መዝሙረ ተዋህዶ ብቻ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

መዝሙረ ተዋህዶ ብቻ

Postby ምሪ » Fri Sep 16, 2005 8:05 pm

እስኪ የየቀኑን መዝሙር ለመዘመር እንሞክር ከእምነቱ ውጭ ያላችሁ እባካችሁ ፖስት አታድርጉ
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

ለስላሴ የሚዘመር

Postby ምሪ » Fri Sep 16, 2005 8:13 pm

የስላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሀል ሚካኤልን ከፊት
አዕላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍርሀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት

የስላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ
በፅድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ (2)

አዝ....

የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር
ሲያወድስ ይኖራል የስላሴን መንበር
ፅድቅና ርህራሄ የተሞላ ሰማይ
እግዚያብሄር ያድለን በትንሳኤ እንድናይ (@)
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

ስላሴን አመስግኑ

Postby ትትና » Sat Sep 17, 2005 9:29 am

ስላሴን አመስግኑ(2) የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ(2)
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
አለማትን ሁሉ ለየፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጧት እስከማት

ብራብ በስላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም ማብላኬ እረካለሁኝ
ስላሴ አምባዮ ክብሬም ናቸውና
ሁሌም ይመሩኛል በሄወት ጎዳና

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክተ ሰማይ የሚዘምሩለት
እኛም ያዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይ በምድር እንጠራሀለን
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

ምን ሰማህ ዮሐንስ

Postby ዲያና » Sun Sep 18, 2005 12:22 am

ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ(2)
ህጻን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ
(2)
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለ ደስታ(2)
ምን አይነት ድምጽ ነው ምን አይነት ሰላምታ
(2)

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደ ክብር
እንዴት ሊገባን ነው የእናታችን ፍቅር


በረሀ ያስገባ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራእይ እንዴት ያለ ብሥራት
እንደ አዲስ ምሥጋና ሰልቶ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ


ክሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍጹም
በማህጸን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ
Pray for Oneness!!!
ዲያና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 364
Joined: Tue Mar 09, 2004 2:25 am

ዲያናና ትትና ዝማሬ መላዕክት ያሰማችሁ

Postby ምሪ » Sun Sep 18, 2005 12:01 pm

እመቤቴ ጥላ ከለላዬ
እረዳቴ የገነት ሙሽራ
የገነት ሙሽራ
የገነት ሙሽራ
ማርያም የልዑል ማደሪያ
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

Postby አክየ » Sun Sep 18, 2005 12:40 pm

ወንድሞቸ እህቶቸ መልካም ፕሮግራም ነው ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን እኔም እሳተፋለሁ እንዲያው አጋጣሚ ጎራ ብየ ነው እንጅ ተዘጋጅቸ ስመጣ እጽፋለሁ በርቱ
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

ምስጉን ነው

Postby ምሪ » Mon Sep 19, 2005 7:17 pm

ምስጉን ነው የተመሰገነ
ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
ይመስገን ይመስገንልኝ
ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ
የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ
ያጣሁትን ካንተ አግኝቻለሁ
ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ

ማቄን የቀደደው ደስታ አስታጠቀኝ
ባዶ የነበርኩት ሁሉም ተሰጠኝ
ሰጪም ነሺም እግዚያብሔር ብቻ ነው
የሰው ድርሻ በር ማንኳኳት ነው

እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም
መሰረቱ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም
ስትሰጠኝ የሚታየውን
እንዳትነሳኝ የዘላለሙን

ቢሰጥ አያልቅበት ለጋስ ክቡር ጌታ
ሁሉን ከወነልኝ በልዩ ችሮታ
ድሆች ስንሆን ሁሉ አለንና
አምላካችን ይድረሰው ምስጋና
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

ደስ ይላል መልክትህ እግዝአብሀር ይባርክህ!!!

Postby አክሱምማርያም » Mon Sep 19, 2005 10:29 pm

ድንግል ማርያም(የእየሱስ እናት) ታማልድህ ትጠብክህ በንሱህ ሀይማኖትህ ያጽናህ እስከመጨረቫው አሜን!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር አሜን!!!::
አክሱምማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 359
Joined: Tue Sep 13, 2005 4:04 am
Location: ethiopia

Postby ምሪ » Wed Sep 21, 2005 9:34 pm

ቸርነቱ በኛ ላይ ስለበዛ
ቸርነቱ በኛ ላይ ስለበዛ
ይክበር ይመስገን
መድሀኒያለም የአለም ቤዛ
ይክበር ይመስገን
መድሀኒያለም የአለም ቤዛ
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

ቢኖ ሊላ ቦታ የጻፈውን አንድ ቦታ ቢሆን ብዬ ነው

Postby NATHRATHE » Wed Sep 21, 2005 9:49 pm

የወደደኝ ጌታ

የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው
ብዘምርለትም ያንስበታል ይሄ
ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝከኝ
ሰባራውን ድድልድይ ገጥመህ ያሳለፍከኝ

በያሪኮ መንገድ ስለምን ቁጭ ብየ
ብርሀን እጅግ ናፍቆኝ ከሰው ተገልየ
የብርሀን ጌታ ወደኔ መጣና
አይኔን አበራልኝ በጁ ዳሰሰና

ልውብዙ ዘመናት አልጋ ላይ ተኝቸ
የሚረዳኝ አጣሁ ጠሉኝ ዘመዶቸ
የኔጌታ አምላኬ ወደኔ መጣና
አልጋህን ተሸከም አለኝ ፈወሰና

አሰራ ሁለት አመት ደም እየፈሰሰኝ
ምራቅ እየተፉ ሁሉም ቢያንቋሽሹኝ
የጌታየን ልብሱን ጫፉን ብዳስሰው
ሀይልም ከእርሱ ወጣ ደሜን ቀጥ አረገው

ሰከራም ዘማዊ ወንበዴ ነበርኩኝ
ያመጸኞች መሪ ደምን ያፈሰስኩኝ
ዛሬ ግን ታሪኬን ጌታ ቀይሮታል
ለሀያሉ ጌታ ምስጋና ይገባል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ውለውላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
_________________
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

12-1-98 ቅዱስ ሚካኤል

Postby ምሪ » Thu Sep 22, 2005 6:31 pm

በየቀኑ ያሉትን መዝሙሮች ለመዘመር እንሞክን ለምሳሌ ዛሬ ቅዱስ ሚካኤል ስለሆነ በለቱ እንዘምር
Last edited by ምሪ on Thu Sep 22, 2005 7:08 pm, edited 1 time in total.
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

Postby ምሪ » Thu Sep 22, 2005 6:46 pm

ለመዝሙሩ ዝማሬ ህይወት ያሰማልን
Last edited by ምሪ on Thu Sep 22, 2005 6:55 pm, edited 1 time in total.
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

12-1-98 ቅዱስ ሚካኤል

Postby ምሪ » Thu Sep 22, 2005 6:49 pm

ቅዱስ ሚካኤል (3) ነብሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ

አንተ ስለሆንክ ሚካኤል
የአምላክ ባለሟል ሚካኤል
ልመናቅ ፈጥኖ ሚካኤል
ካምላክ ይቀርባል ሚካኤል
የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው
ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው (2)

ደዌ የጸናበት ሚካኤል
ባንተ ይድናል ሚካኤል
በአደባባይህ ሚካኤል
ምስክር ሆኗል ሚካኤል
ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ
በቃል ኪዳንህ ህይወቱ ዳነ (2)

ካምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል
ክብርህ ያበራል ሚካኤል
ለጎስቋላው ሰው ሚካኤል
መጠጊያ ሆኗል ሚካኤል
ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ
ለምኖ አግኝቷል ካምላክ በስሙ (2)

በብሉይ ኪዳን ሚካኤል
ከአምላክ ተልከህ ሚካኤል
ሕዝበ እስራኤልን ሚካኤል
ነጻ ያወጣህ ሚካኤል
በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ
በተአምራትህ ትፈውሳለህ (2)
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

R.NATHRATHE

Postby ቢኖ » Thu Sep 22, 2005 7:10 pm

በጣም ነው የማመሰግነው እኔ እራሴ በአዲስ እርዕስ
ለመጻፍ ፍላጎቴ አልነበረም በስህተት ነበር ፍላጎቴ የነበረው ምሪ በከፈተው አምድ ነበር መሳሳቴን ያውኩት ከጻፍኩ ብኋላ ነበር :: አሁን ግን መጻፍ በፈለኩበት ቦታ አስተካክለህ ስላስቀመጥክልኝ በጣም
ነው የማመሰግነው ::
እገረ መንገዴን ይሄን መዝሙር ጋብዠሀለው
ወደማደሪያው ገብቼ

ወደማደሪያው ገብቸ ልስገድ ለእግዚአብሔር(2)
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር(2)

አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአጸደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ስለስሙ ክብር ውድቄ እነሳለሁ(2)

በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በዕዕታ(2)

አስር አውታር ባለው በበገና
በመላዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምቶልኛልና(2)

ለስሙ ልንበርከክ ለዕርሱ እንደሚገባ
ስለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወዳደባባዩ በዕልልታ ልግባ(2)

አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ለሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቸን ዘርግቼ(2)

ውሰብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ውለመስቀሉ ክቡር
ቢኖ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 19
Joined: Sat Jul 30, 2005 1:28 pm
Location: ethiopia

14-1-98አቡነ አረጋዊ

Postby ቢኖ » Sat Sep 24, 2005 6:46 pm

አባ አቡነ

አባ አቡነ አባ አቡነ(3)
መምርነ አባ አረጋዊ(2)እኽ

ውስብሐት ለግዚአብሔር
ውለወላዲቱ ድንግል
ውለመስቀሉ ክቡር
ቢኖ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 19
Joined: Sat Jul 30, 2005 1:28 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests