪክም ስለሆነ ለምን ስለ <ሀዳ ፉሪ ቤት>አናወራም መቼም በዚያን ወቅት መዝናኛችን,መለማመጃችን ---ላኪ አቦ ----ኢጆሌ ቦሬ ነኝ ቸር ይግጠመን::
ወቤ(ጃሎ)
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Wed Jul 28, 2004 6:57 pm

Postby ፖስታቢትሰፈረ » Thu Sep 08, 2005 2:49 pm

አባ ጮማ ሰፈር ትወልደን አድገን
እነ ወንዱ ጫካን አይተን ቀንትን
ከነ ቦችራ ጋራ ካስ ተጫወትን

ምንም ቢደፈርስ ጎርፍ ቢገባበት
የሳህሉ ውሀ ልብስ ቢታብበት
ያልተጎንጨው ማን አለ ተወልዶ አድጎ ክብረመንግስት

እንደምን ከርማቹሀል የወዩ ልጆት በመጀመሪያ እራሲን ላስተዋውቅ ተወልጂ ያደጉት አዶላ ሲሆን ሰፈሪም አዲሱ ፖስታ በት ወይም የድሮው ቆጭ ሰፈር ነው

አዶላ ወዩ ማህበር በአሚሪካ ስለመመስርቱ ታውካላቹ 15-20 አባል ያለው የሚገውም በቺካጎ ሲሆን እኒም ክመስራቾቹ አንዱ ነን

ሳህሉና አብቱ ኪዳነ የሚኖሩት ቺካጎ ነው
ፖስታቢትሰፈረ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Sep 08, 2005 1:51 pm
Location: ethiopia

Postby ፖስታቢትሰፈረ » Thu Sep 08, 2005 3:03 pm

በታም ደስ የምትለን አቆጭ ጉልት
ገበያተናው ሲህድ ወደ በት
በእግራችን ተራርገን ያፈላልግናት
ለናተፋት ሂድን ጀማል ቆቆር ቢት
ደግሞ ያራዳ ልጆት ከየ ሱቅ ባንኮኒያቸውየወስዱትን
ውስደው ያትፋታል ጃማ ሳይ በት

ስለ ራስ ብሩ ትምርት ቢት ስትፉ ቂጂላ ዘበጝ ትዝ አለጝ
ፖስታቢትሰፈረ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Sep 08, 2005 1:51 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest