ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby Gosa » Sat Dec 08, 2012 1:49 pm

ሁለተኛዋ እህትህ ተደርባ ስትሄድ ሚስጥሩን ያወጣው ወንድምህ ስሙ
በገ ጀምሮ በሌ የሚያልቀው ነው አይደል ? ወይ የሱ ነገር ? ከዚህ በፊት እኛ ቤት መቶ ጠጅ ሲጠጣ የሶስት ብርሌ ሂሳብ
ሳይከፍለኝ አረሳስቶኝ መጥፋቱን አስታውሳለሁ ::


ና ለማለት የፈለከውን በላ! :D ለነገሩ የልቡን በደንብ ታውቃለህ:: ኦፊሺያሊ ያገባው አማቻችን እንደ ባህሉ ብዙ አርሶልን ገላና አባያ ድረስ በእግሩ ሄዶ ለከብቶች ቦሌ ጉሬ ብሎ :D :D ስንት ነገር ለፍቶ መሰልህ ያገኛት:: ጆከሩ አማቻችን ግን ያንን ስርዐት ባይፓስ አድርጎ በጋብቻው ቀን ብቻ ዘሎ ያለቦታው ጉብ እንዲል ያደረገው አርክቴክት እሱ ነበር:: ታዲያ የናንተ ቤት ብርሌዎች እስካልጠፉ ድረስ እሱ የነጻ አገልግሎት ይሰጣል ማለት አይቻልም::
አንድ ቀን ምን እንዳደረገኝ ታውቃለህ.....ትዝ ይለኛል እሁድ እለት ነበር:: ትምህርት ቤት ገና መከፈቱ ነበር:: መጣና "ለምን አባ ቁምጣ እስካሁን አልገዛልህም? ላንተ 'አልገዛም' እያለ ነው አሉ:: ሄደህ አልቅስበትና ዛሬውኑ አስገዛው:: ለሁለት ሄደን እንገዛለን" ብሎ ለኩሶኝ ወዳባቴ ይልከኛል:: አባቴ የገበያ ቀን እንድጠብቅ ቢለምነኝም ለቅሶዬን አላቆም አልኩ:: ከዚያ እሱ አንደኛ ሽምግልና ተቀማጭ ሆኖ መጥቶ " የልጅ ነገር በጣም ያናድዳል:: በቃ ከመታፈሪያ ወይም ከበለጠ ባሪሶ ሱቅ ልግዛለት ብሎ ገንዘብ ካባቴ ተቀብሎ ይዞኝ ሲሄድ ለኔ የሚሆን ቁምጣ ይጠፋል:: በመጨረሻ የህጻን ልጅ ቁምጣ አይነት ነገር በትንሽ ሳንቲም ገዝቶልኝ ካጠገቡ አባረረኝ:: የተገዛልኝን ቁምጣ እንዴት ለብሼ ሰው ፊት ልቅረብ! በጣም አጭር! ከድሮ ጄምስ ፓንት (አሁን እንኳ አይቼ አላውቅም:: ይኖር ይሆን?) አይበልጥም:: እሱ በተረፈው ማታ ከናንተ ቤት ጨብሶበት ስለመጣ ገና እቤት ገብቶ እንደተቀመጠ ያለሙን እንቅልፍ መለጠጥ ጀምሮ ነበርና አንድ ሀባ ያባቴን ስድብ እንዳልሰማው እርግጠኛ ነኝ::

መጠናናቱ እና መተዋወቁ መልካም ነው በቤተሰብ አሬንጅ ከሚደረግ ጋብቻ:: ግን እንደው ስንጠናና ከርመን ፍቅራችንን ጨርሰን(ያልቃል ማለቴ አይደለም) ተሰለቻችተን ልንለያይ አካባቢ መሠረጉ ምንድነው ጥቅሙ? በንጹህ ልብ ሠርገህ ተደስተህበት በማግስቱ በሆነ ባልጠበከው ምክንያት ብትለያይ እንኳ ምንም አይደለም:: ግን እንደማይሆን እያወክ ሠርገህ ከዚያ በኌላ ለይሉኝታ ብቻ ለተወሰነ ወር ቆይተህ የምትለያየው ሰርግ እንደ ወንጀል መታየት አለበት :D
ያንተም ጓደኞች ከኔዎቹ አይሻሉም:: እኛስ ከነሱ እንሻል ይሆን? የዛሬ ሁለት አመት የምንመልሰው ጥያቄ ይሆናል::

እዉነትም ሰው ለምን ቅዳሜ እና እሁድ ዋርካ አይገባም? እሱን ነገር እኔም ታዝቤያለሁ:: ማንን እንደታዘብኩ ባለማወቄ ግን እራሴን ታዘብኩ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ባለሱቅ » Fri Dec 21, 2012 6:57 am

ጥይት መቷቹ/ ሰውነታቹን በስቷቹ ያውቃል?
ምን እናንተማ ከእስክፒርቶ በስተቀር መች ወግ ያለው ስራ ሰርታቹ ታውቁና
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እንደምን አላቹ ያገሬ ልጆች.. የሰፈሬ ውዶች
እንዴት ናፍቃቹኛልልልልልልልልል መሰላቹ
ደሞ ቤቱን ጭርርርርርርር አድርጋቹታል...
አደቆርሳም ከመጣ በኃላ እንደዚህ ናቹ ማለት ነው
ህምምምምምምምምምምምምምም
...........................................................//.............................. ይሁና .. አልች ዶሮ
እንዲህ ሆንኩላቹ
...................................................................
የአርባ-ምንጭ ነጭ ሳር ውስጥ ካለው ረጃጅም ጫካ ውስጥ ነኝ
እዚህ ኡጋንዳ
Elephant Grass ይባላል ... ከሁለት ሜትር የበለጠ ቁመት ያለው
የዛሬ አመት የተከልናትን ችካል እየፈለግን ነው... 3 ነን
GPS (Global Positioning System) ይዘናል... ለሁለት ጥቅም እንዲሆነን
1ኛ... የተነሳንበትንና ያለንበትን ቦታ አውቀን... ስንመለስ መንገዱ እንዳይጠፋን
2ኛ... የዛሬ አመት የተተከለችውን ችካል ለማግኘት እንዲረዳን
ስቴፋኒ ዋሻ የሚባል ቦታ ታውቃላቹ ኢትዮጵያ ውስጥ.. ደቡብ ኦሞ.. ጨበተለምዶ ጨው ባህር የሚባለውን ቦታ
ስቴፋኒ የሚባል አበሻ ነው አሉ.... ማለቴ ፈረንጅ.... GPS ባልተፈጠረበት ዘመን.. (መሰለኝ).. እዛ ጫካ ውስጥ ገብቶ.... መመለሻ ጠፍቶበት.... እዛው ቀርቷል ሲሉ የሰማሁ መሰለኝ....
ያኔ ያኔ.... ለሀገሬ ለመስራት ከላይ ታች ስዘዋወር (ድንቄም እቴ አልች... ጫልቱ)
እና እኔም እንዳልጠፋ በግራ እጄ GPS ይዤ በቀኝ እጄ ይህንን ሁለት ሜትር የሚያክል የሳር ጫካ እየከፈትኩ....... በጫማዎቼ የሳሩን እግር እግሩን እየረገጥኩ.... እጓዛለሁ
ለስንት ሰአት እንደተጓዝን አላውቅም...
በመጨረሻ ግን... እግሮቼን እንኳን ማንሳት ነበር ያቃተኝ
ሰውነቴ ዛለ...
የምንፈልገውን ቦታም አገኘንና.... መመለስ ጀመርን
ስንመለስም... እንደዚሁ በግራ እጄ እቃ... በቀኝ እጄ... ስናልፍ አስተኝተናቸው የነበሩት ሳሮችን እንደገና እያስተኛን.... ስንጓዝ
ወደቅን.... ሁላችንም በተራ በተራ
አንዴ አይደለም... ሶስቴ ነበር የወደቅኩት
የዛለ ሰውነት.... እግር ማንሳት ያቃተው ባለሱቅ
በሶስተኛው ስወድቅ..... GPSን ላለመጣል.... ሰውነቴ ሁሉ ያረፈው በቀኝ እጄ ነበር
ቀኝ እጄ ደሞ ያረፈው.... ተሰብሮ በቀረ የሳር ስር
በርቀስስስስስስስስስስስ አደረገው መዳፌን
በመዳፌ ገብቶ በአይበሉባ በኩል
ጲርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ነጭ ሳር
........................................//...........................
እውነት ግን ጥይት እጃቹን በስቶት ያውቃል??
እኮ ምን ስታደርጉ>?
.........................................//........................
አያድርስ ነው አልች ብርቄ
........................
እና እናንተ ለሀገራቹ ስትዋጉ... ስትጋደሉ.... ለነፃነቷ ስትፋለሙ.... ተበሳቹ ቢባል
እኔ ምን ሳደርግ... ለማን ብዬ..... በምን ሂሳብ..... ብዬ ላወራ ነው
ማፈሪያ!.... ነኝ እኮ
ማፈሪያ!
...................................................//................................

አይበቃቹም

እረ በአላህ አትጥፉ

አሁን በጣም ተሽሎኛል.... ባይሻለኝ... ማን ይፅፍልኛል

ለሀገሩ ሲል በኡጋንዳ ጫካ የዘመተው ባለሱቅ.... በሳር ጥይት እጁን ተበስቶ.... ጡረታ ለመውጣት አፕላይ አድርጎል
ተብሎ ይነበባቹዋል.. ዜናው
Read it in the News... አበ ቦብ

ሰላም ሁኑ አቦ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Dec 21, 2012 5:03 pm

ባለኪዎስኩ:-

ተርፈሃል ማለት ነው :roll: ተመስገን :D

'የማያዎች የጥንት ቀን መቁጠሪያን ገባን ያሉ የዘመናችን ሊቃውንት' "ዛሬ ዓለም ታልፋለች" እያሉን ነውና አንድ የባጋንዳ ከዳሚ ፈልገህ ጫት ላይ ብትፈርሽ ይሻልሃል : ምክር ቢጤ ነው :)

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby አደቆርሳ » Fri Dec 21, 2012 11:23 pm

ጥይት በስቷችሁ ያውቃል ወይ ? ነው ያልከው ?
አልበሳንም ! ነገር ግን ምን ዓይነት ጥይት ? ብዬ ልጠይቅህ ከጀልኩና ምንም ዓይነት ጥይት እንደማትለኝ ገምቼ ተውኩት .....ወይም ራሴ በደንብ ብገልጸው መልስ ቢጤ አላጣም ነበር ::
የሆነው ሆኖ ኑሮ ራሱ ጥይት ስለሆነ ስለጥይት ምን ብዬ እንደምነግርህ ግራ ገብቶኝ ነው ::
በፊት በፊት ማነው ይሄ ዘፋኙ
ፍየል ቅጠል እንጂ አትበላም እንጉዳይ
በጥርሷ ሰላሳ ባይኗ መቶ ገዳይ ...... ብሎ ሲዘፍን ዘመናዊው ወደጓሮ .... የጓሮው ደሞ ወደ አደባባይ ብለን ነበር::
ለምን አትልም ?
ነገሩ ኣይንና ጥርሷን ለማሞካሸት ተፈልጎ እንጂ የፍየሏ ቅጠል መብላትና አንጉዳይ አለመብላት ለግጥም አጋጣሚነት እንኳ ብቁ ሆኖ አልነበረም::
እንዲህ ያለ ግጥም የሚገጠመው ጥሩ ጠጅ እየተጠጣ ድንገት መኳንንት ወይንም ሌላ ባለካኪ ጎራ ያለ እንደሆነ እሱን ለማሞካሸት ሲባል
አዝማሪው እዚያው እንደመጣለት ለመግጠም የሚጠቀምበት የግጥም ዘዬ ነው::
መተር መተር አርጎ ይበላል ጉበት
ዞርበል አንፈራራ ሸዋን ልይበት ..... እንዳለ አያልቅበት.....
ታዲያልህ ያኔ ይሄ የጠጅ ቤት ግጥም አደባባይ ሲወጣ ተገረምንና አብረን መዝፈን ጀመርን::
ምን እያላችሁ አትለኝም ?
ታንክ የማይበግረው ያርቤ ሚስት ሆነሽ
ምነው ባልጋ ቀረሽ ጥይት ታቅፈሽ.............. እያልን ነዋ !
ምን መሰለህ ነገሩ በጣም የቆየ ታሪክ ነው ሆኖም እውነተኛ ነው::
አርቤ የምንለው በጣም የታወቀ ጎበዝ ተዋጊ ነበር በብዙ ጥይት ተመቶ ሳይሞት ኖሯል ታዲያ ተለይቶ የሚታወቅበት ልዩ ባህርይው ደግሞ ሴት መውደዱ ነው ሴቶችም በጣም እንደሚወዱት ይነገርለታል::
ታዲያልህ አንድ ጉደና ሌሊት የአርቤ ሚስት ሌላ ሰው ቤት ውስጥ አልጋ ላይ ሳለች በጥይት ተመታ ህይወቷ ያልፋል ማን እንደመታትም በወቅቱ አልታወቀም ምክንያቱም የሞተችበት ቤት ባለቤት በዛን ጊዜ በስፍራውም አልነበረም::
ታዲያ አርቤ በጣም ተጫዋችና ቀልደኛ ዘፋኝም ገጣሚም ስለነበር እንዲህ ብሎ ገጠመ::
ታንክ የማይበግረው ያርቤ ሚስት ሆነሽ
ምነው ባልጋ ቀረሽ ጥይት ታቅፈሽ..
እኛም እዛ አካባቢ የነበርነው በአንድ የአብዮት ዜማ አድርገን እንዘፍንባት ነበር እልሀለሁ::
በጥይት የመበሳት ሁኔታ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኝ ያውቃል አስገራሚም አስፈሪም ሁኔታዎችን አሳልፌያለሁ::
ገለታ ረቢ እኔን ግን በስታኝ አታውቅም
ሰው ዓይኑ ሳያይ ስጋ ለስጋ በጥይት ቢመታ የመርፌ ያህል እንኳን አይሰማውም ይሄ በጣም ይገርመኝ ነበር :: ህመሙም ቶሎ አይሰማውም ምናልባት ከህመሙ አስቀድሞ ደሙን ካላየ በስተቀር ወዲያው ምንም የምት ስሜት አይሰማውም::
ጥይት በሰውነቱ የተሰካችበት ሰው ግን ስስ ብልት የሚባለውን አካል ያላገኘች ጥይት ወይንም ጎበዝ ያልተኮሳት ከሆነች ስቃይዋ ኃይለኛ ስለሆነ ጊዜ ሳያባክኑ መገላገል የሚመረጥበት ጊዜ ነበር ::
የዛሬን አያርገውና በልጅነታችን ተገደን ከገባንበት ካምፕ ሶስት ሆነን አምልጠን ቀን እያደፈጥን ሌሊት እየተጓዝን ሶስት ቀን ካሳለፍን በኍላ ከአንድ ትንሽዬ መንደር አካባቢ ደረስን
መንደሩ ደሞ በኃይለኛ ጅቦች የሚታወቅ ነው እኛ ደሞ ምንም ዓይነት መሳርያ አልያዝንም ብቻ ለመወርወር የሚመች ድንጋይ ሰባስበን በየኪሳችን ይዘናል::
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby ባለሱቅ » Mon Dec 24, 2012 2:51 pm

አደቆርሳዬ
ታንክ የማይበግረው ያርቤ ሚስት ሆነሽ
ምነው ባልጋ ቀረሽ ጥይት ታቅፈሽ

ብለህ ዘፍነህልኝ ስታበቃ
ምነው የጅቦቹን ታሪክ መንገድ ላይ አቆምከው
ወይ ጅቦቹ ይለፉ... ወይ በያዛቹት ድንጋይ... አባሯቸው እንጂ
የምን ተፋጦ መቀመጥ ነው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላምምም ያገሬ ልጆች
እንኳን ለገና በአል አደረሳቹ
ይላቹዋል እየዳነ ያለው እጄ

አትጥፉ በአላህ
ስታስጠሉ... ግን

ቆይ እንገናኛለን
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby ሞፊቲ » Mon Dec 24, 2012 7:17 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ሱቂቲ...እኔን እኔን...እኛ ጃፓን ውስጥ ሆነህ የመሬት መንቀጥቀጡ አንዘፍዝፎህ ይሆን ብለን ስናስብ
አንተ ለካ በ ኡጋንዳ ምድር በሙጃ ተለብልበህልኝ ኖሯል::ሆላ መገኖ አለ ቁንዝሮ?
እኛም እዚህ በክረምቱ ጉንፋን ተሰቃይተን አሁን ገና ነው ተንፈስ ያልነው::አያድርስ እኮ ነው::በሻይ ኮሮንቲ የማይደን
ጉንፋን ምን ይባላል?

አደቆርሳ የጅቦቹን ታሪክ ቶሎ ከች አድርግ....የሳምንቱን የገና እረፍት ባንተ ጨወታ እንቆዝመው እንጂ?

ራስ= ከሄድክበት ቦታ እስካሁን አልተመለስክም እንዴ? ቶሎ እመለሳለሁ ያልክ መሰለኝ?

መልካም ገና!

ቸር እንሰንብት!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby አደቆርሳ » Tue Dec 25, 2012 1:20 pm

አደቆርሳ የጅቦቹን ታሪክ ቶሎ ከች አድርግ ....የሳምንቱን የገና እረፍት ባንተ ጨወታ እንቆዝመው እንጂ
እሺ ጎፍታኮ መቼም ጅብ እንደማይበላኝ ታውቃለህ ወራቤ ሀዳ ኢሺን ያን ሌሊት ከግራም ከቀኝም በጩኸት ሲያጣድፉን ግንዲላውን ለሲጃራ በተያዘ መለኮሻ ለኩሰን ችምችም ያለው ቋጥኝ እስኪጋይ ድረስ ቁጭ ብለን አድረን ሲነጋ ወደመንደሪቱ ገባን::
ያቺ መንደር ደግሞ በሰልባጅ የልባሽ ልብስ ማቀባበያነት የምትታወቅ ስለነበረች ጥሩ ጥሩ የአራዳ ልብሶችን በትንሽ ፍራንክ ሸምተን ስናበቃ ዩኒፎርማችንን ቀበርነው::
ሁለቱ ጓደኞቼም ለግዢ እንደሄዱ በመምሰል አንዳንድ ቦንዳ ገዝተው ነበር የተመለስነው::
ይሄኔ ነበር አስገራሚው ታሪክ የተከሰተው ልብሱ በግመል ተጭኖ የሚቀጥለው ጣቢያ እስኪደርስ ድረስ እናንተ ከኛጋ መሆን የለባችሁም በምትሄዱበት ሄዳችሁ እዛ እንገናኝ ተባልንና ተለያየን::
ወጣት ተብሎ በመንገድም ሆነ በከተማ መታየት ክልክል የነበረበት ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን የጠላበት አስቀያሚ ወቅት ነበር::
በነበረቺን ቀሪ ሳንቲም ጫትና ሲጃራ ገዝተን ውሀ በላስቲክ ይዘን ነበር በረሀውን ማቋረጥ የጀመርነው::
ከተማይቱን ለቀን ግማሽ ሠዓትም አልተጓዝንም ሽፍቶች እጅ ስንወድቅ ::
ለነገሩ ያኔ ሽፍታ አልናቸው እንጂ እንደዛ አይነት ሁኔታ በየግዜው በሚኖርባቸው አካባቢዎች እያሳደዱ ገንዘብ የሚቀሙ ፋኖዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው::
ይህም ሁሉ ሆኖ በዚህ በኩል አድርጋችሁ ያንን ተራራ አቋርጣችሁ እዚህ ከተማ እንገናኝ ብለው ሲልኩን አንዲትም ነገር አልጠጠራጠርንም ::
እነዚያ ፋኖዎች እንድንቆም ሲያስገድዱን በቁጥር አናሳ መሆናቸውን አይቶ ነው መሰለኝ አንዱ ጓደኛችን ነፍሱን ጥሎ ወደቁልቁል ወደኋላው እግሬ አውጪኝ አለ::
( በያኔው አባባል.......ቁልቁል ቀደደው)
ይህኔ እነሱ ደሞ ገንዘብ እሱ እጅ ያለ መስሏቸው ይሁን አላውቅም እሩምታ ሲለቁበት እኛ ባለንበት ቁጭ ብለን ቀረን::
ፈትሸው ፈታትሸው ያገኙትን የእጅሰዐትና ሌሎችም ከወሰዱ በኍላ በጥፊም በካልቾም ብለው ጥለውን ወደጫካቸው ገቡ::
ድንጋጤው ባሳደረብን ድንዛዜ ለሰዓታት ከነበርንበት ቆይታ ተነስተን ወደመጣንበት ለመመለስ ቁልቁል ወረድ እንዳልን የአንደኛውን ጓደኛችን ሬሳ ተጋድሞ አገኘነው::
አልፈነው መሄድ እንዳቃተን እዚያው ሌላ ተጨማሪ ሰዓት አሳለፍንና ሌሊት ጅብ እንዳይበላው ብለን በእጨት ቆፍረን አንድ ትልቅ ግራር አጠገብ ቀበርነው::
ታዲያ እስካሁን የሚገርመኝና የማስታውሰው ከዛ ሁሉ ጥይት የወጋችው አንዲቷ ብቻ ነበረች እሷም ታፋውን ከጉልበቱ ከፍ ብላ::
በዚያች ጥይት ህይወቱ ማለፉ በጣም ይገርመኛል::
አንዳንዱ ደረቱን ተመቶ ይተርፋል ሌላው ደግሞ ታፋውን ተመቶ ያልፋል የጥይት ነገር ስለሚያስገርመኝ ነው ይህን ያነሳሁት:
ባለሱቅ አንተን የወጋህችህ ጥይት ግን እኔን መቶ ግዜ ወግታኛለች ሳብ እያደረኩ እየነቀልኳት ነው ያደኩት::

ባለፈው ሰሞን ዓለም ወደከርሷ ትገባለች ? እያሉ የሰለጠኑት ዓለም የዜና ምንጮች ሲናገሩ በጣም አስቆኝና አስደስቶኝም ነበር: ያሳቀኝ ብልጥነቴ ሲሆን ያስደሰተኝ ደግሞ ሞኝነቴ ነበር :
የምጽዓት ጊዜ መቼ እንደሆነ ማንም ፍጥረት ቀርቶ የሰማይ መላዕክትም አያውቁም .... ይህንን እውነት እያወቅን ሳለን አይ እኛ የተሻለ እናውቃለን የሚሉ ሲነሱ መሸበር መቻላችን ደግሞ አይ ሰው መሆን ያሰኛል ::
ከመሬት ተቆፍረው ስለሚገኙ እጅግ ጥንታዊ የሰው ህይወት መረጃዎች እና ቅሪተ አጽም ምክንያት ዓለም ተዟዟሪ ታሪክ እንዳላት የሚያምኑ ተመራማሪዎች መጽሀፍ ቅዱስን ለማንበብ ጊዜ አለመስጠታቸውና ከግምት አለማስገባታቸው በኃይል ያስደንቀኛል::
በላቲን አሜሪካ ጥንታዊ ከተሞች ከመሬት ሥር በቁፋሮ ስለመገኘታቸው እንዲሁም ከውቅያኖስ ወለል ስር ከእልፍ ዐመታት በፊት ሰዎች የመኖራቸው ምልክቶች ስለመገኘታቸው የዛሬዎቹ ሰዎች የዐለምን ተዟዟሪነት ይመለከቱበታል::
በአየር ብክለት በኬሚካልና አቶሚክ ኃይል ምርዝ ጪስ ልቀት ሰዎች ሲጠፉ እንዲህ ያለው ችግር የማይታይባቸው ስፍራ እንደአፍሪካና አማዞን ጫካ አካባቢ ያሉ ደግሞ ይተርፋሉ....... እነሱም የመጀመሪያዎቹ የሰው ዘሮች ይባሉና እንደገና ከብዙ ሺህ ዓመታት በኍላ ዐለም አሁን ወዳለንበት ቦታ ትመለሳለች ሲሉ ምትሀታዊ እምነታቸውን ይዘክራሉ::
እንደው እንደሞኝ ስናደምጥ ምነው በጠፋችና ይህንን የቂል ህይወት በተገላገልነው ያሰኘኝና ደሞ የኖኅን ዘመን የውሀ ሙላትና የድፍን ዐለምን ጥፋት ሳስብ ያስገርመኛል::
ትክክለኛ ጊዜውን አላስታውስም ሆኖም ከመታት በፊት በቻይናው የመሬት ነውጥ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቅ ህይወት ጠፍቷል በኢንዶኔዢያ (ከመቶ ዓመት በፊት በቮልካኖ ፍንዳታ እንዲሁም እዚያው ኢንዶኔዢያ ውስጥ አሁን ባለንበት ቅርብ ዘመን በሱማትራ የርዕደ መሬት ነውጥ እጅግ ከፈተኛ ቁጥር ያለው ህይወት ተቀጥፏል
በሁለተኛው የዐለም ጦርነት ወቅት በጣሊያን የደረሰ የመሬት እብጠት ፍንዳታ እሳተጎመራ እንዲሁ የበላው የሰው ህይወት ቁጥር የለሽ ነው ::
የሂሮሼማ ቼርኖቪልና የፉኩሺማ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ዓለማችንን ምንኛ እንዳቆሸሿት የምንረሳው ዓይደለም::
ዛሬ ዛሬ ደግሞ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግር ተጋላጭ ያልሆኑ ድሀዎቹ ሀገራት አፍሪካና ደቡብ አሜሪካ በመርዝ ልቀት ከሚቸገሩት ያደጉ ሀገሮች ይበልጥ ስጋት አስተናጋጅ ሆነዋል::
ለሀገር መሪዎች ተዝቆ የማያልቅ ዶላር እያስታቀፉ በየወደቦቻቸውና በከተማ ዳርቻዎች የመርዝ ዝቃጮቻቸውን ማስወገጃ ሠገራ እያደረጓቸው ያሉት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አንድና ሁለት አይደሉም:: ከዐመታት በኍላ ቀዳሚ ተጎጂዎች እንደሚያደርጓት ምንም ጥርጥር የለውም ይህም ነው ታላላቁ የተፈጥሮ ዕልቂት የሚያስነሳው::
በተፈጥሮና በሰውሰራሽ እልቂት እጅግም የማትነካው አፍሪካ በሆዳም መሪዎቿ አማካኝነት ቀድሞም በጥይት ወደፊት ደግሞ በመርዝ እንድንጠፋ ይታገሉልና::
በተፈጥሮ ከሚደሰው የሰው ልጅ እልቂት ይልቅ ይሄ ነው የሚያሳዝነኝ !!
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby ሞፊቲ » Fri Dec 28, 2012 12:01 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ይህኔ እነሱ ደሞ ገንዘብ እሱ እጅ ያለ መስሏቸው ይሁን አላውቅም እሩምታ ሲለቁበት እኛ ባለንበት ቁጭ ብለን ቀረን ::
ፈትሸው ፈታትሸው ያገኙትን የእጅሰዐትና ሌሎችም ከወሰዱ በኍላ በጥፊም በካልቾም ብለው ጥለውን ወደጫካቸው ገቡ ::
ድንጋጤው ባሳደረብን ድንዛዜ ለሰዓታት ከነበርንበት ቆይታ ተነስተን ወደመጣንበት ለመመለስ ቁልቁል ወረድ እንዳልን የአንደኛውን ጓደኛችን ሬሳ ተጋድሞ አገኘነው ::
አልፈነው መሄድ እንዳቃተን እዚያው ሌላ ተጨማሪ ሰዓት አሳለፍንና ሌሊት ጅብ እንዳይበላው ብለን በእጨት ቆፍረን አንድ ትልቅ ግራር አጠገብ ቀበርነው :


ውድ አደቆርሳ= በትዝታህ መሀል ያሳየኧን አሳዛኝ ትውስታ ስቅቅ የሚያደርግ ነው:: በ እርግጥ እንዲህ አይነት ገጠመኞች
በተለይም ከ ብሄራዊ ውትድርና ጠፍተው ከሚመጡ ወንድሞቻችን እየሰማነው የቆየን ቢሆንም ቆንጠጥ የሚያደርጉ
ታሪኮች ሁሌም በታሪኩ ባለቤቶች ሲነገሩ እንደ አዲስ ስሜትን መግዛታቸው የማይቀር መሆኑ ነው::

ድሮ ድሮ በርጫ ላይ ሆነን( በስራፈትነት) ዘመናችን እነ ቡጡ ቢአርና ሌሎችም ስለውትድርና ህይወታቸውና ሊጠፉ
ሲሞክሩ የገጠማቸውን የነሱንም ሆነ የጓደኞቻቸውን ታሪክ ሲያጫውቱን የ ደራሲ ገበየሁ አየለን ""ጣምራ ጦር"" መጽሀፍን ያህል
ልቦለድ መስሎን እስክንሰማው ድረስ ዘልቆ ይሸመቅቀን ነበር::

ለማንኛውም የ አደቆርሳን ትዝታ ለመጋራት ብቅ ብዬ የ ክሪስመስ በአላችሁን በሀዘን እንዳልወጥረው በዚሁ
እንዲበቃኝ እራሴን እየገታሁ በውጪ ያላችሁ ወገኖቼ መልካም አዲስ አመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::

ቸር እንሰንብት!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby የግልነስ » Mon Dec 31, 2012 5:32 pm

ስላም ለቤታቸን ይሁን, እንዴት ናቸው ወዩዎቸ እናም የዋርካ ታዳሚዎቸ.... :?:
አደቆርሳዩ እንኳዎን በደህና ተመለስክ.....ባለሱቃቸን እንዴት ነህልኝ ብሮ ተሻለህ ወይ :?:
እንደጠየቅሽኝ አትለኝም ሶሪ ብሮ......እግዜር ጨርሶ ይማርህ ብያለው

ብዙውን ጊዜ ስፅፍ የልጆቻቸን አምላክ አለ እል ነበር እውነትም አምላክ አለ
ሽልንጌና መሀሙድ ለህፃናቱ በየአቅጣጫው የስበስቡት ገንዘብ በጣም የሚያስደስት ሆናል
$1800.00 ተስብስበ እጅግ በጣም አመስግናለው የኔ ጎበዞቸ ያስባቸሁትን አምላክ ያሳካላቸው
በተለይም ያለማቋረጥ ወላጀ አልባ ህፃናቱን የምትረዱ መሀሙድና ስለሺ ደጉስው ምንግዜም የስባቸሁትን አምላክ ያሳካላቸው..............................

ሌላው እስቲ እዚህ ፔጅ እየገባቸው የምታነቡም ሆናቸው የክ/መ ልጆቸ ለወላጅ አልባ ህፃናት ደብዳቤ ፃፍላቸው, አደቆርሳ. ሞፈቲ, ባለሱቅ, ራስብሩ, አንፈራራቸን, ጎሳ, ኦዶሻኪሶ..መሀሙድ, ሽልንጌ, ስለሺ.
ደጉችስው,እናም ሌሎቻቸሁም, ተድልሽ, እንስት, ብሩክ እናም ሌሉቸ የዋርካ ታዳሚዎቸ በሙሉ ለልጆቻቸን(ወላጅ አልባ ህፃናት) ደብዳቤ ፃፍና አገር ቤት ያነቡታል(ክ/መ)
እስቲ ከኔ ልጀምር

ይቀጥላልል
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby ራስብሩ » Mon Dec 31, 2012 10:09 pm

እንኳን ለ2013 አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ !

ጤና ይስጥልኝ እንደምን ከርማችኍል ?

አዲሱ ዓመት የሠላም የጤና የለውጥ እንዲሁም የልጆቻችንን አዳዲስና የተሻሉ ገጽታዎች የምናይበት ዓመት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ::

በተለያዩ ምክንያቶች ጠፍቼ ነበረ ሆኖም አልፎ አልፎ አዳምጥ ነበር በአዲሱ ዓመት በአዲስ መንፈስ እንገናኛለን::

ራስብሩ
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby ባለሱቅ » Tue Jan 01, 2013 7:29 pm

እንኩዋን ለፈረንጆቹ አዲስ አመት አደረሳቹ
ሁላቹንምም

አደቆርሳ ወንድሜ.... የፃፍከውን ሳነበው ስቅጥጥ ነው ያለኝ
እንዲሁ እንደተራ ነገር ጓደኛቹን ... ጅብ እንዳይበላው ቀበርነው ብለህ ስታወራ..... ስቅጥጥ ነው ያደረገኝ
ወታደር ነበርኩ ብትለኝ እና ስለውትድርና ህይወትህ ብትነግረኝ አይገርመኝም ይሆን ይሆናል

በርግጥ ብዙ በስደት ላይ የሚገጥሙ አደጋዎች እንዳሉ ሰምቼ አቃለሁ.... ግን አንተን ይህ ገጠመኝ እንዳለፈህ አስቤ ስለማላውቅ ይሆን የገረመኝ?

እንኳን ግን ለዚህ ጊዜ በቅተህ ይህንንም ለማውራት አኖረህ ወንድሜ
.....................
የግልዬ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ አስታዋሼ
አሁንማ በደንብ ተሽሎኝ.... ይኸው እየፃፍኩበት ነው እጄን.... አልሀምዱ-ሊላሂ .....ብያለሁ... ለራሴ

በተረፈ እስኪ ደሞ ትንሽ ወደ-ስራዬ

ሁላቹም ሰላም ሁኑልኝ

ጎሳን ያያቹ
እባካቹ
ብያለሁ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby ሞፊቲ » Wed Jan 02, 2013 12:38 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

በተለያዩ ምክንያቶች ጠፍቼ ነበረ ሆኖም አልፎ አልፎ አዳምጥ ነበር በአዲሱ ዓመት በአዲስ መንፈስ እንገናኛለን ::

ራስብሩ


ውድ ራስ እንኳን በሰላም ብቅ አልክ:: ከላይ ባለው ነገር ትንሽ ስስቅ ነበር:: ሳላውቀው ዋርካ ጄኔራል ሬድዮ ጣብያ
ጀመረ እንዴ? ብዬ ግራ ገብቶኝ ሁሉ ነበር:: አልፎ አልፎ አዳምጥ ነበር ስትል? የሚያነብልህ ሰው ነበር ? ወይስ
እንዴት ነው ነገሩ? የአይን ችግር መጣ እንዴ?
ለማንኛውም ፕሊስ አትጥፋ!

የግል እንደምን አለሽልኝ? የዘውትር ሰላምታዬ ይድረስሽ::የደብዳቤው ሀሳብ አልገባኝም::
እዚሁ ዋርካ ላይ ነው? ወይስ በ ፖስታ ቤት? በኔ በኩል ትንሽ ይከብደኛል::ድንጋይ ሳልወረውር ብዙ ስለቆየሁ
ባዶ ደብዳቤ ባዶ ሀሳብ እንዳይሆንብኝ ብዬ ነው::
ለመሀሙድና ለሽልጌ ምርቃቴ ይድረሳቸው:: መሀሙዶ ጋ ብዙ
ተጠፋፍተናል:: ጥፋቱ ከኔ ይሁን ከሱ አላወኩም::መልካሙን ሰላምታዬን አድርሽLኝ::

ቸር እንሰንብት!!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby የግልነስ » Wed Jan 02, 2013 3:11 pm

ሞፊቲ wrote:ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

በተለያዩ ምክንያቶች ጠፍቼ ነበረ ሆኖም አልፎ አልፎ አዳምጥ ነበር በአዲሱ ዓመት በአዲስ መንፈስ እንገናኛለን ::

ራስብሩ


ውድ ራስ እንኳን በሰላም ብቅ አልክ:: ከላይ ባለው ነገር ትንሽ ስስቅ ነበር:: ሳላውቀው ዋርካ ጄኔራል ሬድዮ ጣብያ
ጀመረ እንዴ? ብዬ ግራ ገብቶኝ ሁሉ ነበር:: አልፎ አልፎ አዳምጥ ነበር ስትል? የሚያነብልህ ሰው ነበር ? ወይስ
እንዴት ነው ነገሩ? የአይን ችግር መጣ እንዴ?
ለማንኛውም ፕሊስ አትጥፋ!

የግል እንደምን አለሽልኝ? የዘውትር ሰላምታዬ ይድረስሽ::የደብዳቤው ሀሳብ አልገባኝም::
እዚሁ ዋርካ ላይ ነው? ወይስ በ ፖስታ ቤት? በኔ በኩል ትንሽ ይከብደኛል::ድንጋይ ሳልወረውር ብዙ ስለቆየሁ
ባዶ ደብዳቤ ባዶ ሀሳብ እንዳይሆንብኝ ብዬ ነው::
ለመሀሙድና ለሽልጌ ምርቃቴ ይድረሳቸው:: መሀሙዶ ጋ ብዙ
ተጠፋፍተናል:: ጥፋቱ ከኔ ይሁን ከሱ አላወኩም::መልካሙን ሰላምታዬን አድርሽLኝ::

ቸር እንሰንብት!!!!


###############################################################

መልካም አዲስ አመት, 2013 የስላም የፍቅር ብሎም ለልጆቻቸንን የት/ርት እድገት የምናይበት ጊዜ ይሁንልን
ሞፈቲኮ መልካም አመት ላንተም ለቤተስብህም ጨምር ማዘር ሲስተርስ ደህና ናቸው ስላም በልልኝ......
ከላይ ያልከው የራስ ነገር እኔንም ግርም ብሎኛል ቅቅቅቅቅቅቅቅ አዳምጥ ነበር ወይይ ራሳብሩአቸንን ቅቅቅቅቅቅቅ
እስቲ እንዴት እንዳዳመጥክ ግለፅልንን ገደልከኝኝኝ...........

ሌላው ሞፈቲኮ አይዞኝ እትደንግጥ :lol: እዚሁ ዋርካ ላይ ነው የሚያነቡት ፕሪንት ተደርጎ ይሄድላቸዋል
ለምሳሌ እኔ ልጀምር አንተ ቀጥል ደብዳቤውንንን.............. ሌሎቻቸሁምምም


ደብዳቤ ከዋሽንግተን, ዲሲ

ይድረስ ለውድ ልጆቻቸንን እኔ የናተው አሳቢ እናም አሳዳጊ ከሆኑት አንደኛው ነኝ, እንዴት ናቸሁልኝ ት/ርቱስ እንዴት ነው መቼም ጎበዝ እንደሆናቸው ነው ከአቶ ደበበ የምንስማው እኛም የድሮ ራስብሩ ተማሪዎቸ እናም የአሁኑ አዶላ ወዩ ተማሪዎቸ የነበርን እናነተን ለመርዳት እላይ ታቸ እያልን እንገኛለን..........እናተም በርቱልንን..............

የግል ነኝ
ስላምና ፍቅር አይለየን ከብዙዎቸ መውድድ ጋር::
Last edited by የግልነስ on Mon Jan 07, 2013 2:55 pm, edited 1 time in total.
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby ሞፊቲ » Sun Jan 06, 2013 9:37 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ለ ክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት
በዓል አደረሳችሁ::
እጅግ ያማረና ትዝታን የሚፈነጥቅ በዓል እንዲሆንልን እራሳችንን ብቻ በማስደሰት ሳይሆን
የተቸገሩ ወገኖቻችንንም በጸሎትና እጅን በመዘርጋት እነሱም ደስ ብሏቸው ይህን ታላቅ በዓል እንዲያሳልፉ በመርዳት
ጥሩ ግዜን እናሳልፍ::


ደብዳቤ ከዋንግተን , ዲሲ

ይድረስ ለውድ ልጆቻቸንን እኔ የናተው አሳቢ እናም አሳዳጊ ከሆኑት አንደኛው ነኝ , እንዴት ናቸሁልኝ ት /ርቱስ እንዴት ነው መቼም ጎበዝ እንደሆናቸው ነው ከአቶ ደበበ የምንስማው እኛም የድሮ ራስብሩ ተማሪዎቸ እናም የአሁኑ አዶላ ወዩ ተማሪዎቸ የነበርን እናነተን ለመርዳት እላይ ታቸ እያልን እንገኛለን ..........እናተም በርቱልንን ..............

የግል ነኝደብዳቤ ከጋልጋሪ!

ውድ የአዶላ ልጆች ተማሪዎቻችን!!
እንደምን አላችሁልን? ሁሌም በሀሳብ ከናንተው ጋ ነንና በርቱልን::
ትልቅ ደረጃ ደርሳችሁ እንደምንያችሁ ተስፋችን ነው::
በተለይም በትምህርታችሁ ጎብዛችሁ የሚረዷችሁን ወንድምና
እህቶቻችሁን ጥሩ ደረጃ በመድረስ እንደምታስመስግኗቸው እምነት አለኝ::
በርቱ!! እግዚያብሄር ሁሌም ከናንተው ጋ ነው::

ቸር እንሰንብት!!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jan 07, 2013 4:21 pm

ሰላም ለዚህ የፍቅር ቤት ቤተሰቦች:-

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሣችሁ::


በአካል ለማላውቃችሁ በመንፈስ ግን አብሬያችሁ ላላችሁት የአዶላ (ወዩ) ሕፃናት:-

በተሠለፋችሁበት የትምህርት መስክ ጠንክራችሁ ከተማራችሁ ነገ ለእናንተ ብሩህ ቀን ይሆንላችኋል:: በርቱ እና ተማሩ:: እግዚአብሔር ያሠባችሁትን ያሣካላችሁ::

ወገናችሁ

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests