ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ያንፈራራ ዳገት ጡት የለው ደረት:ከጭኑ ሥር ቀረ ወይ አያልቅበት::

Postby ራስብሩ » Fri Sep 16, 2005 2:46 pm

ጤና ይስጥልኝ ወዩዎች እንዴት ከረማችሁ:
ይህችን የዋርካ አምድ የአዶላ ወዩ የራስ ብሩ ልጆች መሰባሰቢያ ካደረግናት እነሆ ሁለት ሳምንታት ተቆጠሩ::እስካሁንም ደስ በሚል ሁኔታ እየተሳሰብን ላደግንባት ትምህርት ቤት የበኩላችንን ለማድረግ ርብርባችን ተስፋ ያለው በመሆኑ የመጣችሁትን እያመሰገንን:የምታውቋቸውን በቴሌፎንም በ ኢ_ሜይልም ወደገጻችን እንድንጋብዛቸው በድጋሚ ጥሪያችን ይድረሳችሁ:
አደቆርሳ
ቅሩንፉድ
ባለሱቅ
ቀልቤለጌ
የግልነስ
ፖስታቤትሰፈረ
ዝምታ
ወቤጃሎ :ምስጋናችን ይድረሳችሁ
ጨዋታችሁ የየዕለት ስንቅ ሆነን እኮ.
በሉ በርቱ አምላክ ይባርካችሁ !!!
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

Postby አደቆርሳ » Fri Sep 16, 2005 4:25 pm

እናንተ ልጆች አንዳችሁንም ሳላውቃችሁ ትናፍቁኝ ጀመር::ወይ ጉድ: እንዴት ከረማችሁ::ቅሩንፉድ አደራሽን በተቻለሽ መጠን አንዳንድDrop አርጊልን::
ባለሱቅ ያቆብ ገብረትንሣኤ ተንኮለኛ ነው???በጣም ተንኮለኛ እንጂ !አንዴ ምን ሆነ መሰለህ::እሱና ሰለሞን አባስሜ ሆነው ቅዳሜ ገበያ ሽንኮራ ሊበሉ ሄደው ኖሯል::እየበሉ በሚካኤል በኩል ሲመለሱ የገበያ ክፍል ልጆች ኳስ ይጫወቱ ነበርና ትንሽ ቆመው እንዳዩ መጫወት ፈለጉ:(በነገራችን ላይ ያቆብ ሸንኮራ ሲበላ ለዋንጫ ነው የሚመስለው:በጣም ይወዳል) መጫወት እንፈልጋለን ብሎ ያቆብ ሲናገር: ፋሲል አገኘሁ እናንተ የሰፈራችን ልጆች አይደላችሁም እኛ
ኳስ የገዛነው አዋተን ስለሆነ ክፈሉን እና ተመራርጠን እንጫወትይለዋል:ያቆብ ትልቅም ስለነበር በሁኔታውም ይናደድና አንድ ሁለት ሲባል ::እሱና ሰለሞን ከተመልካቾች(በደንብ ከማይችሉት)ይመርጡና ሌሎቹ የገበያክፍል ልጆች ሆነው መጠኑ ትዝ አይለኝም (0,50c)ይሆናል አስይዘው ለመጫወትይስማማሉ:: እነ ያቆብ አንድ ብር እንደተበሉ ያቆብ ከአጫዋቹ ላይ ፊሽካውን ተቀብሎ እኔ ራሴ እየተጫወትኩ አጫውታለሁ ብሎ ድርቅ ይላል:/እስካሁን በጣም ያስቀኛል/ትልቅም ጉልበተኛም ስለነበረ:አይሆንም ሲባል ካልሆነ ብራችንን መልሱ በናንተ ሰፈር ዳኛ አይሆንም ብሎ ከተበሉ በኍላ ይጮህና ዳኛውን ስንታየሁ(ሾቶላ)ን ያንቀዋል::ገነነ ጋረደው ለጎል መስሪያ ያስቀመጠውን የሰለሞን አባስሜን ራንግለር ጃኬት ይዞ እግሬ አውጪኝ ሲል ዱላ ይነሳል::ከነበሩት ውስጥ የማስታውሰው:ቴዎድሮስ ጋረደው:ወንዱ ደጋጋ:አባቡታ:ተሾመ ከበደ:መሰለ ጥላሁን: መንግስቱ ብዙነህ:አስፋ መንግሥቴ:እኔም ያኔ ገበያ ክፍል ነበርኩ::ከዚያ የሆነውን አትጠይቀኝ::በሶስተኛው ቀን ሱካሬ ያኔ የሚችለው አልነበረም ግዙፍም ነው ብቻ እንደጠበበው ቢያስታውቅም ያቺን ራንግለር ለብሶ ይወጣል: ያገኙትና.......አሰለቸሁዋችሁ መሰለኝ:የአራዳና የገበያ ክፍል ልጆች ታሪክ አያልቅምና ለዛሬ በዚሁ ላብቃ::የምታስታውሱ እንደምትኖሩ አልጠራጠርም:እስቲ አንድ በሉ:
አንተ ባለሱቅ የመሀመድ ረሺድ ወንድም ነህ?????
አንተ ስለ ቆንጆ ያልከውን ሳስብ ገረመኝ ቆንጆ ያንተ እህት ትንሿ ነች እንጂ ጸሀይ የመሰለች ውብ::(ዳሬሰላም)
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 976
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

አደቆርሳ! ታቆማለህ

Postby ባለሱቅ » Sat Sep 17, 2005 3:17 am


ዳሬሰላም ፀሀይ አልከኝ...
እኔም አቃታለሁ... ታላቄ ናት... ግን እህቴ አይደለችም.... መሀመድ ረሺድም ወንድሟ አይደለም......... ግን ጎረቤታችን ናት....
ታዲያ ታቆማለህ... ብዙ ብዙ አትጠይቀኝ... ቅቅቅቅቅ አፍራለሁ....

ስለያቆብ ስታወራ ... ምንም ጎሮቤቴ ቢሆንም.. አላቀውም ማለት ነው ብዬ ግርምምም አለኝ...
እኔ እኮ ያቆብን ማቀው መኪና ይዞ ነው... ተማሪ ሆኖ በፍፁም አላቀውም..... ምናልባት ጎሮቤቴም ስለሆነ ይሆናል ያውኩት እንጂ.... ምንም ታላውቅምምም... ይልቅ ሸንኮራ ለዋንጫ ነው ሚበላው ስትለኝ...የራሴ ትዝ አለኝና .... የገበያ ክፍል ሸንኮራ አይኔ ላይ ዞረ...
የባላንበራስ መኮንን ሸንኮራስ.... ታስታውሰዋለህ... 01ቀበሌ ቤተልሄም ሆቴል ፊትለፊት... ካለው ግቢአቸው ውስጥ ይሄ ሸንኮራ ዝርግፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ሲል... በሩ ከተከፈተ... ስርቅቅቅቅቅቅ አድርገን... እንክትትትትት.... አቤትትትትትትትትት የጎን አፌ እስኪደማ ነበር ምበላው...
ያኔ የበላሁት ሸንኮራ አይደለም ብለህ ነው.. እንዲህ ከንፈሬን እንዲጣፍጥ ያደረገው.... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ኖ ኖ ... አሬራና ገፉማው ነው ዋናው.... ሸንኮራው አይደለም....
ዋውውውውውው ገበያ ክፍል.... ማክሰኞ ከክፍል እየፎረፍን ሁሉ ነበር... ዳቦ-ሸዌ.. በትኩስ ወተት... በቆራስማ እብድድድድድድድድ ያለች ወተት.... ዋውውውው ለሀጬን አንጠባጠብከው አቦ ስለ ገበያ ክፍል አውርተህ::

እስኪ ቸር ይግጠመን....

ቅሩንፉድዬ እስኪ ብዙ ብዙ ትዝታዎች አጫውቺኝ... አንቺ የ02 ቀበሌ ልጅ ትመስያለሽ.... ድምፅሽን ስሰማ..... የማነህ ደፋር እንዳትይኝ ብቻ.... ቅቅቅቅቅቅቅቅ

ጋሽ ራስ-ብሩ.... ጥሪ አቅርበናል የምናቃቸውን የማናቃቸውን.. በሙሉ.... በቅርብ ጊዜ ይመጣሉ ብዙ ብዙ ሆነው....
እኛ ብቻ ቤታችንን እናሟሙቅ...
የሞቀ ቤት ,ማይገባ የለም....
ይመጣሉ
አይዞንንንን
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

እንዴት ናቹ አዶላዎች

Postby ቅሩንፉድ » Sun Sep 18, 2005 9:14 pm

የግል ስለስፖርተኞች እንኳን ብዙም አላውቅም:: ለምለም በርሄ የታወቀች ቮሊቦል ተጫዋች ነበረች:: ባለሱቅ ልኳንዳ ሰፈር ባልሳሳት 02 ቀበሌ መሰለኝ: ትንሽ ቆይተህ ማነሽ እንዳትለኝ እንጂ :lol: :lol: :lol: :: አደቆርሳ የገበያ ክፍል ልጅ አልማዝ ጉተማን ታውቃታለህ :?: አንድ ጊዜ በጣም ትንንሾች ሆነን ነው ከአጥር ጊቢ ወጥተን የሆነ ግቢ ገብታ ትርንጎ ይዛ ወጣችና ጉዞ ጀመርን:: ምንም ያህል ሳንሄድ አንድ ልጅ አጋጠምንና : ምንድ ነው የያዥው አምጭ ቢላት : መጀመሪያ ምንም አልያዝኩም አለች:: ልጁ ድርቅ ሲልባት የያዘችውን አሳየችው:: ከየት አመጣሽው ብሎ ይጠይቃታል:: ጦልቤ ነው አላለችው መሰላችሁ:: በወቅቱ መቼም የሳቅነው የሚረሳ አይደለም:: አይ ልጅነት እንዴት ደስ የሚል ነበር :)
ቅሩንፉድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 346
Joined: Fri Apr 15, 2005 9:07 pm
Location: germany

እርማት !!!

Postby አደቆርሳ » Mon Sep 19, 2005 6:49 pm

ቅሩንፉድ ሰላም ላንቺ ይሁን ዊኬንዱን አንቺና ባለሱቅ ብቻ ናችሁ ብቅ ያላችሁት:ቤታችን ከሰርግ የተበተነ ድንኳን መስሏል::አንቺና ባለሱቅ ደህና:ሁኑ እንጂ ፍርፍር ለመብላት:ቀስ ብለው ሁሉም ይመጣሉ::
ባለሱቅ ይገርምሀል እንዳልከው አሁን አስተዋልኩ:ጽሁፌም "ያንተ እህት ትንሿ"በሚለው ፋንታ "የነመሊክና የነቡሽራ እህት ትንሿ" ተብሎ ይነበብልኝ:: ግን መሀመድ ረሺድ የት ነው?:ከናንተ ሰፈር ያሲን ከማል እና ሙሁዲን ሀሰን ደረጀ ዓለሙ አብረን ተምረናል::ከያሲን ጋር አንድ በጣም የሚገርምና የማይረሳ ትዝታ አለን ::የሰፊና ሀጂከድርን ኬክ በደንብ በልተናል::ኸረ በናትህ ባለሱቅ አስፋው መድሀኔ የት እንዳለ ታውቃለህ?መሀሪ ሀይሌስ? እስቲ ጻፍልኝ አቦ::
ያንን የባላንበራስን ሸኮራ እኔስ ብሆን ቀላል በላሁ እንዴ!!!!!!አንዱን ወፍራሙን በስሙኒ::
አንቺ ቅመም:..የልኳንዳን ነገር ተይኝ አላልኩሽም:የነዚያ የቆንጆዎች የነትግሥት እና መሰረት ዓለማየሁ:ሰፈር::የሚጠጣው የሚበላው ያለበት::ግን ድሮ የታደለ ደገፋ:የስራ ቦታው ልኳንዳ ነበር::የበሬ ሽንጥ ይሸከም ነበር በኍላ ግን የሰው ሽንጥ....ይገርማል.ዳዊት ሀብተማሪያምን ሰላም በይልኝ ::አይገርምሽም ልኳንዳ ልክ እንደ ጋዛ ሰርጥ በጣም ቀጭን እና ትንሽ ናት ግን ስሟ በጣም ትልቅ ነው::ከስፖርተኛ ቡኔን እና ማስረሻን(ቮልቮ)የት ተውሻቸው ?
በሉ ቸር ያቆየን::
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 976
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

እረ ማነህ

Postby ባለሱቅ » Tue Sep 20, 2005 3:59 am

እረ አንተ ሰው ማነህ!
ሆ ሆ.... የሰፈሬን ልጆች ስም እኮ አንድ ባንድ ደረደርካቸውሳ!....
ያሲን ከማል... ወንድሜ ነው ልበልህ.... የ3ጊዜ ታላቄ.... ግን ሀይስኩል ነጌሌ ቦረና እንደተማረ ነው ማቀው... ተሳስቼ ይሆን?... አሁን ድሪሊንግ ተምሮ 3ነገር ድሪል ያደርጋል በየቀኑ.... 1ኛ የአላሙዲን ወርቅ... 2ኛ የመንግስት ታንታለም እና 3ኛ የራሱን ሚስት.... ሻኪሶ ነው ያለው.. የሁለት ሴት ልጆች አባት ሆኖልሀል... እስኪ ባክህ ከሱ ጋር ያለህን ትዝታ አጫውተኝ... አብረን ስላልኖር ብዙ አላቀውም....
ሙሁዲን ሀሰን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ታሞ እንደነበር ነው ማስታውሰው... በእውነት የት እንዳለ አላቅም... አዲሳባ ሲዘዋወር ታይቶ ነበር.. አንድ ሰሞን ወደአረቡ አለም ለመጓዝ የሆነ ነገር ሲያማክረኝ ነበር... ተሳክቶለት ይሁን አይሁን.. ጌታ ያውቃል...

ደረጀ አለሙ... የዛሬ3 አመት ክ/መንግስት የሄድኩ ጊዜ በጣምምም ታሞ .. በራቸው ላይ ቁጭ ብሎ ነው ያገኘሁት... ፊቱ አባብጦ ቁስል በቁስል ሆኖ ነበር ሳገኘው... እያገላበጥኩ ስስመው ሰው ሁሉ ገርሞት ነበር... ያ! የ9ኛ ክፍል ትዝታዬ ላይ ምስራቅ አበራን ሊመታ የነበረው ልጅ ደረጀ አለሙ ነው እንግዲህ.... አንተነህ አለሙ (የታናሹ ታናሽ)... አንድ ክፍል ነበርን ማለት ነው....

መሀመድ ረሺድ... ከ4አመት በፊት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል... የአንድ ልጅ አባትም ሆኗል... አላህ ነፍሱን በሰላም ትቀበላት....
ቡሽራ ራህመት ሰኢድ መሊክ ፀሀዩዋ ዳሬሰላም... አሁን የት እንዳሉ አላቅም.... አለም ሰፊ ናት... እዛች ሰፊ አለም ውስጥ ዋና እየዋኙ ይሆናል... ባሉበት ሰላም ይቆዩን...
መሀሪ ሀይሌ... ጓደኛዬ ባይሆንም.,.. እህቱ ትዕበ ሀይሌ ጓደኛዬ ነበረች..... የዋደራ ልጆች.... መሀሪ ኃይሌ እስከማቀው ድረስ መልካ-ዋከና ሀይድሮ-ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ላይ ሲሰራ ነበር... አስግደሞና ብርሀኔ ሀይሌ (ታናናሾቹ) አሁን የት እንዳሉ አላቅም....

አስፋው መድሀኔ እኔ 12ኛ ክፍል ማትሪክ ስወስድ እሱ ሱቅ ይጠብቅ ነበር... ከዚያ በኃላ አይቼው አላቅም... ባለበት በሰላም ይቆየን .. እስኪ ኪዲዬን(ወንድሙን) ጠይቄ አሳውቅሀለሁ.... ክ/መንግስት ስሄድ.. በየካቲት...

ታደለ ደገፋ ለካስ ሽንጥ አውራጅ ነበር... የበሬ!... እዛ ተለማምዶ ነዋ የወንድሞቻችንና የእህቶቻችንን ሽንጥ ሲመትር ሲለካ ሲሰፋ ሲቀድ የኖረው.... ካልተሳሳትኩ ከንቲባው ታደለ ደገፋ ነው አይደል ሽንጥ አውራጁ... እረ ቆይ እስኪ ጠይቀዋለሁ አዋሳ ሳገኘው... እድሜ ለዲሞክራሲ .. መጠየቅ መብታችን ነው አይደል.... ቅቅቅቅ

ድሮ ድሮ 5ኛ ወይም 6ኛ ክፍል.. ሳለሁ እነቅሩንፉድ ሰፈር የታዳጊ ኪነት አቋቁመን ነበር... እነ ብርቃየሁ አለሙ(ነፍሷን ይማረውና) ትግስት አለሙ.. እነ ትግስት አለማየሁ ወይም እህቷ .. የምንትዋብ ልጅ (--- እሸቴ) ስሟን ረሳሁት አቦ!..... አሁን እስራኤል ናት (የእዮብ እሸቱ እህት)... አንድ ላይ ሆነን እንጨፍር(እንለማመድ) ነብር... የጣሳ ከበሮ እየደለቅን... በቆርኪ የተሰራ ፐርከሽን እያንኮሻኮሽን... አሰልጣኛችን መኪያ አወል ነበረች... የምንሰለጥነው ከነ ትግስት አለማየሁ መኖሪያ ቤት በላይ ካለች ግቢ ውስጥ ነበር... የልጅቷ ስም ጠፋኝ እንጂ.... አይይይ ጊዜ.... እረ እንደውም ሻለቃ ደስታን አስፈቅደን... ኪነት ሁሉ አሳይተናል... መድረክ ተውሰን... እኔና ብርቃየሁ ነበርን መድረኩን ለማስፈቀድ የሄድነው.. እሳቸው ሻለቃው ጋር... አይ ልጅነት....

የመግቢያ ዋጋ ስሙኒ

ቀን ላይ የጌታቸው ሞገድን መኪና ተውሰን ከተማ ውስጥ እየዘፈንን ቅስቀሳ ስናካሂድ ዋልንና.. ማታ ላይ አስነካነው... ቅቅቅቅቅ
ከዚያ በኃላ በነፍቃዱ አቦምሳ መፎገሪያ ሆኜልህ ነበር እልሀለሁ... አይ ልጅነት ስንጣፍጥጥጥ ግን...

እስኪ የዛን ጊዜ ከዘፈንኩት ዘፈን አንዱን ላሰማህ...
መቸም እንደማትሰለቹኝ እርጝጠኛ ነኝ
ሳክስፎኑ ጊታሩ አፋችን ነው እንዳትረሳ..... ሳክስፎኑ ጀምሯል.....
ደረንደረረረረ... ድድድሽ
ደረንደረረረረ... ድድድሽ
የኢምፔሪአሊዝም አስከፊ ባህሎች
ዝሙትና ስካር የሱስ ተገዢዎች
እረካሽን ባህል ማራገፊያ መሆን
ጆሊ ነን እያሉ.. ጆሊ ነን እያሉ አብዮት መቃረን

ቅቅቅቅቅቅ... ሳስበው ደምበኛ ቀስቃሽ ነበርን... ለአብዮታችን.... ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ በሳቅ ልፈነዳ ነው

ከጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ኅ/ማርያም ቆራጥ አመራር ጋር ... ወደ------... ረሳሁት መጨረሻውን

ቸር ይግጠመን

ቅሩንፉድ አውቃኝ ይሆን የሉካንዳ ሰፈር ልጅ ከሆነች ታውቀኛለች.... ቅቅቅቅ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

Postby አደቆርሳ » Tue Sep 20, 2005 11:45 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!!የመሀመድ ረሺድን ሞት አልሰማሁም ነበር በውነት በጣም አዘንኩ:ደረጀ ዓለሙ ከ2ዓመት በፊትእንዳረፈ አውቃለሁ::አሁንማ ሞት ቀላል ነገር የሆነ ይመስላል::ወደፊት እንዴት ይሆን ብዬ ሳስብ መልስ አጣለሁ:: ዛሬኮ በዕድሜ 40 ዓመት መድረስ ጣር ሆኗል::ምን ዓይነት ክፉ ዘመን ላይ ደረስን አቦ???????
የእነምስራቅ አበራ: የጋሽ አህመድመሀመድ ሰኢድ ልጅ:(የባቡ ታናሽ) ወንድወሰን ገሌና ንጋቷ ክፈለውን ሞት ሳስታውስ ለቀብራቸው በከተማው ዕብድ እንኵዋን አልቀረም::ሀዘኑም ጥልቅ ነበር::ያሁኑን ያለመናገር ይሻላል::""ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች""እንዳለ ወንጌል እንድንዘረጋና ምህረትን
እንድናገኝ እግዚአብሄር ይርዳን!!!አሜን!!!!!!!!!!!!!!
ትናንት አንድ ወዳጄ በ(Pvt@) ደስ የሚል መልዕክት ልኮልኛል:: ሌሎችንም:አመሰግናችኍለሁ::
ታደለ ደገፋ ከልኳንዳ ሥጋ እየተሸከመ በየቤቱ የሚያደርስ ኩሊ ነበር(እንዴት እንዳላወክ ይገርማል)
ትንሽ ተምሮ ነበርና (ምናልባት6ተኛ ክፍል)ባለምባራስ ዓለማየሁ በንቲ ረድተውት ገንዘብ ሚኒስቴር በተላላኪነት ተቀጠረ::እዚያው እያለ የህዝብ ድርጅት ሲመሰረት ነበር ይሸከም በነበረው የከብት ሥጋ ፋንታ የሰው ሥጋ መቁረጥ የጀመረው::
ያቺን ትዝታ እንዳላወጋህ አሁን ሰዓት ያጥረኛል እና
ከቻልኩ ዘግየት ብዬ እመለሳለሁ.ደህና ያድርሰን::
Last edited by አደቆርሳ on Tue Sep 20, 2005 12:43 pm, edited 1 time in total.
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 976
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

ወይኔ በናትኅኅ

Postby ባለሱቅ » Tue Sep 20, 2005 12:22 pm

አደቆርሳዬ ቀጥል የጀመርከውንንንን

ባንተ ፅሁፍ ተመስጬ ልሞት ነው በናትህ ቀጥል ቀጥል... አታቁምምምም

ምን አይነት ነገር ነው...
ደረጀ መሞቱን አላቅም ነበር... ንጋቷ ክፈለው አርፋለች እንዴ... ወይ ጉድድድድድድድድድ... ምን አይነት ዘመን ውስጥ ነው የመጣነው ባካቹ...

እኔ እኮ ድሮ ስለሞት ሲወራ .. ወይም በኢሀፓ ወይ በሱማሌ ጦርነት ጊዜ ሽፍታ እየተባለ ስለሚገደል ሰው የማቀው እንጂ ሰው ሲሞት ሰምቼ አይቼ አላቅም ነበር

ምን አይነት በላ ነው ባካቹዱአ በጣምም ያስፈልገናል

እስኪ አጫውተኝ.. አደቆርሳ
ባንተ የትዝታ የማስታወስ ችሎታ ቅናት ሞቼ ላብድ ንው

ሰው ከሞተ ያብዳል እንዴ>

ምን አይነት ነገር ነው...
ከዚህ በፊት የፃፍከውን አይቼ እኮ ስራ መስራት ሁሉ አቅቶኝ ነበር... የሆነ ነገር ስቆርጥ በስተት ሱሪዬን ቀድጄ ተናድጃከሁ.. በትዝታ ይዘኸኝ ሄደህ..

ቱ ምን አይነቱ ልጅ ነህ ግን

ታዘብኩህ

በል ቸር ሰንብት

ወዳጅህ ነኝ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

በማንበብ ብቻ ለቆይ ለግዚው

Postby ፖስታቢትሰፈረ » Tue Sep 20, 2005 1:50 pm

ባለ ሱቁ እንዳለው የጂነኔረስን ጋፕ ስላለ የኔ ተሳትፎ ማንበብ ብቻ ሲሆን.. አንዳንድ የማውቀውን ጥያቄዎች ለመመለስ እሞክራለው
1. አስፋው ምድሀኔ የሚኖረው Chicago ሲሆን የወዩ ማህበር አባል ነው...

2. አስግዶም ና ብርሀኔ ሀይሌ ያሉት Nairobi, Kenya ነው.......
ፖስታቢትሰፈረ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Thu Sep 08, 2005 1:51 pm
Location: ethiopia

Postby ወቤ(ጃሎ) » Tue Sep 20, 2005 2:17 pm

ይድረስ ለአዶላ ወዩ ልጆች: ባለሱቅ -- ስለቀድሞ ስፖርተኞች ባልከው ላይ : ኮርማ ዱግዳ በእውነቱ ፈጣን ቀልጣፋ ስፖርተኛ ነበር:: የቦሬ ልጅ ረዥሙ ያልከው ናስር አብድሽኩር ባጣም የሚደነቅ ልጅ ነው::የቅርብ ጓደኛዬም ነው:: አሁን ይርጋ ጨፌ መምህር ነው:: ሌላው ድሮ ከማስታውሰዉ ልካስ (ልጅካስ)የሚባል ከዋደራ የሚመጣ መምህር በወፍራም ሰውነቱ የሚጫወተው ኳስ በጣም ይገርመኝ ነበር:
ወቤ(ጃሎ)
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Wed Jul 28, 2004 6:57 pm

ስላም የወዩ ልጆች

Postby ቅሩንፉድ » Tue Sep 20, 2005 4:22 pm

የግል እንዴት ነሽ አደቆርሳ አንተስ የምትገርም ነህ::የክብረመንግስት ልጅ አንድ የማታውቀው ያለ አይመስለኝም:: ዳዊቴን ታውቀዋለህ ሕይወትንስ አስተማሪዋን የሚያስታውስ የለም ድሮ በጣም ትንንሾች ሆነን ለክለክቾ ስንጫወትበአጠገባችን ስታልፍ የምንጫወትን ውርውረን የምናያት:: አንድ ጊዜ በአጠገባችን ስታልፍ አይ ጸጉር ተተኩሳነውተተኩሳነው ስንባባል መጋኛ ይተኩሳቹ ስትለን አፋችንን ይዘን በሳቅሞትን የዛን ጊዜ ከፊቴ የማትጥፋው ልጅ ባልሳሳት የጃማ ቤት ልጅ መስለችኝ::ስለልኳንዳ ያልከው ልክነህ የጠፋችብ ልጅ ኮኮብ እሽቱናት አሁን እስራሄል ናት ያለችው::አንተ ማን እንደሆንክ በፍጹም አላስታወስም:: ታሪኩን ስለማውቀው በሳቅ ነው የሞትኩት ዘፈኑን ማስታወስህ ራሱ ገርሞኛል ግን አወቀዋለሁ ስል አባል አለነበርኩም:: ቀልቤ ሌጌ የት ጠፋ በሉ እስከሚቀጥለው :!:
Last edited by ቅሩንፉድ on Tue Sep 20, 2005 4:31 pm, edited 1 time in total.
ቅሩንፉድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 346
Joined: Fri Apr 15, 2005 9:07 pm
Location: germany

Postby አደቆርሳ » Tue Sep 20, 2005 4:25 pm

ፖስታቤትሰፈረ ትክክልነህ ግንኮ ክብረመንግሥት ታሪከብዙ ናት የምታውቀውን ብታነሳ ሁላችንም እናውቀው ይሆናልና እባክህ ከትዝታዎችህ ደስ የሚሉህን አውጋን::ስለሰጠኸኝ መልስ ከልብ አመሰግና
ለሁ::አስፋው መድሀኔ ሰላምታዬ ይድረስህ::
ወቤ ጃሎ በጣም ተቀራራቢ ክላስ እንደነበርን እገምታለሁ 7ተኛ ምን ክፍል ነበርክ?
ቅድም ወዳቆምኩት ልመለስ:
ኮክና ዘይቶን የሚገዙት ያራዳ ልጆች ናቸው እኛ አንገዛም በየማሳው እየሄድን መስረቅ እያለ:ሳንቲም አናወጣም ሳንቲሙም ያኔ ለኛ ሩቅ ነበር ላራዳ ልጆች ግን..................::አንድ ቀን ያሲን ከማል እኔ ዘይቶን
የሚሰረቅበት ማሳ እንድወስደው ጠየቀኝ በማግስቱ በጠዋት ተቀጣጥረን ከሙሁዲን ጋር መጣ እኔም ከኔየተሻለውን: ሲሳይ መርሻን ጠራሁና ተያይዘን ከሚካኤል በታች ወዳለው ወደ አባባ...........ማሳ አመራን ያሲን ከማል መቼም አቸኳኮሉ ለብቻ ነበር:ድምጽ አጥፍተን ገብተን ሲሳይ ወጥቶ ሲያራግፍ እኛ እንለቅማለን ሳናስበው የሚያስፈራ የሰው ድምጽ አምባረቀብን ሲሳይ እንኳን ከዛፍ ላይ ወርዶ ስናመልጥ ያሲንከማል ብንጠብቀው ብንጠብቀው አይመጣም::እንደያዙት አውቀን:ስለረፈደ ወደ ት/ቤት ሄደን የሆነውን ለነገብርዬ ነገርናቸው:እሱን ያገኘነው በረፍት ነበር::ምናልባት ያንን አመት ሙሉ አላናገረኝም::በየት በኩል እንደሚሮጥ ስላላወቀ ደንግጦ ወደሰውዬው ሲሮጥ ነበር የያዙት:
ሲጠይቁትም የማን ልጅ እንደሆነ ስላልተናገረ በጅራፍ ሁለቴ ቀምሶ የኪሱን አራግፎ ነበር የተመለሰው::ገብረክርስቶስ ተስፋዬ ረዥም ግዜ ይስቅበት ነበር::አሁን ለገደምቢ እንዳለም አውቃለሁ::
ወቤ ጃሎ ክብረመንግሥት አራዳ መሀል እንድ የቦክስ
ሪንግ እንደነበር ታስታውሳለህ?ባለሱቅ ከነታሪኩ እንደምትነግረን አልጠራጠርም::
ቸር ያቆየን::
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 976
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

ሞት-እምቢ

Postby ባለሱቅ » Tue Sep 20, 2005 5:46 pm

አንድ ጊዜ.... የእንግሊዘኛ አስተማሪያችንን (ሽንክሌ) አንድ ተማሪ ይጠይቀዋል...
ቲቸር DIZZY ማለት ምን ማለት ነው ብሎ....አስተማሪው ምሳሌ ሲፈልግ እያለ

በላይ የሚባል የሜጫ ሰፈር ልጅ.. ቀጭኑ ረጅሙ.... እጁን ያነሳና

ቲቸር .. እንደጭር ያለች ዶሮ ማለት ነው አይደል.. ይለዋል......

ኖ ኖ ኖ ኖ .. እንደሱ ሳይሆንንን.. ብሎ አሁንም ሲጨነቅ

ባትሪ.. የሚባል ከአርባምንጭ የመጣ ግዋደኛችን... እጁን አንስቶ...
ቲቸር እንደቢሆኔነኝ (ሞት-እምቢ) ማለት ነው አይደል ... ብሎ ያሳቀን ትዝ አለኝ
ለምን ትዝ እንዳለኝ አላቅም

ምናልባት የዚህን ቤት ጭርታ አይቼው ይሆን.. ወይስ እኔው ጭር ብዬ ይሆን... የግል የት ጠፋሽ አንቺ ወርቅ ልጅ


ፖስታቤትሰፈሬ...
አውቃለሁ የእድሜ ልዩነት ብዙ ብዙ ነገር እንደለያየን... አንተ ምታቀውን እኛ አንቅም... እኛ ምናቀውም አንተ አታቅም.. እኔና አደቆርሳ ግን ትንሽ ትንሽ የተግባባን ይመስለኛል.. ንባካል ባላቃቸውም በስም የማቃቸው ብዙ ብዙ ልጆች እየጠራልኝ እያዝናናኝ ስለሆነ .. በደስታ ፍንክንክክክ ብዬ ልሞት ምንም አልቀረኝም... ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ውቤ(ጃሎ) ናስር አብዱሹኩርን የማቀው የጎረቤታችንን ልጅ ሲያባልግ ነው... መስርዬ(ሰይድ ናጂ እናት) ቤት ነበር የተከራየው... ይዟት ሲገባ በቀዳዳ እንመለከት ነበር.... ምን እንደሆነ አትጠይቀኝ...ቅቅቅ... እግርኳስና ቫሊቦል ሲጫወት ግን ትዝ ይለኛል ጎበዝ ነበር... የልጅ-ካስ አጭሩ ድቡልቡሉ መላጣው.... በዚያ ቁመቱ ሲሾር... አንዴ ናስር ነው መሰለኝ መላጣው ላይ ብሎታል Vአሊቦል ሲጫወቱ.... ቅቅቅ.... ከልጆቹ ጋር አንድ ሴሚስተር ቤታቸው አጥንቻለሁ... አስጠንቻለሁ ልበልህ ይሆን... ቅቅቅቅ ከተስፋዬ ጎሚስታው ቤት በታች ነበር ቤታችው.... አሁን የት እንዳለ አላቅም

ቅሩንፉድ ዘፈኑን አስታውሰሽ... የኪነት ቡድኑን አስታውሰሽ.. ታሪኩን አስታውሰሽ እኔ አንድ መናጢ ደሀውን ከረሳሽኝ እታዘብሻለሁ... ከ6ሴቶች መሀል አንድ ወንድ እኔ ብቻ ነበርኩ እኮ... ዘፋኝም ጃሰሪም ሳክስፎን ተጫዋችም ባፍ... ቅቅቅቅ
ኮኮብ እሸቱን ስላስታወስሽኝ አመሰግንሻለሁ.... ድምፅዋ ጆሮዬ ላይ አቃጨለብኝ..... ከርቀት የሚሰማ ድምፅ ነበራት.... ቅቅቅቅቅ

እስኪ ቸር ይግጠመን....

አውርተን እንዳናልቅና.....

እወዳቹዋለሁ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ከአያልቅበት ግጥሞች ለዛሬ እናንተ ግጠሙ!

Postby ራስብሩ » Tue Sep 20, 2005 7:51 pm

እንዴት ዋላችሁ አዶላዎች:ሰላም ለናንተ ይሁን!!
የአራዳው ጨዋታ ደርቶ የለምእንዴ?
ፖስታቤትሰፈረ በጣም ጠፍተህ ነበር ዛሬ በመምጣትህ ደስ ብሎናል::በጨዋታ(በትዝታ)መሀል የጊዜ ልዩነት ሊኖር እንደሚችል ይታወቃል::
ነገር ግን መድረካችን ሁለገብ እንዲሆንእና በደንብ እንድንገናኝ ሁላችንም የፈለግነውን የየራሳችንን ትዝታ እና ገጠመኝ በመጻፍ መድረካችንን ስፊ እንድናረገው ይሁን::ከሰፈርህ ልጆች ሁሉንም አውቃለሁ:, ዛሬ ስለ ገብርዬ(ገ/ክርስቶስ ተስፋዬ)
ሲነሳ ያ የናንተ ሰፈር በሙሉ ታወሰኝ:: : ከገብርዬ እና ከነያሲን ጋር አብሬ ተምሬያለሁ.: በነገራችን ላይ የያሲን ወንድም ሸምሱ ከማል አሁን የት ነው?::ከ11ዓመት በፊት አዋሳ ተገናኝተናል::
የግልነሽ በዚያ በፈረንጅ ውሀ ዳገት በነአባቡሎና በነ ጌቱ ዘውዴ ሰፈር በትዝታ አንሸራሸርሺኝኮ::
ያደኩበት የት/ቤቴ መንገድ::
ቸር ይግጠመን:ወዳጃችሁ ራስብሩ ነኝ.:
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

እንደምን ዋላቹ ወዮዎች

Postby ቅሩንፉድ » Tue Sep 20, 2005 9:25 pm

ባለሱቅ ኪነታቹ ውስጥ እኔ አልነበርኩበትም የነበሩትን ስዎች በከፊል አውቃችሁለው:: የወንድ ዘፋኝ አንተ ብቻ ከነበርክ በጣም ትታወቃለህ ማለት ነው:: :lol: :lol: :lol: የማቃችው ልጆች ውስጡ ስለነበሩ እንዲያውም አንዱ ክራር መቺ መድረክ ላይ ከወጣ በኃላ የክራሩ እንጨት እየደጋገመ እየወደቀበት ስውን ሁሉ በሳቅ ጨርሶል እረባካቹ ወሬውን ሁሉ ጨርስን የሚወራም እንዳናጣ የክብረ መንግስት ልጆች ሁላቹም ከያላቹበት ብቅ በሉ ጨዋታ በስፊው ሲሆን ነው የሚደራው::
ቅሩንፉድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 346
Joined: Fri Apr 15, 2005 9:07 pm
Location: germany

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests