የማማለድ ትክክለኛ ትርጉም

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የማማለድ ትክክለኛ ትርጉም

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Oct 15, 2005 11:01 pm

እስቲ መጀመርያ የማማለድን ትርጉም በትክክል የሚያውቅ ያብራራልን::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

የማማለድ ትርጉም በመጸሀፍቅዱስ ውስጥ ::

Postby ግሸንማርያም » Sun Oct 16, 2005 2:21 am

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

አማላጅነት ማለት ትርጉሙ ምንድነው ? ማማለድ
የአማላጀነት ትርጉም ማስታረቅ ነው ::

መጽሀፍቅዱስ እንዲህ ይላል::

በመጀመሪያ ደረጃ ማማለድ የሚችሉት ሰዎች እግዚአብሔር ያከበራቸው የመረጣቸውና የሾማቸው ቅዱሳን መሆን አለባቸው :: በመጽሀቅዱስ ውስጥ ብዙ እግዚአብሔ ያከበራቸው እና የመረጣቸው ቅዱሳን ነበሩ :: ከእነርሱም ውስጥ ኖህ , ሎጥ አብርሀም , ይስሀቅ , ያእቆብ, ኤልያስ , ኤልሳእ ሙሴ, ዳዊት...... ሁሉንም ለመዘርዘር ግዜ የለኝም ሕብራውያን 11 :32::

ስለዚህም እነዚህ ቅዱሳን በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ሲያማልዱ አይተናል :: ለምሳሌ ያህል የአማላጅነት ትርጉሙንና ማን ማማለድ እንደሚችል ከሚነግሩን የእግዚአብሔ ቃላት መካከል ጥቂቱን እንመልከት ::

1ኛ. ኦሪት ዘፍጥረት ምህራፍ 18 ቁጥር 18 ላይ አብርሀም ስለ ሰዶም እና ገሞራ ሲለምን ወይም ሲያማልድ እናያለን :: እግዚአብሔርም ለቅዱስ አብርሀም እንዲህ ብሎታል በዚህች ሀጢያተኛ ከተማ 10 ጻድቃን ቢኖሩ ኖር ይህችን አገር ከማጥፋት እመለሳልሁኝ ብሏል እግዚአብሔር :: ይህ የሚያሳየን አማላጅነትን ነው :: እግዚአብሄር ያችን አገር እሳት ከማውረድ ያልተመለሰው በ አንድ አገር ውስጥ 10 ጻድቃን በመታጣታቸው ነበር ::

2ኛ. በኦሪት ዘፍጥረት ምህራፍ 20 ቁጥር 1 - 7 ስንመለከት ደግሞ :: ንጉስ አቤሜሌክ የነቢዩን የቅዱስ አብሐምን ሚስት ሳራን ወሰደ :: በዚህን ጊዜ ማታ እግዚአብሔር ለንጉሱ በህልሙ ተገልጾለት :: እንዲህ አለው አቤሜሌክ የነቢዩን ሚስት ስለወሰድክ አንተ ሙት ነክ አሁን ሚስቱን ለነቢዩ መልስ አብርሀም ነቢይ ነውና ስለ አንተ ይጽልይልሀል አንተም ትድናለክ አለው እግዚአብሄር ለንጉሱ ለአቤሜሌክ:: አቤሜሌክ ሳራን ለአብርሀም መለሰለት:: አብርሀምም ለንጉሱ አማለደ ወይም ጸለየ እግዚአብሄርም የአብርሀምን ጸሎት ሰማ ምህረትም ለአቤሜሌክ ላከ ይላል ::

3ኛ. ኢዮብ 42 ቁጥር 7 - 10 ስትመለከቱ :: እግዚአብሔር አምላክ አልፋዝና ሁለቱን ጉዋደኞቹን እነደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር አልተናገራችሁምና ቁጣዬ በአንተና በሁለቱ ጉዋደኞቹ ላይ ነው ነገር ግን እንዳላጠፋችሁ ወደ ባሪያዬ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ የሚቃጠልንም መስዋት አሳርጉ እንደ ስንፍናችሁም እንዳላጠፋችሁ ባሪያዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል/ ያማልዳል :: እኔም የኢዮብን አማላጅነት እቀበላለሁኝ ይላል እግዚአብሄር::

4ኛ. ትንቢተ ኤርምያስ ምህራፍ 42 ቁጥር 1- 16 ስትመለከቱ ሰዎች ውደ ቅዱሱ ነቢይ ወደ ኤርምያስ መጥተው አማልደን አሉት :: ኤርምያስም ከእግዚአብሄር ጋር ሕዝቡን አማለደ ::

5ኛ. ኦሪት ዘጸዐት ምህራፍ 32 ቁጥር 7 - 14 ስትመለከቱ እስራኤላውያን ለጣኦት ሲሰግዱ እግዚአብሄር ህዝቡን ለማጥፋት ወሰነ እንዲህም አለ ""ሙሴ እባክህ ተውኝ""ይህንን የሚለው እግዚአብሔር ነው:: ሙሴ እባክህ ተወኝ ይህንን ሕዝብ ላጥፋው አለ እግዚአብሔር :: ሙሴም እግዚአብሔር ሆይ ስለ አብርሀም ስለ ይስሀቅ ስለ ያእቆብ ብለክ ማራቸው ብሎ አማለደ :: እግዚአብሄርም የሙሴን አማላጅነት ተቀብሎ ማራቸው ከማጥፋትም ተመለሰ::
ይህንንም ቅዱስ ዳዊት በመንፈስቅዱስ ሲገልጸው በመዝሙር 105 ቁጥር 23 ላይ እንዲህ አለ ዳዊት "" የተመረጠው በመቅሰፍት ጊዜ ሙሴ ባይቆምላቸው ኖሮ እስራኤላውያን ይጠፉ ነበር ይላል::


የቅዱሳንን የማስታረቅ አገልግሎት ሲገልጽ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ አለ በመንፈስቅዱስ ::

2ኛቆሮንጦስ ምህራፍ 5 ቁጥር 20 ላይ ክርስቶስ አለሙን ከራሱ ጋር አስታረቀ ይልና: የማስታረቅን አገልግሎት ለእኛ ሰጠ: ሰለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናቹሀለን ይላል :: ይህም የቅዱሳንን የማማለድ ስልጣን እራሱ እግዚአብሔር እንደሰጣቸው የሚናገር ነው::

የማስታረቅን ስልጣን ለእኛ ሰጠን ሲል ቅዱስ ጳውሎስምን ማለቱ ነው ? ምክንያቱም በብሉይ ጊዜ ብዙ ቅዱሳኖች ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲያስታርቁ ነበር እግዚአብሔር ስልጣኑን ድሮ ነው የሰጣቸው ታዲያ እንዴት ቅዱስ ጳውሎስ በእኛ የማስታረቅን ቃል አኖረ ይላል ? ካላችሁ በብሉይ ጊዜ ምንም ቅዱሳኑ ሰዎችን ቢያማልዱም ሰዎቹን ከሲኦል የሚያወጣ ምልጃ አልነበረም ::አሁን ግን ማለትም በአዲስ ኪዳን ጊዜ በዮሀንስ ምህራፍ 20 ቁጥር 21 - 23 እንደተጻፈው የቅዱሳን አማጅነት በነፍስም እንደሚጠቅም ይናገራል::
እኛ ጥቅሶቹን በድንብ መጸሀፍቅድሱን እየገለጽክ ስታነበው ደግሞ ከዚህ በላይ ግልጽ ይሆናል ::

ቅድስት ንጽህይት ማርያምና ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት እና ቅዱሳን መላእክት ሁሉ ሁሉ እንደሚያማልዱ መጽሀፍቅዱስ ይናገራል :: አንድም ቦታ ግን ቅዱሳን አያማልዱም የሚል ቦታ በመጸሀፍቅዱስ ውስጥ የለም:: የለም :: ስለዚህ ውድ ወንድሜ እነዚህን ቅዱስን ከመጸሀፍቅዱስ ውስጥ የጠቀስኩልክ ለምሳሌ ያህል ነው:: እነዚህ ቅዱሳን የሚያማልዱንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስ አለማትን የፈጠረ እርሱ እግዚአብሔር ነውና ኤፌሶን ምህራፍ 2 ቁጥር 10 እና ህብራውያን ምህራፍ 1 ቁጥር 10ን ተመልከት ::

የእግዚአብሔር ቸርነት የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳንን የጻድቃንን ሰማእታት ጽሎትና አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ::

ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ::

ወስብሀት ለእት
ግሸንማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 366
Joined: Mon Aug 15, 2005 8:11 pm
Location: ethiopia

አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን !!!

Postby አክሱምማርያም » Sun Oct 16, 2005 4:50 pm

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አሜን::

ሁሉንም እውነት ወንድማችን ከላይ አብራርቶታል: እኔ የምጨምረው የለኝም: ይህ ሁሉ በቂ ነው: ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃዋል አይደል የሚባለው? ስለዚህ ጆሮ ያለው ይስማ!!! :lol:

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር:ክህደት እስከዘላለሙ ይጥፋ አሜን::
አክሱምማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 359
Joined: Tue Sep 13, 2005 4:04 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Oct 16, 2005 7:51 pm

ግሸን ማርያም:-ሰላም ላንተ ይሁን

ለሰጠኸኝ መልስ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው::የጠቀስካቸውን ጥቅሶች ገና አላመሳከርኳቸውምና ለጊዜው የምለው የለኝም::አንድ ጥያቄ ግን ይኖረኛል::ጽሑፍህን ስትጀምር ከተለመደው በተለየ መልኩ 'በስመ አብ በስመ ወልድ ወበስመ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ነው::'ምክንያት ይኖርህ ይሆን?የጽሑፍህ ማሳረጊያ ያደረግከውን ደግሞ ወስብሐት ለአብ ብዬ ነው ያነበብኩት... ታይፕ ስታደርግ እንደተሳሳትክ በመረዳት::

አክሱም ማርያም:- ላንተም ሰላም ይሁንልህ እያልኩ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ልትኖር አትችልም ብልህ ምን መልስ ልትሰጠኝ ይሆን?በተረፈ እኔም አሜን ብያለሁ::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

ደብረ ዲማ ከቅድስት ሐገር ከኢትዮጵያ መልስ::

Postby ደብረ ዲማ » Sun Oct 16, 2005 11:18 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::
ሰላም ውድ ክርስቲያን ወገኖቼ እንደምን ሰነበታችሁ እኔ በጣም ደህናነኝ ላልተወሰነ ጊዜ አልነበርሁም አሁን ግን ክርሄድሁበት ተመልሻላሁ አብረን እንወያይ:: ለዛረው ይዥ የቀረብሁት >. የሐመረኖሕ ዘጌ ኡራ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አጭር ታሪክን ነው::

በሐገራችን ከሚገኙት ታላላቅ መካነ ቅዱሳት መካከል ይህ ገዳም አንዱ ነው ::

ጣና ሃይቅ 3ሺህ 6መቶ ስኩዬር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ሲኖረው በውስጡም 37 ደሴቶች እና 29 ገዳማት ይገኙበታል; እነዚህም ገዳማት ከ11ኛው እስከ 16ትኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ተስፋፉ ይነገራል :: በጣና ሃይቅ አካባቢ ከሚገኙት ገዳማት መካከል ኡራ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አንዱ ነው :: የኡራ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ዘጌ ከሚባል ደሴት አካል ቦታ ላይ የተቆረቀረ ሲሆን ከባህር ዳር ከተማ በአማካኝ በጀልባ የአንድ ሰአት ጎዞ ወይም በየብስ ደግሞ ወደ 35ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል::
> ገዳመዘጌ ኡራ ኪዳነምሕረት በክብ ደርብ የግንብ ሕንፃ ጥበብ የተሰራ ሲሆን በአራት ማዕዘን በተሰሩ የእንጨት ግማዶች እና በጥንታዊ የሰዕል ጥበብ የጌጠ ታላቅና ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው:: በተጨማሪም የዕቃ ግምጃቤት እና አባ ዮሐንስ ቤተክርስቲያኗ ከመታነጿ በፊት ያነጹት ቤተ ዮሐንስ ወይም ቤተ ማዕድ { ቤተ ምርፋቅ} በዙርያው ይገኛል:: የኡራ ኪዳነ ምሕረት የደብረ ሥላሴ እና የአዝዋ ምርያም ገዳማት ከአባ ዮሐንስ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሥረዐተ ዮሐንስ ተጠብቆ በአንድ መምህር እና በአንድ አበ ምኔት ይተዳደራሉ::

> አባ ናሆም ;

ገዳመ ዘጌ የጸናችው በአባ ናሆም መሆኑ በታሪክ ይነገራል የአባ ናሆም ታሪክ በአብርሃ ወአጽብሃ በኃላ አንደኛ ረድፍ ሁለተኛ አሞሲን እና ሶስተኛ ሣልሣይ የተባሉ ነገሥታት ከነገሱ በኃላ እንደ ሆነ ይነገራል :; ከዚህ ጊዜ በኃላ አባታችን አባ ናሆም በኢየሩሳሌም ደሴት ዝጋግ በተባለች ደሴት በጸሎት እንዳሉ የልኡል እግዚአብሔር መልአክ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ አዘዛቸው :; ከመጡም ጊዜ የነበሩበት ቦታ በእግዚአብሔር ኃይል ከእሳቸው ጋር መጥቶ በጣና ሐይቅ እንደ ተቀመጠ ይነገራል: ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ይህን ቦታ { ዝጋግን } ለማስታወስ ሲባል ደሴቱ ዘጌ እንደተባለ ይነገራል:: አባታችን አባ ናሆም ከበአታቸው በጸሎት እንዳሉ { የዋልድባው አባ ሳሚኤል ከመወለዳቸው በፊት ] ለዋልድባ ገዳም ሰባት አክሊላት ከሰማይ ሲወርድ አይተው ; መንፈሳዊ ቅናት አድሮባቸው ; ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰዕል ፊት ወድቀው እያለቀሱ ይለምኗት ጀመር ;; በዚህ ጊዜ የእመቤታችን ስዕል ድምጽ አእጥታ አባ ኖሆም አትዘን አታልቅስ ; እንሆ ምድርህ ዘጌ እንደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ትሆንልሐለች መነኮሳቷ ልጆችህም እንደ መላዕክት ይሁኑልህ አለቻቸው :: ያን ጊዜ ለገዳመ ዘጌ አስራሁለት አክሊላት ከሰማይ ወረደላት; አባታችንም አባ ናሆም የሰጠሽኝን ቃል ኪዳን ያጽናልሽ ልጅሽን ኢየሱስ ክርስቶስን አስመጭልኝ ብለው ለመኗት እመቤታችንም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ አባ ናሆም አስመጣችው :: ይህችም ቢታ ዛሬ አስመጭ በመባል ስትጠራ ትኖራለች::

የአባ ዮሐንስ ታሪክ ይቀጥላል ::

ደበረ ዲማ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ::

እመቤታችን ለአባቶቻችን የተለመንች እኛንም ትለመነን ታማልደን ታስታርቀን አሜን:

{ ቅኔ }

ዝምዝም ወርቅ መንገድ { መወድስ}

ማርያም ግዮን ፈለገ ኅሊብ
ማርያም ጳዝዮን ማርያም እንቁ ሶፎር
ማርያም ዓለም ዘይስሕብኪ ፍቅር
ማርያም ፈለገ ደም ላባዕድ ዘኢይትትከሰት ማርያም ምሥጢር
ማርያም ጸሐየ ክብር እንተ ፈጠረኪ ወልድ ማዕከለ ተሰዶ ጠፈር ::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

እንኩዋን በሰላም መጣሕ ደብረ ዲማ ወንድማችን!!!

Postby አክሱምማርያም » Sun Oct 16, 2005 11:41 pm

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አሜን::

ወንድማችን ደብረ ዲማ እንክዋን በሰላም ከቅድስት ሀገራችን ከኢትዮጵያ በሰላም ተመለስክ::
በጣም የታደልክ ነህ ገዳማትን ጎብኝተህ በመምጣጥሕ እኛንም በጣም ነው ያስቀናከን: ወደፊት እኛም ለመሄድ ስለምናስብ እንዲሳካልን በጸሎትህ አስበን:: ላካፈልከን የገዳማት ሁኔታም በጣም ነው የምናመሰግነው: በጣም የሚያስደስት ነው!!!
እንዴት ደስ እንዳለን ይህ ምስል እንደእኛ ሲስቅ እየው :lol:
እና እግዚአግሄር ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን::
አክሱምማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 359
Joined: Tue Sep 13, 2005 4:04 am
Location: ethiopia

ወንድሜ ደብረ ዲሚ እንክዋን ደህና መጣህ ::

Postby ግሸንማርያም » Mon Oct 17, 2005 2:51 am

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

በመጀመሪያ ወላዲተ አማልክ ቅድስት ንጽህይት ድንግል ማርያም በሰላም እነዚህን ትላላቅ ገዳማት በመልጃውያ ለማየት አበቃችህ :: ስለ ገዳማት የጻፍከውን ታንብቤዋልሁኝ :: እጅግ ደስ ያሚል ነው :: ለ 10 ደቂቃ ያህል እኔም ተመስጬ ጣና ገዳማት ላይ ነበሩኩ ::

የተከበርክ ደብረ ዲማ ስለ ተመለከትካቸው ገዳማት እባክህ የኢትዮጵያ ገዳማት በሚል ወይም በሌላ አንተ በመረጥከው ርእስ አውጥተህ እባክህ ታሪካችንን አስተምረን ::

ሌላው ደግሞ ገዳማትን በምትጎበኝበት ጊዜ በገዳሙ ውስጥ ድምጸ አራዊትን ሰዋን አጋንንትን ችለው በጾ በጸሎት ለኢዮጵያና ለአለሙ ሁሉ ያለመሰልቸት የሚተጉትን የባህታውያንና መነኮሳትን ጽናት እምነት ትእግስት እንዴት አየከው ? ይህንንም ብትጽፍን ድስ ይለናል ::

በተረፈ እግዚአብሔር ከፈቀደ እኔም ገዳማትን ማየት ፍልጌያለሁኝ የእርሱ ፈቃድ ከሆነ ማለት ነው ::
በተረፈ መድሀኒያለም ቸር ይግጠመን :: ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን :: ቅዱሳን መላእክት በክንፎቻቸው ከክፉ ሁሉ ይጠብቁን ቅዱሳን ስለ ሐጢያታችን ሁል ጊዜም ይማልዱልን አሜን ::
ግሸንማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 366
Joined: Mon Aug 15, 2005 8:11 pm
Location: ethiopia

ማማለድ

Postby ፎግር » Mon Oct 17, 2005 3:59 am

ብዙ አትፈላሰፉ የኢየሱስ ምልጃ ብቻ ያድናል:: Romains 8:34, hebrew 7:25...ሌላም ሌላም
love
ፎግር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Sun Feb 20, 2005 12:18 am
Location: united states

Re: ማማለድ

Postby NATHRATHE » Mon Oct 17, 2005 4:32 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ፎግር wrote:ብዙ አትፈላሰፉ የኢየሱስ ምልጃ ብቻ ያድናል:: Romains 8:34, hebrew 7:25...ሌላም ሌላም


ዛሬ ደግሞ ፉከራ ጀመራችሁ::መፎከር የት የሚያደርስ መሰለህ::የጠቀስካቸው ጥቅሶች ኢየሱስ እንደሚያማላድ አይናገሩም::የመጀመርያው እንዲህ ይላል እግዚያብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ ውግዚያብሄር ነው የሚኵንንስ ማን ነው? የሞተው ይሉቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚያብሄር ቀኝ ያለው ደግሞም ስለ እኛ የሚፈርደውክርስቶስ ኢየሱስ ነው::ሮሜ8:34 ይህን ጥቅስ ከ19ኛ ክ.ዘ ወዲህ የሚታተሙ መጽሐፍ ቅዱሶች ይፈርዳል የሚለውን ያማልዳል በሚል ተተክቶ ሲታተሙ ይታያሉ::ከዛ በፊት የታተሙ ለምሣሌ በአፄ ሚንልክ ግዜ በ1889 ዓ.ም አካባቢ ከአውሮታ ታትሞ የመጣው የመጀመርያው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብንመለከት ይፈርዳል እንጂ ያማልዳል አይልም::በግዕዙም እንዲሁ ነው::ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሾልኮ እንዲገባ የተደረገው ቃል ስንቱን እንዳሳሳተ ቤቱ ይቁጠረው::

ከርዕሱ ወጣ ብዬ የጻፍኩት በአጋጣሚ ጥቅሱ ሲጠቀስ በዛው እውነቱን እንድናውቅ ነው::

ደብረ ዲማ እንኳን በሰላም መጣህ:: የጻፍከውን የገዳም ታሪክ በጣም ደስ ይላል ወደፊት እንዲሁ የሌሎችን እንደምታካፍለን እምነቴ ነው::እንደው እንግዳ ሆነህ መጀመርያ ያገኘህው ቦታ ላይ ጻፍክ እንጂ የራሱ የሆነ እርዕስ ጀምረህ አንተም እኛም ሆላችንም እኛው ላይ ብንሳተፍ የሚሻል ይመስለኛል::የዚህ ርዕስ ስር ከምልጃ ጋር የተገናኙ ነገሮች ቢጻፉ የበለጠ ጥሩ የሚሆን ይመስለኛል::ቤተ ክርስቲያናችን የስርዐት ባለቤት ናትና እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ለመንፈሳዊው ብቻ ሳይሆን በአለማዊውም ለሌሎች አርዐያ ልንሆን ይገባል እላለሁ::

ውይይቱ ላይ የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ወንድሞቼና እህቶቼ ስላቀረቡ እኔ የምጨምረው የለም::ሌሎች ተቋዋሚዎች የተለየ ሀሳብ ካላችሁ አቅርቡና ከዚያ በትርጉሙ ላይ መወያየቱን እንቀጥላለን::ማማለድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከተግባባን ሌላው ብዙ የሚያስቸግር አይመስለኝም::

ይቆየን
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

ለደብረ ዲማ...

Postby Acts 8:26-39 » Mon Oct 17, 2005 5:11 am

ወንድማችን ደብረ ዲማ እንኳን ከቅድስት ሐገር ኢትዮጵያ በሰላም ተመለስህ! ከላይ እንደተጠቆመው የቅዱሳት ገዳማትን ታሪክ በሚመለከት አዲስ ርዕስ ከፍተህ የበኩልህን ብታቀርብ ሌሎችም ቢያክሉ መልካም መማማርያ ይሆነናል::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

እግዚአብሔርን በሁሉ እናምስግነው::

Postby ደብረ ዲማ » Mon Oct 17, 2005 5:22 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን :: የእግዚአብሔር ወዳጆች የቅድስት ድንግል የእናታችን የማርያም ልጆች :: ውድ ወገኖቼ : እክሱም ማርያም / ግሸን ማርያም/ እንዲሁም /ናዝሬት የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ይሁን አሜን :: እናንተም እንኮአን ደህና ቆያችሁኝ::
ናዝሬት እንዳልህው ስርአት ባለው መልኩ ቢቀርብ ለአንባቢ ጥሩ ይሆን ነበር ነገር ግን እኔ ደግሞ ቅድስት ሐገር ኢትዮጵያ የቆየሁትኝ ልትንሽ ቀን ስለነበር ሁሉንም ገዳማት ለመጎብኘትና ማስታዎሻ ይዞ ለመመለስ ጊዜ አልነበረኝም ነገር ግን በአጋጣሚ ለበረከት ያህልነው:: ስለዚህ ወደቅድስት ሐገር የሚሄዱ ምዕመናን በአገኙት አጋጣሚ ይህን ታላቅ ቦታ ጎብኝተው በረከት እንዲያገኙ በማስብ ስለሆነ :: ከአጠፋሁም ይቅርታ ይደረግልኝ ::

እግዚብሔር አምላክ ኦርቶዶክስ ሃይማኖታችንን ይጠብቅ አሜን ::

ደብረ ዲማ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቀዳማዊት::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

Postby አባጋዲስ » Mon Oct 17, 2005 9:27 am

የማስታረቅን ስልጣን ለእኛ ሰጠን ሲል ቅዱስ ጳውሎስምን ማለቱ ነው ? ምክንያቱም በብሉይ ጊዜ ብዙ ቅዱሳኖች ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ሲያስታርቁ ነበር እግዚአብሔር ስልጣኑን ድሮ ነው የሰጣቸው ታዲያ እንዴት ቅዱስ ጳውሎስ በእኛ የማስታረቅን ቃል አኖረ ይላል ? ካላችሁ በብሉይ ጊዜ ምንም ቅዱሳኑ ሰዎችን ቢያማልዱም ሰዎቹን ከሲኦል የሚያወጣ ምልጃ አልነበረም :

በሕይወት እያሉ በእኛ የማስታረቅ ቃል አኖረ ሲል ትክክል ነው:: ለምን ቢባል መንፈሱ በህይወት እያለ በውስጡ ስላለ:: ለኛም አሁን ይሰራል:: ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በተመለከተ
መጽሀፉ የሚለው
1.
ሮሜ 8:34 የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ሰለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ::

2.
ዕብ 7:24-25 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ::ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል ::
ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ በእግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል


መቼ ቢባል ለአባቱ ማለትም ለመንፈሱ ደሙ ሲያቀርብ እንዲህ ይላልና
1.
ዕብ .7:27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።

2.
ዕብ .9:24 ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።
ዕብ .9:25 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤
ዕብ .9:26 እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።

አንዴ ፈጽሞታል ዕለት ዕለት መሞት አያስፈልገውም::
አባጋዲስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 10
Joined: Wed Oct 12, 2005 6:57 am
Location: ethiopia


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 6 guests