መዝሙረ ተዋህዶ ብቻ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ወርቅነች » Fri Dec 30, 2011 8:31 am

እግዚአብሄር ይምሰገን እግዚአብሄር ይምሰገን
ማርያምን ደክሎ እየሱሰን ለገሰን
እግዚአብሄር ገፈኛው ማርያምን ፍጥሮልን
መልሶ እንደሰው ማርያምን ደከለልን
እኔም ይመስለኛል የሰው ልጅ ሲወልድ
አንተም ልጅህን ሰትወልድ
እንደ እግዚአብሄር ደክላት አቡና ጴትሮሰን ትወልድለሀለች
ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና ትላለች :lol: :lol: :lol: :lol:

እግዚአብሄር አይታክተው ሶጦታው ብዙ ነው
አንተንም ያሰርግዛል እሱ ምንም አይታክተው :lol: :lol:
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby እማማ » Sat Dec 31, 2011 9:18 pm

ቤተልሔም (4) ተማርን ካንቺ ፍቅር ሰላም
ተገኝቶብሽ መድሐኔዓለም (2)

የቃል ሥጋ ምሥጢር ቤተልሔም የተገለጠብሽ ቤተልሔም
ፍጹም ተዋህዶ ቤተልሔም በእምነት ያየንብሽ ቤተልሔም
የድህነት ቤታችን ቤተልሔም አንቺ የሰላም ስፍራ ቤተልሔም
ተገኝተን ካንቺ ዘንድ ቤተልሔም እናድንቅ ይህን ሥራ ቤተልሔም

ትንቢት ተነግሮለት ቤተልሔም ኤፍራታ እንደሚያድር ቤተልሔም
ስሙም ሀያል አምላክ ቤተልሔም ሊባል ድንቅ መካር ቤተልሔም
የመስቀልን ጉዞ ቤተልሔም ሥራ ሲጀምር ቤተልሔም
ተወለደ አማኑኤል ቤተልሔም ሊያኖረን በክብር ቤተልሔም

ያከበረሽ አምላክ ቤተልሔም ፍቅር ያሸነፈው ቤተልሔም
ጊዜው ሲደርስ መጥቶ ቤተልሔም ተወስኖ አየነው ቤተልሔም
በአጭር ቁመትና ቤተልሔም በጠባብ ደረት ቤተልሔም
ወርዶ ቢገኝባት ቤተልሔም ምድርም ደነቃት ቤተልሔም

እጅግ ያስገርማል ቤተልሔም አምላክ ሰው ሲሆን ቤተልሔም
ባክነን ለነበርነው ቤተልሔም ዘመድ ሲያደርገን ቤተልሔም
ምስጋና አቀረበ ቤተልሔም በሰማይ በምድር ቤተልሔም
ትህትናን ሲያስተምር ቤተልሔም ልጅ ከእናቱ ጋር ቤተልሔም
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Sat Dec 31, 2011 9:29 pm

ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ (2)

አንዲት ብላቴና የአሥራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላዕክት አዋጅ
በህቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ

ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋህዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ

አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
ከምድር ተፈልጎ እንደ አንቺ አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንጹህ ስለሆነች
ለአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች

ፍጹም ድንግልና ክብር የተሞላች
እንደምን አምላክን በማህጸን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Sat Dec 31, 2011 9:36 pm

በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ (2)
ቤዛ ኩሉ ዓለም (2) ዮም ተወልደ (2)

በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ (2)
የዓለም መድሀኒት (2) ዛሬ ተወለደ (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Sat Dec 31, 2011 9:54 pm

እሰይ እሰይ ተወለደ
እሰይ እሰይ ተጠመቀ
ከሰማያት ሰማይ ወረደ (2)
ከድንግል ማርያም ተወለደ::

እርሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ ቸሩ አባታችን እሰይ እሰይ
እርሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ መድሀኒታችን እሰይ እሰይ
መች ትገኝ ነበረ እሰይ እሰይ ገነት ምድራችን እሰይ እሰይ

ብርሀን ወጣላቸው እሰይ እሰይ ለእውነት ወገኖቹ እሰይ እሰይ
በጨለማ ጉዞ እንዲያ ሲሰለቹ እሰይ እሰይ

እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ አንድያ ልጁን እሰይ እሰይ
እርሱ ወዷልና እሰይ እሰይ እንዲሁ ዓለሙን እሰይ እሰይ

እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ ከሰማይ ወደኛ እሰይ እሰይ
ወገኖቹን ሊያድን እሰይ እሰይ ከክፉ ቁራኛ እሰይ እሰይ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Sat Dec 31, 2011 10:04 pm

እምሰማያት ወረደ ወእምማርያም ተወልደ ተወልደ (2)
አኸ ከመ ይኩን ቤዛ (2) ለኩሉ ዓለም ለብሶ ሥጋ ማርያም

ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ (2)
አኸ እንዲሆነን ቤዛ (2) ለዓለሙ ሁሉ ለበሰ የማርያምን ሥጋ


አስተርአየ ገሀደ (4)
በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ (2)

አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ (2)
በድንግል ማርያም ተከናወነ (2)

ኢየሩሳሌም (3) በሆን
አምላክ ሲወለድ ባየን

እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆን በሆን
አምላክ ሲወለድ ባየን

እንደ እረኞች ወይ ሰብዓሰገል በሆን በሆን
አምላክ ሲወለድ ባየን


በቤተልሔም ተወልደ (2) አማኑኤል (2)
እምዘርዐ ዳዊት (4) ተወልደ አማኑኤል

ትርጉም

በቤተልሔም የተወለደ አማኑኤል
ከዳዊት ዘር ነው የተወለደው
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

የጽድቅ በር ነሽ

Postby እማማ » Fri Feb 03, 2012 2:11 am

የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹህ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን (2)

እመቤታችን ለኛ ምርኩዝ ነሽ
እመቤታችን ከለላም ሆንሽን
እመቤታችን የእሳት ሙዳይ
እመቤታችን እሳት ታቀፍሽ
እመቤታችን በብርሀን ተከበሽ
እመቤታችን ወርቅ ለብሰሽ
እመቤታችን ከሴቶች ሁሉ
እመቤታችን አብ መረጠሽ

እመቤታችን ድንግል ሆይ ልጆችሽ
እመቤታችን ዘወትር ይጠሩሻል
እመቤታችን ስምሽን ለልጅ ልጅ
እመቤታችን ያሳስቡልሻል
እመቤታችን በተሰጠሽ ጸጋ
እመቤታችን በአማላጅነትሽ
እመቤታችን ምህረትን አሰጪን
እመቤታችን ከመሀሪው ልጅሽ

እመቤታችን ያልታረሰች እርሻ
እመቤታችን ዘር ያልተዘራባት
እመቤታችን የህይወትን ፍሬ
እመቤታችን ሰጠችን የኛ እናት
እመቤታችን የታረደው መሲህ
እመቤታችን እናቱን ወደዳት
እመቤታችን በቀኙ ቆማለች
እመቤታችን ድንግል እመቤት ናት

እመቤታችን የእውነት ደመና
እመቤታችን ዝናብ የታየባት
እመቤታችን ወዳናለች ድንግል
እመቤታችን የታተመች ገነት
እመቤታችን ክብርት ለሆነችው
እመቤታችን ኑ እንዘምርላት
እመቤታችን ደስ ይበልሽ እንበል
እመቤታችን ለብርሀን እናት

የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹህ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Fri Feb 03, 2012 2:17 am

ለተክለሀይማኖት ጻድቅ መጠነ በዝሀ ህማሙ (2)
ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ (2)

እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአጽሙ (2)
ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ (2)

እምነ አድባራት ኩሎነ ዘተለዓለት በስሙ (2)
ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ (2)

ኢየሱስ ክርስቶስ እንተቀደሳ በደሙ
ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ቸርነትህ ነው

Postby እማማ » Fri Feb 03, 2012 2:45 am

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ (2)

መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሀብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ

አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
በአንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ሥራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ

በሰው እጅ መመካት አቁሜያለሁ
ረዳቴ አንተ ነህ አውቄያለሁ
አንተ ከጠበቅከኝ በህይወቴ
ቅጥርህ አይደፈርም መድሀኒቴ
የኔን ሥራ ተወው ተግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
እየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Sun May 19, 2013 2:37 am

መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላዕክት ሚካኤል
ሰዓል ወጸሊ በእንቲአነ
አእርግ ጸሎትነ
ቅድመ መንበሩ ለመድሀኒዓለም
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ሰላም ወገኖች

Postby እማማ » Sat Feb 22, 2014 7:32 am

እንኳን ለታላቁ ዓቢይ ጾም በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ስለኛ ብሎ

Postby ጎነጠ » Mon Feb 24, 2014 9:48 pm

ስለኛ ብሎ ልጅሽ ተሰቅሎ
ልብሽ በህእዘን ተወግቶ ቆስሎ(2)
ከመስቀሉ አውርደውት
በአንች ደረት ደግፈውት
ያለቀሽው የእንባሽ ብዛት(2)
ይጠብልን የኛን ህእጢአት(2)
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests