ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ኦዶ ሻኪሶ » Tue Jan 15, 2013 8:20 pm

አደቆርሳ wrote:
ነገርን ነገር ያነሳዋል አይደል የሚባለው አንዴ ክብረመንግሥት እኛ ጎረምሶች በምንባል ጊዜ ነው
አንትዬ ከበደ ገበያክፍል ኬላው ጋ ነበር የምትኖረው እሷጋ ደሞ መቃም ይቻላል ከዛ አንዱን ቀን እየቃምን ሳለ አንድ የሻኪሶ ልጅ እሁን አላስታውሰውም እየሮጠ ይመጣል አንትዬ አንትዬ እያለይገባና ተያይዘው ይወጣሉ ቆየት ብለው ሲመለስ አንትዬ አይኗም አፍንጫዋም በደስታ ሲፍነከነኩ አየሁ ሆኖም እስክትናገር ምንም ቃል አልወጣኝም እሷም ጸጥ አለች ::
ሀሳቧም ከኛ ተለየ ብቻዋን ሁሉ መሳቅ ይቃጣት ጀመር
በኋላ መጠበቅ ሲሰለቸኝ አንትዬ ምንድነው ልጁ የሆነ የምስራች ነግሮሻል ምንድነው ስላት አይ ምንም አይደለም አለችና ሲስተር ወልዳ ነው አለቺኝ
እንክዋን ደስ አለሽ ምናምን አልናት ነገሩ እውነት ቢመስልም እኔ ግን እንደሆነ ነገር አልተቀበልኳትም ::
ለመናገር እንዳልፈለገች ገባኝና በቃ ወደሻኪሶ መሄድ አለብኝ ስትል አብሬ ብድግ አልኩ::
ሌሎቹ ሲለዩ እኔ እስከከተማ ድረስ ተከትያት ሄድኩና አራዳ ስንደርስ ስሚ አንትዬ ሲስተርሽ ወልዳ አይመስለኝም አልኳት ሳቅ አለችና እንዴት ገመትክ ? በቃ ገባኝ
ባክህ የሆነ ነገር ተገኝቶ ነው
ምን ተገኘ
ቡችላ
ተው ባክህ ? ደነገጥኩ ይገርምሀል የሆነ ነገር እንደሆነ ሆዴ ነግሮኝ ነበር ለመሆኑ ማንነው ያገኘው
ጸጋዬ ግዛው
ትልቅ ነው ?
በጣም ትልቅ አሁን ሄጄ መካፈል አለብኝ
በቃ እኔም ልምጣሀ ?
እ እ አንተ ከመጣህማ ለምን አመጣኸው ይሉና ይደብቁኛል
ስለዚህ እኔ ከማገኘው ላይ አካፍልሀለሁ አንተ እዚሁ ሁን
በዚህ ተስማምተን አንትዬን ሸኝቼ ሌሊቱን ሙሉ ቁጭ ብዬ አደርኩ
ለእማማ ሶፋ ወንበር ስገዛላት ቤታችንን ጣውላ ሳስነጥፍ
ራንግለር ሱሪ ቆዳ ጫማ ስገዛ ለምወዳት ልጅ ስጦታ ስሰጥ ከዛሬ ወዲህ ቤታችን ባለኮርኒስ መሆኑን ለጣራው እየነገርኩት ሌሊቷ እንዲሁ ነጋች ::
ጥዋት ተነስቼ እነ አንትዬ ቤት ስሄድ አልመጣችም
ብጠብቅ ብጠብቅ ምንም ድምጽ የለም ምሳ ሰዓት አለፈ
ዝም ብዬ ወደከተማ ሄድኩና መኪና ተራ ከሻኪሶ የሚመጣ ሎንቺን ስጠብቅ ስንታየሁ ጎበናን ሲወርድ አገኘሁት የሆነ ነገር እንደምሰማ ተማምኜ ሰላም ካልኩት በኍላ ከተማ አይቶኝ ስለማያውቅ ምን ታረጋለህ ሲል ጠየቀኝ ምንም መልስ ስላልነበረኝ አንትዬን እየጠበቅኳት ነው አልኩት
ሳቅ እያለ ለምን ? አለኝ
አይ ትናንት ስትሄድ የቸርነትን ጫት አመጣለሁ ስላለች ምናምን .................... ቀበጣጠርኩለት
መሳቅ ጀመረ
እንዴ ምን አሳቀህ ?
አይ አንትዬን ስታነሳ የሆነ ነገር አሳቀኝ
ለምን ?
ትናንት እነጸጋዬ ሰሩላት
ምን ብለው
አፕሪል ዘፉል ............
ፉልል ያርግህ ያባቴ አምላክ አልኩትና በሆዴ በአንትዬ መሸወድ አስመስዬ ከት ብዬ ሳቅኩና እርር ባለው አንጀቴ ወደሰፈሬ ተመለስኩ
ሰፈር ስደርስ በተቻለኝ መጠን አንትዬን ሸወድኳት እያልኩ አስወራሁ::
ይህኔ አንትዬ ደሞ እኔንው አፕሪል ዘፉል ልታፎለኝ ስትሸርብ ቆይታ ማታላይ መጣችና አስፈለገቺኝ
ቀጥብዬ ሄድኩ
ወርቁ ተሸጦ ብሩን አምጥቻለሁ ላካፍልህ ነው
ኸረ ? ልታካፍዪኝ ነው እንዴ ለአቶ አፕሪል አካፍያቸው.......
እንዴ ማን ነገረህ ?
ትናንቱንም እኮ አውቄያለሁ መኪና ተራ ድረስ በሆዴ እየሳቅኩ ነበር የሸኘሁህ !


አደቆርሳሳሳሳ እጅ ወደላይ ..... ቁም ...... እንዳትነቃነቅ .... ዋ... ነቅነቅ ብትል ውርድ ከራስህ ነው ......................?
አሁን ተገኝተሀል ይቺን የዛሬ አመት የተጻፈች ታሪክ ይዤ ሻኪሶ አውጫጪኝ ሰብስበን ሲደረስብክ ከመሀል ፍትልክ ብለህ ልትጠፋ ስትል እጅ ከፉ ቅቅቅቅቅ ::
ኦ ማይ ጋድ today is my day
እኔጋ ድብቅ የለም ሴመ ወንድሙ ታሪኩን ሙሉ በሙሉ ነው የነገረኝ::
ረስተህ ነው መሰለኝ እነጸጋዬ ያልከው እንጂ ከሻኪሶ ወንድዬና መስፍን ሚደቅሳ ናቸው ተንኮሉን ባጋጣሚ ያሰቡትና ከዛም ተሳካላቸው::
በሀቁ ቦጋለ የሚባል ልጅ ብታስታውስ ጥሩ ነበር ዳሩ አንተ አታቀውም አይባልም እሱን በግሩ ክብረመንግሥት ባንክ ድረስ ልከው ያደረጉትንስ ታቃለህ ?
ወይ አደቆርሳ ????? አሁንም እንዳትነቃነቅ እጅ ወደላይ
ቁጭ በል ....ብድግ በል ....ተኛ ....ተንከባለል.... ተንበርከክ.. ......... መሳሪያው እንደተደገነብህ ነው ...... ለማምለጥ እንዳትሞክር ::
May God bless Adolla
ኦዶ ሻኪሶ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Fri Sep 22, 2006 12:24 pm
Location: adolla lagadembi

Postby አደቆርሳ » Wed Jan 16, 2013 10:31 pm

በሳቅ ፍርስስስ እያልኩም ቢሆን እጄን እንደሰቀልኩ ነኝ !
ኦዶ እንደምን አለህ እጅከፉ አልከኝ? ደስ የሚል አገላለጽ ነው ::
ሆኖም ይሄንን ያህል ካላሽ አስወድሮ መሬት ለመሬት የሚያንከባልል ምን አዲስ ነገር አግኝተህ እንደሆነ አልገባኝም::
ኦ ማይ ጋድ today is my day

ለምን ብዙ ደነቀህ ? ወይስ ሌላ እኔ ያልገባኝ ነገር ተገኘ ?
ለማንኛውም ይሄንን ልተወውና ወደጨዋታህ ልመለስ በሀቁ ቦጋለን አሳምሬ አውቀዋለሁ በተፈጥሮውም የማይረሳ ልጅ ነው ቁመቱና ነገረስራው ልዩ ልጅ ነው::
በሀቁ የተለየ ባህርይው በትንሹም በትልቁም መሳቅ መውደዱ ነው አንዳንዴ የማያስቅ ነገር ሁሉ እሱን ልቡ እስኪጠፋ ያስቀዋል::
እንደውም እናቱ የመንግሥት ሠራተኛ ስለነበረች በኛ የልጅነት ጊዜ የተማረ እናት ያለውና እኩያችን የሆነ ብዙም አላውቅም ነበር:
ፋሲል አገኘሁን እና አቡዬ (እርዳቸው በተላን) በዚህ አጋጣሚ አስታወስኳቸው::
አቡዬ ከዚህ ዓለም ከተሰናበተ ቆየት ብሏል ፋሲል ግን ባንገናኝም እዚሁ አለ ::
ታዲያ በሀቁን ማንሳትህ ለምን እንደነበር ምንም አላልክምሳ ? እኔም አውቀዋለሁ ከማለት በቀር ምንም ማለት አልቻልኩም ለማለት ነው::
እነጸጋዬ ማለቴ ረስቼ ሳይሆን እንዳንተ ያለ አውጫጪኝ ሰብሳቢ እጅ ከፉ እንዳይለኝ ፈርቼ ሳይሆን ይቀራል ?
በነገራችን ላይ ወንድዬ አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት መዛወሩን ከሰማሁ ቆየሁ መስፍን ያው ውጪ ነው መቼ ነው ብቻ መጥቶ እንደነበር ሰምቻለሁ ::
አንተ ግን አሁን የት ነህ ? በፊት በፊት ውጪ እንዳለህ አውቅ ነበር አሁን ግን ከሻኪሶ እግሬን አልነቅልም ያልክ ነው የምትመስለው ::
ማን እንደናት ማን እንዳገር
የት ይገኛል ምሰሶና ማገር ....እንዳለ ዘፋኙ
ዞሮዞሮ ከቤት
ኖሮ ኖሮ ከመሬት .... ይላል ደሞ ያገራችን ሠው
ሁሉም እውነተኛ አባባል ነው::
በዓለም ላይ ብዙ ሀገሮች ውስጥ እውነት የሆነ ነገር እንደተረት ይነገራል በሀገራችንም ዘመን ከሚጥላቸው አንዳንድ ክብረ ነክ አባባሎች ውጪ ብዙ ቁምነገር እና እውነት መስካሪ ተረቶች አሉን::
እስቲ ብቅ በልና ካንከባለልከኝ አፈር ላይ አንሳኝ ለአንድ ከንቱ ወረኛ መሳሪያ መደገን አያስፈልግህም ኑሮ ያደከመው ሰውነት መንከባለል አይችልምና ይልቁንም እጄን ይዘህ ቀና አድርገኝ ::

ቸር ያቆየን ወዳጅህ አደቆርሳ

ቆይማ ያ ! ጥሩ የት ሄደ እባካችሁ ?
አንተ ጥሩ እባክህ ብቅ በልና ድምጥህን አሰማኝ ባክህ !
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby ሞፊቲ » Sat Jan 19, 2013 7:11 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ኦዶና አደቆርሳ የጀመራችሁት ጨወታ ምቾት ሰቶኝ ነበር ::አንድ ሁለት ትባባላላችሁ ብዬ ብጠብቅም
""ኤቤሉን ጩሉቴ "" ብላችሁ ጠፋችሁ :በተለይ ኦዶ ) አደቆርሳ ና እንሟከር እያለህ ምነው ፈራህ ?

ሰሞኑን እንግዲህ በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፈውን ብሄራዊ ቡድናችንን ለማየት በመታደላችንና ለዚህ በመብቃታችን
ከደስታችን ብዛት መረት ጠባናለች :;በኔ እድሜ ሀገሬ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፋ ስትሳተፍ የማየት እድሉን ሳገኝ
ይህ የመጀመርያዬም በመሆኑ መታደል ሆኖብኛል ::
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጨወታውን እንደማያስተላልፍ ፍርሀት ብለቅብንም

ይሄ ነገር ሲውል ሲያድር አንድ ቀን እንደሚያስጠይቀን ያስታውቅ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የቤኒን አቻውን ከሜዳው ወጪ ሲገጥም ጨዋታው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈበት መንገድ ሕጋዊ መስመርን ያልተከተለ ነበር፡፡ የአዲስ አበባው ጣቢያ LC 2 ከተባለ የፈረንሳይ አስተላላፊ ድርጅት ላይ የወሰደውን የቀጥታ ሥርጭት ክፍያ ሳይፈፅም ለሀገር ውስጥ እና ባህር ማዶ ተመልካቾቹ መልቀቁ ይታወሳል፡፡ ኤቲቪ የኦምዱርማኑንም ጨዋታ በተመሳሳይ መንገድ ለማስተላለፍ ሙከራ ያደረገ ሲሆን በቴክኒካዊ እክሎች የተነሳ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ በአህጉሪቱ የሚገኙ አንዳንድ ጣቢያዎች ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ የጣቢያውን ሥርጭት እንደሚያስተላልፉ የተረዳው LC 2 ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገሮች ተገቢውን ክፍያ ካልፈፀሙ ደንበኞቻቸው የአፍሪካን ዋንጫ በብሔራዊ ቴሌቪዥኖቻቸው በኩል እንደማያገኙ ጠበቅ ያለ ማሳሰቢያ አውጥቷል፡፡ የሰሞኑ የኤቲቪ ክፍያ ካላገኘሁ የቀጥታ ሥርጭት አይኖረኝም ማቅማማት ከዚህ የመጣ ነው፡፡ እስካሁን እዚህ ግባ በማይባል ክፍያ የሚገኙ የዓለም እና የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ከፍተኛ የስፖንሰርሺፕ ክፍያ እየተጠየቀባቸው በብሔራዊው ጣቢያ ሲለቀቁ ኖረዋል፡፡ ዛሬ ነገሩ ወደ ብርሃን ሲወጣ በወሳኝ ሰዓት የዋልያዎቹ በኤቲቪ መታየት አጣብቂኝ ውስጥ ገባ፡፡ እንደ ኬፕ ቬርዴ ያሉት የኩባንያውን ማሳሰቢያ ተቀብለው የሕዝባቸውን የኳስ ጥም ለማርካት ተነስተዋል፡፡ ኤቲቪስ ?
http://www.ventures-africa.com/2013/01/ ... afcon-2013 ኤርምያስ አማረ
/
ጨወታውን የምናገኝበትን መስመር አዘጋጅተን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን::

እንግዲህ እንደተለመደው ጨወታው ከመጀመሩ በፊትና ዛሬ ስለሚኖረው የምክፈቻ ስነስራት እንዲሁም የተለያዩ ጆሮ ገብ የሆኑ ዜናዎችን ይዘን ቤታችንን ሞቅ ደመቅ
እንደምናረገው ተስፋው አለ!!
ድል ለብሄራዊ ቡድናችን!!

ቸር እንሰንብት!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ሞፊቲ » Sat Jan 19, 2013 6:59 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን;;

የምክፈቻው ጨወታ አሁን ተጠናቀቀ::

ደቡብ አፍሪካ ከግምት ውጪ በሆነና በወረደ ጨወታ በደጋፊዋ ፊት ከኬቨርዲ ጋ 0ለ0 ወታለች::
ዘርዘር ያለውን ወሬ እመለስበታለሁ::መልካም ቅዳሜ!!!

ቸር እንሰንብት!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ኦዶ ሻኪሶ » Sat Jan 19, 2013 8:05 pm

ኽረ ጩለቴ ? ዛሬ ማየቴ ነው ሞፊቲኮ ጠፍቼ አደለም::
ስማ አደቆርሳ ለምን ብዙ ደነቀህ ማለት ምን ማለት ነው ?
በግል የተጻጻፍናቸውን እዚ መለጠፍ አለብኝ እንዴ ?
ወዪስ ነገሩ አናደደህ ?
አይዞህ እጅ ከፉ የምትባለውኮ ስትታወቅ ነው አብረው የፈሱት አይሸትም ሲባል ውነት መሰለህ እንዴ እሱ ተረት ነው::
የተናደድከው እንድተወው ስለፈለክ መስሎኝ ተውኩት ግን ዱላ ቀረሽ ከምትወርድብኝ ስቀህ ብታልፈው ጥሩ ነበር ::
ካንተ የያዘኝ ፍቅር ስላለቀቀኝ ቁጣውን ተቀብዬ ጭጭ እላለሁ ::
በል አሁን ተነስና አዋራህን አራግፍ ::
በሀቁን እንደምታቀው እየተጠራጠርኩ ነበር ምክንያቱም ራስብሩ ትርምሯል የናንተ አካባቢ እድመ ስላልመሰለኝ ነው::
እኩያችን ማለት እስካረጋግጥ ድረስ እየገረመኝ ነው ::
ምክኒያቱም መልክቱን ይዞ የመጣው እሱ ነው ያው እሱንም ካውጫጪኝ ለመሸሽ ነው የዘለልከው ማለት ነው::
አገሬ አንድ ሁለቴ ብቅ አልኩና እግሩን አይነቅልም ትላለህ ሚካኤል ቢረዳኝ እዛው እግሬን ተክዬ መቅረት ይሻለኛል::
አንዳንድ ልጆች ብቅ እያሉ ነው የማነም አሁን እዛ ነው ያለው ::
ባለፈው የጻፍኩልህ የለገደምቢ ወርቅ ማምረቻ የሚጠቀምበት መርዘኛ የኬሚካል ዝቃጭ በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚያረገውን አሳዛኝ ችግር በሚመለከት ነበር::
ይህንን ጉዳይ ሁላችንም አውቀን አንድ ነገር ማረግ አለብን ::
መንግሥት ከድርጅቱ የሚያገኘው ገቢ ካለም ቀጥታ ቦታው ላይ ይዋል ከለለም ድርጅቱ አስቾካይ መፍትሄ ያምጣ ::
በዛ ቦታ ያሉ ሰዎች እየታመሙ የሚሞቱት በወባና ኤድስ የሚሳበበው ለምንድነው ?
አካባቢውም ወደፊት ምንም የማያበቅል መርዝማ አፈር ነው ሚሆነው ::
እኛ ነን መጮህ ያለብን እና ይሄንን ሀሳብ እዚ እንደማመጣው ካንዳንድ ልጆች ጋ ተነጋግሬ ነው ::
ባካችሁ ሁላችንም ለመፍትሄ እንነሳ::
አንዱ ልማት አንዱን ማጥፋት የለበትም::

ሞፊቲኮ የሳውዝ አፍሪካ ቡድን 0 ተስፋ ነው ያለው
ድንገት ድንጋጤ ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ እኔ ግን ሶዳቴ ብያለው::
May God bless Adolla
ኦዶ ሻኪሶ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Fri Sep 22, 2006 12:24 pm
Location: adolla lagadembi

Postby ሞፊቲ » Mon Jan 21, 2013 6:01 pm

ስላም ሰላም

ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ..... አሁን ገና ተነፈስኩ! ብሄራዊ ቡድናችን ኩራታችንን ጨምሯል::
የዛምብያን ቡድን ተቋቁሞ 1 ለ 1 ከመውጣቱም ባሻገር ሳላሀዲን ያገኘውን ፔናሊቲ ተጠቅመንበት ቢሆን ኖሮ
አሸናፊነታችን በጅ ይል ነበር::
የሚገርመው በ10 ልጅ የተጫወተው ቡድናችን ይህን ሁጤት ይዞ መውጣቱ ብቻ ሳይሆን የተሻለ ሙከራም ለማድረግ
የተንቀሳቀሰበትና በመጨረሻም ሁጤቱን አስጠብቆ ለመውጣት ያደረገው ተጋድሎ ነው!!!!!!
ድል ድል ድል ለብሄራዊ ቡድናችን!!!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ባለሱቅ » Mon Jan 21, 2013 9:09 pm

ከተደበቅኩበት ገጠር
ዛሬ የብሄራዊ ቡድናችንን ጨዋታ ለማየት መጥቼ
ደስታዬን ልገልፅ ብቅ ስል ሞፍቲ ቀድሞኝ ጠበቀኝ
እጅግ በጣም ደስስስስስስስስስስ ብሎኛል
ከዚህ በኃላ ቢያሸንፉ... ባያሸንፉ.... እንደዛሬው ስሜቴን የሚነኩ አይመስለኝም
እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ እኔን
ደስ ያላቹ ሁሉ... እንኳን አብሮ ደስ ያለን
ደስ ያያላቹ ደሞ... ደስታን ጨም,ሮ ይስጣቹ..... ውይ ለካስ ላለው ይጨመርለታል ነው ያለው መጣፉ
እንደፍጥርጥራቹ
................................//.................................
ሰላም ያገሬ ልጆች
ኦዶ-ሻኪሶ..... ብራቮ ብያለሁ
አደቆርሳን,.... ሳይዘጋጅ... እጅ ወደላይ ስላልከው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ያለው ሁሉ ገብቶኛል...... ፕሊስ እስኪ ለኔም ሹክ በለኝ ያንን እጅ ወደላይ ያልክበትን ጠመንጃ.... እኔም እንዳንተ.... እንዳንበረክከው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ስላምታዬ ለሁላቹም ይድረስልኝ

ቪያ ወደ-ገጠሪቷ አፍሪካ
እስክመለስ
ሰላም ቆዩኝ
በፍቅር
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby ራስብሩ » Tue Jan 22, 2013 1:31 am

ጤና ይስጥልኝ
ዛሬ ለኔም የደስታ ቀን ነው::
ቡድኑ ከሆቴሉ ወደ ስታዲየም ሲያመሩ ይመስለኛል በጉዞ ላይ ለጋዜጠኛው ሰጥተውት ከነበረው አስተያየት ሳላዲን ሰይድ የተናገረው ገና ከጨዋታው በፊት ደስታ ፈጥሮብኝ ነበር የቆየው::
((እኔ በብሄራዊ ቡድን ውስጥ እስከዛሬ በነበረኝ የጨዋታ ዘመን እንደዚህ ያለ አንድነት ስምምነትና መደጋገፍ ተፈጥሮም ኖሮም አይቼ አላውቅም ይህም በራሱ ለውጤት የሚያበቃ ነው::
ዛምቢያውያን ያለፈውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሱ ቢሆንም ዘንድሮ አቋማቸው ወርዷል እኛም በቂና ጥሩ ልምምድ ስላደረግን አሸንፈን እንወጣለን !!!))
እንደዚህ ያለ አስተያየት ነበር የሰጠው
እያንዳንዱ እንቅስቃሴና የኳስ ቁጥጥር ለቦታው በቂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ::
የበረኛው የጀማል ጣሰው ስህተት ሳላዲን ከመከነችበት ኳስ በላይ ቆጭቶኛል::
በኢትዮጵያ በብሄራዊ ፉትቦል ታሪክ ውስጥ እንደዛሬ ተደስቼ አላውቅም ::
በጨዋታ ላይ በነበረው የቡድናችን እንቅስቃሴ አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ለካ ኢትዮጵያ ያጣችው ተጫዋች አልነበረም ? የሚል ነው::
ምናልባትም ችግሩ እንዲወገድ የዛሬው የደቡብ አፍሪካ ውሎ ግሩም መነሻ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ::
የዛሬ ስንት ዓመት ነበር ? ሀገራችን የምስራቅና መካከለኛውን አፍሪካ ዋንጫ ከዚምባብዌ ጋር ተፋልማ ያስቀረች ግዜ
የነበረው የደስታ ስሜት የሚረሳኝ ባይሆንም የዛሬው ሁኔታ ከግምቴ ውጪ ስለነበረም ጭምር ደስታዬን እጥፍ አድርጎታል::
ብዙ ጊዜ ስለ አትሌቲክስ ስናወራ የጀርመን ኮሜንታተሮች የሚናገሩት መስማት እንደሚያደስተኝ እነግራችሁ ነበር ዛሬ ደሞ በፉት ቦሉ ሜዳ ውስጥ
ሲናገሩት የነበረውም እንደዚያው አስደሳች ስሜትን ይፈጥር ነበር::
ልጆቹ ድል ለማግኘት የሚያደርጉት ተጋድሎ ከልባቸው መሆኑና የችሎታቸውን ሲጫወቱ ማየታችን ሞፊቲ እንዳልከው ከደስታ አልፎ ኩራታችን ነው::
ወደፊትም በፉትቦሉ ተስፋችን እንዲለመልም ሆነናል::
ጨዋታውን የተመለከትኩት ስራላይ ሆኜ ነበር በኍላ ግን ስራ እስከማቆም ድረስ ደረስኩ::
ከአዳነ ግርማ በኍላ ከዚህ ትልቅ ድል ጋር የማይረሳውና ታሪክ የሠራው በስታዲየሙ የተገኘው የኢትዮጵያ ቡድን ደጋፊ ነው
የቴሌቪዥን ጋዜጠኞችንም እስከሚያስገርም ድረስ ነበር ድጋፋቸው በውነት በዚህም ረገድ ትልቅ ደስታ ፈጥሮብኛል::
አሁንም ድል ለብሄራዊ ቡድናችን ይሁን !!!
ራስብሩ ወልደገብርዔል
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 22, 2013 4:20 am

ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ቤተሰቦች:-

የዛሬውን ደስታዬን ከእናንተ ጋር ሣልጋራ ብቀር አምላካችሁ ያዬኛል::

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቀድሞዎቹ የሚለየው በምን ይመስላችኋል? በእኔ ግምገማ ከመሐል ወደ አጥቂዎች የሚላኩት ኳሶች እንደ ድሮው ብዙ አይባክኑም:- የአሁን አጥቂዎች ወይ ጎል ያገባሉ : አልያም ቢያንስ ጥሩ የጎል ሙከራ ያደርጋሉ:: ስለዚህ ይህ ቡድን በሚቀጥለው አርብ 'ከጭንቅት አልባው' የቡርኪና ፋሶ ቡድን ጋር ቢያንስ አቻ ከወጣ ጉረኞችን ናይጄሪያውያን መሣቂያ አድርጎ ለሩብ ፍፃሜ እንደሚያልፍ መገመት አይከብድም::

መልካም ዕድል ለጥቁር አንበሣው ቡድናችን::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ጌታ » Tue Jan 22, 2013 7:27 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ቤተሰቦች:-

የዛሬውን ደስታዬን ከእናንተ ጋር ሣልጋራ ብቀር አምላካችሁ ያዬኛል::

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቀድሞዎቹ የሚለየው በምን ይመስላችኋል? በእኔ ግምገማ ከመሐል ወደ አጥቂዎች የሚላኩት ኳሶች እንደ ድሮው ብዙ አይባክኑም:- የአሁን አጥቂዎች ወይ ጎል ያገባሉ : አልያም ቢያንስ ጥሩ የጎል ሙከራ ያደርጋሉ:: ስለዚህ ይህ ቡድን በሚቀጥለው አርብ 'ከጭንቅት አልባው' የቡርኪና ፋሶ ቡድን ጋር ቢያንስ አቻ ከወጣ ጉረኞችን ናይጄሪያውያን መሣቂያ አድርጎ ለሩብ ፍፃሜ እንደሚያልፍ መገመት አይከብድም::

መልካም ዕድል ለጥቁር አንበሣው ቡድናችን::

ተድላ


ያኔ የጃ ሉድን የእርግብ አሞራ አብረን እናዜማለን :D
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሞፊቲ » Sun Jan 27, 2013 3:05 am

ሙከራ ..ሙከራ...ሙከራ..1 2 3 3 2 1....
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ሞፊቲ » Sun Jan 27, 2013 3:19 am

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ዋርካ ሰሞኑን ቅዠት በቅዥት ሆና ስለሰነበትች መገናኘት አልቻልንም::

ብሄራዊ ቡድናችን የገጠመው ሽንፈት ያልተጠበቀ ቢሆንም በራሴ በኩል ምንም ይሁን ምንም ልጆቹ ለዚህ መድረክ
ከ 31 አመት በኌላ ስላበቁን ምስጋናዬ እንደተጠበቀ ነው::

በአርቡ ጨወታ እስከ 20 ደቂቃ ድረስ ልጆቻችን ተርብ ሆነው ከባድ የማጥቃት እንቅስቃሴ በማሳያታቸው
ቡርኪናዎች ኳስ ማግኘት እንኳ ተስኗቸው ታይተዋል::በኛ በኩል የ አዳነ ግርማ በጉዳት መውጣትን ተከትሎ የመ
ጀምርያዋ ጎል ስትገባ ቡድናችን ከባድ የስነልቦና ችግር ውስጥ ገብቶ ሊያደርጉ የሚገባቸውን የጨወታው ዲሲፒሊኖች ማድረግ ሳይችሎ ከፍተኛ ሽንፈት ደርሶባቸዋል::
ምንም ምክንያት ሳይሰጥ በ10 ልጆች የተጫወቱት ቡርኪናዎች በልጠውን አሸንፈውናል::

በሚቀጥለው ከናይጄርያ ጋር በምናደርገው የመጨረሻ ጨወታ የማለፍ እድላችን ስላልተሟጠጠ ጥሩ ተጭውተን ብዙም
የማያስፈራውን ናይጄርያን አሸንፈን በውድድሩ እንድንቆይ ጸሎቴ ነው::ይህ ካልሆነም ጥሩ በመጫወት
እስከዚህ ላበቁን ልጆቻችን ምስጋናችንንና አክብሮታችንን በመስጠት እንደምናስታውሳቸው አስባለሁ::

ድል ለብሄራዊ ቡድናችን::

ቸር እንሰንብት!!!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jan 27, 2013 5:33 am

ሰላም ለዚህ የፍቅር ቤት ቤተሰቦች:-

ሰላም ሞፊቲ:-

አይዞን! "ከ31 ዓመታት በኋላ' እያልክ ለስንፍናችን ምክንያት አትደርድር:: አሁን ለፍፃሜ ጨዋታ አልፈዋል : አልፈዋል:: በቃ :!: ባለፈ ታሪክ ቢሆን ኖሮ 7 ጊዜ ዋንጫውን የበላው የግብፅ ቡድን : እስከ ዛሬ ሁለት ዓመት ድረስ ኃያል የነበረው የግብፅ ቡድን : በ2012ቱ ዋንጫ በእነ ሴራሊዮን እና በዘንድሮው የፍፃሜ ውድድር ለመድረስ የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፑብሊክን ማሸነፍ አቅቶት መንገድ ላይ አይቀርም ነበር:: ስለዚህ አሁን የምንፈልገው ያለፈ ታሪክ ሣይሆን አዲስ ታሪክ መሥራት ነው::

ልጆቹ የሥነ-ልቦና ውጥረት ከሌለባቸው በስተቀረ ናይጄሪያን ማሸነፍ አይከብዳቸውም:: ቁም ነገሩ በምን ሥሌት ለሩብ ፍፃሜ ያልፋሉ ነው:: የእኛ ቡድን ለማለፍ እኛ ናይጄሪያን ማሸነፍ ብቻ ሣይሆን ቡርኪና ፋሶ ዛምቢያን ማሸነፍ ወይም ቢያንስ እኩል መውጣት አለበት::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ሞፊቲ » Sun Jan 27, 2013 8:03 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ለዚህ የፍቅር ቤት ቤተሰቦች:-

ሰላም ሞፊቲ:-

አይዞን! "ከ31 ዓመታት በኋላ' እያልክ ለስንፍናችን ምክንያት አትደርድር:: አሁን ለፍፃሜ ጨዋታ አልፈዋል : አልፈዋል:: በቃ :!: ባለፈ ታሪክ ቢሆን ኖሮ 7 ጊዜ ዋንጫውን የበላው የግብፅ ቡድን : እስከ ዛሬ ሁለት ዓመት ድረስ ኃያል የነበረው የግብፅ ቡድን : በ2012ቱ ዋንጫ በእነ ሴራሊዮን እና በዘንድሮው የፍፃሜ ውድድር ለመድረስ የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፑብሊክን ማሸነፍ አቅቶት መንገድ ላይ አይቀርም ነበር:: ስለዚህ አሁን የምንፈልገው ያለፈ ታሪክ ሣይሆን አዲስ ታሪክ መሥራት ነው::

ልጆቹ የሥነ-ልቦና ውጥረት ከሌለባቸው በስተቀረ ናይጄሪያን ማሸነፍ አይከብዳቸውም:: ቁም ነገሩ በምን ሥሌት ለሩብ ፍፃሜ ያልፋሉ ነው:: የእኛ ቡድን ለማለፍ እኛ ናይጄሪያን ማሸነፍ ብቻ ሣይሆን ቡርኪና ፋሶ ዛምቢያን ማሸነፍ ወይም ቢያንስ እኩል መውጣት አለበት::

ተድላ


ተድልሽ= እንዳልከው የኢትዮጵያ የማለፍ እድል የሚወሰነው ቡርኪና ዛምብያን ማሸነፍ ና እኛም ናይጄርያን
ማሸነፍ ግድ ይሆንብናል::
እንግዲህ ሊሆን የሚችለው ነገር ያለፈውን ነገር ና ስህተት በማየት ከናይጄርያ ጋ ጠንክሮ መገኘት ነው::

መልካም እድል ይግጠመን!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby ሞፊቲ » Sun Jan 27, 2013 11:14 pm

ሰላም ሰላም

Ermias M Amare
Rustenburg – A town of Rest
የማክሰኞ ተጋጣሚዎች ተያይዘው በአንድ አውሮፕላን ረስተንበርግ ገብተዋል፡፡ ከሞምቤላ የተነሱት ዛሬ ረፋድ ላይ ነበር፡፡ ጥቋቁር አናብስቱ ሳቫና በተባለ ሆቴል ያረፉ ሲሆን አመሻሽ ላይ ልምምዳቸውን ሠርተዋል፡፡ የናይጄሪያ ተጫዋቾች የሞምቤላን ሜዳ ክፉኛ ወቅሰዋል፡፡ የእኛ ልጆች ደግሞ ከአዲስ አበባ ስቴዲየም ጋር ሲያስተያዩት ነው መሰለኝ አወድሰውታል፡፡ በናይጄሪያዎች አስተያየት የማንዴላ ሀገር ሰዎች አልተደሰቱም፡፡ እ.ኤአ በ1996 ሁለቱ ሀገሮች ተወዛግበው ናይጄሪያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሳይመጣ መቅረቱ ይታወሳል፡፡ አሁንም ባገኙት አጋጣሚ አንዱ ሌላውን መተንኮሱን አላቆመም፡፡ “ቡርኪናዎች ተመችቷቸው አራት አገቡ፤ ኢትዮጵያም ጥሩ ፉትቦል ተጫወተች፤ ፕሮፌሽናል ነን የሚሉት ናይጄሪያዎች ግን ሜዳውን ተቹ” ሲሉ በርካታ ደቡብ አፍሪካዊያን በድረ ገፆች የንሥሮቹን አባላት ወርፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያረፈበት ሆቴል በቱሪስቶች የተጨናነቀ ነው፡፡ በዛሬው ልምምድ አሥራት እና አዳነ አልተሳተፉም፡፡ እንደ ሐኪሞች ግምት ሁለቱም ለማክሰኞው ጨዋታ አይደርሱም፡፡ ይህን ተከትሎ በአሰላለፍ ላይ ለውጥ ይኖራል፡፡ አበባው፣ ሲሳይ እና ዩሱፍ በቋሚ አሥራ አንድ ውስጥ የመካተት ዕድል ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ለማንኛውም ነገ ረፋድ ላይ ጨዋታው በሚካሄድበት ሮያል ባፎኬንግ ስቴዲየም ሁለቱ ቡድኖች “ለፕሪ ማች ሚቲንግ” ይገናኛሉ፡፡ ነገ ከሰዓት ማን በቋሚ አሥራ አንድ ውስጥ እንደሚካተት ፍንጭ ይገኛል፡፡ የማክሰኞውን የዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ ጨዋታ ካሜሩናዊው አሊዮም ይመራዋል፡፡ የናይጄሪያ እና የኢትዮጵያን ደግሞ ለሞሮኮው ኤል አህራክ ተሰጥቶታል፡፡ ወይኔ አሊዮም ለትንሽ አመለጠን!

ጨዋታው የሚካሄድበት ሜዳ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሳልሃዲን ጎል ከደቡብ አፍሪካ ጋር 1-1 የተለያየችበት ነው፡፡ ይህ ስቴዲየም ለ2010 ዓለም ዋንጫ የማሻሻያ ዕድሳት ተደርጎለታል፡፡ በሰሜን ምዕራብ ክፍለ ሀገር የምትገኘው ረስተንበርግ ከጆሃንበስርግ በ132 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከገዢዎቹ ደቾች ተገልብጦ አፍሪካንስ በሚል መጠሪያ ስሙን ብቻ ቀይሮ ለሀገሬው ሰዎች በግድ በተሰጠው ቋንቋ “የዕረፍት ከተማ” የሚል ትርጉምም ይዛለች፡፡ ማነው ወደ ዕረፍት የሚገባው?


ኤርሚ ለዘገባው አመሰግናለሁ::
መልካም እድል!!
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests