መዝሙረ ተዋህዶ ብቻ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby እማማ » Fri Oct 08, 2010 3:51 am

አለፍኩኝ ድንግል ማእበሉን
አለፍኩኝ ድንግል ውጣ ውረዱን
ምርኩዜ ስለሆንሽ ስጠራ ስምሽን (2)
አለፍኩኝ ድንግል በእመቤቴ ምልጃ
አለፍኩኝ ድንግል ወንዙን ስሻገር
አለፍኩኝ ድንግል ያባረረኝ ጠላት
አለፍኩኝ ድንግል ቀረ ሰምጦ ባህር
አለፍኩኝ ድንግል ከበሮውን ላንሳ
አለፍኩኝ ድንግል እንደ ሙሴ እህት
አለፍኩኝ ድንግል ምስጋና ልሰዋ
አለፍኩኝ ድንግል ለዓለም እመቤት
አለፍኩኝ ድንግል ወንድሞች ቢሸጡኝ
አለፍኩኝ ድንግል አሳልፈውኝ
አለፍኩኝ ድንግል በባእድ ከተማ
አለፍኩኝ ድንግል ድንግል ሾመችኝ
አለፍኩኝ ድንግል በቅን የማመልከው
አለፍኩኝ ድንግል ልጅሽ ክርስቶስ
አለፍኩኝ ድንግል ምልጃሽን አጽድቆ
አለፍኩኝ ድንግል ሰጥቶኛል ሞገስ
አለፍኩኝ ድንግል በስምጥ ሸለቆ
አለፍኩኝ ድንግል ሆኜ በአጣብቂኝ
አለፍኩኝ ድንግል የምደገፍበት
አለፍኩኝ ድንግል አንዳች ሳይኖረኝ
አለፍኩኝ ድንግል በአንቺ ተርፌያለሁ
አለፍኩኝ ድንግል ምርኩዝ ሆነሽኝ
አለፍኩኝ ድንግል ሰው የለኝምና
አለፍኩኝ ድንግል ድንግል አትራቂኝ
አለፍኩኝ ድንግል አንቺ ነሽ እናቴ
አለፍኩኝ ድንግል የማትሰለቺኝ
አለፍኩኝ ድንግል ውለታዋ ብዙ
አለፍኩኝ ድንግል የድንግል ማርያም
አለፍኩኝ ድንግል እርሷን ለኔ የሰጠ
አለፍኩኝ ድንግል ይክበር ዘላለም
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ያከብርዋ ለሰንበት

Postby እማማ » Fri Oct 08, 2010 4:07 am

ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት
ወኩሉ ፍጥረት ዓሣት ወአናብርት
እለውስተ ደይን ያእርፉ ባቲ
እስመ ባቲ አእረፈ እምኩሉ ግብሩ

ያከብሯታል ሰንበትም መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በገነት
ፍጥረታት በሙሉ ዓሣዎችና አንበሪዎች
በመቃብር ያሉም ያከብሯታል
አምላክ በርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

አለማመኔን እርዳው

Postby እማማ » Wed Dec 15, 2010 8:42 pm

አለማመኔን እርዳው ጌታዬ (2)
አንተ ነህና መሸሸጊያዬ አለማመኔን እርዳው ጌታዬ

ፍሬ ያላዘልኩኝ ብሆንም ጎስቋላ
ነፍሴ አብራህ ትኑር በማደሪያህ ጥላ
አታውጣኝ ከቤትህ ባጣም ቅድስና
ይቺን ዓመት ተወኝ ጉልበቴ እስኪጸና

ያልጸናው ህይወቴ ቢያስቸግርህ ላልቶ
እስኪቆም ታገሰኝ ጉልበቴ በርትቶ
እንደ ቃልህ ባልኖር ደስ ባላሰኝህ
ዛሬም ከኔ ጋር ኑር በጸናው ኪዳንህ

ለምጼ እጅግ በዝቶ ከሰዎች ብገለል
ልትዳስሰኝ ፍጠን ምህረትህን ልታድል
ደባልቀኝ ከመንጋው ከበረታው ወገን
አዘንብል ወደኔ በፍቅርህ ልሸፈን

መዓዛዬን ለውጥ ጠረኔን ቀይረው
እንደ ናርዶስ ሽቱ የከበረ አድርገው
ቅረበኝ በፍቅርህ በደሌን ትተኸው
ሳበኝ በምህረትህ ቤቴን ደስ አሰኘው
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ሚካኤል ስለው

Postby እማማ » Thu Dec 16, 2010 2:14 am

ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍጹም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ (2)

ከአለቆች ጋራ ሕዝቡን የመራ
የሚመላለስ በእሳት ተራራ
ባሕሩም ሸሸ ከማደሪያው
የጌታ መልዓክ ሲያናውጸው

ዘንዶውን አሸንፏል
ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ከባዱ ጋራ ሜዳ ሆኖኛል
የወህኒው መዝጊያም ተከፍቶልኛል
አልናወጥም ከቶም አልፈራ
የጌታ መልዓክ ነው ከኔ ጋራ

ዘንዶውን....

ትዕቢተኛውን አሸንፎታል
ዲያብሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል
ታላቅ ጸጥታ በሰማይ ሆነ
እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ

ዘንዶውን....

ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሹ
የሚቃወሙን አጥብቀው ሸሹ
ታላቁ መልዓክ ከፊት ቀደመ
ታሪክ ተሠራ እንባችን ቆመ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

የጥበብ ሰዎች መጡ

Postby እማማ » Tue Jan 04, 2011 12:49 am

ሰማይና ምድር የማይወስኑት (2)
ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ (2)
አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ (2)

የጥበብ ሰዎች መጡ (2) ሰምተውት በዜና
እያበራላቸው ኮከቡ እንደ ፋና (2)

ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ (2)
ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ (2)
ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድህን (2)
ኩነኔን አጥፍቶ ክብሩን ሊያወርሰን (2)

ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም (2)
ሐዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም (2)
እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት (2)
ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት (2)

ሰብዓ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ (2)
የእስራዔል ንጉሥ ወዴት አለ እያሉ (2)
እጅ መንሻውን ሰጡ እንደየ ሥርዓቱ (2)
እጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ
እጣኑን ለክህነት ከርቤውን ለሞቱ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ተወልደናሆ እምድንግል

Postby እማማ » Tue Jan 04, 2011 1:42 am

ተወልደናሆ እምድንግል (4)
ሲነገር ነበረ በነቢያት አፍ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
በአንዱ በእግዚአብሔር በአንዱ በመንፈስ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
አንድ ቀን እንዲሆን ጸሐይ እንዲወጣ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
የናፈቅነው ንጉሥ ሥጋ ለብሶ መጣ ተወልደናሆ እምድንግል (2)

ተወልደናሆ እምድንግል (4)

አብርሀም ያንን ቀን ለማየት ናፈቀ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
ዳዊት በኤፍራታ ልደቱን አወቀ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
ኢሣያስ ከድንግል ሲወለድ አየና ተወልደናሆ እምድንግል (2)
ትንቢት ተናገረ ምልክት አለና ተወልደናሆ እምድንግል (2)

ተወልደናሆ እምድንግል (4)

ኮከብ ከያእቆብ ይወጣል ሲባል ተወልደናሆ እምድንግል (2)
ሰማይ ሆነችለት እናቱ ድንግል ተወልደናሆ እምድንግል (2)
በሕዝቡ መካለል ሆኖ የሚያበራ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
መልሱ ፈራረሰ የጨለማው ሥራ ተወልደናሆ እምድንግል (2)

ተወልደናሆ እምድንግል (4)

ከእረኞች ጋራ ቤተልሔም ክቦ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
ከነገሥታቱ ጋር አምሐን አቅርቦ ተወልደናሆ እምድንግል (2)
እንስገድ ለህጻኑ ይገባዋልና ተወልደናሆ እምድንግል (2)
አለቅነት ሥልጣን በጫንቃው ነውና ተወልደናሆ እምድንግል (2)

ተወልደናሆ እምድንግል (4)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

እምድንግል

Postby እማማ » Tue Jan 04, 2011 3:12 am

በወንጌል አናፍርም አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
እንመሰክራለን አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
ኦ መድሐኒታችን አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል

እምድንግል (3) ተወልደህ አማኑኤል (2)
ተወልደህ አማኑኤል (4)

የነገሥታት ንጉሥ አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
ቤዛ ኩሉ ዓለም አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
መድህን ተወለደ አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
መድሀኔዓለም አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል

እምድንግል (3) ተወልደህ አማኑኤል (2)
ተወልደህ አማኑኤል (4)

ባሕር ተጨነቀች አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
ሸሸች ወደ ሁዋላ አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
እንዴት ብዬ ላጥምቅ አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
አምላኬን መድህን አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል

እምድንግል (3) ተወልደህ አማኑኤል (2)
ተወልደህ አማኑኤል (4)

አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል

አንቺ ቤተልሔም አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
ምንኛ ታደልሽ አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
የዓለም መድሀኒት አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
ተወለደብሽ አማኑኤል ተወልደህ አማኑኤል
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን

Postby እማማ » Fri Jan 21, 2011 4:16 am

በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ (2)
ሰማያዊ (5) ኢየሱስ ናዝራዊ (2)

ወረደ ወልድ (6)
እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት (2)

መጽዓ ቃል እምደመና ዘይብል ዘይብል (2)
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

እመኑ በእርሱ

Postby እማማ » Fri Jan 28, 2011 3:23 pm

እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደርጋል ጌታ
በረድ አዝንቦ ጠላት እየመታ
ውቅያኖስ ጥልቁን ፈጥኖ እያተነነ
ነገር ለወጠ ሁሉ በእርሱ ሆነ

እመኑ በእርሱ ተራራው ነደደ
እመኑ በእርሱ ሸለቆው ታወከ
እመኑ በእርሱ ዝግባው ተሰባብሮ
እመኑ በእርሱ አለቱ ደቀቀ
እመኑ በእርሱ የአሕዛብ ጣኦታት
እመኑ በእርሱ በፊቱ ረገፉ
እመኑ በእርሱ በስሙ የታመኑት
እመኑ በእርሱ ወጀቡን ቀዘፉ

እመኑ በእርሱ የማይነጋ ሌሊት
እመኑ በእርሱ የማያልፍ ቀን የለም
እመኑ በእርሱ ሁሉ ይቻለዋል
እመኑ በእርሱ ጌታ መድሐኔዓለም
እመኑ በእርሱ ፍቅር ነው ዘላለም
እመኑ በእርሱ ደግ አባት ለልጁ
እመኑ በእርሱ ሁሌ ተዘርግታ
እመኑ በእርሱ ትኖራለች እጁ

እመኑ በእርሱ ሞገድ የማይሰብረው
እመኑ በእርሱ ጽኑ መርከብ አለን
እመኑ በእርሱ አንፈራም አንሰጋም
እመኑ በርሱ ከእርሱ ጋር እያለን
እመኑ በእርሱ ጠላት ተሸንፏል
እመኑ በእርሱ ሰይጣን አፍሯል ዛሬ
እመኑ በእርሱ ወህኒው ይነዋወጽ
እመኑ በእርሱ በታላቅ ዝማሬ

እመኑ በእርሱ ባዶ ነው አይሠራም
እመኑ በእርሱ የጠላት ፉከራ
እመኑ በእርሱ የማይተወን ጌታ
እመኑ በእርሱ አለ ከኛ ጋራ
እመኑ በእርሱ እጅግ አትረፍርፎ
እመኑ በእርሱ ጸጋህ ከበዛልን
እመኑ በእርሱ በሞት ጀርባ ቆመን
እመኑ በእርሱ ገና እንዘምራለን
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

እንባን አልሰፍርም

Postby እማማ » Thu Feb 03, 2011 3:46 am

እንባን አልሰፍርም በመዳፌ
የክብርህ ዜማ ሞልቶ በአፌ
ሰልፍ አስተምረህ ለእጆቼ
አመሰገኑህ ከንፈሮቼ

ቀራንዮ ሆነህ ባይህ አሻግሬ
ከቄዳር ተነቅሎ ተከተለህ እግሬ
ሰገነት አይደለም የልቤ ናፍቆቱ
እንደ ምድረ በዳ አንተ ነህ ጥማቱ

ታሪኬን ቀያሪ ውበት ማንነቴ
የጠራኸኝ ጌታ አንተ ነህ እረፍቴ (2)

በማዕበል መካከል ልትሆነኝ ጸጥታ
ጭንቄን እየረገጥክ ደረስክልኝ ጌታ
መቼ ያቆየኝ ነበር የሰው ትከሻማ
ቀኝህ ባትደግፈኝ መገፋቴን ቀድማ

ታሪኬን ቀያሪ ውበት ማንነቴ
የጠራኸኝ ጌታ አንተ ነህ እረፍቴ (2)

የተረዳኝ ማነው የረዳኝስ ቀርቦ
ከመናገር በቀር ቃላትን አስውቦ
ያመንኩት ጥሎኛል ያመለጥኩት ያዘኝ
ከጠላት መንጋጋ በደም የገዛኸኝ

ታሪኬን ቀያሪ ውበት ማንነቴ
የጠራኸኝ ጌታ አንተ ነህ እረፍቴ (2)

የነ አፍኒንን ድንኳን ተጸየፈች ነፍሴ
ውስጤ ባያርፍ ነው በፊትህ ማልቀሴ
ከስደት መልሰህ የሾምከኝ በጸጋ
አበርታው አምላኬ ልቤም እንዳይሰጋ

ታሪኬን ቀያሪ ውበት ማንነቴ
የጠራኸኝ ጌታ አንተ ነህ እረፍቴ (2)

እንባን አልሰፍርም በመዳፌ
የክብርህ ዜማ ሞልቶ በአፌ
ሰልፍ አስተምረህ ለእጆቼ
አመሰገኑህ ከንፈሮቼ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

አየሁዋት በዓይኔ አሻግሬ

Postby እማማ » Fri Feb 11, 2011 3:51 am

አየህዋት በዓይኔ አሻግሬ
የያሬድን ውብ ዝማሬ
ተቀኘሁ እንደ አባቶቼ
እጄን ለክብሯ ዘርግቼ

ድካምና እንቅልፍ እንደምን ሊረታኝ
ድንጋይ ብንተራስ ፍቅርሽ አያስተኛኝ
ዓይኔ ቢከደን አለሽ በምናቤ
አልተከለልሽም ነግሠሻል በልቤ (2)

መረማመጃ የሎዛ መሰላል
የዜማ ቤቴ የመቅደስ ጸናጽል
የሰማይ ንጉሥ በበላይሽ አለ
ድንኳን አድርጎ አንቺን የተከለ (2)

ስምሽ በሁሉ ስለተወደደ
ድንግል ለክብርሽ ፍጥረት አረገደ
ካላመኑት ዘንድ ቢሆንም ዝምታ
ከገብርዔል ነው የስምሽ ሰላምታ (2)

ሳደርስ ውዳሴ መጽሐፉን ገልጬ
ተመለከትኩሽ ዓይኔ እንባ እየረጨ
በገናን ዳዊት መሰንቆንም እዝራ
ሰጡኝ ላነሳሽ በክብሩ ተራራ (2)

አየህዋት በዓይኔ አሻግሬ
የያሬድን ውብ ዝማሬ
ተቀኘሁ እንደ አባቶቼ
እጄን ለክብሯ ዘርግቼ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ምሥጋና አምልኮ ስግደት ውዳሴ

Postby እማማ » Fri Feb 11, 2011 3:58 am

ምሥጋና አምልኮ ስግደት ውዳሴ
ይገባል በሉ ሰዎች ለቅድስት ሥላሴ (2)

ዘላለም ዓለም ቅዱስ ነህ
አምሳያም ወደር የሌለህ
መተማመኛ ሆነኸኛል
ሥላሴ ባንተ ደስ ይለኛል

የታመነ ነው የተፈራ
የጽድቅን ጸሐይ የሚያበራ
ዓለሙ ጸንቷል በሥላሴ
ትዘምርለት ለርሱ ነፍሴ

ዘመናት በእጁ በመዳፉ
ሁሌም የርሱ ሙሉ ሰልፉ
የእሳት መድረኮች ያሉት ጌታ
የማያልፍ ነው የማይረታ

አብርሀም አምኖ ተሰደድ
በእርጅናው ወራት ልጅ ወለደ
የተስፋውን ቃል ፈጸመለት
ሥላሴ በሉ በቀን በሌሊት

የታመነ ነው የተፈራ
የጽድቅን ጸሐይ የሚያበራ
ዓለሙ ጸንቷል በሥላሴ
ትዘምርለት ለርሱ ነፍሴ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

የአብ ቃል አክብሮሽ

Postby እማማ » Thu Apr 07, 2011 3:01 am

የአብ ቃል አክብሮሽ እናቱ ያደረገሽ
እግዚአብሔር በቃሉ ፍጹም ያከበረሽ
የምንመካብሽ መሰላል አንቺ ነሽ (2)

ቅድስና ለአንቺ ጽድቅም ለአንቺ ሆኖ
ዓለምን የፈጠረ በአንቺ ተወስኖ
የገነት ፍሬ ነሽ ሕይወት ያፈራሽ
አንቺን ለመረጠ አንቺን ላነጻሽ
ምስጋና ይድረሰው ለቸሩ አምላክሽ (2)

አዳም የኖረብሽ የኤዶም ገነት ነሽ
የኤፌሶን ወንዝ ወርቅ የሚፈልቅብሽ
የግዮን ማዕበል ኢትዮጵያን የከበብሽ
ዮርዳኖስን ሆነሽ አሕዛብን ፈወስሽ
በልጁ ቃልነት አብም አከበረሽ (2)

መዓዛሽን ወዶ ወልድ ዋሕድ ዋጀሽ
አብም በሰማያት በሕሊናው ጻፈሽ
መንፈስ ቅዱስ መጥቶ አንቺን አከበረሽ
እመካብሻለሁ እመቤቴ ስልሽ (2)

ወልድ በመውደዱ ከአንቺ መወለዱን
ንጹሕ ሆኖ አግኝቶት ቅዱሱን ሥጋሽን
ለቃሉ ማደሪያ ጽላትና ታቦት
በብሩህ ደመና ተመስለሽለት
ከሥጋሽ ተከፍሎ ከደምሽ ደም ወስዶ
ከነፍስሽም ነፍስ ፍጹም ተዋህዶ (4)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ገና እንዘምራለን

Postby እማማ » Wed Apr 27, 2011 1:14 am

ገና እንዘምራለን (4)
እንደ መላእክቱ ብርሀንን ለብሰን
ገና እንዘምራለን (2)

ወላዲተ አምላክን ከፊት አስቀድመን
በዳዊት በገና መሰንቆ ታጅበን
ለሥላሴ ክብር ገና እንዘምራለን
ገና እንዘምራለን

በምሥጋና ሥርዓት ከሰለጠኑት ጋር
ልብን የሚመስጥ መዝሙር እየዘመርን
ያልተሰማ ዜማ ያልታየ ምስጋና
ይፈልቃል አይቀርም በእኛ ልቦና
ገና እንዘምራለን

በትዕቢት ሳይሆን በታላቅ ትህትና
በልዩ ተመስጦ በፍቅር ልቦና
ሥራችን ይሆናል ለአምላክ ምሥጋና
ገና እንዘምራለን

ዳዊት በተመስጦ እርቃኑን ቢሆንም
ሜልኮል በዝማሬው ብትስቅበትም
አምላክን ወደደ እንዲያመሰግነው
በደስታ እንዳይዘምር ከልካዩ ሰው ማነው
ገና እንዘምራለን
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

እጹብ ድንቅ ነው

Postby እማማ » Sat May 21, 2011 3:52 am

እጹብ ድንቅ ነው ውለታው
እግዚአብሔር ለኛ ያደረገው
ከቶ አይጥለንም ለዘላለም
እንደ አምላካችን ማንም የለም::

ወድቀን ነበረ ተነስተናል
ባሕር አቁሞ አሻግሮናል
ድንቅ አደረገ ተዓምር ሠራ
እያንሳፈፈ ያን ተራራ

የጠፋውን በግ የፈለገ
እራሱን ባዶ አደረገ
መስቀል ታቅፎ ክንዱ ዛለ
ምን ያልሆነልን ነገር አለ

ከአባትም በላይ አባት ነው
የልጆቹ እንባ የሚገደው
የጭንቀታችን ተካፋይ
አዛኝ ጌታ ነው ሁሉን ቻይ

ዳግም እንድንቆም በሕይወት
ጨክኖ ወደደን እስከ ሞት
ከእንግዲህ አንፈራም እንጸናለን
ለክፉ የማይሰጥ አባት አለን::

እጹብ ድንቅ ነው ውለታው
እግዚአብሔር ለኛ ያደረገው
ከቶ አይጥለንም ለዘላለም
እንደ አምላካችን ማንም የለም::
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests