የትምህርት ቤት ትዝታ..አስተማሪ እና የክፍል አለቃ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የትምህርት ቤት ትዝታ..አስተማሪ እና የክፍል አለቃ

Postby ሰላም ኢትዮጲያ » Sat Oct 08, 2005 5:40 pm

ሰላም እንዴት አላችሁልኝ??

እስኪ ስለ ትምህርት ቤት ትዝታ, ስለ አስተማሪዎች እንዲሁም ስለ ክፍል አለቆች ያላችሁን ገጠመኝ አካፍሉን......
.............................................................................................

...........የኔን እስኪ ልንገራችሁ.............

ለዛሬ የማወራችሁ ስለ ክፍል አለቃ ነው:: አራተኛ ክፍል እያለን አንዲት ሴት አለቃ ነበረችን በእድሜ ከኛ በጣም ትበልጥ ነበር:: በጣም ሲበዛ ታሰቃየን ነበር:: የማታዘን ነገር የለም:: አንድ ባንድ እያስወጣች ስትፈልግ ታዘፍነናለች, ስትፈልግ ጊዜ ቤት ታስቆጥረናለች:: እና ደግሞ በጣም የሚገርመው, ለመዝፈን የወጣው/ችው ተማሪ የሚዘፍነው ዘፈን የሚመረጥለት/ላት በእስዋው በአለቅየው መሆኑ ነው:: አንድ ቀን የማልረሳው ጉዋደኛዬን ታስወጣትና የንዋይ ደበበን እሸት በላሁኝ የሚለውን ዘፈን እንድትዘፍን ታዛታለች:: ጉዋደኛዬም ዘፈኑን መዝፈን ጅምራ በመሀል ግጥሙ ይጠፋትና ታቆማለች:: እናም ይችው አለቃ በያዘችው ጎማ ዴስክ ላይ አጋድማ እንደገረፈቻት አስታውሳለሁ.......

ሌላው በኔ ላይ የደረሰውን ደግሞ ልንገራችሁ:: በሆነ ቀን ነው ምሳ ሰአት ከመደወሉ በፊት አለቃችን <ዛሬ ለምሳ ወደ ቤት የምትሄዱ እጃችሁን አውጡ?> አወጣን:: እኔም ነበርኩበት:: ከዛ ሁላችንንም የተለያየ ነገር ከቤታችን ይዘንላት እንድንመጣ ታዘዝን:: ያላዘዘችው ነገር የለም ብርቱካን, ሙዝ, ዳቦ በስክዋር, ሎሚ ምናምን አለችና እኔ ጋ ስትደርስ ምን እንደምትለኝ ግራ ገባት መሰለኝ < አንቺ በቃ የሆነ ልዩ ነገር ይዘሸ ነይ?> አለችኝ:: በጣም ግራ ገባኝ ልዩ ነገር ምን ሊሆን ይችላል?? በጣምም ጨነቀኝ ምክንያቱም የተባልኩትን ይዤ ካልተመለስኩ ልትገርፈኝ ነዋ...... ከዛ ቤት ሄጄ ምሳ ከበላሁ በሁዋላ አንድ የማር አበባ የምንለው አበባ ነበር:: ንቦች የሚቀስሙት:: አበባውን ፈልቅቀን ስንመጠው የሆነ የሚጣፍጥ ነገር ነበረው እና እሱን ከቤታችን መአት ቀጠፍኩና ይዤ መሄድ..... ከዛም ክፍል ስንገባ ሁሉም ያመጣውን ነገር አስተማሪ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ እያደረገ ይገባል... እኔም ያመጣሁትን አስቀምጨ ወደ ወንበሬ ሄድኩና ቁጭ ከማለቴ......ማነው ይህንን ያመጣው ብላ ጮኸች አበባውን ይዛ........ተነሳሁ........ነይ ውጪ......ወጣሁ.....እናም ደህና አድርጋ እስኪበቃኝ ገረፈቺኝ:::; ይህንን መቼም አልረሳውም:: በአሁን ጊዜ እንድዚች አይነት አለቃ ይኖራል ብዬ አላስብም::

ሰላም ሁኑልኝ::
ሰላም ኢትዮጲያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 162
Joined: Mon Oct 03, 2005 1:00 pm
Location: planet earth

ቆንጆ ጨዋታ

Postby ጌታ » Sat Oct 08, 2005 9:24 pm

መቼም እርጅና ሲጫጫን ብዙ ነገር ይረሳልና ብዙ ገጠመኝ እንዳለኝ ባውቅም የማስታውሳቸውን ጥቂቱን ልንገርሽ/ህ::

አንደኛ ክፍል እያለሁ ነው:: ስሙ ተፈራ ይባላል-የሕብረት አስተማሪያችን ነበረ:: ክፍል ውስጥ ገና ሲገባ በጣም ስለምንፈራው እጃችንን አጣምረን ጸጥ እንል ነበር:: ዝም ብሎ ይመለከተንና አንዱን ተማሪ "ና ውጣ' ብሎ መለጥለጥ ይጀምራል:: በቀን ስንት ተማሪ ይገረፍ እንደነበር አሁን አላስታውሰውም:: አንድ ጊዜ ብዙ ተማሪዎችን አስወጣ:: የተለያዩ ስዕሎችን ሰሌዳው ላይ ከሳለ በኋላ አንዱን ተማሪ 'ስምህ ማነው?' ብሎ ጠየቀው:: 'አፈወርቅ' ብሎ መለሰ:: አፍህ ላይ ያለ ወርቅ የታለ ብሎ ግርፍ ካደረገው በኋላ ከጀርባው ብብቶቹ ስር ገብቶ አቀፈውና ብላክቦርዱ ላይ ያለውን ስዕል ካሳመው በኋላ አየር ላይ ለቀቀው:: ይህ ልጅ ስሙ አበራ: አበበም ቢሆን የታለ የምታበራው ወይም ያበብከው የሚል ጥያቄ አይቀርለትም ነበር::

አሁን ሳስበው ይህ ሰውዬ ትልቅ የአዕምሮ ችግር ነበረበት:: የሚገርመው ነገር ግን አንዳችንም ለወላጅም ሆነ ለዳይሬክተር ተናግረን አናውቅም:: ማንንም አልፈራም ሲለን እውነት መስሎን ይሆናል:: ካደኩኝ በኋላ ከዛሬ ነገ ትምህርት ቤቱ ድረስ ሄጄ የተፈራን አድራሻ አፈላልጌ አናግረዋለሁ ብዬ ሳስብ ሳይሟላልኝ ወደ ውጭ ወጣሁ:: ይህ ሰው በሕይወትም ቢኖር የስቃይ ኑሮ እንደሚኖር እገምታለሁ::

እኔም አራተኛ ክፍል እያለሁ በግድ ውጡና ዝፈኑ የምትለን አለቃ ነበረችኝ:: ካንቺ ጋር አንድ ክፍል እንዳልነበርን ያወኩት ግን ያኔ ንዋይ ካሴት አላወጣም ነበር:: እኔ የጥላሁንን ዘፈን ነበር የምዘፍነው:: ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የሙዚቃ ፈተና ላይ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያንም ለመዘመር ስንት እፍረት ነበረ::

ያቺ ያልሻትንም አበባ አውቃታለሁ:: ጣዕሟ አሁን ትዝ አለኝ!!!

እስቲ ደግሞ የሌሎቹን እንስማ!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

ቆንጆ ጨዋታ

Postby ሰላም ኢትዮጲያ » Mon Oct 10, 2005 4:17 pm

ስላም ጌታ እንዴት አለህልኝ?

የመምህር ተፈራ ነገር በሳቅ ገደለኝ:: የራሴን ለሎች ትዝታዎች ሰሞኑን ይዠ ብቅ እላለሁ::

ሰላም ሁንልኝ:;
ሰላም ኢትዮጲያ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 162
Joined: Mon Oct 03, 2005 1:00 pm
Location: planet earth


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests