ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

መተር መተር አርጎ ይበላል ጉበት : ዞርበል አንፈራራ ሸዋን ልይበት!!!

Postby ራስብሩ » Thu Sep 08, 2005 7:46 pm

አያልቅበት የሚናገረው ሁሌ በግጥም ነው:ላስተዋላቸው ግርም ይላሉ ! ሰላም ወዩዎች እንዴት ከረማችሁ::ዛሬ ከደረሱ ትዝታዎች:በ አሜሪካ ቺካጎ የምትገኙ የራስ ብሩ ልጆች እንኳን ደህና መጣችሁ!ማህበራችሁ እንዲያድግ ምኞታችን ነው
በርቱ::ፖስታቤትሰፈሬ በጣም አመሰግንሀለሁ::እግረ መንገድህን የራስ ብሩን ነገር ለማህበርተኞችህ አስታውቀህ በዚሁ የዋርካ ገጽ ሥር እንድንገናኝና አንድ ነገር እንደናረግ አደራዬ የበረታ ነው::ሌላው ለአምዳችን ዕድምተኞች የትዝታ ጥያቄዎች--:የክ/መንግስት ራስብሩ ወልደገብርኤል ተማሪ የነበሩና በስፖርት ጥሩ ደረጃ የነበራቸው/ያላቸው/አሁን ያሉበት ደረጃና ሁኔታ:የምታስታውሱትን/የምታውቁትን/አጫውቱን::
ቸር ይግጠመን !
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

ስላምና ጢና ለወዩ ልጆቸ

Postby የግልነስ » Thu Sep 08, 2005 11:41 pm

እንዲት ከረማቸሁልኝኝ የወዩ አዶላ ልጆቸ እኒም ባለሁበት ደህና ነኝኝ የያንዳዳቸውን ጽሁፍና ግጥምም ባነበኩኝ ቁጥርርር በቁሚ ህልም ይዞኝ ጭልጥ ይላል ወደ ክ/መ ካገሪ ከወጣሁኝ ብቆይም 2ት ጊዚ ሂጃለሁኝ ሆኖምም ምን ጊዚም ይናፈቅቀኛል ሀገሪ ወዩ በተለይም ያቺ ከነዘገዩ ቢት ተነስታቸው(ከ01 ቀበሊ ) ተነስታ የፈረንጅ ወሀን አሻግራ የምትወስደው መንገድ ጠባብ ዳገታማ መንገድ ወደ ራስ ብሩ የምታደረስንን መንገድ ባብዛኛው በህልሚ አያታለው ይገርመኛል በጣም እናም ወደ ሚካኢል ቢተ/ክርስቲያን አካባቢ ነውው የማየውው እስቲ ቅርንፍድዩ ሊላስ ሻይቢት አታስታውሽምም ቁጢ ሻይ ቢት ገበትንን ሻይ ጠጥተን የበስለ ኮክ ስብስበንን የምነወጣበት የወሮ ውቢቱ የ10ሳንቲም ዳቦስ ቅቅቅቅቅቅ በረፍት ሳት የነበረው ግርግር የነስመኝ አለማየው ቢትማ ብድር አይወራ ቅቅቅቅቅ ሊላው ቺካጎ ላይ የተቃቃመው የክ/መ ልጆቸ ማህበር ሁላቸንንም ከያለንበት ሳያገናኝን አይቀርም የሚል ግምት አለኝኝኝ እኒምም በቅርቡ በስልክክ እያገኝሀቸው ነውው እና በጣም ደስ የሚል ነውው ሞራል ያስፈልጋቸዋልል ባይነኝኝ በተረፍ እንግዲህ እንዲሁ እስካገኛቸውው የወዩ አድባር አትለዩንን ቁጥራቸንን ከፍ ታድርግልን እላለው የናተው የወዩዋ የግል ነኝኝኝ
እምምምምጷ
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby ባለሱቅ » Fri Sep 09, 2005 5:13 am

ይህ ዝምታ በስተት ሌላ ቦታ ፖስት ያደረገው ነው.... ሁላችንም, ማንበብ ስላለብን ነው ያለደራሲው ፍቃድ እዚህ ያመጣሁት...

ፅሁፉም ደስ ብሎኛል... ብዙ ብዙ ወርቅ ልጆች አሉንሳ!.. ያገር ልጆች... ወዩ ትጠብቃቹ...

የሉፍ ጫት እጋብዛቹዋለሁ.. አውቶቡስ ተራ ከመጣቹ... 02 ቀበሌ!...

በጠሶ-ቀጠሶ ... ቢሆነኝ... ሞት-እምቢ... ወፉ(አንዴ ቦቅሶኛል) ... ብርሀኔ ፃድቃን... ሸተለኮ...(ከጃማ ቤት ጠዋት ጤዋት ዳቦ ይዞ ይሰጠኝ ነበር)... እና ስለሌሎቹም በሰፊው እንጨዋወታለን...

የበጠሶ-ቀጠሶ አካሄድ ግን አሁን ፋሽን ሆኖዋል አሉ... የምታቋት ልጆች እንግዲህ በሀሳብ ከበጠሶ-ቀጠሶ ጋር ወደማርያም ሜዳ ሂዱና ተዝናኑ...
አባ-ቡሉኮን ሚያቅ ማነው... ሜጫ ሰፈር.... ከነዲሞትፈራቸው.. ሽፍታና ኢሀፓ ገዳይ...
ቡ ቡ .. ቡ ቡ....
የሰማይ ልቡ....

እስኪ በሌላ ጊዜ ብቅ ልበል መሰለኝ... ቦታ እንዳላጣብብ

እወዳቹዋለሁ
Author Message
ዝምታ !Joined: 01 Sep 2005
Posts: 2
Location: sweden
Posted: Thu Sep 01, 2005 5:40 pm Post subject: እንዲያ እንዲያ ነው ! ወጣ ወጣ በሉ እንጂ ....

--------------------------------------------------------------------------------

መቼም ራስ ብሩ ሲጠራና ቀጥሎ ወዩን በማስከተል ንግግር ሲሞቅ እንኩዋን የተኛውን ቀርቶ የሞተውንም ሳይቀስቅስ የሚቀር አይመስለኝም ::
እንደምን ሰነበታችሁ በማለት ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ ::አዎ እኔም በዚችው ምስኪን ትምህርት ቤት ተምሬ አሁን ያለሁበት ያደረሰቺኝ የራስ ብሩ ው /ገብራኤል ት /ቤትናት ::ሰለሆነም እኔም ለዚች ት /ቤት ባለእዳ ነኝና ከእናንተ ጋር ለመቆም ፈቃደኛ መሆኔን በዚህ አጋጣሚ ልገልጽ ይፈቀድልኝ ::
በተረፈ ራስብሩ :አዶቆርሳ :ቀልቤለጌ :ቅሩንፉድ :ባለሱቅ ና የግልነስ ሁላችሁም ስለ አዶላ ወዩ ስታነሱና ስትጫወቱ እያነበብኩኝ ለተወሰነች ሰከንድ -(ደቂቃም ሊሆን ይችላል ) ሰውነቴ ነው እንጂ እኔ መሀል አራዳ መሀል ቆሜ የማስተውል ሆኜ ነው ያገኝሁት ::ከጥንት ከጠዋቱ ከነ አያልቅበት ና ወፉ ጀምሮ ከዚያም የጋሼ ክብረትን ቅጣት እንዲሁም በጣም የማውቀውን የአባባ እልፍንህን ማሳ አካባቢ ሲነሳ ደግሞ ፍርክርክ ነው ያልኩት ::እኔ ከወጣሁኝ ትንሽ በመቆየቴም ምክንያት ሆኖም ይሆናል ::መቼም እግዜር ብሎ ወዩ እዚህም ብታሰባስበን ና ከጫወታውም ባሻገር ሌላም ቁም ነገሮችንም ለወዩና ለነዋሪው የሚጠቅም መስራት የምንችልበትን በተወያየን በነበር :: እንግዲህ ማሰባሰብ የመጀመሪያ ስራችን ይሁንና ... እንቅጥል ::እዚህም እኔ አካባቢ ፈቃደኝነታቸውን በምጠየቅ ለማሰባሰብ ሞክራለሁ ::

ደህና ቆዩ
_________________
Peace!!

Back to top ይህ ጽሁፍ መሰረዝ አለበት


ራስብሩJoined: 25 Aug 2005
Posts: 6
Location: ethiopia
Posted: Fri Sep 02, 2005 11:45 am Post subject: እንኩዋን ደህና መጣህ !

--------------------------------------------------------------------------------

በመጀመሪያ ጥሪውን ተቀብለህ በመምጣትህ እና በሰጠኸው አስተያየት ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ ::ባለህበት ስላሉት ሁሉ በማሳሰብ :እድሜያችን ወደ Retirment ከመግባቱ በፊት ለተማርንበትና ላደግንበት አሁን ትንሽ ነገር እናድርግ ::በዚሁ ከተሰባሰበን በሁዋላ ስለሁሉም እገልጽለሀለሁ ::
በሀሳቤ አራዳ መሀል ቆምኩ አልክ :የአራዳዎቹን እነ ጋሽ ተስፋዬ መርጊያን አበራ ክፈለውን እና አበበ ኦጋን በደንብ አስታውሳለሁ :በተለይ እነ ሸምሱ መሀመድ እና እንድሪስ ሀሰን (ሸምሱ አሁን በህይወት የለም እንድሪስ የት እንዳለ አላውቅም )ካሱ አለማየሁ (ለጠምባ )አሁን የኢት .ብሄራዊ አትሌቲክስ ም /አሰልጣኝ በት /ቤት የታወቁ ረብሸኞች ነበሩ ::ያኔ የራስብሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ በተላ በዛብህ እማማ አምሳለ ደሞ የጅ ስራ አስተማሪ ::በል በቸር ይግጠመን ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!!!!
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ከኤፍሬም ጎርፉ ትዝታ

Postby ባለሱቅ » Fri Sep 09, 2005 12:00 pm

ኦቶቡሲ ማሞ ካቻ
የት ትሄዳለህ ቀብረ-ጉራቻ
ምን ልታሜጣ ማር በስልቻ
ትርፉ ስንት ነው ስልቻ ብቻ

ማሞ ካቻ... እራሳቾ
ሹፌር ናቾ
በኛ በኩል... መስመራላቾ

ግን ግን ግን ግን

ቱ ሀዻራው .. ቡሽቲ ናቾ
...........................................

ቡሽቲ ግን ምን ማለት ነው?

ሰላም ሰንብቱ!
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Thank you Rasbiru

Postby አደቆርሳ » Fri Sep 09, 2005 3:49 pm

ትናንት ጽሁፍህን ካነበብኩ በኋላ የማውቃቸውን ስፖርተኞች ሳስብ አደርኩ:
እኔ ከማውቃቸው የመጀመርያዋ በዓለም ታዋቂ የክብረ መንግሥት ልጅ እስከ 2002 በ800mt.እና በ1500mt. ተደጋጋሚ የድል ባለቤት የነበረች አሁን ከአትሌቲክሱ መንደር የራቀች::
አትሌት ቁጥሬ ዱለቻ:ወንድሟ አዱላ ዱለቻ(የ ጁኒየር አስተማሪ) ያስተማራችሁ ካላችሁ ታውቁታላችሁ:
2-አትሌት ዱቤ ጅሎ በመካከለኛና ረዥም ርቀት በ አለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት የነበረ:አሁን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ መምሪያ ሀላፊ::
3-ካሱ አለማየሁ :የደቡብ ኢትዮጵያ የ10,000mt. ሻምፒዮን የነበረ:አሁን የባንኮች ስፖርት ክለብ አትሌቲክስ አሰልጣኝ:: እሱ ለደረጃ ካበቃቸው አትሌቶች መሀል=አሰፋ መዝገቡ
ሚልዮን ወልዴ
ወርቅነሽ ኪዳኔ እና የአሁንዋ የሀገራችን ዕንቁ አትሌት መሰረት ደፋር እና ሌሎችም::
ሌላው በፉትቦል አክሊሉ ተስፋዬ ቢራቱ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይጫወት የነበረ(አሁን ሀይስኩል ቲቸር):ሳሙኤል አቦምሳ ዳባ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የወጣቶች ምርጥ የነበረ(አሁን በግብርና የልማት ኤክስፐርት):ቦቸራ ገላን የመድን አጥቂ:(አሁን ካልተሳሳትኩ በቺካጎ የወዩ ልጆች ማህበር አባል)
እነ ረይሶ.....,መኮንን ታደሰ,ተሾመ ተፈራ(ጅቦ),አዳነ በቀለ,እነ ጥላሁን ከበደ/ባርባ/ ቡጡ እሸቴ,ወንዱ ጫካ,ሸምሱ እና ሰበታ አህመድ,ዮሀንስ አለማየሁ::ከአራዳ ደሞ የማነ ርዕሶም እና ተስፉ አለማየሁን አብዶ የሚችላቸው አልነበረም::ፍቃዱ አቦምሳ/አፈኔ/አብዶሼ ሀጂከድር እና እንግዳወርቅ ጸጋዬ ሐይሉ በረኞች ነበሩ..አቤት ስንቱን አልኩት በሆዴ የቀረ የለም::የረሳሁት ካለግን እስቲ አስታውሱን::
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

የግልነስ በጣም ከልቤ አመሰግናለው

Postby ፖስታቢትሰፈረ » Fri Sep 09, 2005 10:21 pm

የአዶላ ወዩ ልጆች ሀሳብ, ትዝታ, ያሳልፉብትን ሁኒታ,የሚውያዩብትን መድረክ ፔጅ ስለሰጠሽን ከልቤ አመሰግናለው.

በተለይ አዶቆርሳ, ባለሱቅ, ቀልቤለጊ የሞኬ ወንድም የምትፅፉት ከአስድሳችነት አልፎ በትዝታ ወደ ክብረመንግስት ይዞኝ ጭልጥ.

ራስ ብሩ ትምህርት ቤት ለምርዳት ያንሳቹት ሀሳብ የሜደግፍ ሴሆን በግሌ የሚቻለኝ ከማድረግ ወድዋላ አልልም. ባሜሪካና በአውሮፓ ለሚገኙ የክብረመንግስት ለጆች ስለ ራስብሩ ትምህርት ቤት ወቅታዊ ቪዲኦ ሰላለን ደፕሉኬት አርገን ለንልክላቹ እችላለው. በጣም በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነው. if you gays see that Video, you wil cry. we should have to help to fix at least Window. there is no window each class.
ፖስታቢትሰፈረ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Sep 08, 2005 1:51 pm
Location: ethiopia

Postby ቅሩንፉድ » Fri Sep 09, 2005 11:51 pm

ውድ የወዩ ልጆች እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!

አምላክ መጪውን ዓመት ለሀገራችንና ህዝቦቿ የሰላም የደስታና የብልጽግና ዘመን ያድርግላቸው::

እዚህ ምስሉ ላይ ጠቆም አድርጉ::

[url=http://www.123greetings.com/eventsnew/ejan_ny_cheers/8607-006-23-1075.swf#560#380]Image[/url]

ውድ እህታችሁ ቅሩንፉድ!
ቅሩንፉድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 346
Joined: Fri Apr 15, 2005 9:07 pm
Location: germany

ባለሱቅ

Postby ፖስታቢትሰፈረ » Sat Sep 10, 2005 12:30 am

በመጀመሪያ እንካን ለመገናኘት አበቃን
በመጀምሪያ የጠቀስከው ስም የውንድሜን ሲሆን የመጨረቫ እኔው ንኝ. I just found your email adress from Hara white page and i wrote to you,but it wasn't delivered to you.i will write by your privet email. thank you
ፖስታቢትሰፈረ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Sep 08, 2005 1:51 pm
Location: ethiopia

አሚንንንንንን የኒ ቆንጆ

Postby የግልነስ » Sat Sep 10, 2005 6:00 am

ላንቺምምም መልካም አዲስ አመትት ይሁንልሽሽ ቅርንፍድዩ በጣም ከልቢ አመስግናለውውው ያውው የሻምፓኙን ጽዋ የወዩ ልጆቸ ተስባስበንን ቸርስስ እንበልላት ላዲስ አመትትትትት መልካም አዲስ አመትት ይሁንልንንን ለሁላቸንምምም መጪው ጊዚ የስላም የፍቅርር ያዲስ ህይወት ግንባታ እናም የወዩ ልጆቸ በራስብሩ አስባሳቢነት የተዘጋጀውንን እቅዳቸንን ያሳካልንን ዘንድድ በዳላ ወዩ ስምም ጸልያለውው አያለየንንን አሚንንንንንንንንን
የናተውውው የወዩዋ የግልልል ነኝኝኝ
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

ፖስታቤትሰፈር

Postby ባለሱቅ » Sat Sep 10, 2005 9:03 am

ወንድሜ ያገሬ ልጅ...
አመሰግናለሁ እንዳወከኝ ሁሉ አውቄሀለሁ...
የሀረር ሆምፔጅ ውስጥ ያለው ኢ-ሜል አድራሻዬ ተለውጧል... ሌላ አድራሻ ነው ያለኝ....
እስኪ ልክልሀለሁ...
ለተወዳጁ ወንድምህ ሰላምታዬን አቅርብልኝ..

ስልክ ደውላለሁ እያልኩ ስላልተመቸኝ ነው በለው.. መቸም አያምንም እሱ እንደሆነ....
ባለፈው ከዲሲ ተደዋውለን አናግሬዋለሁ....
የሉፍ ጫት እየቃመ እንደነበር አጫውቶኛል...

የምወዳቸው እናትህ እና እህትህ እንዴት ናቸው...

እስኪ በሰፊው እንጨዋወታለን....
መጥቼ አያቹዋለሁ...

ኢንሻላህ!!!

መልካም አዲስ አመት እመኝላቹዋለሁ

ቻዎ!!!
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ትንሽዬ ትዝታ

Postby ባለሱቅ » Sat Sep 10, 2005 9:18 am

አደቆርሳ... የሰው ስም ዝርዝር ደርድረህ በትዝታ አንበሸበሽከኝ እኮ....

የፍቃዱ አቦምሳ ኩርኩም ያልቀመሰ... የኔ ባች የ02 ቀበሌ ልጅ ይኖር ይሆንንንንንንንንንንን....

አንዴ ምን አደረገኝ መሰላቹ... 7ኛ ክፍል ሳለሁ.... እዛች ነጯ በድንጋይ የተሰራችው ክፍል ውስጥ ነበር የተማርኩት... እነ ፍቃዱ አቦምሳ ደሞ 8ኛ ክፍል ነበሩ መሰለኝ... በእንጨት የተሰሩ ክፍሎች ትዝ ይሉኛል.....
ከነጀማል ሀሰን ጋር ሲያጠኑ እላላክ ነበር.... የሀጂ ሀሰን የኪስ ክፍል አለች .. ከጎን ተለጥፋ የተሰራች.... ታቋት ይሆን????... ኤኒዌይ እየተላላኩ አብሬአቸው የተወረወረ ጫትና ገራባ እያቃምኩ ሳጠና ይመስላኛል.... ትንሽ ትንሽ ጎበዝ ነበርኩ መሰለኝ
"አንተ ነገ ልትደርስብን ነው እንዴ ብሎ የመታኝ ኩርኩም አይረሳኝም"..... ለኔ ግን ብርታት ነበር የሰጠኝ...
ሳላመሰግነው አላልፍም በዚህ አጋጣሚ....

በቡጡ እሸቴ ላይ ደሞ ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም.... በዚያን ዘመን አንድ ወንድ ከሴት ጋር ተያይዞ መሄድ ማለት ነውር ነበር... አይተን አናቅማ.... ባለጌ እያልን.... ልጅቷን ልቀቃት እያልነው ተከታትለን ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም የ02 ልጆች ጫጩቶ ብል ይሻለኛል.. ተሰባስበን ከቆጪ ገባያ አንስተን በማርያም ዳገት አድርገን... በኳስ ሜዳ ድረስ እየተከተልነው.. ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም... ልጅቱ ደሞ የሻኪሶ ልጅ ነበረች.... እሱ ደሞ የተደነቀ የተጨበጨበለት አብዶ ሰሪ... ዋውውውው...
አሁን እህት ኖሮኝ ብክሰው ደስ ይለኝ ነበር.... ግን ቆንጆ እህት የለኝም.... ቅቅቅቅቅ

ግፉ ግን በኔም ላይ ደርሶብኛል አሰላ ሳለሁ... አሁን አይነገርም... ኡስስስስስስስስስስስስስስ

ባለፈው ሄጄ ያየሁት ጊዜ ያፈርኩት እፍረት... እሱ ረስቶት ይሆናል.. እኔ ግን ሁሌ ባየሁት ወይም ባስታወስኩት ቁጥር አፍራለሁ...
አይ ልጅነትትትት....
አይ ሞኝነትትትት....

በሚቀጥለው ጊዜ ሲኖር.... አባባ ክብረት ከአሳምነው (አሳምሚት) ጋር ያስተዋወቁበትን የልጅነት ትዝታዬ አወጋችዋለሁ...
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ቅሩንፉድዮ

Postby ትትና » Sat Sep 10, 2005 9:40 am

እግዚአብሔር ያክብርልኝ ለግብዣው! ተቀብያለሁ እመጣለሁ!! እናንተ ብቻ ተሰባስባችሁ በአንድ ተጠናከሩ እኛ ወገኖቻችሁ ደሞ አለን ከጎናችሁ!!!

አክባሪህ

ቅሩንፉድ wrote:ትህትናዬ ስለአድናቆትሽ አመስግንሻለው :!: ሲዳሞ ማለት በጣም የሚናፈቅ አገር ነው::እንደው በዝና ከሆነ የምታውቂው አንድ ቀን እንጋብዝሻለን መቼም ወረድ አላልሽ ይሆናል እንጂ ላንጋኖን ወንዶገነትን የምታውቂው ይመስለኛል::በዚያው መስመር ነው ይቺ ትንሽ ከተማችን የአዋራዋ ትዝታ ከፊት አይጠፋም::ስውም በጣም ሰለሚዋደድ ነው መሰለኝ ::
በይ ቸር ይግጠመን
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Re: ለትትና

Postby ትትና » Sat Sep 10, 2005 9:43 am

ባለሱቅዮ ሙት አስጎመጀህኝ!!! የቆራስማዋን ወተት ወደ ሀረር ስለማውቃት ምራቄን ነው ያስዋጥከኝ በጾሙ :D :D !!! እመጣለሁ በጉሎ ቅጠል ተጠቅልላ የምትሸጠዋን ቅቤም አልረሳም!! አደራ እናንተ ያገር ልጆች ስትገናኙ እንዳትረሱኝ እንጂ!!!

አክባሪያችሁ

ባለሱቅ wrote:ወተት ከናፈቀሽ... በቆራስማ ቅል
እሸቱን በቆሎ በገፉማ ሙልሙል
ባዶላ ወርቅ ጌጥ ካማረሽ መሽቀርቀር
ምጭና ተደሰች ጀምጀም ለሽርሽር::

በቦሬ ነጭ ማር በጀምጀሟ ቅቤ
በገብስማ ቆሎ በእንሰት ተከብቤ
እጠብቅሻለሁ ምርጥ አቀራርቤ::

ለጁስ አሬራችን ለኬክ ዳቦ-ሸዌ
ሀሪቲ ለሽታ ጤናዳም ለደዌ
ጠጁን ለመዝናኛ ቦርዴ ለቁርሳችን
ሁሉም ይዘጋጃል ነይ ነይ አዶላችን
እንጠብቅሻለን ዘርግተን እጃችን

ታዲያ እዛች ወዩ ዛፍ ላይ የሚንጠለጠል የስሙኒ ቅቤ ገዝተሽ መምጣት እንዳትረሺ.... አድባሯ ቅቤ ትወዳለችና

ሰላም ክረሚ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

እንኳን አደረሳቹ

Postby ባለሱቅ » Sun Sep 11, 2005 12:22 pm

ለአዶላ ክብረ-መንግስት ልጆችና.. ለመላው ያገሬ ልጆችችችችች

እንኳን ለ1998 አመት አዲስ አመት በሰላም አደረሳቹ..

ይህ አመት የሰላም የፍቅር የተድላና የደስታ እንዲሆንላቹ ከልቤ እመኝላቹዋለሁ!!!!

ሱቅ መጥታቹ አትጡኝ....

ያለናንተ ማን አለኝ

ገበያዬዬዬዬ
ገንዘቤቤቤቤ

ባዲስ አመት አዲስ ብዙ ነገር ይዤ እጠብቃቹዋለሁ

ሰላም ሁኑ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

እንኳን አብሮ !!!!!!

Postby አደቆርሳ » Mon Sep 12, 2005 1:16 pm

እንኳን አብሮ አደረሰን ወገኖቼ !!!
ወንድሜ ወቤጃሎ በቀደም በጻፍከው ትዝታ እስካሁን እንስቃለን:ያቺን ዱኩላ ለሚስተር ባክስተር ለመሸጥ ሀሳቡን ያመጣው ማነው?በነገራችን ላይ ሚ/ር ባክስተርን እና ሚስቱን ሚሲዝ ባክስተርን አስታውሳቸዋለሁ:እሷ ሁሌ ጠዋት ጠዋት የት/ቤቱ ደረጃ ላይ ቁጭ ብላ ሲጋራዋን ስታጨስ እኔና አምዶም ሀብተማርያም/አምላክ ነፍሱን ይማረው/ሰልፍ ላይ ሆነን እጅግ በጣም እየገረመን እናያት ነበር(በዚያን ግዜ ሴትና ሲጋራ...)ወደጨዋታዬ ልመለስና ሚዳቆ እና ድኩላ ማደን ክ/መንድስት እንዴት እንደተጀመረ ባላስታውስም:እኔ ሳውቅ በዚያን ግዜ ጥሩ አዳኝ ከነበሩት:ሳህሉ ኪዳኔን ሲሳይ ሳንታን መስፍንሞልቶታል/አባቡታ/: አስታውሳለሁ: (ወርቃፈራሁ/ቀኬ/ እና ታፈሰ ዳዲ አሁን በህይወት የሉም)ሳህሉ ኪዳኔ የወረወረው ጦር መሬት አይወድቅም ነበር::አደን መጀመሪያ የወጣሁት ከሳህሉ ኪዳኔ ጋር ነበር:የአጥናፌን ቁልቁለት ሽቅብ ወጥተን ዳገቱን ድኩላ መፈንጫ የሚባለው ቦታ:ማዶ ደሞ እነቀልቤ ለጌ /እነ ስመኝ እልፍነህ/ ማሳ ያለ ድኩላ በሬ ነበር የሚያክለው::አንዳንዱም የተወጋበትን ጦር ይዞ ይጠፋ ነበር::ካሳዬ በርሄ ዘይት ከጋሽ በርሄ ሱቅ /ጋሽ ገብሬን/ አታሎ በ20 ሳንቲም ግማሽ ሊትር ይዞ ይመጣና ሳህሉ መቼም ሲያርድም ፈጣን ነው:እዚያው ጠባብሰን እምሽክ.............. ነበር::እኔ ያኔ በዕድሜ ከነሱ ታናሽ ስለነበርኩ ብዙም ስራ አይሰጠኝም ነበር ቢሆንም ሳህሉን ተከትዬ በየጥሻው ስፈናጠር የዋዛ አልነበርኩም::
ወቤ ጃሎ ምስጋናዬ ይድረስህ በትዝታ ከ አውሮፕላን ማረፊያ ማርያም ዳገት ስላሴን እና ሚካኤልን አገሩን ቀዬውን ያሉትን የሌሉትን ወንድሞቼን ስንቱን አስታወስከኝ አቦ::
Last edited by አደቆርሳ on Thu Apr 26, 2007 9:28 am, edited 2 times in total.
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests