መዝሙረ ተዋህዶ ብቻ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ልመናዬን ሰማኝ

Postby እማማ » Thu Sep 22, 2011 2:52 am

ልመናዬን ሰማኝ መድሀኒቴ (2)
አፌን ከፈተው ለምሥጋና ቸሩ አባቴ (2)

ከጨለማ ጉዞ መድሀኒቴ ከዓለም ለለየኝ ቸሩ አባቴ
እርሱ ፈቅዶ ወዶ መድሀኒቴ ከቤቱ አበቃኝ ቸሩ አባቴ
ለቸሩ አምላኬ መድሀኒቴ ለፈጠረኝ ጌታ ቸሩ አባቴ
እቀኝለታለሁ መድሀኒቴ ሁሌ ጠዋት ማታ ቸሩ አባቴ

ማክበር ያውቅበታል መድሀኒቴ ምንም አይሳነው ቸሩ አባቴ
በእውነት ከጠየቅነው መድሀኒቴ ሁሉም በእጁ ነው ቸሩ አባቴ
ያልሰጠን ምን አለ መድሀኒቴ ለእኛ ያላደረገው ቸሩ አባቴ
ፍቅሩን በመስቀል ላይ መድሀኒቴ በሞት የገለጸው ቸሩ አባቴ

የነገሥታት ንጉሥ መድሀኒቴ የጌቶቹ ጌታ ቸሩ አባቴ
ተስፋዬ አንተ ነህ መድሀኒቴ የሕይወቴ ዋልታ ቸሩ አባቴ
ልመና ጸሎቴን መድሀኒቴ የምትቀበለው ቸሩ አባቴ
በእኔ ሥራ አይደለም መድሀኒቴ በቸርነትህ ነው ቸሩ አባቴ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ኦ ሚካኤል

Postby እማማ » Thu Sep 22, 2011 2:59 am

ኦ ሚካኤል (2) ሊቀ መላእክት
በሀጢአት እንዳንወድቅ እንዳንሞት
ፈጥነህ ተራዳን አጽናን በእምነት (2)

ለያእቆብ ነገድ ሚካኤል ለእሥራኤል ሚካኤል
ጠባቂያቸው ነህ ሚካኤል መልአከ ሀይል ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት (2)

ነጸብራቃዊ ሚካኤል ተክህኖ ልብስህ ሚካኤል
ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ዓይኑ ዘርግብ ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት (2)

በሥእልህ ፊት ሚካኤል እሰግዳለሁ ሚካኤል
ፈጥነህ አረጋጋኝ ሚካኤል አለሁ በለኝ ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Re: ኦ ሚካኤል

Postby ዘመድኩን » Thu Sep 22, 2011 5:17 pm

ሰላም ለዚህ ቤት

እጠበኝ ቆሽሻለሁ
አምላኬ በድያለሁ
ያለ እናት ያሳደከኝ
ያለ አባት የጠበከኝ
ያን ሁሉ ዛሬ ረሳሁ
እጠበኝ ቆሽሻለሁ
ያን ሁሉ ዛሬ ረሳሁ
እጠበኝ ቆሽሻለሁ
ከድንኳንህ ብታስገበኝ ሞገስ ሰተህ
የአፍኒን ምግባር ይዤ አስቀየምኩህ
ቅባ ሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ
እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ
አዝ + + + + + +
ሃይል አኑረህ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ
ጎልያድን አስጥለኽኝ በጠጠሬ
አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸነፌ
ደጅ መጣሁ የእንባ መባ በአይኔ አቅፌ
አዝ + + + + + +
እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርፀህኛል
እንዳተወኝ ያለመጠን ወደኽኛል
በታሰነዝር ልትቀጣኝ የሞት በትር
የትግስትህ ሰሌዳ ነው ለኔ ክብር
አዝ + + + + + +
ከከነፍሬ ጥበብ ፅፈህ ቅኔ ቢፈስ
በመተባይ አሳዘንኩት ያንተን መንፍስ
ፍቅር ግተህ ከቅፍህ ስር ያሳደከኝ
እባክህን በበዴላ አትቅሰፈኝ
አዝ + + + + + +
ሮሜ 1:16 በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና ።
ዘመድኩን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2529
Joined: Tue Nov 16, 2004 3:11 pm
Location: united states

እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ

Postby እማማ » Tue Sep 27, 2011 12:28 am

መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም (2)
መሠረተ (3) ቤተክርስቲያን

መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ (2)
መድሃኒትነ ለእለ አመነ /2/

በወንጌሉ ያመናችሁ /2/
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ /2/

እሌኒ ንግስት ሀሰሰት መስቀሉ (2)
እንባቆም ነብይ ዘአንከረ ግብሩ (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Postby እማማ » Tue Sep 27, 2011 12:48 am

ወሪዶ እምመስቀሉ (2)
እምመስቀሉ አብርሀ ለኩሉ
እምመስቀሉ ለኩሉ አብርህ (2)

ጥልን በመስቀሉ ገደለ (2)
በመስቀሉ ለሰው ልጅ ሰላምን አደለ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

መስቀል አበባ

Postby እማማ » Tue Sep 27, 2011 12:55 am

መስቀል አበባ ነህ ውብ አበባ
አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ

መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር
አደይ አበባ ሥነ ስቅለቱ
መስቀል አበባ እሌኒን አገኛት
አደይ አበባ ደገኛይቱ

መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው
አደይ አበባ አይሁድ በክፋት
መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ
አደይ አበባ መስቀል ካለበት

መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ
አደይ አበባ ሸለቆ ዱሩ
መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው
አደይ አበባ ለአንተ መሰከሩ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Re: ኦ ሚካኤል

Postby ዘመጽኩን » Wed Sep 28, 2011 4:13 pm

እማማ wrote:ኦ ሚካኤል (2) ሊቀ መላእክት
በሀጢአት እንዳንወድቅ እንዳንሞት
ፈጥነህ ተራዳን አጽናን በእምነት (2)

ለያእቆብ ነገድ ሚካኤል ለእሥራኤል ሚካኤል
ጠባቂያቸው ነህ ሚካኤል መልአከ ሀይል ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት (2)

ነጸብራቃዊ ሚካኤል ተክህኖ ልብስህ ሚካኤል
ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ዓይኑ ዘርግብ ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት (2)

በሥእልህ ፊት ሚካኤል እሰግዳለሁ ሚካኤል
ፈጥነህ አረጋጋኝ ሚካኤል አለሁ በለኝ ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት (2)


ሚካኤል አምላክ ነው እንዴ ?
ስእል የሳለውስ ማነው ?
ይህ ነው እንግዲህ.......
ዘመጽኩን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Sun Jul 10, 2011 3:13 pm

ኢዮሐ አበባዬ

Postby እማማ » Thu Sep 29, 2011 3:56 am

ኢዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ (2)
መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ
ሕዝበ ኢትዮጵያን እዩ ችቦውን ሲያበራ
በታላቁ በዓል በመስቀል ደመራ (2)

በሐጢያት ጨለማ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ተውጠን ሳለን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የክርስቶስ መስቀል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ብርሀን ሆነልን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ትምህርተ መስቀል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ሆኖን ላመንነው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በቃሉ ለምንድን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የእግዚአብሔር ሐይል ነው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

መስቀል ባንዲራችን የነጻነት አርማችን (2)

በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
አይሁድ አክብረው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ያዳናቸውን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
አናውቅም ብለው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የድሉን መስቀል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ከመሬት ቀብረው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
መስሏቸው ነበር አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ምድር የሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

በቀራንዮ ጎልጎታ ጠላታችን ድል ተመታ (2)

ንግሥቲቷ እሌኒ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በጣም የታደለች አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ደመራን አቁማ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ጸሎት አቀረበች አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
መስቀለ ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ወዴት ነው እያለች አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በእጣን ጢስ ተመርታ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
መስቀሉን አገኘች አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

በመስቀል መከታ ቆስጠንጢኖስ ድል መታ (2)

ነገር ግን መስቀል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ተቀብሮ አልቀረም አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ተራራ አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ጠላት አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
መስቀል ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ቀና ጎባጣ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ድውይ ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
አንካሳ መጣ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ሙታን ተነሱ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ይመስገን ጌታ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

ብርሀን ወጣ ከመስቀሉ ከመስቀሉ ክርስቲያኖች እልል በሉ (2)

መስቀል መከታ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ይሁን ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
እንዳይደፈር አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ዳር ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ኢትዮጵያ ኑሪ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በእምነት ጸንተሽ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ጌታ በመስቀል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የባረከሽ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

መስቀሉ አበራ እንደ ጸሐይ ጮራ (2)

መስቀሉን አምነን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ከክብሩ ዙፋን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
እርሱ ረድቶናል አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የጸጋ ስግደት አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በእርሱ ላይ ስላለ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ሐይለ መለኮት አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

መስቀል የኛ ጋሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ (2)

የኢትዮጵያ መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
_______ ክንፉን???? አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የመስቀሉን ብርሀን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ነጸብራቁን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
እጸ መስቀሉን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
______ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የተሰጠን ለኛ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

በመስቀል እንመካለን እንድንበታለን (2)

የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የአገራችን ምኩራብ (መኩሪያ)? አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
አገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
እጣኑን ሲዘራ (?) አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ብርሀን እያበራ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

የመስቀሉ ፍቅር በኛ ላይ ይደር (2)

መናገሻ እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ጌራራ አምባ ጉራ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ሲፈልግ ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የመስቀል ተራራ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ጊሸን ላይ አገኘው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በአምባሰል ተራራ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ግማደ መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
አርፏል ከዚያ ሥፍራ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

መስቀል መስቀላችን የክርስቲያን ሐይላችን (2)

የመስቀል ለታ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
የደመራው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ተደስተው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በአገር ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
አምረው ደምቀው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ
መስቀል ብለው አበራ መስቀሉ ለኛ አበራ

የመስቀሉ ደመራ በኢትዮጵያ ሲያበራ (4)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ምን ሰማህ ዮሐንስ

Postby እማማ » Wed Oct 05, 2011 11:42 pm

ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ (2)
ህጻን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ (2)
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ (2)
ምን ዓይነት ድምጽ ነው ምን ዓይነት ሰላምታ (2)

ከተፈጥሮ በላይ ያዘለለ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ክብር (2)
ሌላ ድምጽ አልሰማም ከእንግዲህ በህዋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ (2)

በረሀ ያስገባ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት (2)
እንደ አዲስ ምሥጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ (2)

ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍጹም (2)
ከማህጸን ሳለ ተመርጦ ለጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ሥላሴን አመስግኑ

Postby እማማ » Thu Oct 13, 2011 1:36 am

ሥላሴን አመስግኑ (2)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምሥጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምሥጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴ አምባዬ ክብሬም ናቸውና
ሁሌ ይመሩኛል በህይወት ጎዳና

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑህ
መላዕክት በሰማይ የሚዘምሩልህ
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይ በምድር እንጠራሀለን
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

እግዚአብሔር መልካም ነው

Postby እማማ » Thu Oct 20, 2011 1:20 am

እግዚአብሔር መልካም ነው
በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው (2)

ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን
ሞት ነግሦብን ሳለ በኛ በሁላችን
ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነው
በመከራው ጊዜ መሸሸጊያ ሆነው (2)

አብርሀም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት
ከነዓን ሲገባ ሲሰደድ በእውነት
ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎድልበት
እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት (2)

በሐዘን በችግር በመከራ ጊዜ
ጭንቄን የሚያርቅ ነው የነፍሴን ትካዜ
የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ
እግዚአብሔር መልካም ነው ሐዘኔን አስረሳኝ
የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ
ክርስቶስ ኢየሱስ ሐዘኔን አስረሳኝ

እግዚአብሔር መልካም ነው
በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ሚካኤል ስለው

Postby እማማ » Thu Oct 20, 2011 1:35 am

ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍጹም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ (2)

ከአለቆች ጋራ ሕዝቡን የመራ
የሚመላለስ በእሳት ተራራ
ባሕሩም ሸሸ ከማደሪያው
የጌታ መልዓክ ሲያናውጸው
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ከባዱ ጋራ ሜዳ ሆኖኛል
የወህኒው መዝጊያ ተከፍቶልኛል
አልናወጽም ከቶም አልፈራ
የጌታ መልዓክ ነው ከኔ ጋራ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ትዕቢተኛውን አሸንፎታል
ዲያብሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል
ታላቅ ጸጥታ በሰማይ ሆነ
እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሹ
የሚቃወሙን አጥብቀው ሸሹ
ታላቁ መልዓክ ከፊት ቀደመ
ታሪክ ተሠራ እንባችን ቆመ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍጹም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ (2)
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

Re: ሚካኤል ስለው

Postby ፊሊፖስ » Thu Oct 20, 2011 4:17 am

እማማ wrote:ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍጹም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ (2)

ከአለቆች ጋራ ሕዝቡን የመራ
የሚመላለስ በእሳት ተራራ
ባሕሩም ሸሸ ከማደሪያው
የጌታ መልዓክ ሲያናውጸው
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ከባዱ ጋራ ሜዳ ሆኖኛል
የወህኒው መዝጊያ ተከፍቶልኛል
አልናወጽም ከቶም አልፈራ
የጌታ መልዓክ ነው ከኔ ጋራ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ትዕቢተኛውን አሸንፎታል
ዲያብሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል
ታላቅ ጸጥታ በሰማይ ሆነ
እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሹ
የሚቃወሙን አጥብቀው ሸሹ
ታላቁ መልዓክ ከፊት ቀደመ
ታሪክ ተሠራ እንባችን ቆመ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል (2)

ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሀን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍጹም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ (2)


እንደምን ከረሙ: እማማ! እግዚአብሔር ይስጥልን!
A QuEstion oF BalAnCe

Image
ፊሊፖስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 123
Joined: Thu Nov 08, 2007 12:16 pm

የጥበብ ሰዎች መጡ

Postby እማማ » Fri Dec 09, 2011 1:03 am

የጥበብ ሰዎች መጡ (2) ሰምተውት በዜና
እያበራላቸው ኮከብ እንደ ፋና (2)

ሰማይና ምድር የማይወስኑት
ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት
ዘጠና ዘጠኙን መላዕክት ትቶ
አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ

ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ
ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ
ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድህን
ኩነኔን አጥፍቶ ጽድቅን ሊያወርሰን

ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም
ሀዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም
እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት
ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት

ሰብዓሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ
የእስራኤል ንጉሥ ወዴት አለ እያሉ
እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ
ዕጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ
ዕጣኑን ለክህነት ከርቤውን ለሞቱ
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

Postby እማማ » Fri Dec 30, 2011 1:42 am

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ቸል ያላለን አምላክ ስንጓዝ ማዕበሉን አቋርጠን
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

የህይወት እስትንፋስ ዘራብን ህያው እንድንሆን
ይህን ያደረገ አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ነፋስን ገስጾ ማዕበል አቁሞ የሚያሻግር
የዓለም ፈተና ቢበዛ እርሱ መጠጊያችን
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ዳግም እንዳንሞት በሞቱ ሞትን የረታልን
የምንመካበት ትንሣኤ ሰላምን ለሰጠን
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ከሲዖል እስራት ተፈተን ነጻ የወጣንበት
መስቀሉን ለሰጠን ለአምላካችን እንዘምር በእውነት
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
እማማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 129
Joined: Sat Feb 07, 2004 6:42 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 4 guests