ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby brookk » Mon Dec 03, 2012 4:29 pm

ዋርካ ህይወቷ ዋርካ ውበቷ - እስትንፋሷ አንዱ ይህ ቤት ነው :: ይህ ቤት ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ተሰጥዖን የምናይበት ነው :: ስሜት መኖሩ ብቻ ሳይሆን ስሜትን በትክክል መግለጽ መቻሉ ምንኛ መታደል ነው?
አደቆርሳ ስሜትህ - አመለካከትህ - ስጋትህ - ብሶትህ - ለፍቅር ሽንፈትህ ውስጥን ሰርስሮ የሚገባ ነው ::
ለሞፊቲ ጥሪ አፋጣኝ መልስህ ርካታው የሁላችን ነው :: በውነት ነው የምልህ ተስፋ ቆርጣችሁ ስትጠፉብን - ይቺን አንድየዋን መተንፈሻችንን ርቃችሁ ስትሄዱ ከውስጥ ስሜታችሁ ጉዳት ይልቅ ለራሳችን "እጦት" አድልተን በጣም አዝነንም ነበር :: የናንተን ምክንያት ከመረዳት ይልቅ የዋርካን ጉድለት ከሁሉም በላይ በጀመራችሁት ትልቅ ስራ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን "ኔጋቲቭ ኢምፓክት" አስበን ተናደንባችሁ ነበር --- ስለዚህም እኛም ከሩቅ የምንከታተላችሁ "መኖራችንም - መጥፋታችንም" የማይታወቀው አብረን ተሰደን ነበር --- አሁን መታችኋልና -- መምጣችን ባይታወቅም -- የሚጨምረው ምንም ነገር ባይኖርም --- ደስስስስስስስ ብሎን መተናል -- አቀባበሉንም ከዳር ሆነን ለማድመቅ ተሰልፈናል ---
ወቤ ጃሎ --- ወቤ ጃሎ --- ወቤ ጃሎንም የምናይበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይሰማናል ----
ምንኛ ውሀ ነው የጠጣችሁት ? --- ፍቅራችሁ ብቻ ሳይሆን -- ጽሁፋችሁኮ ልዩ ነው --- ቢያነቡት ቢያነቡት የማይጠገብ ---
አንፈራራ --- ጥሪው ላንተም ነው --- "የናት አገር ጥሪ" :lol:
ኑ --- "ምጡ" -- እናንብባችሁ -- እንማርባችሁ --- ከጎናችሁም እንድንቆም -- በአንድነት ቆማችሁ ጋብዙን --- "ቆዳችሁን" አወፍሩት --- በማንነታችሁ ላይ በውሏችሁ ላይ -- ሌሎች ተጽዕኖ እንዲያደርጉ አትፍቀዱላቸው
"አያ ሆሆ ማታ ነው ድሌ"ንም አስጨፍሩን

እኔና ብሩክ ነን
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ገልብጤ » Mon Dec 03, 2012 5:15 pm

ዋርካ ህይወቷ ዋርካ ውበቷ - እስትንፋሷ አንዱ ይህ ቤት ነው :: ይህ ቤት ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ተሰጥዖን የምናይበት ነው


ልክ ብለሀል ብሩክ እኔም ባንተ ሀሳብ እስማማለሁ..እዚህ ቤት የተጻፈ ጽሁፍ አምልጦኝ አያውቅም... እውነትም የዋርካ ውበት ይህ ቤት ነው ...እውነተኛ ፍቅር ያለው እዚህ ቤት መሆኑ ምንኛ ደስ ይላል ...
ገልብጤ በዚህ ቤት ፍቅር የቀናው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ባለሱቅ » Mon Dec 03, 2012 8:44 pm

ዎውውውውውውውውውውውውውው
ነው ያልኩት በራስብሩ ትዛዝ ይህንን ቤት እንዳይ ተጋብዤ
ሞፍቲኮ.... ምን እንደምልህ አላቅም.... እንትፍ እንትፍ ግንባርህ ላይ
እናትህ በደንብ አድርገው ሳይመርቁህ አልቀሩም
ያዘዝከው ሁሉ ይታዘዝልህ.... ሳይሉህ አይቀሩም ከምር
ያንን ሁሉ አቤቱታ... ለማየት ጊዜ አጥቶ
ያንተን የዛሬው የፍቅር ደብዳቤ አንብቦ... ወንዱ ሳይቀር... ሴቱም.....
ብቻ ተወው
እንኳን.... ብቻ አደቆርሳን ይዞልን መጣ አቦ
አደቆርሳዬዬዬ
ምን እንደምል አላውቅም
1. ከደስታዬ ብዛት
2. ከመቅናቴ ብዛት
3. ከመናደዴ ብዛት
የፍቅር ስኳሬ ተነስቶ...... ልቤ ቀጥ ብሎልህ ነበር
እርግጤና ነኝ ምን ማለቴ እንደሆነ እንዳብራራልህ እንደምትጠይቀኝ
አዎን.. የኔ ጽሁፍ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ሰዎች ግራ እንደሚያጋባ... ሳልረዳ ቀርቼ አይደለም.... እንግዲህ... ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም ይባል የለ... እንደናንተ ባልታደለውም... ባለችኝ መቦጫጨር... እስካልተከለከልኩ ድረስ
እናልህ
1. ደስታዬ.... ያንተ መምጣት እና የፍቅርህ ኃያልነት..... በዚህ የተነሳ የማነበው ... የነብሩክ.. ጥኡም ....ሀይለቃል.... የነገልብጤ መልካም ቃላት... የኔ የልቤ ፌሽታ
2. ቅናቴ... ምነው እንደ-አደቆርሳ በተወደድኩ.. የሚል... እውነተኛ መንፈሳዊ ቅናት......... ነው
ቆይ ምን ብታቀምሳችው ነው ሰው ሁሉ.... አደቆርሳ.. ሀደ-ቆርሳ የመዳኒት እናት እያለ ሚያሞካሽህ እና... አንተን ለመስማት እንዲህ የሚሆነው እያልኩ በቅናት ቅጥልልልልልልልልልልል...
3. ንዴቴ.... አንድም ሰው ባለሱቅ ጠፋ ብሎ ሲፈልገኝ ባለማየቴ...... ያው ከቅናቴ ጋር የተያያዘ ነው.............. ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ውይ ሞት ይርሳኝ.. ለካስ ጎሳ ወንድሜ ስጠፋበት እሱ ይፈልገኝ ነበር
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ኤኒዌይ.... ቀልዱን በቀልድነት ስቀንበታደቆርሳን በማየቴ
ሞፍቲሻን አምላክ ያሰብከውን ሁሉ ያሳካልህ እላለሁ... አደቆርሳን ስላመጣህልን

እስኪ ይህንን አይተው... ራስብሩም.. አንፈራራም.. ሽልንጌም... ውቤ-ጃሎም... ያ-የኩባው ልጅም ይመጣሉ ብለን እናስባለን
እንጠብቃለን
ቅሩንፉድና መናኸሪያ ግን ምን ነካቸው
የቦሬዋ እና አይፊቲስ
የግል እንኳን ብር እየቆጠረች ስለሆነ... አይፈረድባትም

ይኅንን አንድነትና ፍቅር እስከመጨረሻው ያዝልቀው... አላህ
አሚን
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby እንሰት » Mon Dec 03, 2012 9:10 pm

ባለሱቅ wrote:2. ቅናቴ... ምነው እንደ-አደቆርሳ በተወደድኩ.. የሚል... እውነተኛ መንፈሳዊ ቅናት......... ነው
ቆይ ምን ብታቀምሳችው ነው ሰው ሁሉ.... አደቆርሳ.. ሀደ-ቆርሳ የመዳኒት እናት እያለ ሚያሞካሽህ እና... አንተን ለመስማት እንዲህ የሚሆነው እያልኩ በቅናት ቅጥልልልልልልልልልልል...
3. ንዴቴ.... አንድም ሰው ባለሱቅ ጠፋ ብሎ ሲፈልገኝ ባለማየቴ...... ያው ከቅናቴ ጋር የተያያዘ ነው.............. ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ይኅንን አንድነትና ፍቅር እስከመጨረሻው ያዝልቀው... አላህ
አሚን


ባለሱቅ እንዲህማ አይባልም! መጀመሪያ ስትጠፋ ለምን እንድምትጠፋ ትናገራለህ ሰው አይጨቀጭቅህም እንጂ አድፋጭ አንባቢዎችማ ናፋቂዎችማ አለን::

ሞፊቲ በፊት ለፊትም በጉዋሮም ሲያወራ እንዲህ ነው:: አጣጣል ያውቅበታል አይደል እሁድ እሁድ የሚያስቀድስበት ገብሬል ፈጣን መልክተኛ ነው ማለት ነው:: በቃ የኛም እንዲሰማ ወደ ሞፊቲ ገብሬል እንዞራለን::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ሞፊቲ » Mon Dec 03, 2012 9:54 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ንዴቴ .... አንድም ሰው ባለሱቅ ጠፋ ብሎ ሲፈልገኝ ባለማየቴ ...... ያው ከቅናቴ ጋር የተያያዘ ነው .............. ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ


ቆይ አንተ ደግሞ መች ጠፋህና ነው የምትፈለገው? በስራ አሳበህ ዞር ስትልም እኮ ነግረኧን ነው::ያም ቢሆን የምትሄድበት
ሀገር ከታንክ በስተቀር ምንም ስለማይገባበት ፍለጋችን ከንቱ ይሆንብንና እንተወዋለን እንጂ መች ቦዝነን እናውቃለን::
ወዳጅህ ጎሳ ሰሞኑን ጥፍት ያለበትን ምክንያት እያጣራሁ ነበር:: በጓሮ በኩል ሳይቸግረን አደፋፍረነው መጽሀፉን
ለማስጠረዝ ሲንገላወድ በዋጋ ያለመስማማት የ እጅ ቦርሳውን ተሸክሞ በየማተምያ ቤቱ እየዞረ እንደሆን ሰምቻለሁ::ምንጭ;-አይፋ ናት::


ሞፊቲ በፊት ለፊትም በጉዋሮም ሲያወራ እንዲህ ነው :: አጣጣል ያውቅበታል አይደል እሁድ እሁድ የሚያስቀድስበት ገብሬል ፈጣን መልክተኛ ነው ማለት ነው :: በቃ የኛም እንዲሰማ ወደ ሞፊቲ ገብሬል እንዞራለን ::


ወዳጄ እንሰት በሳቅ ገደልከኝ እኮ? በጓሮ የማወራው ደግሞ ምን ይሆን? ቆይ ብቻ ምን ለማለት እንደፈለክ
ገብቶኛል::ለማንኛውም እንዳልከው የኔን ገብርኤል ጠበቅ አርገህ ያዝልኝ::

ውድ ብሩክ= አቤት አገላለጽህ? ዋው ውስጥህን ነው ያየሁት::አይዞን የቤቱን ሞጎሶች ካሁን ወዲህ
በቁጥጥራችን ፍቅር ውስጥ እንከታቸዋለን::

ገልብጤ ወንድሜ እንዴት አለህልኝ? የናፈከውን የዋርካን ውበት አሁን ታገኘዋለህ::

ቸር እንሰንብት!!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Dec 03, 2012 10:42 pm

ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ልጆች:-

ሰላም ወንድማችን አደቆርሳ:-

ይህንን የጥላሁን ገሠሠን ዜማ የመረጥኩላችሁ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ ስለሞላና ስለተትረፈረፈ ሣይሆን የፍቅርን ኃያልነት ለመዘከር ነው::

ጥላሁን ገሠሠ : ምግብማ ሞልቷል::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby አደቆርሳ » Tue Dec 04, 2012 12:14 am

አክባሪዎቻችን ክበሩ !
ይገርማል በፊት የነበሩን ወዳጆች አሁንም እንዳሉ ማየት መታደል ነው !
brookk ወትሮም የቤታችን ወዳጅ ነህ አሁንም እንወድሀለን አትጥፋብን ::
ገልብጤ ባለፈው አንድ ጥያቄ በሲዳምኛ ይሁን ብቻ አላስታውስም አቅርበህ ራስብሩና ሞፊቲ ሲሞክሩ አይቼ እኔም ትንሽ ለማለት ዳድቶኝ እንደነበር ትዝ ይለኛል
አሁን ገጹን መገላለጥ አልችልም መጻፍና መስደድ ብቻ ነው ::
እንሰት አኔኪራ ሠላሜቴ ? ሂእቶቲ ?
ሁላችሁም ሰላማችሁ ይብዛ ስለ አስተያየታችሁ ስለ ምስጋናችሁ ጎንበስ ብያለሁ !
እንደው ስለምትወዱን እንጂ የዚህ ሁሉ ችሎታ ባለቤትማ አይደለንም : በፍቅር ከልብ አመሰግናችኍለሁ::
እንደምን አላችሁ የራስብሩ ቤቶች ባለፉት ጊዜያት ብቻዬን ያነበብኳቸውና ሳይቀየሙኝ ያኮረፍኳቸውን ጽሁፎች የማስታውሳቸውን ለመነካካት እረፍት ላገኝ አልቻልኩምና አቅሜ እንደፈቀደ ልዳስሳቸው ወደድኩ ::
ከመንፈቅ በፊት ይሆናል የምወደው ባለሱቅ በሞዛምቢክ ካሜራዬና በኪሴ የነበረው ዶላር ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ..... የሚል ዜና አስነብቦ በጣም አስቆኝ ነበር ምክንያቱም በሞት የተለየው ካሜራው ነው እንጂ ዶላሩማ ከሞት ተነሳ እንጂ በሞት አልተለየውም ነበር ::
እናንተ ሰዎች ዶላራችሁን ወደዚህች ምድር ስታመጧት ካላት ጉልበት በላይ እጥፍ እንደምትሆንና አንዷ አስር እንድምትረታ ትረሳላችሁ ልበል ?
ገና መልኳ ሲታይ ከውብ ኮረዳ ይልቅ በፍቅር እንደምታቀልጥና በደስታ ሳቅ ፍንድቅድቅ እንደምታደርግ ትዘነጋላችሁ ልበል ?
እርግጥ ካሜራዋ የዛን ቀን በሞት ተለይታለች ይህ ትክክል ነው ሞዛምቢክ መሰረቋን ብታውቅ ቀድማ ራሷን ሳታጠፋ ትቀራለች ብላችሁ ነው ? ነፍሷን ይማረው::

በዚያንው ሰሞን አንድ እንግዳ ጀምጀም የሚባል ብቅ ብሎ ነበር ብዙም አልበረከተም ሆኖም የጨዋታ አያያዙና አስታዋሽነቱ ቀልብ ገዢ ነው ::
ኔንቆ ስለሚባል ልጅ እና ስለ ዶክተር ሽፈራው ነጋሽም የክፍል ትዝታ አውግቶናል ኔንቆን አላውቀውም ሺፈራውን ግን አውቀዋለሁ : ከሁለቱም ጋር በዘመን ልዩነት ምክንያት አብረን አልተማርንም ::
በአስተያየቱ መደምደሚያ የተናገራት ነገር ፈተና ወደክ አለፍክ ሳይሆን ቀድሞ በተጻፈልህ ነው አይነት የምትል ነበረች እርግጥ ነው ቀድሞ በተጻፈልህ ነው::
ኑሮ የዕድል ብቻ እንደሆነች ያወቅኩት በኢሀዴግ ዘመን ነው አንድም በፖለቲካ አንድም እንዳልከው በእድል እኔም አሁን በጣም ዘግይቼ ነው እንጂ ድሮ አውቄ ቢሆን ኖሮ የማገኛትን አንድ ብር ሁለት ማድረግ ብቻ አጠና ነበር::
አንተ ስላነሳኸው የጎበዝ ተማሪዎች ነገር ያነበብኩ ቀን ትዝ ያለኝን ላጫውታችሁ ::
በዚያ በእርጉም ዘመን በአንድ ወቅት መምህር ሆኜ በጣም ጥቂት ጊዜ አገልግያለሁ የቅጥር መምህር ሳይሆን የሰርቪስ /አገልግሎት/ መምህር እና በክፍሉ ውስጥ ሸዋፈራሁ የሚባል ተማሪ በጣም ቀጭን እና ስስ የሆነ ልጅ ነበር :
ምናልባትም የሚማርበትን ክፍል የማስተማር እድሉን ቢያገኝ በሚገባ ማስተማር የሚችል ብቃት ነበረው::
በተዘጋጀው የሌሰን ፕላን መሰረት የሚሰጡ ትምህርቶችን በሚገባ ያውቃል ፈተና ላይ ስህተት አያመጣም ነገር ግን አንድ የሚገርመኝ ፕሮብሌም የምለው ችግር ነበረበት ከትምህርት ውጪ ምንም ነገር አያውቅም::
ስለ ምንም ነገር አያነብም ጋዜጣም እንኵን አያነብም ራዲዮም አያዳምጥም ከደብተሩና ከመጽሀፉ ውጪ ምንም አያውቅም ከዚህ የተነሳ መምህሮቹ የነበሩትም ስለሱ ብዙ መነጋገራቸውን አስታውሳለሁ::
በኍላ ልጁ ወደአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ሳይወጣ መቅረቱን ሰማሁና አዘንኩ ::
ልጁን የሚገራው ቤተሰብ ወይንም የትምህርት ቤቱ አካል ባለመኖሩ እሱ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱም ትልቅ ጥቅም እንደምታጣ አስባለሁ ዳሩ አስቤ አስቤ ደከመኝና ተውኩት አለ እንደተባለው ከመሆን ማለፍ አይቻልም::
የሚገርመው አንዲትም ፈተና አምልጣው አታውቅም ስህተትም አምጥቶ አያውቅም ይሄንንን እና እንደዚህ ያሉ ልዩ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች የመንከባከብ ጅማሮ በናይጄሪያ ደቡብ አፍሪካና ጋና አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ልዩ ድጋፍና ይዞታ ማድረግ አንድ ድርጅት እንዳለ አንብቤ ይሁን ሰምቼያለሁ ::
ገነባን ገነባን ይህንን ያህል ወጪ አወጣን ከሚል የኪስ ፖለቲካ ይልቅ ለእንዲህ ያለው ሁኔታ ጥቂት ድጋፍ ቢያደርጉ ሀገርን የመገንባት ቅድሚያ ፕሪዮሪቲ ፐርፎርማንስ ማዳበር ይቻላል::
ሀገርን መገንባት ማለት ወጣትን ማስተማር ማለት ነው !
የሚገርማችሁ ይሄ ሁኔታ እነመለስም እነ መንግሥቱም ድሮ ድሮ ከተቀበሉት የርዕዮተዓለም መርህ ውስጥ ያለ ነገር ነው::
መንግሥቱ በዚያ ሥርዓት ውስጥ የካድሬና የገበሬ ትምህርት ቤቶችን በከፍተኛ ወጪ አደራጅቶ ኢትዮጵያን የሚያደሙ ካድረዎቹን ማስተማር እንጂ ሌሎች አካዳሚክና ቴክኒክ ትምህርት ቤቶች ባይኖሩም ደስታው ነበር ::
መለስ ደሞ ከትምህርት ቤት ሲወጡ ካልፈረሙ መማር ዋጋ የለውም ብሎ እንደሀገር ልማት ሳይሆን እንደፓርቲ ልማት ነው የሚመለከተው ::
በትምህርት ቤት ውስጥ ልዩ ልዩ ችሎታ ያላቸውና አካዳሚክ ብቃታቸው ከፍተኛ የሆኑ ስፔሻል ልጆች የሀገር ሀብት መሆናቸው አሁንም ድረስ ምንም ትኩረት ያጣ ጉዳይ መሆኑ ያሳዝነኛል::
የአንድ ዜጋ ሙሉ መብት ትምህርት ነው !
ይህ ደሞ በእኛ ሀገር አይሰራም !
እኔ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ ጀምሮ አሁን እስካለሁበት እድሜዬ ድረስ አንድም ቀን እንደኢትዮጵያዊነቴ በሃገሬ ላይ ሰርቼ ተደስቼ አስቤ ኖሬ ተምሬ አስተምሬ ሄጄ መጥቼ ………..አላውቅም::
ህዝባችን እስከመቼ የመሪዎቹ ሰልፈኛ ሆኖ እንደሚኖርም አላውቅም:: ?
እስከመቼ እሳቸው ይቅደሙ እያልን እንኖራለን ?
ያኔም ታላቁ መሪያችን ይቅደሙ ይባላል አሁንም ጀግናውና ባለራዕዩ ይባላል ህዝብ የሚቀድመው መቼ ነው ? አንድ ሰው ከሀገር እንዴት ይቀድማል ??
አሁንኮ የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ብታዩ የመለስን ጀግነትና የኑሮን ውድነት ብቻ ነው የሚወራው ሌላ ፖለቲካ ጠፍቷል ወይንም ቀርቷል ::

ምናልባት በቅርቡ <<መለስ ከመቃብር ይነሳልን>> ብላችሁ ሠልፍ ውጡ ሳንባል እንቀራለን ብላችሁ ነው ? አትሳቁ ይሄ ይደርስብን ይሆናል ::
እንዲህም ሆኖ አቶ መለስ ጥሩ ነገር አላደረጉም ለማለትም አልችልም በተለይ ካለፈው ጉዳይ ወዲህ ሳሳ ያለ የአመለካከት ለውጥ እያሳዩ መምጣታቸው አሌ አይባልም የሆነው ሆኖ ክፋታቸው ይበዛል::
አዬዬ የኔ ነገር ከየት ተነስቼ ወደየት.... . የሆነው ሆኖ ሁሉም አብሬያችሁ ልተነፍስ ያሰብኩት የነበረ ስለነበረ ከሆዴ ወጥቶ እስኪያልቅ አልያም እስኪደክመኝ አወራችኍለሁ ::
መተንፈሻችን ብሎ የለ ብሩክ እንደዛ ነው ..........................
In the blind Country One eyed man is king እንደሚባለው አቶ መለስ በተፈጥሮ ባላቸው ብልጥነት ከቀሪዎቹ ተሽለው መገኘታቸው ወንበሩን የግላቸው በማድረግ ጥሩ ዲክታተር ሲሆኑ እንጂ የችሎታቸው ብቻ ሰው ቢሆኑማ ሀገሪቱን የጋራ አድርገው እናይ ነበር ነገር ግን ይህንን አላየንም : አዎን ጎበዝ ናቸው ነገር ግን ዲክታተር ናቸው :: አዎን ጥሩ የፖለቲካ ችሎታ አላቸው ነገር ግን ዲክታተር ናቸው :
በዛሬ ጊዜ የሀገርን መሪ ዲክታተር ነው ማለት ያስቃል ያለው የትኛው መሪ ነበር ረሳሁት ስሰማው ግን አስቆኝ ነበር
በድህነት እየሞትን እኮ ነው እኛም የሳቸውን ትንሳኤ የምንዘምረው ታዲያ ይሄ አያስቅም ?
ኢትዮጵያ በትምህርት ፕሮግራም ከፍተኛ እድገት አስመዘገበች ኢትዮጵያ በኤኮኖሚ ከፍተኛ እድገት አስመዘገበች አዎን በጣም ነው ያደግነው አይ ኤም ኤፍ አልያም የአለም ባንክ ወዘተ አድጋችኍል ይሉናል ነገር ግን ማነው የዚህ የድህነት እድገት ተጠያቂ ?
ማነው እንደዚህ አድርጎ በድህነት ያሳደገን እኔ እሱን ነው ማወቅ የምፈልገው ?
እስከመቼስ ነው እንዲህ ያለ እድገት የምናድገው ?
ዘመናችንን በሙሉ ቁልቁል ?
በልጅነታችን በአደባባይ ስንወገር; በዱር በገደል ያለ ፍላጎታችን ያለ እድሜያችን የጥይት ራት ሆነናል ; በሃገራችን ባይተዋር ሆነን ኖረናል ; የዘርና የጎሳ ቋንቋ ተወስኖልን እውቀታችን እንዳያድግ ተደርገናል ; የአንድ ጎሳና ዘር ተገዢ ሆነናል ; ለዴሞክራሲ ጮሃችሁ ተብለን ዳግም ሞተናል ; ተግዘን የጊንጥና የዘንዶ መቀለጃ ሆነናል ; ታዲያ እክሰመቼ ድረስ እንሙት ? ይሄ ነው ማደግ ጎበዝ በቃ ! ማደግ ይቅርብን !
በቃ !! በቃ ! በቃ !
አሁን አንድ ሌላ እድገት እንደግ እነ አይ ኤም ኤፍ እና ኢቲቪ እንደሚሉት ያልሆነ ሌላ እድገት ::
ይሄኛው እድገት ይብቃ !
ስንት የተማሩና አድገው ሰማይ ለደረሱ ሃገሮችን ፖለቲካ የሚቀምሩ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አሉ በእነሱ ሃሳብና ምክር እንዲሁም በዓለማቀፍ ጫና እና በብልህ ፖለቲካ ለውጥ የሚያመጣ ድርጅት መፈጠር አልያም በዚህ መልክ መዋቀር ያለበት ይመስለኛል::
እንጂ ከአሁን በኍላ የኢትዮጵያን ህዝብ ተነስ ሙት የሚል ጭፍን ፖለቲካ ከእንግዲህ መኖር የለበትም
ትንሽ ጥሩ ጭላንጭል ያለ የሚመስለኝ አንድ ነገር ግን
ባለፈው የቀድሞዋ የቅንጅት ታጋይ ብርቱካ ሚደቅሳ እና አቶ ሥዬ አብርሃ በተናገሩት ድንቅ ንግግር
አንጀቴ ርሷል እንደዚህ ዓይነት ሰው ነው ኢትዮጵያ ከአሁን በኋላ የሚያስፈልጋት ሞትን እና የሞትን ድግስ የሚጠራ ተቃዋሚ ህዝባችን አያሻውም:
እኛስ እስከመቼ እንሙት ? እስከመቼስ እንሰደድ ? እስከመቼ እንራብ ? እስከመቼስ እንሰቃይ ?
በአመጽና በግድያ ሃገራችን መንግስታት መለዋወጥ ከጀመረ ስንት ዓመታት ተቆጠሩ ? የተቀየሩትስ መንግስታት ምን አደረጉ ? ለዚህ ህዝብስ ምን ጠብ አለለት ?
ህዝብ በኑሮ ውድነት ምክንያት በማይረባ የፖለቲካ አስተዳደር በጉቦ በሌባ ኃላፊዎች ከመቼውም በላይ ተማሯል በዚህ ላይ በየቀኑ ከሃገር የሚሰደደው የበረሃ አሸዋና የባህር ከርስ የሚበላውን አበሻ ቤቱ ይቁጠረው ::
ለኢትዮጵያ ህልውና ሲል ለድሃውና ለሚወደው ህዝቡ ሲል ራሱን ዝቅ አድርጎ ወገኑን ከወደቀበት የሚያነሳ ድርጅት ያስፈልገናል::
ያኔ ሪቮሉሽኑ ለውጡን ይወልደዋል !!!!
እኔም አቶ መለስ እንኳን ሞተ ብዬ አልመጻደቅም ምክንያቱም ይሄ የግዚአብሄር ሥራ ነውና ነገር ግን በምንም ይሁን በምን ያቺን ወንበር እንዲለቅ የለት ተዕለት ምኞቴ ነበር ተሳክቶልኛል::

ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby ኦዶ ሻኪሶ » Tue Dec 04, 2012 5:09 pm

አይ ሞፊቲኮ ትልቅ ሰው
በጊያ ነጋን ዱፍታ አደቆርሳኮ
ጽሁፍህ ደስ ብሎኝ አንብቤው መጨረሻ ላይ እኔም ተሳክቶልኛል አልኩ ::
ግን ምን ተሳካልኝ ብዬ ራሴን ጠየቅኩና ከሰውዬው ሞት በስተቀር ምንም አዲስ ነገር የለም::
የሆነ ነገርህ ግን ደስ ብሎኛል አጻጻፍህ ልክ እንደብሩክ አባባል ውስጥን ሰርስሮ የሚገባ ነው::
ስሜትህን በግልጽ መጻፍ ያስተማራችሁኝ አንተና ባለሱቅ ናቹህ ንል ስተት አይደለም ስለዚ ደግሜ ደጋግሜ አመሰግናቹሀለሁ::
የባለሱቅ ዶላርና ካሜራ እሱ ከጻፈው ይልቅ ያንተ ነው በሳቅ የገደለኝ::
እኔም በቅርቡ አንድ አሪፍ ካሜራ አዲሳበባ ላይ ተበልቻለሁ ይቅርታ ካሜራየ ራሷን በራሷ አጥፍታለች::
እስቲ ሞፊቲኮ በጓሮ በኩል ስቦ እንዳመጣህ የአዶላን የኦዶን የራስብሩን የቦሬን ታሪኮች በጓር አምጣቸው::
ባለፈው ግዜ አንትዬ ከበደን ያረካትን ነገር እነ ፍሰሀ መላኩና ጸጋዬ ግዛውም ሳያውቁት አይቀሩም ::
ሌላ ተመሳሳይ ነገር ስለሰማሁ መጀመሪያ ካንተ እንድሰማ ዝም ያልኩት::
በመጨረሻ
ለኢትዮጵያ ህልውና ሲል ለድሃውና ለሚወደው ህዝቡ ሲል ራሱን ዝቅ አድርጎ ወገኑን ከወደቀበት የሚያነሳ ድርጅት ያስፈልገናል ::
ያኔ ሪቮሉሽኑ ለውጡን ይወልደዋል !!!!

ይቺን አባባል እንደገና ብታብራራልኝ ? አመሰግናለሁ::
May God bless Adolla
ኦዶ ሻኪሶ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Fri Sep 22, 2006 12:24 pm
Location: adolla lagadembi

Postby Gosa » Wed Dec 05, 2012 3:42 pm

ይህ ቤት ቀዝቀዝ ብሎ ስለነበር አንዳንዴ ዋርካ ገብቼ ፍቅርን ፍለጋ ዋርካ ፍቅር ውስጥ ስዳክር አመሽና "ማንም አይጽፍም " እያልኩ እዚህ ጎራ ሳልል እወጣለሁ :: እንዳጋጣሚ ዛሬ እዚህ ጎራ ስል ባመት አንዴ ብቅ የምለው ብሩኬ እንኳ ስለ አደቆርሳ መምጣት ሰምቶ የተሰማውን ተንፍሷል :: ከየት እንደሚያመጣቸው የማይታወቁ አስቂኝ እና አሳዛኝ አጫጭር የፍቅር መጣጥፎችን ዋርካ ፍቅር ውስጥ እየለጣጠፋቸው ሲጫወትብኝ የነበረው ገልብጤም ዱቅ ብሎ ከህዝቡ ጋር ተቀላቅሎ በቦታው ያልተገኘሁ እኔ ብቻ መሆኔን ስረዳ ማንንም ሰው በጓሮ በኩል የመጥራት ሱስ የተጠናወተው ሞፊቲ እንኳ ባቅሙ እንዴት ጓሮዬን ንቆ ሳይጠራኝ እንዳለፈ ልገባኝ አልቻለም :: ይህ የአይፊቲ ሴራ ነው ብዬ ነው የደመደምኩት :: ገና ለገና ጆንያ ሙሉ ሉክ ተሸክሜ በየማተሚያ ቤቱ ስዞር አይታኝ ኖሮ ብር መስሏት በቅናት አብዳ ድሮም የሳንቲም ነገር የማይሆንለት ወንድሜ ሞፊቲን አነሳሳችብኝ ::
ዛሬ ቤቱ እንደዚህ ሞቆ ሳይ ማንንም አይደለም ...ባለሱቅን ነው ያስታወስኩት :: እኔም አገር ቤት ሄጄ ጠፍቼበት ቤቱ ባዶ ሆኖ ብቻውን ተስፋ ሳይቆርጥ ይጽፍ ነበር :: አንድ "በርታ እያነበብንህ " ነው የምለው ሰው ሳይኖር ማለቴ ነው ::
የትልቁ ጸሀፊ የአደቆርሳ መመለስን ከምን ጋር ላነጻጽረው ይሆን ...መቼም ያገባሁበት የሰርጌ ቀን አልልም ብቻ ያኔ ማንዴት ያገኘሁ ቀን የተሰማኝ ደስታ አይነት ነበር ድራሼን ያጠፋው :: ስራ ቦታ ሆኖ ነው እንጂ ፌይንት ሁሉ በላ ነበር :: እንኳን መጣህልን የቤታችን ምሶሶ ሞተር :: አድናቂህ መሆኔን ድሮም ነግሬህ ስለነበር መደጋገሙ አያስፈልግም :: ዛሬ እዚሁ ላይ ላቁምና ትልቁን ኮካ ከፍቼ ሰለብሬት ላድርግ ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ሞፊቲ » Wed Dec 05, 2012 8:59 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ጎሳ ጎሳ! ውይ ውይ ውይ...ምነው? ምነው? የሆነ ቦታ አንድ ወሬ ሰምቼ ነው እየሮጥኩ ወደዚህ የመጣሁት::
የቡድሂዝት ሀይማኖት ለመቀበል ዝግጅት ላይ ነህ አሉ:;እንደውም ወዳጅህ ደጉ ወደፊት ከዚህ አለም ስትለይ ቢራቢሮ ሆነህ እንድትመጣ እየጸለየልህ መሆኑንም ሰማሁ::
ምነው ምነው ልጄ? ኧረ ባክህ አደብ ግዛ? እኔማ በዚሁ የምለቅህ አይደለሁምና አዮ ጋ ደውዬ ኢያ ደበርሲ አደርጋለሁ::
አይፋ አንቺስ ምን ትያለሽ? ጓደኛሽን አንድ በይው እንጂ? ባይሆን አንቺን እንደሚሰማ ስለማውቅ ትንሽ ጎነጥ አርጊልኝ::
ለመሆኑ ደጉን ታውቀው ይሆን? ባይገርምህ ሱኬም
ጎሳም እያለህ.....አብሮህ ነበር::
እንዴት ብለህ አትጠይቀኝ? ደጉ ካልፈቀደ በስተቀር አልነግርህም::

አደቆርሳ=የሀገርህን ብሶት ዘመን ሙሉ ያመከውን እዚህ መተህ ስትዘረግፈው ትንሽ ቀለል እንዳለህ ይሰማኛል::
አይዞን...ብለን ብለን ብለን እያልን ያለነው ነገር ስለሆን መቼስ ማልጎዳኒ..ብሎ ማልፉን መርጬአለሁ::

ተድልሽ ምግብ እየበላሁ ሳለ የመረጥክልንን የጥሌን ዜማ አድምጬልሀለው::
ያው የተለመደው ምስጋናየ ይድረስህ::

ቸር እንሰንብት!!!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby አደቆርሳ » Thu Dec 06, 2012 12:03 am

ውድ ኦዶ እንደምን ሰንብተሀል ስምህን ሳይ ገና ያቺ የትምህርት ቤቱ ጊቢ ውስጥ ያለችው ስታዲየም
ትዝ አለቺኝ ለነገሩ እኔ ወርቅ ለመቆፈርና የቡሴቶ ሽታ እየናፈቀኝ እንጂ ሻኪሶ ኳስ ለማየት የምመጣው በጋሽ
ከድሮ አልያም በጋሽ ዓሊ ትሬንታ ደጋፊ ተብለን ተጭነን ነው::
ያኔ ደሞ አንተ ግብ ካገባህ እንደሆን ማታ በድንጋይ እሩምታ አናሳልፍህም ነበር ::
ጽሁፍህን አነበብኳት ጥያቄህንም አየሁት የቸርነት ዛፍ ላይ መውጣት ካቆምክ ወዲህ ነገር ጠፍቶብሀል መሰለኝ እንጂ
እኔም ራሴን ሳልጠይቅ መልሱን ከየት አመጣዋለሁ ብለህ ነው አንዳንዴ አሪፍ ህልም አይቻለሁ ብለህ ህልም ፈቺ ስትፈልግ ትውልና ያልሆነ ወይንም የማይመስል ፍቺ ነግረውህ ተመልሰህ አታውቅም ? እንደዛ ነው እንጂ ነገሩማ እንዳልከው እጅግም ለውጥ አላመጣም::
ለዛኮ ነበር ፓርቲዎች ሁሉ አስጠሉኝ እንደማለት የፈለኩት::
ዋናው ነገር ዛሬ ሌላ ቀን ነው ! ሞፊቲኮ አንተ መቼም የልብ አውቃ ነህ ብለን ብለን የደከመን ያልከው ትክክል ነህ እዚህም እኮ አልቋል ብቻ የልቤ የመተንፈሻ ቀዳዳ ያለችው እናንተ ጋ ስለሆነ ነውውውው::
የአንትዬ ከበደን ታሪክ ያነሳኸው ለነገር እንደሆነ ገብቶኛል ምናልባት ወቤ(ጃሎ) ያኔ ከነአንትዬ ቤት የ10 ሜትር ርቀት ላይ ይኖር ስለነበረና ነገሩን በትክክል ስለሚያውቅ እሱ ሊመሰክር ይችላል ብዬ አምናለሁ ::
ያኔኮ ለነሱ እኔ የገጠር ልጅ ነበርኩ አንተም ምናልባት ያኔ ገበሬ አልነበርክ ወይ እንዴት አራዶቹን ሸቀልካቸው ልትለኝ ከሆነ አሁን ነው ገበሬ የሆንኩት ልልህ ነው::
ፍሰሀን እና ጸጋዬን ስታነሳ ሌላ ሌላ ነገር ነው ትዝ ያለኝ
የጸጋዬ ወንድም በኃይሉ ግዛው አይገርምህም አንተ በህይወት ተርፈህ እንደዚህ መገናኘት መቻላችን ራሱ ለኔ ትልቅ ታሪክ ነው::
የካሜራህን ነገር ስታጫውተ ደሞ ምን ትዝ አለኝ መሰለህ ? እዚህ አንዳንዴ ካሜራ ይዞ የሚንጎራደድ የፈረንጅ ሀገር ሰው ሲያዩ ያዲሳባ ተረብኮ አይጣል ነው
....ይቺኮ ሲያልቅ ማያ ነች ...... ይሉታል::
ሲያልቅ ማያ ነች ያለው ልመንህ ታደሰ ነው ቅቅቅቅቅ አለች የግሏ
ምናልባት ምክሬ ከረዳህ ወደፊት ስትመጣ ውድ የሆነ ካሜራ ይዘህ አትምጣ
ብዙ ጊዜ በውስጧ ያለውን የፎቶግራፍ ማጠራቀሚያ አውጥተህ መያዝ ስትፈልግ ደሞ መጨመር ::
ምክንያቱም መሰረቅም ብቻ ሳይሆን የሆነ ቦታ ገባ ብለህም አስቀምጠህ ረስተህ ትወጣለህ ማንም ታማኝ ባለሱቅና ባለሆቴል አይገኝም ::

ጎስሽክም መቼም ትጽፈዋለህ ነው ሚባለው ያለህ ማን ነበር ? ውነቱን ነው ትቀሽረዋለህ እንጂ !
ከደስታ ቀኖችህ ሁሉ የሰርግህን ቀን ማስታወስህ ድንቅ አነጋገር ነው ምናልባትም ሰብሰብ ማለታችንን ወደኸው እንደሆነ ባውቅም ለሰውልጅ እንደሰርጉ ቀን የሚደሰትበት ምንም ቀን አይኖርም::
የሰውልጅ ሶስት አበይት ነገሮች በተፈጥሮው ውስጥ ይከወናሉ ሲወለድ ሲያገባና ሲሞት :
ሲወለድ በእርሱ ብዙዎች ይደሰታሉ
ሲያገባ እርሱ ከማንም ይልቅ ይደሰታል
ሲሞት ደግሞ ሁሉም ያዝናሉ
ስለዚህም ይመስለኛል <<በምድር ደስታ ብቻ የለም>> የተባለው ምክንያቱም ቀደም ያሉት መወለድና ማግባት የደስታ ቀኖች ሲሆኑ ሞትም አለ ነው የሚለው ብዬ አምናለሁ::
ሠርግ በምድር ላይ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ ሁሉ የነበረ ያለና የሚኖር ነገር ነው: ሠርግ ባህል አይደለም ልማድም አይደለም የሰዎች ህግም አይደለም ሠርግ ተሰጥዖ ነው የተፈጥሮ ህገ ተሰጥዖ እግዚአብሄር በአዳም እንቅልፍ ጥሎ ከጎኑ አጥንት ነስቶ ሚስቱን ሲፈጥራት በዚያችው ጊዜ ለእኛ የሰጠን የህግ ስጦታ ነው::
ሠርግ ባህል አይደለም ነገር ግን ሠርግ በብዙ የባህል ሥርዓቶች ይፈጸማል ::
እርሱም ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹህ ነው ይለዋል ! ጋብቻ በአለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ ቀዳማይ የአማርኛ ቃል መፍቻ ግብ (ሲነበብ ጠበቅ ይላል) ውህድ; አንድነት; እያለ ይፈታዋል ::
ጋብቻ በተፈጥሮ የህግ ስጦታ ነው ስለሆነም ጋብቻ በሁለት ተፈቃቃጆች መካከል የሚፈጸም በመንግሥት ህግም የሚጸና የተፈጥሮ ሥርዓት ነው::
በድሮዎቹ ቀደምት ባለታሪክ ሀገራት ለምሳሌ በቀድሞዋ ቆስጠንጢንያ ቱርክ በእስራኤል በግሪክ በባግዳድና በሌሎችም ከተማ ውስጥ ጋብቻ ሲደረግ የከተማው ሰው በሙሉ ነበር የሚታደመው ::
የጋብቻ ጥሪ ብሎ በግል ወይንም በጎሳ አልያም በዘር አልነበረም ::
የታሪክ አካሄድና አዘማመን ዛሬ የጥሪ ካርድ ካልያዘ ሰርግ መታደም አይፈቀድም::
አሁን አሁን ደሞ የጥሪ ካርድ የያዘም አለባበሱ እየታየ ካርዱን ፎርጅድ አሰርቶ ነው ተብሎ በበር ጠባቂ ይመለሳል::
የሆነው ሆኖ ሠርግን ያደረጉ ሙሽሮች በህይወት ዘመናቸው ሊያደርጉት የሚገባቸውን ትልቅ ምዕራፍ አድርገዋልና በእለቱ የሚያገኙት ደስታ በጣም ትልቅ ነው::
ለነገሩ እኔ እስካሁን ድረስ ገሌ ከመግባት በስተቀር ይህን ያህል ሱፍ አስለብሶ የሚያንቀባርር ነገር አላደረኩም::
ወገቧን ይዛ እንዲህ ነችና እኔ በተወለድኩበትና ባደኩበት አገር ሙሽራ ሆኜ አምሬ ደምቄ ሀይሎጋ ሳላስጨፍርና አገር ጎረቤቱ ሳይሸኘኝ ያንተን ዲቃላ ይዤ
ወደቤት ተመልሼ ልገባልህ ነው ? ..... ኸረንሽቴ ..... ያለቺኝን ቀን ሳስታውሰው ሰርግ የሚለውን ቃል ጠላዋለሁ::
በውነት ሠርግ ለሰው ልጅ ሊያመልጠው የማይገባ ትልቅ ስጦታ እንደሆነ አምናለሁ ብዙ ያገቡ ሰዎች ሲናገሩም እንደምንሰማው የሰርጋቸውን ዕለት በጣም ይኮሩበታል::
ጎስሻ በደስታህ እኔም ተደሰትኩልህ !
በጆንያ የተሸምካትን ግን በሉክ ሳታሳብብ ለኛም አቅምሰን አይፋ የያዝከውን ሳታውቅ እንዲሁ የምትሸወድ አይደለችም ዝም ብላ ጨርቋን አትጥልም::
ልጅ ተድላ ወደቤትህ ጎራ ብዬ ያለውን የቀማመስኩት ዛሬ ነው መቼም አንተ ቤት ተገብቶ ምን ጠፍቶ ሁሉ በጅህ ሁሉ በደጅህ ! ስለግብዣህም ምስጋና ይግባህ !
የጥላሁን ገሠሠን ዘፈኖች ማዳመጥ እወዳለሁ ::
ጥላሁን ለዘፈን የተሰጠ ሰው ነው
አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
የሙዚቃው መሪ ጥላሁን ገሠሠ ..... እያልን ልጆች ሆነን እንገጥም ነበር ::
ይገርምሀል ልጆች ሆነን የአውሮፕላን ድምጽ ስንሰማ ከየቤታችን ወጣ ወጣ እያልን አንጋጠን እናይ ነበር ምክንያቱም አውሮፕላን ምን ሊያረግ እዛ ይመጣል::
የመጣ እንደሆነም ደሞ በዚያ በኛ ሰማይ ላይ ሲያልፍ በጣም በጣም ከፍ ብሎ ስለሆነ አንዳንዴ ከድምጹ በቀር በአይናችንም አናየውም ነበር አቤት ስንበሽቅ ምን ገገማ ሹፌር ነው በናታችሁ እያልን ::
የጥላሁን ታዋቂነት ለምን ከአውሮፕላን ጋር እንደተያያዘ ባላውቅም እንደዛ እያልን ግን መግጠማችን በፍጹም አይረሳኝም::
ምናልባት እንደአውሮፕላን ድምጽ አገር ምድሩ ስለሚሰማው ይሆን ?

ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby አደቆርሳ » Fri Dec 07, 2012 2:06 pm

ዛሬ የዓመቱ ዓርብ ነው: በፊት በፊት ታስታውሱ እንደሆን ዓርብ ዓርብ እዚህች ቤት ብቅ ሳልል ቀርቼ አላውቅም ግን የነበረኝ ጥድፊያና ጭቅጭቅ አይረሳኝም::
ዛሬ ያ ጥድፊያና ጭቅጭቅ ባይኖርም ዓርብ መሆኑ ግን ልዩ ቀን ነው የሙቀቱ መጠን ደግሞ ከቁጥጥር ውጪ ይባላል::
እንግዲህ ማንም ብቅ ያለ የለም ሲመቻችሁ ብቅ በሉ
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ነኝ
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby Gosa » Fri Dec 07, 2012 2:27 pm

ጎሳ ጎሳ ! ውይ ውይ ውይ ...ምነው ? ምነው ? የሆነ ቦታ አንድ ወሬ ሰምቼ ነው እየሮጥኩ ወደዚህ የመጣሁት ::
የቡድሂዝት ሀይማኖት ለመቀበል ዝግጅት ላይ ነህ አሉ :;እንደውም ወዳጅህ ደጉ ወደፊት ከዚህ አለም ስትለይ ቢራቢሮ ሆነህ እንድትመጣ እየጸለየልህ መሆኑንም ሰማሁ ::
ምነው ምነው ልጄ ? ኧረ ባክህ አደብ ግዛ ? እኔማ በዚሁ የምለቅህ አይደለሁምና አዮ ጋ ደውዬ ኢያ ደበርሲ አደርጋለሁ ::
አይፋ አንቺስ ምን ትያለሽ ? ጓደኛሽን አንድ በይው እንጂ ? ባይሆን አንቺን እንደሚሰማ ስለማውቅ ትንሽ ጎነጥ አርጊልኝ ::
ለመሆኑ ደጉን ታውቀው ይሆን ? ባይገርምህ ሱኬም
ጎሳም እያለህ .....አብሮህ ነበር ::
እንዴት ብለህ አትጠይቀኝ ? ደጉ ካልፈቀደ በስተቀር አልነግርህም


:D :D :D ዛሬም እንደጥንቱ ሁሉ እግሮችህ ለወሬ ከጥይት ይፈጥናሉ ማለት ነው:: በስተእርጅናም ለውጥ የለ? ምነው ሌላ ቀን አታወራም እንዴ? ወድቀህ ብትሰበርስ? ኧረ ወንድም ተረጋጋ :D
ደግሞ ደጉ እንዴት እኔ ሳላውቀው ጎሳ እና ሱኬም አብሮኝ ይሆናል? በረሮ መሆን እንደምፈልግ እንጂ እንደነበር'ኮ አልነገረኝም:: ዬትም የሚከተሉኝ እነሱ ነበሩ :D :D ደጉ ገደለኝ እዚህ ቤት ገብቶ ካነበበው:: ለነገሩ ምን አገባኝ...ያንተ ስራ ነው:: እኔማ ስንት የበረሮ ማጥፊያ ኬሚካሎች ከጥፋት በሚተርፉት አለም በረሮ ሆኜ ከምፈጠር ቢራቢሮ ሆኜ "ባበቦች" ዙሪያ ላንድ ሳምንት ባንዣብብ ይሻለኛል::

ወይ አደቆርሳ ! ስለ ሠርግ አንስተህ ስንት ነገር አስታወስከኝ መሰለህ :: አይ ችሎታ !! ሠርግን ለመጀመሪያ ጊዜ የሄድኩት አልል መቼም እቤታችን ስለተሠረገ ያየሁት ብል ይሻለኛል መሰለኝ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው :: እህቴ እና የሚያገባት ባሏ ለአንድ ቀን ተነጋግረው አያውቁም ነበር :: አባቴ እና የአማቼ አባት በጣም ይቀራረቡ ስለነበር ሁሉም ነገር ያለቀው በሁለቱ ብቻ ነበር :: ሰዎቹ ባካባቢው እና በወቅቱ መስፈርት ሲገመገሙ "አሏቸው " ከሚባሉት የሚመደቡ ስለነበር እና ልጁም መልከመልካም ነገር ስለነበር (ካደኩ በኌላ ነው የተገለጠልኝ ) እህቴም የጠላችው አይመስለኝም :: እየተዋደዱ መገናኛ መንገድ ግን አልነበራቸውም :: ልጁ ደግሞ ከኔም በላይ ዝምተኛ ነገር እንደነበር አስታውሳለሁ :: እቤታችን ሲመጣ አንዳች ቃል አይተነፍስም ስሙን ጠርተው ካላናገሩት :: ያኔ ታዲያ ሰንጋዎች ከአንበሶቹ እኩል ግቢ ተሰርቶላቸው ለቱርስት መስሂብነት ብቻ ማገልገል አልጀመሩምና በየበረቱ አራት አምስት ሰንጋ ስለማይጠፋ ድል ያለ ድግስ ተደገሰ :: ሰርገኞቹም የሊሞ እና ሀመርን ወሬ ሰምተው ስለማያውቁ ተራራ የሚያካክሉ ፈረሶችን በማስዋብ አየር ላይ እያስደነሷቸው ነበር የመጡት :: ከተጠበቀው በላይ ሆነው ቢመጡም " የጥሪ ካርድ አሳይ " አልተለመደምና የነበረውን ቀማምሰው ሀይለኛ ጭፈራ ጀመሩ :: ትልቁ ቤት እና ለዚሁ ጉዳይ ተብሎ የተሰራው ጊዜያዊ አዳራሽ ነገሩም ጠቦ ሜዳ ላይ መጨፈር ተጀመረ :: ያ ዝምተኛ እና አይናፋር የሚመስል ልጅ እራሱ ከፊቱ ላይ የሚነበብ ፈገግታ የሚገርም ነበር :: እህቴም ብትሆን እኛን ጥላ በመሄዷ ይሰማት እንጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምትወደው ልጅ ጋር ለማደር ሳትጓጓ የምትቀር አይመስለኝም :: የምታገባዋን እህቴን ከሌሎቹ በላይ ስለምወዳት ነው መሰለኝ ልክ ሰዎቹ እንደመጡ ነበር ለቅሶ ነገር የጀማመረኝ :: እስከተወሰነ ጊዜ ሸኝተናት ተመለስን :: ወደ ማታ ላይ ሁላችንም ተሰብስበን ስንቆጠር አንድ ልጅ ይጎድላል :: ያገባችዋ እህታችን ተከታይ ከዬት ትምጣ :: በየጎረቤቱ ተበታትነን ብንፈልጋት ከጭፈራው በኌላ አየኌት የሚል ሰው ጠፋ :: ታዲያ ሰውም ሆነ ከብት ሲጠፋ ኡ ኡ ኡ እዪ እያ ዳባርሲ ማለት የተለመደ ነውና ( ሞፊቲም ያውቃል ይህንን ) ጩኽቱ ሲጀመር አንድ ደህና ጨባሽ ወንድሜ ምስጢሩን በደንብ ያውቅ ነበርና " ያ ሁሉ ሕዝብ የመጣው ላንዷ ልጃችሁ ብቻ መስሏችሁ ነበር እንዴ ? አንዷ ባስደገሰችው እሷም አገባች " ብሎ አረዳን :: በአንድ ሠርግ ሁለት ሰው ሲዳር ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት :: ያ ያኔ ነበር የገረመኝ ::
አሁን እዚህ አገር የገረመኝ ነገር አለ :: ከልጁ ጋር አብረን እየኖርን ሳለን ነው ድንገት ተነስቶ የተሰወረብኝ :: መጨረሻ ላይ በስንት ፍለጋ ሳገኘው አደገኛ ፎንቃ ጠልፎት ሻንጣውን ሳይወስድ በለበሳት ልብስ ብቻ እቤቷ መግባቱን ሲነግረኝ በደስታው ተደሰትኩለት :: ሁለተኛው ልጅ ከተወለደ ወዲህ ነበር ነጋ ጠባ እንደሚጨቃጨቁና መኖር እናዳልቻለ ቢቻል ከቤቷ ለመውጣት እያሰበ መሆኑን በምሬት የነገረኝ :: አንድ ሁለቴ አስታርቄያቸው ከዚያ በኌላ የነሱንም ነገር ላለመስማት ብዙ ጊዜ እቤታቸው መሄዱንም ተውኩት :: ታዲያ አንድ ቀን ኢትዮጵያ ሄደው ሊሠርጉ ማሰባቸውንና አዳራሽ ሁሉ እንደተከራዩ ሲነግረኝ በጣም ነበር የገረመኝ :: ፍቺ እየታቀደ መሠረጉ በፍጹም አልገባኝም :: ለምን በዚህ ሀሳብ እንደተስማማ ስጠይቀው "እኔ ከማን አንሼ ነው የማይሠረግልኝ :: ገንዘብህ እንዲነካ ባትፈልግ እንኳ የዕለቱ ለት ብቻ አጠገቤ ቁም " አለችኝ :: እኔም ምን አከራከረኝ ብዬ ዝም አልኳት :: እንደፈለገች ታድርግ " አለኝ ::
አገር ቤት ሄደው ሠርገው ሲመለሱ ቪዲዮውን አሳዩኝ :: በጣም የገረመኝ "ከውጭ የደረሱን የእንኳን ደስ ያላችሁ የስልክ መልዕክቶችን ተቀብለናል ...ጎሳ ከ ....ደውሎ እንክዋን ደስ አላችሁ ብሏል " ይላል አንዱ ቀባጣሪ :: እኔ የሰርጋቸውም ቀን ትዝ አላለኝም እንኳን ልደውል :: "መች ነው የደወልኩት አንተ ቀሽም !" ስለው "እነሱ የሚሰሩት ስራ ነው :: እኔ ምን አውቃለሁ " አለኝ :: ታዲያ የሠርጋቸውን አንድ አመት እንኳን ሳያከብሩ ተለያዩ :: አሁን አሁን አንዳንድ ሠርግ ለምን እንደሚሰረግ እራሱ ማወቅ እየተሳነን ነው ::
Last edited by Gosa on Sat Dec 08, 2012 5:30 am, edited 1 time in total.
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Dec 07, 2012 5:46 pm

ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ልጆች :-

ያንን ባለኪዮስኩን ልጅ ያዬ አለ ይሆን :roll: :roll: :roll: እሱኮ በጫት ምርቃና ከመሬት ነውጥ የሚተርፍ እየመሠለው አዚያው ጃፓን እየፈረሸ ይሆናል::

ባለሱቅ :- በሕይወት ካለህ ድምፅህን አሠማን :lol: :lol: :lol:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ሞፊቲ » Fri Dec 07, 2012 11:40 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

አደቆርሳ እንዳልከው አርብ አርብ ሳምንቱ የሚጠናቀቀው ባንተ ፖስት ነበር::እኔ ደግሞ ቅዳሜን እሁድንና ሰኞን
አልወዳቸውም::በብዛት ማንም ሰው ጎራ ብሎ የማይጽፍበት ቀን ቢኖር እነዚህ ሶስቱ ቀኖች ናቸው::

ጎሲቲ=ያስነበብከን የሰርግ ታሪክ ልዩ ነው:: ሁለተኛዋ እህትህ ተደርባ ስትሄድ ሚስጥሩን ያወጣው ወንድምህ ስሙ
በገ ጀምሮ በሌ የሚያልቀው ነው አይደል? ወይ የሱ ነገር? ከዚህ በፊት እኛ ቤት መቶ ጠጅ ሲጠጣ የሶስት ብርሌ ሂሳብ
ሳይከፍለኝ አረሳስቶኝ መጥፋቱን አስታውሳለሁ::

የዘንድሮ ሰርግ ብለህ የሰጠኧው አስተያየት በሰፊው የሚያነጋግር ነው::
በተለይ ያን ሁሉ ወጪ አውጥተው ሰርገው በማግስቱ አይንህ አይንሽ ላፈር የሚባባሉ ሰርገኞች ጤናቸው ሁሉ ያጠራጥረኛል::
አንተ እንዳልከው እነም እዚህ ባለሁበት ከተማ እንዲሁ አይነት ነገር ስለገጠመኝ ትዝብቴ በጆንያ ሙሉ ነው::
እንደውም እኔ በምልህ ሰርግ ላይ የኔም አስተዋጾ ከፍ ያለ ስለነበርና ትልቅ መስዋትነት የተከፈለበት ስለነበር
ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለራሴም በጣም አዝኛለሁ::እንዲህ ዘለቄታ ለሌለው ነገር መልፋቴና መድከሜ እራሴን እንድወቅሰውም አስገድዶኛል::ትላንት እጅግ ከፍ ባለ ወጪ
ሁለት የሚዋደዱ የሚመስሉ ጥንዶችን ድረህ በማግስቱ ለሽማግሌ ለያዥና ገላጋይ የሚያስቸግሩ ሰዎችን ስታይ ቀድሞውኑ
አይተዋወቁም ነበር እንዴ? ያስብልሀል::አንተ ከላይ እንደገለጥከው ድሮ ብዙዎቹ ጋብቻዎች የሚጠነሰሱት
በወላጆቻን ፍቃድ በመሆናቸው ኌላቀርነት ነው ብለን መጠናናት መተዋወቅ ወደሚለው ዘመናዊ ጋብቻ ብንመጣም እንኳ
በብዛት መተዋወቁና መጠናናቱ መበላላት እየሆነ ስለተቸገርን
የአባቶቻችንን ፍቃድ ሳንመኘው የምንቀር አይመስለኝም::

ተድልሽ= እንዳልከው የዚህ ልጅ ነገር ሳያሳስብ አይቀርም::ያቺ ጃፓን የሚሏት ሀገር ጣጣዋ ለምን እንዲህ
እንደበዛ አላውቅም::
ለማንኛውም ሱቂቲ ደህንነትህን አሳውቀን::

ቸር እንሰንብት!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests