ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ሞፊቲ » Tue Jan 29, 2013 8:46 pm

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን::

ብሄራዊ ቡድናችንን ዛሬ ተሰናብተናል!!
እግር ኳስ ማለት ስህተት ማለት ነው::በተቃራኒው ቡድን ላይ ስህተት እንዲፈጠር በማድረግ ሁጤት ማግኘት ማለት ነው::
ቡድናችን ዛሬ ናይጄርያን ተቋቁሞ ድንቅ ጨወታ አሳይቶን ነበር::

ግሩም ግሩም የሆኑ የጎል እድሎችና ሙከራዎችንም አድርገዋል::በቡርኪናው ላይ ያየሁት ቡድን ስጋት ውስጥ
ከቶኝ ስለነበር ዛሬም ፍራቻው ነበረኝ::የመጀመርያው አስር ደቂቃም አስፈሪ ነበር::የናይጄርያን እንቅስቃሴ ወድያው በመረዳት ልጆቻችን
ወደ ማጥቃት እንቅስቃሴ ገብተው ተስፋ ጭረውብን ነበር::ባንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ስፖርት የፍቅር መንደር እንደሆነ
ላሳያችሁን ውድ ልጆቻችን ምስጋናዬ ይድረሳችሁ::

Ermias M Amare
አላዘንኩም! ይህ በዚህ ሰዓት የሚሰማኝ ስሜት ነው፡፡ ሃያ ዘጠነኛው የአፍሪካ ዋንጫ ትርፉ ስላመዘነብኝ በቡድናችን ውጤት አልተከፋሁም፡፡ እግር ኳሱ መሠረት ሳይኖረው በእናንተ ጥረት እዚህ ደርሰናል፡፡ ከወራት ለበለጠ ጊዜ ይበልጥ ወደ ባንዲራው ስላቀረባችሁን፤ ባንዲራውንም በስፖርት አደባባዮች ስላሰቀላችሁልን እስከ ወዲያኛው ስንዘክራችሁ እንኖራለን፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ እንወዳችኋለን! እናከብራችኋለን!


ኤርሚ የባለሙያ ትንተናህን ሰሞኑን መኮምኮም ነው :;
ሞፊቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 837
Joined: Thu Dec 15, 2005 9:18 pm

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed Mar 20, 2013 8:01 pm

http://youtu.be/WTMZyphw4YM

ሰላም ለናንተ ይሁን ወገኖች; ባዶ እጀን ብቅ እንዳልል ብየ ነው:: ለመሆኑ ሁላጩም ሰላም ናችሁ?
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ባለሱቅ » Fri Mar 22, 2013 2:12 pm

አቤትትትትትትትትትትትትትትት

ዋርካ እንዴት አስቸጋሪ ልጅ ሆኖዋል ባካቹ.........

እንደምን አላቹ ያገሬ ልጆች

ስትናፍቁቁቁቁቁቁ.... ኡ ኡ ኡ ኡ

ከጃኒዋሪ (ሞፍቲ ከሞጫጨረው መልክት ይመለከቷል) ጀምሮ ይህንን ቤት የጎበኘ ሰው እንደሌለ ሳይ...... ምን ነካብኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝ ወንድሞቼን ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል

እውነት ግን ምን ነካቹ ጃል!

እኔ አልሀምዱሊላሂ ሰላም ነኝ..... ኔትዎርክ እና ዋርካ ተጫውተውብኝ.... ነፍሴም ባተሌ ሆና ባጅታ
\ህምምምምምምምምምምምም

ጃሚቲ አንቺ ቀበሮ.... ከየት ተገኘሽ ባክሽ....

የሰው ልብ በሰላም ተቀብለሽ ስታበቂ..... በትርፍ መቸርቸር ጀምረሻል የሚባል ወሬ ሰምቼ!.................
እውነት ነው ግን?

ለማንኛውም ተመልሰናል.... ካላቹ
አለን በሉ
ከሌላቹም ደሞ
ያላቹበትን አሳውቁንና.... መጥተን እንያቹ

እስክንገናኝ ሰላሙን ሁሉ ባላቹበት አብዝቶ ይስጥልን

አሚን

ሰላም ሁኑልኝ

የጥንቱ ዲታ
አሁን የከሰረው
ባለስቅ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby Gosa » Fri Jun 14, 2013 7:00 am

ያቺኑ ሳይበር-ኢትዮጵያን የሙጢን ብል የሚሻል መስሎኛል እንደ....ጎሳ

የሚያናድደው ግን ሳይበር ውስጥ መግባትም አልቻልኩም....
ጎሳ በዚህ እንደምትተባበረኝ አምናለሁ

እዚህ ጭር ያለ ቤት ውስጥ የምለጥፈውን ዝባዝንኬ... ወስደህ ሳይበር ላይ ልጥፍ ብታደርግልኝ ደስታውን አልችለውም
ምክንያቱም አንባቢ አላጣም ብዬ ነው እዛ ቤት ውስጥ
ምን ይመስልሃል???

ባለሱቅ ነበር ከላይ ያለውን ሌላ ፎረም የጻፈው:: ባለሱቃችን የዚህ ቤት የመሰረት ድንጋይ ነው ብንል መሳደባችን እንዳልሆነ ይታወቅልን ቅቅቅ:: ብዙዎቻችሁ ጽሁፉን እንደምትናፍቁ ስለማውቅ እኔም በደስታ በሀሳቡ ተስማምቼ ለእናንተ ለአድናቂዎቹ ግሩም ጽሁፉን አምጥቼላችኌለሁ:: በዚያውም የተዘጋውን ቤት ከመጠነኛ እድሳት ጋር መክፈታችንን ስንገልጽ በደስታ ነው::

እንደምን አላቹልኝ
ስለስደት ስታነሱ እኔም ያለኝን ልጣል ብዬ መጣሁና

ሳስበው ግን
እኔ ስለስደት ብናገር ያምርብኛል ወይ... ብዬ አቅማማሁ... እራሴንም ጠየኩት
ልምን ብትሉ
ተሰድጄ አላውቅማ!
... አቤ......ት .. ጉራ... ሲሉ ሰማሁዋቸው..... ጎሳ እና አደቆርሳ

ያው እንግዲህ ተሯሯጡብኝ በብዕራቹ
....................//...........
እናላቹ ምን ልላቹ ፈልጌ መሰላቹ
ስደት
አዎን ስደት... የሃገራችን ስደት... ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ እንደመጣ ነው ሚሰማኝ አሁን አሁን
ቲፒንግ ፖይንት (Tipping Point) ሲባል ሰምታቹ ይሆን.....
አንድ አዲስ ነገር (ለምሳሌ ፋሽን ቀሚስ/ጫማ/ምርጥ ዘር/ማዳበሪያ/አይ-ፓድ/ስደት/)ይመረትና ለገበያ ይቀርባል (ስደት ምርት ነው እንዴ እንዳትሉኝ ብቻ)
የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች... ሪስክ-ቴከር... ወይም አዲስ ነገር ለመሞከር የፈጠኑት ሰዎች ብቻ ይሆናሉ...
እንግዲህ ይህ አዲስ የተፈጠረ ነገር ቀስ እያለ ቀስ እያለ... ይስፋፋና.... የሆነች ቦታ ላይ ሲደርስ (ጃፓኖቹ 10% ሲደርስ ይላሉ... ስለሃገራቸው ገበያ ሲናገሩ).... መመለሻ የለውም.... ጉዳቱ ኖሮት ጉዳቱ መነገር ቢጀምር እንኳን መመለሻ የለውም....
የሚጠፋውና የሚቀዘቅዘው... ሌላ አዲስ ከዚህ የበለጠ ነገር እንደገና ወደ-ገበያ ሲቀርብ ነው.... ይላሉ... ተመራማሪዎች
እንግዲህ ለስደታችን መዳኒቱ... ሰውን እንዳይሰደድ የሚያደር አዲስ ነገር መፍጠር በሃገር ውስጥ... ሊሆን ነው ማለት ነው?
እንዴት ያለ ነገር ቢሉ..... ማንም የሚጠፋው ያለ አይመስለኝም
አሁን ግን ስደት ሱስ ሆኖዋል በሃገራችን... ቲፒንግ ፖይንቱን ስላለፈ

ምን ገጠመኝ መሰላቹ ባለፈው ለአዲስ አመት ኢትዮጵያ የሄድኩ ጊዜ
አዲሱን አመት ያሳለፍኩት ሸዋ ሮቢት ነው ብያቹ አልነበር.... እስረኞች ሳስፈታ

ከዚያ መልስ .... በሚኒባስ ከኃላ ወንበር አንዲት ትንጭዬ የገጠር ልጅ ተቀምጣ ሳጫውጣት ነው የመጣሁት አላልኳአቹም
እስኪ ትዝ ከሚለኝ ምልልስ ውስጥ በትንጩ ላውጋቹ
> አባትሽ ምንድነው ሚሰሩት
* እረግ... ገበሬ ነዋ... እዛ ገጠር ውስጥ ምን ሊሰራ ብለህ
ድምጽዋ... ለየት ያለ ነው.... የገጠር.... በየአረፍተ-ነገሯ ውስጥ... እረግ... ኃላስ... የሚሉ ቃላቶች አሉበት
> ምን ምን ታመርታላቹ
* እረ አባቴ ጎበዝ ገበሬ ነው... የማያመርተው የለም... ጤፍ ብትል... ዳጉሳ ብትል... ይሄ ደሞ አዲስ የመጣው... አረንጓዴው ምንድነው ስሙ
ከፊት-ለፊታችን ተቀምጦ የነበረ ወጣት ስሙን ነገረን.... አተር የሚመስል አዲስ ምርት ነው... ጥሩ ገበያ ያወጣል አሉ... ገበሬውን ሃብታም በማድረግ የታወቀ... ከጤፍ ቀጥሎ
> እሺ... አባትሽ ሃብታም ገበሬ ነዋ
* ኃላስ
> ቤታቹ እስኪ እንዴት ነው
* እንዴት ማለት.. እንደሰው ነዋ
> ማለቴ ቆርቆሮ ነው
በመገረም አይን እያየችኝ
* ኃላስ.... ሆ ሆ .. ምን ይላል ባካቹ... የሰፈሩ ቤት ሁሉ ቆርቆሮ ነው ስልህ
> አንቺስ ትማሪያለሽ
* ነበር .. ግን ምን ያደርጋል ተምሮ የት ለመድረስ... አቁሜአለሁ
> ምነው ለምን አቆምሽ
* አንዲት ጉዳይ ስላለችኝ
> ቆይ ቆይ ግን አዲስ አመት ገና ሳምንት ሳይሆነው ቤተሰብ ጥለሽ አዲሳባ የምትሄጅው ለምንድነው
* አይ አንዲት ትንሽ ጉዳይ ስልህ
>ምን አይነት
* ፓስፖርት እያወጣሁ ነው
> ለምን
* እንዴ ለምን ይላል እንዴ... ልወጣ ነዋ
> ወዴት
* እንዴ ሰው ሁሉ ወደሚሄድበት አረብ አገር ነዋ
> ቆይ ስንት አመትሽ ነው
እንደማፈር አለችና... ወደ-ውጪው በመስኮት እያየች
* እውነተኛውን ነው ወይስ የፓስፖርቱን
> ምን ማለት ነው
* እውነተኛው 17 ነው ብዬ ነው... የባስፖርቱ ደሞ... 24
ገባኝ ምን እያልች እንደሆነ
> ግን አረብ አገር ያለውን ስቃይ እና መከራ.... ሰምተሻል?
* አዎን ሰምቻለሁ.... የዕድል ጉዳይ ነው... ሰምቻለሁ
> መደፈር አለ... ከፎቅ መወርወር አለ.... ስቃዩ እኮ ብዙ ነው... ለምን ግን መሄድ ፈለግሽ
* ሴት ልጅ ለሚያሰራት ወንድ ፊት ካላሳየችው... ስራዋን ብቻ ከሰራች.. መደፈር የሚባል ነገር.... እውነት አይመስለኝም
> እንዴት እርግጠኛ ልትሆኚ ቻልሽ
* እንጃ ሴትነቴ የሚነግረኝ ስሜት ነው
> ቆይ ቆይ... ግን ቤተሰቦችጭሽ እንዴት ፈቀዱልሽ
* ባይፈቅዱልኝ.. በወልዲያ እህዴ የለ.... አባቴ ቁርጡን ሲያውቅ ነው የፈቀደልኝ
> እንዴት ወልዲያ ምን አለ
* በወልዲያ በኩል አድርጎ በጅቡቲ .. በመርከብ የሚያጫግሩ ሰዎች አሉ.... የኛ ሰፈር ብዙ ሰዎች በዚያ ሄዳለሁ
> የኔ ቆንጆ በመርከብ ሲኬድ እኮ...... ብዙ ሰዎች ሞተዋል
* አውቃለሁ አውቃለሁ
> እያውቅሽ ነው ልትሄጂ የወሰንሽው በመርከብ
* አዎን.... ሞት እንደሆነ እዚህም እዚያም .. ያው ነው... እግዜር በፈቀደልህ ቦታ እና ጊዜ መሄድህ አይቀርም.... እዚህ ስላለሁ አልሞትም እዚያ ከሄድኩ ሞታለሁ ማለት... እግዚአብሄር ዘንድ የለም
> ቆይ ግን የኔ እህት... ካልጨቀጨኩሽ... ለምን መሄድ ፈለግሽ
* እንዴ ሁሉ ይሄድ የለም እንዴ.... እኛ ጎረቤት 12 ቤቶች አሉ... ሁሉም አንድ አንድ ልጅ ልኳል.... እንደውም በቀደም ጎረቤታችን ሁለተኛ ልጃቸውን ልከዋል
እኔ ምንድነኝና ነው እዚህ ተቀምጬ... የማየው.... ምን አለና ነው.... ባል ከማግባት በስተቀር....
እሱን ደሞ እሞታታለሁ እንጂ አላደርገውም
> እና ባል ላለማግባት ነው ምትሄጂው ማለት ነው
* እሱና ... ሁሉም ሰው ስለሚሄድ... እንዴ ምነው አንተ ግን ገረመህ
ብታይ እኮ... እኛ ሰፈር.... እዚያ እነ-እንትና.... ሰፈር ከተራራው በስተጀርባ ያሉትማ.... ሁለት ልጁን ያልላከ የለም
እኔም እሄድና ትንሹ ውነድሜ ትንሽ አደግ ሲል... እንዲመጣ አደርጋለሁ.. አሁን ገና 12 ነው... አልጠነከረም
> የመሄጃ ገንዘብ ግን ማን ይሸፍንልሻል... ግን
* አባቴ 100,000ብር ይሰጠኛል... ትልቁ ወንድሜም የምፈልገውን ያደርግልኛል
> ታላቅ ወንድምም አለሽ... የት ነው ያለው
* ሳውዲ ነዋ... እሱ ጋ እኮ ነው ምሄደው.. እሱም ቶሎ ነይ እያለኝ... ነው ያለ!
ምንም ልናገር አልቻልኩም
> ይሄ እግርጭ ስር ያለው ከረጢት ምንድነው
* ጤፍ
> ለማን
* ለአክስቴ.... እሱዋ ጋር ነው ማርፈው ባስፖርቴን ለመቀበል አዲሳባ ስቆይ
> አዲሳባ የት ነው ያክስትሽ ሰፈር
* ለገጣፎ
> ምን አልሽ
* ለገጣፎ.. ምነው
> እንዴ እንደዚህ የሚባል ሰፈር አለ እንዴ አዲሳባ
ከፊታችን ያለው ልጅ አሁንም ማብራሪያ ሰጠኝ
............... አዲሳባ ለካስ እንደዚህ ሰፍታለች .....
........... እረ ተንቦርቅቃለች ...............

ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት
በከንቱ ፈሰዋል ለብዙ ሺ አመታት
ይውጡ መአድናት ላገራችን ጥቅም
ህዝቧም ታጥቆ ይስራ በተቻለው አቅም
.................... ድንቄም ግድብ........
በመጀመርታ
ይህ የስደት ጎርፍ ይገደብ
የሙስሊም እምባ ይገደብ
የቃሊቲ በር ይገደብ
የኑሮ ውድነት ይገደብ
የሻኪሶ ወርቅ ይገደብ (አላሙዲ እና ጨሪኮቹ ... የበቃቹዋል)
እንዴ... ወርቅ መአድኑ የተጨጠበት ዋጋ ታውቃላቹ.... 170ምናምን ሚሊዩን ዶላር
አንድ የቢራ ፋብሪካ በቀደም 250ምናምን ሚሊዩን ዶላር እኮ ነው የተጨጠው

እረ ግፍ ነው.. እረ ግፕ ነው... አይን-ያወጣ ግፕ

ከዚህ መአት ይሰውራት አገራችንን

አሚን

..........................//.....................
ቀደድነው ነው ሚባለው ዛሬ
ምናባቱ የአመቱ ቅዳሜ አይደል.... ይቀደድ

በተረፈ
በቸር ያቆየን

ስደቱን በቃ ይበለን... የፈጠረው ትውልድ እራሱሁለተኛው
እንደምን አላቹ ያገሬ ልጆች
ዛሬ ምን ላወራ መጣሁ መሰላቹ
ስለ-ውሻ
ወይ ውሻ.... ምን ሊወራለት ይሆንንንንንን
...........................//.....................

ከዛሬ 8ወር በፊት ነው ድርጊቱ የተፈጸመው
እኔ እና 4 ጃፓኖች (2ወንድ 2 ሴት)
ስማቸውን ባችህሩ ላስተዋውቃቹ
ሴቶቹ 1ኛ. አይዋ.... 2ኛ ዩሚኮ
ወንዶቹ 1ኛ ሳቶ...... 2ኛ ሱጂ
እና እኔ አይዋ ዩሚኮ ሳቶ እና ሱጂ ... እራት አዘን እየጠበቅን ነው,.... ኡጋንዳ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ.... አርብ እለት
አንዳንድ ቢራ ይዘናል
ስለስራ .. ትንሽ ካወራን በኃላ... የግል እና የጋራ ችሀዋታ ተጀመረ
እንደሚከተለው ይነበባል
> ዩሚኮ........ ባካቹ የማነበው መፃፍ አለቀብኝ.... ካገሬ ስወጣ ብዙ ቆያለሁ ስላላልኩ... ይዤ የመጣሁት መፃፍ ትንሽ ነበር እና.. አለቀብኝ.... ካላቹ አውሱኝ ፕሊስ
* ሳቶ.... እኔ ጋር አንድ ሁለት መጻፍ አለ... ውሰጂ
> ዩሚኮ.... አንተ ጋር ያሉትን አውቃቸዋለሁ.... አንብቤአቸዋለሁ
+ አይዋ.... እኔ ጋር የኢኮኖሚክስ መፃፍ አለልሽ... ትፈልጊያለሽ?
> ዩሚኮ.... እኔ የት/ት መፃፍ አልፈልግም... ልብወለድ መፃፍ ነው ምፈልገው.... አቤት ቅዳሜና እሁዱ ሲደብር መፃፍ ከሌለ..... ምን ይሻለኛል???
የተከፋ እና የደበረው ፊት ታየኝና.. እኔም የሃሳቤን ለመወርወር ... አልኩኝ
..................
*ባለሱቅ.... ለምን ያነበብሽውን መፃፍ ድጋሚ አታነቢውም
> ዩሚኮ.... አንተ ደሞ አይገባህም... ሰው እንዴት ያነበበውን መፃፍ ድጋሚ ያነባል... እኔ በፍጥሱም አላደርገውም.... ሳነብ እያንዳንድዳንድዳዋን ነገር ስለማነብ .. መድገም አያስፈልገኝም
* ባለሱቅ.... እኔ ግን.... ማንም ሰው በመጀመሪያ ጊዜ የሚያነበውን መፃፍ በደንብ የሚያነበው አይመስለኝም.... ዋናው ታሪክ ላይ ብቻ ስለምናተኩር.... ብዙ ሚስ ምናደርገው ነገር አለ
+ አይዋ.... እስኪ በምሳሌ አስረዳን... ምን ለማለት እንደፈለክ
ዋውውውውው
የምፈልገው ይችን አይደል.. ብዬ ቀደዳ ጀመርኩ
.....................//................
10ኛ ክፍል ሳለን
አዎን 10ኛ ክፍል ሳለን.... የአማርኛ አስተማሪያችን (ኬኒያ ማመጫ)... አንብባቹ ገምግሙ ብሎ... የበአሉ ግርማን መጻፍ እንድናነብ አድርጎን ነበር.... ከአድማስ ባሻገር.... ደራሲው..... ትዝ ይሉኛል
ከአድማስ ባሻገር ላይ ያለችውን ሉሊትን... አፍንጫዋን (ቀጥ ብሎ ወርዶ እታች ሲደርስ የሚቀለበሰውን)... ምን ያህል እንደተመራመርንበት ትዝታዬ... ይቀመጥና
ደራሲው የሚለው መፃፉ ላይ የገጠመኝን ነበር ያጫወትኳችው

ደራሲው የሚባለውን መፃፍ... ከሶስት ጊዜ በላይ አንብቤዋለሁ... ከ1984 በፊት....
10ኛ ክፍል
ዘመቻ ጣቢያ
ዩኒቨርሲቲ
ብዬ ጀመርኩላቸው

እዚህ መፃፍ ውስጥ አንድ የሚያላዝን ውሻ አለ.... እረ ትንፋጭ እስኪያጥራቸው የሚያስሉ አሮጊትም ነበሩ እንጂ
አሁን አራቱም ጃፓኖች እያዳመጡኝ ነው
በተለይ አይዋ... በጣም ነበር ምትከታተለኝ
ታሪኩን አራዝሜ አራዝሜ.....
እዛ መፃፍ ላይ ያለው ውሻ ለኔ የታሪኩ አዳማቂ እንጂ.... የራሱ ታሪክ እንዳለው አላውቅም ነበር 3ጊዜ አንብቤው እንኳን .. ሁሌ የሚኦያላዝነው ውሻ ታሪክ እኔን ታይቶኝ አያውቅም ነበር
አንድ ቀን ግን... በ1984 መስከረም 4
ከሆነ ሰው ጋር ስለመፃፍ እያነሳን ስናወራ... ስንቀድና ስንጥል
የሚከተለውን አይነት ምልልስ አደረግን... ከዚያ ሰው ጋር
> ደራሲው የሚለውን መጻፍ አንብበሕዋል?
* አዎን በጣም የምወደው መፃፍ ነው
> የውሻው ታሪክ አያሳዝንም
* የምን ውሻ
> ያ ሚያላዝነው ውሻ
* እንዴ ...ቅቅቅቅ ውሻ ው ደሞ ምን አይነት ታሪክ አለው.... እኔ እኮ ሶስት ጊዜ ነው ያነበብኩት.... ዝም ብሎ የሚያላዝን ውሻ አይደለም እንዴ,... ደራሲውን የሚረብሽ.. እንዳይጽፍ
> ኖ ኖ እንደገና አንብበው.... ውሻው የሚያሳዝን ታሪክ አለው.... አሁን አትጨቃጨቅ...እንደገና አንብበው
በማግስቱ... አነበብኩት እንደገና
ውሻውን ፈልጌ ስለውሻው ብቻ ለማወቅ አነበብኩት.... ለ4ኛ ጊዜ
ያ... የሚያላዝን የደራሲው የጎረቤት ውሻ.... ለካስ... አባቱ ዘመቻ.... ካራማራ ተራራ ላይ ሆኖበት ... እሱን አጥቶ ነበር የሚያላዝነው
እዬዬ ማለቱ ይሆን... አባባባባባ..... እያለ....
የጋሽ በቀለ ውሻ
ጋሽ በቀለ ከዘመቻ የተመለሱ ቀን ግን... ማላዘኑን እንዳቆመ.. ሁሉ .... መፃፉ ላይ ተፅፎአል
በስመ-አብ ወወልድ... ይህንን ሁሉ ታሪክ እንዴት ሳላነብ እና ሳይከሰትልኝ
አቤት ውርደትትትትት በችኮላ ማንበብ

ይህንን ታሪክ እያወራሁላቸው ሳለ....
ዩሚኮ.... እዬዬዋን አቅልጣዋለች ለካስ በእንባዋ
እኔ አላየኃትም ነበር አይዋ ነው የነገረችኝ.... በቃ አቁም ብላ
ምን ተፈጠረ
ዩሚኮን ምን አስለቀሳት

እስኪ እስዋን አባብለን እንመለሳለን

ቸር ቆዩኝ
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby የግልነስ » Tue Jun 18, 2013 2:13 pm

ስላም ለቤታቸን ይሁን እንዴት ናቸሁልኝ ውድ ያገሪ ልጆቸ ሁሉም ስላም ነው አማን ነው በጣም ተጠፋፋን አይደል አልበዛም ታንክስ ጎሳቸን ዋርካን ጎትተህ ስላመጣሀት..............
ቦሀላ ላይ የማወራቸው ጥቂት ነገር አለቸኝ እና ብቅ ብላቸው አንብቡኝኝ

የጠፋቸው
የግልልልል
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby brookk » Fri Jul 05, 2013 3:18 pm

ጠፋን
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ባለሱቅ » Thu Jul 11, 2013 1:57 pm

በለውውውውውውውውው

በስትን መከራ እዚህ ቤት ገባሁ መሰላቹ

እንደምን አላቹ ያገሬ ልጆች

አንቺ ቀዥቢ የግል... ምነው እመጣለሁ ብለሽ ጠፋሽ

የሳይበር በሩ ተዘግቶብኝ... ተቸግሬ እያየሽ..... ህምምምም
ያ ጎሳ ምነው አንዴ ብቻ አቤቱታዬን ለጥፎ ጠፋሳ

አይይይይይይ ይሁና አለች ሶስት ጊዜ ጴጥሮስ ላይ ያስካካችው ዶሮ

ደህና ናቹ ግን

ብሩኬ እንዴት ነህ ያገር ልጅ....... የሰፈራችን ልጆች ቤታችንን ዘግተው..... እኛንም አስዘግተው ...
እልምምምምምም አሉ አይደል

እስኪ እንግዲህ እና ብቻችንን እዳንቀር አንተም እንኳን መጣ መጣ እያልክ.. ጎብኘን

እስኪ እንግዲህ እንዲህ ሲመቸንና... ሳይበር ሲታረቀን.... እየመጣን እንዘባርቃለን

ቸር ሰንብቱ

ከከሰረው ባለሱቅ ባንኮኒ ስር
ሆኜ
ሰላም ሁኑ
እላቹዋለሁ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby Gosa » Sun Jul 14, 2013 1:01 am

ወይ ባለሱቅ!!! አንድ ሁለቴ ያንተን መልዕክት ለጠፍኩልህና ከዚያ በኌላ ሀይለኛ ጥርጣሬ ውስጥ ገባሁ:: እንዴ...እዚያኛው ቤት ገብተህ እንደልብህ መጻፍ እየቻልክ እዚህ ቤት ገብተህ መጻፍ ያልቻልክበት ጉዳይ ምንም ስላልገባኝ በተቻለኝ መጠን ከየት ገደል እየጻፍክ እንደምትሰዳቸው ለማጣራት ደፋ ቀና በማለት ላይ እያለሁ ነው አሁን እዚህ ብቅ ብለህ የገላገልከኝ:: እኔ ዱካህን እየተከተልኩ ጊዜ አጥቼ ነው የጠፋሁት:: እንኳን መጣህልን::

ባለሱቃችን ማንም እንደሚያውቀው አንተ ቆይተሀል ማለቴ ከመናፍስቱ ሳይበር አለም:: እና እንደ እርሻ ምናምኑ የሳይበሩም ዓለም ወቅት አለው እንዴ? አንዴ ሰው ግር ብሎ መጥቶ ሳይበሩን በጽሁፍ የሚያጨናንቅበት...ከዚያም ትንሽ ቆይቶ ሰው ሁሉ hibernation ውስጥ የገባ ይመስል እንኳን ሰው ዝር የምትል አንዲት ወፍ የምትጠፋበት? በል አሁን እኔና አንተ ከእንግዲህ ከዚህ ቤት ላንጠፋ ቢያንስ በሳምንት አንዴ ብቅ ልንል በዋርካ ስም እና በወዩ ስም ቃለ መሀላ እንፈጽም:: ምን... ለነገሩ አንተ በየሜዳው እየማልክ ስለምትሄድ ይኽኛውን መሀል በቁምነገር አስታውሰህ በየሳምንቱ ትመጣለህ ብዬ ስለማላስብ እንዲሁ ካንተ ጋር በመማል እራሴን አላደክምም::

የግልማ "ተመልሳችሁ አንብቡኝ " ብላን ያኔ አዋሳ እያለሁ ቤተክርስቲያን ከተመላለስኩት በላይ ጧት እና ማታ አመላልሳኝ ጫማዬን አልልም አይኔን አስጨረሰችኝ:: ከሰራችው በላይ ይስጣት ቅቅቅቅ ፔይ ቼኩን ነው ያልኩኝ::

ብሩኬ ደግሞ ካልጠፉ የአማርኛ ፍደላት "ጠፋን "ን ብቻ ይዞ መምጣቱ ግርም ብሎኛል:: ኧረ ትንሽ ጨምርበት ቅቅቅ

በል ሱቃችን ብቅ ብለህ ስለነበርክበት ቦታ ትንሽ አውጋን:: ሰው በሰው በጨከነበት ዘመን ለውሻ ብናነባ ትዝብት ውስጥ እንገባ ይሆን? ቅቅቅ:: ከምር ጥሩ ጨወታ ነበር ባለሱቃችን:: እኔም ያነበብኳቸውን ታሪኮች ለመገረብ ተነሳስቻለሁ:: ይመችህ!!!
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ባለሱቅ » Tue Jul 16, 2013 3:17 am

ጎሲቲ
ይኸውልህ እራሴኑ ገልብጬ መጣሁልህ.... በአዲስ ኮምፒተር
አንድ ሰሞን ሳይበርን በቫይረስ አላጠቁብንም... አልቃይዳዎች...? ይወውልህ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኮምፒተሬ .. እምቢ አለች.... በቃ.... ዲ..ዴ!
ሳይን ኢን ማድረግ ነበር ያስቸገረኝ በተለይ.... ጃቫ-ስክሪፕት ከ30 ጊዜ በላይ ነው ዳውን-ሎድ አድርግ እያለኝ ያደረኩት.. ለሳይበር ስል
ኤኒዌይ... አሁን አዲስ ኮምፒተር ተገዝቶልኛል... እንደ-ህፃን ልጅ.. ሳለቃቅስ አይተው....
ይኸኛው በአልቃይዳ ቫይረስ እስኪጠቃ ድረስ እንግዲህ.... ቃል ባገባም.. በሳምንት አንዴ.. ብቅ እያልኩ
እዘባርቅልሀለሁ.... የተገኜውን
ያው እንግዲህ እዛኛው ቤት የፃፍኩትን እዚህ አምጥቼ ልጥፍፍፍፍ
መልካም ጊዜ
ጎሳ ወንድሜ
በጣም አመሰግናለሁ ከዚህ ድብርታም ቤት ውስጥ አውጥተህ መልክቴን ስለለጠፍክልኝ... በድሮው ቤታችን
አየህ አይደል እኛን አይታ ያቺ ቀዌ... የግልነሽ እንደመጣች
ገና ትመጣለች... አንተ ብቻ ተባበረኝ እንጂ.... ከዚህ ግርግዳ ነቅለህ.. እዚያኛው ላይ መልክቴን ከለጠፍክልኝ
..................................//.......................
ምን እያወራሁ ነበር ባካቹ,,,,,,,,,,,, አይ እርጅና... ይጫወትብኝ ጀመር ማለት ነው...

ኣዎን ዩሚኮ አለቀሰች ብያቹ ነበር........... ምን አስለቀሳት... ምን ነበር የነገርኳት

አዎን የውሻ ታሪክ.... ደራሲው የሚለው መጽሃፍ ላይ ስለሚያላዝነው ውሻ
አንድ ቀን የውሻው በየጊዜው ማላዘን ያስመረረው ደራሲው (ጋሽ ስብሃት) ... ለስሞታ ጎረቤት ሄደና..ጠየቀ
እናትና ልጅ.... ልጅ የናትየውን ቀሚስ ይዞ... ደራሲውን አይን አይኑን እያየ
በሃሳቡ.... አሁን ምን ልሰራ መጣሁ... እያለ .. በአመጣጡ እያፈረ..... ደራሲው.. ሲራክ
በመጨረሻ... አጫወቱት እማማ.. ሁሉንም......
ባለቤቴ,... ወደ-ኦጋዴን ከዘመተ ጀምሮ ይሄ ውሻ እያላዘነ አስቸገረኝ
አቤት ደራሲውን በዚያች ቅጽበት የታየው..... ጎፈሬውን ያጎፈረ.. ቁምጣ እና ከስክስ የወታደር ጫማ የተጫማ... .... በበረሃ የነደደ ፊቱ የተቆጣ ... ጀግና ወታደር....ካራማራ ተራራው ላይ ቆሞ.. የኢትዮጵያን ባንዲራ በጀግንነት ሲያውለበልብ
ሶስት ጊዜ አንብቤው... ያላየሁት ታሪክ
ይሄ አሁን ምኑ ያስለቅሳል
........................//...........
እንባዋን ጠራርጋ ስትጨርስ ጠየኳት
> ምን አስለቀሰሽ ግን?
+ ውሻው.... ውሻዬ................ እምምምም ትላንትና ከቤት ስልክ ተደውሎልኝ... የልጅነት ጓደኛዬ.. ውሻዬ ሊሞት 10ቀን እንደቀረው ሃኪሙ ለቤተሰቤ ነግሮአቸው....
እንደገና ማልቀስ ስትጀምር... አቆመች
አለቃችን ሳቶ.... እናንተ አገር እንደዚህ አይነት መጻፍ ይጻፋል? አርስቱ ምንድነው.. ማነው የጻፈው... ተተርጉሞዋል?... በጥያቄ አጣደፈኝ
አይዋ ... ዩሚኮን አባበለቻትና ስታበቃ... ወደኔ ዞራ
* የመንደሪኗ ልጅ ናት አይደለም ... እንደገና እንድታነብ ያደረገችህ... አለችኝ
ክውውውውውውውውውው ነው ያልኩት .. በውነት.... እንዴት ልታውቅ ቻለች.... ማን ነገራት.... ይህንን ታሪክ ለሰው አውርቼ አላውቅም እኮ..... የሁሉም ሰው አይን ጆሮ የሆነ ይመስል... ሁሉም አፍጥጦ አየኝ እና የምለውን ሲጠብቅ
> ማን ነገረሽ... እንዴት እንደሱ ልትገመቺ ቻልሽ.. ስላት
*የዛሬ ሶስት አመት ስለዚች ልጅ አጫውተኅኛል... እና እንዲህ አይነት ደስ የሚል ታሪክ ያላት አንተ ህይወት ውስጥ እሷ ብቻ ነው ምትመስለኝ..... ግን እሷ እንዴት ይሄ የውሻ ታሪክ ሊስባት ቻለ
ህምምምምምምምምምምምምምምምም
ታሪኩ ረጅም ነው... ነገር ግን... አባቷን በጣም ትወድ ነበር.... እሱም እንደዚያው.... በልጅነቷ አባቷን ከመውደዷ የተነሳ... እናቷን በጣም ትጠላ ነበር
ምክንያቱም.. ማታ ስትተኛ ካባቷ አጠገብ ሆኖ ሳለ... ጠዋት ስትነሳ.. አባቷን እናቷ አልጋ ላይ ስታገኝ... ቅናት አይሉት ምን... ታለቅስ ነበር..... እርር ድብንንን ብላ
እና ያ በልጅነቷ የምትወደው አባቷ..... የኦጋዴን ጦርነት ካለቀ በኋላ... ወደ-ሰሜን ሄዶ.... ድምጹ ከተሰማ ከአስር አመታት በላይ ተቆጥረዋል
ከዛሬ ነገ ይመጣል እያለች የምትጠብቀው አባት
ይሙት
ይኑር
መንግስትም አልነገራት.... እሷም አላወቀች

አንተ አሞራ... መጥተህ ንገረኝ.. ያብዬን እጣ
የኔ ጀግና .. አልተመለሰም... እንደወጣ

........................//......................
ሱጂ የሚባለው ጃፓናዊ ምርቅንንንን ብሎ ነበር ለካስ ሚያዳምጠኝ.... መዝፈን ጀመረ
አንቺ የመንደሪን አበባ... የሚል ጃፓንኛ ዘፈን.... ሰምቼው አላውቅም... ግን ደሥ የሚል...
ወዲያውም ሁሉም በአንድነት...
ትገናኛላቹ አሁንም ከመንደሪኗ ልጅ ጋር....አሉኝ
እኔ ከመመለሴ በፊት ግን አይዋ ተሽቀዳድማ.... አዎን ይገናኛሉ.. አለች
እኔም እየሳቅኩ.... አዎንታዬን ስነግራቸው
ይደወልላት... እና ይሄ ዘፈን ይዘፈንላት.. ይላክላት
ባንድ አፍ.. ብዬ እኔም ስልኬን አውጥቼ
ቂሪሪሪሪሪሪሪሪሪ

አይበቃም

ቸር ሰንብቱ

አደራ መጻፍ ስታነቡ.... ደጋግማቹ አጣጥሙት... ብዙ ሳናውቅ የምናልፋቸው ታሪኮች ስላሉበት

እንደኔ እንዳትዋረዱ

ቺርስ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby የግልነስ » Thu Jul 18, 2013 2:00 am

ስላም ለቤታቸን ይሁን እንዴት ናቸሁልኝ ጎስሽና ባለሱቅ ስላም ነው አማን ነው :roll:

በጣም አሳዛኝ ዜና እረፈት ልንገራቸው....

ጋሽ አለማየሁ በንቲ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል....ቁርንፍድዩ, ፈቅርት, ቲጂ, መቅደስ, ቴዲ, መአዚ እና ሌሎቻቸሁም እግዚር መፃናናቱን ይስጣቸው, ራስብሩም እንደዛው...............

ጋሽ ታምራት መርጊያ የአማሪኝ አስተማሪያቸን የነበረው እሱም እንዲሁ ከዚህ አለም ተስናብታል ለሱም ቤተስቦቸ መፃናናትን እመኛለው, ጋሽ ታምራት ያአባቴ የቅርብ ጋደኛ ነበር በጣም ነው ያዘንኩት.....

የግል ነኛ
ይቀጥላልልል
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby የግልነስ » Thu Jul 18, 2013 2:37 am

ስላም በድጌ...................

ከዚህ በፈት እመለሳለሁኝ ብይ የነበረውን ዘና አሁን ልንገራቸው የጠፋሁትም ያው ባለሱቅ እንዳለው የሳይበር ቫይረስ የኔንም ኮምፒዩተር አታክ አድርጎት ነብርና በዛ ምክንያት ነው የጠፋሁት እኔ ግን እንደ ባለሱቅ ሀብታም ስላልሆንኩኝ እራሳው ቫይረሱን አፅድቺ ባለኝ እየተንገዳገድኩኝ ነው ቅቅቅቅቅ ገደልከኝኝ...........

ስለ ሽልንጌ ጥቂት ላውራቸው.................. ሽልንጌ ሀገር ቤት ለመሄድ ከመነሳቱ በፈት የቅርብ ጕደኞቼ የሚላቸውን የክ/መንግስት ልጆቸ እየደዋወለ ገንዘብ ካስባስበ ቦሀላ አገር ቤት ወስዶ 31,000.00 የኢትዩ. ብር ለወላጅ አልባ ህፃናት አካውንት ውስጥ ገቢ አድርጕል በዛም አላበቃም ዲክሺነሪ, መፅሀፈ, እርሳስ, እስክሪፕቶ, ደብተር ልብስ, ጫማ እረ ምን የቀረው ነገር አለ አንብሽብሾ ተመልሳል.............አሁንም እምትወደው አማላክ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ ሀሚዲዩ ውድድድድ ነው ያማደርግህ እሺ ......

ቁርንፈድም እንዲሁ በሄደቸባት ጊዚ ዶኒት አድርጋለቸ

ፍቅርትም.................$10,000.00 የኢቲዩ. ብር ገቢ አድርጋለቸ ፍቅርትና ቁርንፍድዩ ህንፃዋን የስራቸሁላት ማሪያም ትጠብቃቸው አመስግናለሁኝ ከብዙ መውደድድ ጋር እምምምጵዋ......

በመጨረሻም ከቅዱስ ኡራኢኤ ቤ/ክርስቲያን.... መሀሌት.......$50.00 ዶላር ዶኒት አደርጋለቸ አመስግናለሁኝ መሀልዩ የምትወጂው ኡራኢል ያስብሽውን ያሳካልሽ

ሪፓርተር የግል
መልካም ሳምንት
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby የግልነስ » Sun Jul 21, 2013 3:40 pm

ስላም ለቤታቸን ይሁንልንን በስላም ነው ፅጥታውው................
ባልሱቅ ጎሳቸንን ብቅ በሉ እንጂ :roll:

ዛሪም ሌላ ለወላጅ አልባ ህፃናት ዶኔት ያደረገቸዋን የቅዱስ ኡራኤል ጕደኛዩን ይዢላቸው መጣሁኝ.......
እመቤት(እሙሽ)......$50.00 ዶኒት አድርጋለቸ እሙሽዩ የምትወጂው ቅዱስ ኡራኢል ያስብሽውን ያሳካልሽ የኔ ቆንጆ እጀግ በጣም አድርጌ አመስግናለው......

ሌላው በነዚህ ህፃናት ዙሪያ የምታድርጉትን እርዳታ እባካቸው አታቁሙ እንዚህ ህፃናት ያሉት በእናንተ ሀይል ነው በተለይም ክ/መንግስት እየሄዳቸው የምትመለሱ ልጆቸ አደራዩ የጠበቀ ነው እስቲ እናተም እንደነ..... ሰኒያ, ሀሚድ, ቁርንፍድ, ፍቅርት.......ምሳሌ ሁኑ.....ጋሽ ደበበ ሳህሌን አግኝታቸው ለማናገር ሞክሩ..........እነዚህ ህፃናት የናነተን ድጋፍ....እርዳታ ይሻሉና ................. በዚህ አጋጣሚ ስለ ወላጀ አልባ ህፃናት በተነሳ ቁጥር እጀግ አድርጊ የማመስግናቸው መሀሙድ, ስለሺ, ደጉ ስው ሳላመስግና አላልፈም ብሩክ የሆኑ የክ/መንግስት ልጆቸ ምሳሌ ናቸውና......

ደጉስው ምነው ጥፍቱ አልክብኝሳ ስልክም ደጋግሜ ሞከርኩኝ..........ደውልልኝ እስቲ :lol:
ብሩክ(ካናዳው) ስላም ነህልኝ ብሮ ያ የሚጥመውን ፅሁፍህን ግባና ፃፍልን እንጂ ጎስሽ እንዳለውም በሶስት ቃላት አትዝጋን ቅቅቅቅቅቅቅ

በሉ አትጥፋ ብቅ እያላቸው ፃፍልን አስተያየታቸው ወሳኝነት አለው....................

በጀሮንድ የግል ነኝ
ስላም ዋሉ
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby ባለሱቅ » Mon Jul 22, 2013 3:36 am

ኦህ ኖ....................

የግል በጣም የሚያሳዝን ዜና ነው ይዘሽልን የመጣሽው

አባባ አለማየሁን ነፍስ ይማር ብያለሁ
ለቅሩንፉድዬ እና ለቤተሰቦቹዋ የጠነከረ መፅናናቱን ይስጥልኝ

ጋሽ ታምራትንም (የአማርኛ አስተማሪያችን).... አምላክ ነፍሱን በገነት ትቀበለው

በተረፈ

የግል የሽልንግዬ ዜና እጅግ በጣም ሲያስደንቀኝ ነው የከረመው
በፌስ ቡክ ከአዶላ ሆኖ ይፅፍልኝ እና ፎቶ ይልክልኝ ነበር እኮ... የቱላ-ረጃጅሙን ጫት እየቃመ (ወይ ሊቅም እየተዘጋጀ)
አንዲትም ቀን ስለዚህ ጉዳይ አልተነፈሰልኝም
መቸም እንዴት ደስስስ እንደሚል መግለፅ ያቅተኛል

ሽልንግዬ.... በዚህ በረመዳን አላህ ጨምሮ ይስጥህ አቦ
ተባረክ
ተባረክ

በተረፈ

ሰላም ሁኑልኝ

ትንሽ ቢዚ እየቀመቀምኩ ነው
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby brookk » Mon Jul 22, 2013 3:33 pm

ሀይ የግል - የክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች ሰላምታዬ ይድረሳችሁ
አሁንም እየተንቀሳቀሳችሁ መሆኑን መስማት የሰጠኝን መጠነኛ እፎይታ ልገልጽላችሁ አልችልም
ሁሌ እናንተ በተለይም እነዛ ህጻናት ወገኖቼ ከሀሳቤ ወታችሁ አታቁም
ዋርካም አረጀች እኔም ሳላውቀው አረጀሁ መሰለኝ - ገብቶ ማንበብ እንጂ መጻፉ እየከበደኝ ነው -- እናንተም ዋርካን ትታችሁታልና ምንን ተመርኩዘን እንጻፍ -- የማይደክመው ትልቁ ባለሱቅ እንኳን የጀመረልንን የተለያየ ታሪክ ሳይጨርስ ተሰወረብን -- ኡጋንዳ - ፊያሜታ --- ስንት ታሪክ ጀምሮ አንጠልጥሎ ተወው --
አደቆርሳ ሁሌ እንደተናፈቀ ነው - የሚጽፈው ታሪክ ገሪሙ ነበር ሁሌ
ወቤ ጃሎ የሱ ነገር ግን እንቆቅልሽ ሆነብን - አገባ -- ጠፋ - ውብ ነበር ጽሁፉ

የግል - የዋርካው ኢሜይል አይሰራምና እስቲ ኢሜይል አድራሻሽን በዚህ ላኪሊኝ brook_2222@yahoo.com

brook_2222 ነው

ሰላም ሁኑ
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby የግልነስ » Mon Jul 29, 2013 4:44 am

ሀይ ብሩክዩ በስጠህኝ ኢ-ሜል ደጋግሜ ሞከርኩኝ......ባውንስ እያደረገብኝ ተቸገርኩኝ....ቁጥሪ ካለህ ደውልልኝ እና የሆድ የሆዳቸንን እናውራ ......ብሮ ወይም በፕራይቤት ቁጥርህን ሴንድ አድርግልኝኝ

የግል ነኝኝ
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest