መንፈሳዊ ምግብ ከማር ይስሐቅ የተወሰደ::

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

መንፈሳዊ ምግብ ከማር ይስሐቅ የተወሰደ::

Postby ደብረ ዲማ » Mon Oct 17, 2005 5:48 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::

እየመጸውትሁ እኖራለሁ ብትል ሰውነትህን አለመለያየት አስለምዳት :
ካለመለያየት ወደመለያየት ሄደህ አንድም ከወንጌል ወደ ሕገ ኦሪት ሂደህ አድልዎ እንዳትሻ ;; በአንድ እጁ እየሰበሰበ ባንድ እጁ እንደሚበትን ሰው እንዳትሆን :; ይህ ይደረጋልን ቢሉ አዎ ደዌ ቁጣ ታስደርገዋል:: በኦሪት ያለ ፈቃድ አንድም: በመለያየት ያለ ፈቃድ አድልዎን ይሻልና :: በወንጌል ; በመመጽዎት ያለ ፈቃድ ግን ሰፊ አእምሮ ያሻል::

እግዚአብሔር ይጠብቀን አሜን
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

እንኳን ደህና መጣህ

Postby ቢኖ. » Mon Oct 17, 2005 2:30 pm

ወንድሜ ደብረዲማ እንኳን ደህና መጣህ የምትመግበንን መንፈሳዊ ምግብ በመቋረጡ ተጎድተን
ነበር አሁን ደግሞ በመምጣትህ ተጽናንተናል::


አክባሪህ ቢኖ
As for me. however, I will boast only about the cross of our Lord Jesus christ. Gela 6:14
ቢኖ.
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 529
Joined: Mon Oct 17, 2005 2:20 pm
Location: ethiopia

Postby ትትና » Tue Oct 18, 2005 6:47 am

እንደምን ሰንብተሀል ወንድማችን ደብረ ዲማ? ብዙ ጊዜ ሆነኝ ድንቅ ጽሁፎችህን ካነበብኩ:: እክርክር መድረክ ላይ መግባት ስለማልወድ ነው እንጂ አንድ ሁለቴ ስምህን አይቼው ነበር:: ለማንኛውም እስቲ ዛሬ የጻፍክልንን ነበር በደንብ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻው አብራራልን እንዳው ቁንጽል ብሎ ነው መሰለኝ ብዙም አልገባንም:: የኔ ነገር ቶሎ አይገባኝም::

መልካሙን ሁሉ እመኝልሀለሁ
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

አጠር ያለ የገዳማት ታሪክ ::ከትናት የቀጠለ:;

Postby ደብረ ዲማ » Tue Oct 18, 2005 8:11 am

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::

የአባ ዩሐንስ ታሪክ ::

አባታችን አባ ናሆም ከክብራቸው የተነሳ የገዳሟ ሁኔታ ተገልጾላቸው ከእኔ በበለጠ ገዳሟን የሚያጸና አባ ዩሐንስ የሚባል ታላቅ መነኩሴ ይመጣል በማለት ተናግረው ወዲያውኑ አርፈዋል:: ቀብራቸውም ; ሲጸልዩበት በነበርው ገዳም/ ክልል / ጎጥ /ውስጥ ተፈጽሟል:: በዚህም ቦታ ካልዕ መብዓ ጽዮን የተባሉ ጻድቅ እና አባ ማቴዎስ የተባሉ መነኩሴ እንደ ተቀበሩበት በታሪክ ይነገራል::
አባ ዩሐንስ በሸዋ ሐገረ ስብከት ከአባታቸው ከየማነ ብርሐን እና ከእናታቸው ከሐመረወርቅ ተወለዱ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሲማሩ እንደነበር የዚህ ዓለም ኑሮ አላፊ መሆኑን በመገንዘብ ከወላጆቻቸው እና ከቤት ንብረታቸው ተለይተው መነኑ :: ከአባ ጸጋ ኢየሱስ ከሚባሉ መነኩሴ ለአስራ አምስት አመታት ሥርዓተ ምንኩስናን ሲማሩ ቆይተው በአባ ጸጋ ኢየሱስ እጅ አስኬማ መላዕክትን ተቀበሉ :: ከዚያም ትንሽ ቆይተው ዋልድማ ገዳም በመግባት የዕድሜ ሽማግሌ አረጋውያን/ አባቶችን እና መነኮሳትን እንጨት በመልቀም ውኃ በመቅዳት እና በመታዘዝ እንዲሁም ሕሙማንን በመፈወስ እና ሙታንን በማንሳት ሰባት አመታት ተቀምጠዋል:: ከዚያም በኃላ በልኡል እግዚአብሔር በተላከ መላክ ወደቅድስቲቱ ሐገር ኢየሩሳሌም እንዲሄዱ ታዘዙ :
አባታችንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ወደ ሐገረ ኢየሩሳሌም ተጉዘው የጌታችን የመድሐኒታችንን የትውልድ ቦታ ቤተለሄምን. የተሰቀለበትን ቀራንዮን እና የተቀበረበትን ጎልጎታን ተሳልመው በዮርዳኖስ ውኃ ተጠምቀው ገዳማትን ለመሳለምና በረከት ለመቀበል ወደ ግብጽ ሐገር ጉዟቸውን ቀጥለዋል::
{ ታቦተ ኪዳነምህረት}
አባ ዩሐንስ ግብጽ ሐገር ከደረሱ በዃላ ወደ ገዳመ አስቄጥስ አቀኑ :; በዚህም ገዳም ከአምስት መቶ አመት በላይ ዕድሜ ያለው ዳግማዊ እንጦንስ የተባሉ ጳጳስ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ስለነበሩ ገና ከሩቅ ሲያዩአቸው አባ ዩሐንስ መጣህን ??? አሏቸው:: አባዩሐንስም በስማቸው ስለጠሯቸው አደነቁ እና አባቴ ሆይ በስሜ የጠሩኝ የት ያውቁኛል??? ስሜንስ ማን ነገርዎት???አሏቸው:: ጳጳሱም እውነት እልሐለሁ ከአምስት መቶ ዓመት በፊት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደው ልጇ ጋር በደብረ ምጥማቅ ተገልጻ አራት አባቶችን :: ታቦተ ሥላሴን: ታቦተ ኢየሱስን: ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እና ደብረ ምጥማቅን ከኢትዮጵያ አንድ ታላቅ ደግ መነኩሴ ስሙም ዩሐንስ የሚባል በዃላኛው ዘመን ይመጣል :: እነዚህን ታቦቶች ስጠው ብላ አዝዛኛለች እናም ተቀበለኝ አሏቸው:: አባዩሐንስም የጌታችን የአምላካችንን ሥራ እያደነቁ እነዚህን ታቦቶች ተቀበሉ:: ከጳጳሱም በረከት በመቀበል ላይ እንዳሉ በራዕይ አንዲት ድንጊያ በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል ; ዛሬ ሜጫ በሚባል አካባቢ ልዩ ስሙ ጉታ በታባለ ቦታ እንደ ጸሐይ ስታበራ አዩ:: { ጉታ ወይም ሜጫ የሚገኘው ባህርዳር አካባቢ ነው} ወዲያውም ከእግዚአብሔር የተላከ መልአክ ቅዱስ ኡራኤል እየመራ ጉታ ወደ ተባለ የኢትዮጵያ ክፍል አደረሳቸው :: በዚህም በታ ይኖር የነበረ ውሮ የሚባል ባለአባት አባታችንን ተቀብሎ ከአስተናገዳቸው በዃላ ደግነታቸውን { ቅድስናቸውን } አውቆ መሬት ሰጣቸው:: አባ ዩሐንስም በታውን ተረክበው ቤተክርስቲያን አንጸው ታቦተ ኢየሱስን አስገብተዋል:: ገዳሙን አጽንተው የባለአባቱን ስም ለማዘከር ሲባል ቦታውን ውራ ኢየሱስ ብለው ሰይመውታል:: ይቆየን::ይቀጥላል

ዩ የሚላው ቃል ለምን ዮ ; አልሆንም የሚል አንባባ ከአለ ዩ ብሎማንበብ የግድ ይሆናል ስማቸው ; የሚጀምረው በዩ ነው እና :: ደብረ ዲማ የአባቶቻችን በረከት ይደርብን አሜን::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

የገዳማት ታሪክ የቀጠለ::

Postby ደብረ ዲማ » Tue Oct 18, 2005 6:57 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
ሰላም ወገኖቼ ዛሬ የመጨረሻውን ክፍል ይዠ ቀርቤአለሁ አብረን እናንብ::

አባ ዩሐንስ በውራ ኢየሱስ ገዳም ሲጸልዩ ገዳመ ዘጌ ውስጥ የብርሃን አምድ ተተክሎ በመንፈስ ቅዱስ ታያቸው:: አባታችንም የዚህን ትርጎአሜ እንዲገለጽላቸው ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ላይ እንዳሉ ቅዱስ ኡራኤል መልአክ እየመራ ታቦተ ሥላሴን ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እና ታቦተ ደብረ ምጥማቅን ይዘው ከአባ ፋኑኤል ጋር ከ300 መቶ መነኮሳት ጋር ወደ ዘጌ ገቡ:; ይህንን ጸጋ እግዚአብሔርን እያደነቁ ከተለመደው ጸሎታቸው ጋር እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ሐመረ ኖሕ ኡራ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አንጸው ከዳግማዊ እንጦንስ የተቀበሏትን ታቦተ ኪዳነ ምሕረት አስገብተዋል :: ታቦተ ሥላሴን ቤተክርስቲያንም አንጸው መካነ ቀኖና ብለውታል:: ታቦተ ደብረ ምጥማቅንም ሰርተው አዝዋ ማርያም በማለት ሰይመውታል:: ደጃዝማች ወረኛ የተባለ ሀገረ ገዥ ከንጉሥ አድያም ሰገድ እያሱ ዘንድ ወደ ጎንደር ሲሄድ የአባዩሐንስን ደግነት ሰምቶ ቡራኬ ለመቀበል ወደ አባታችን መጣ :: አባታችንም ሀገረ ገዥውን በክብር ተቀበሉት አክለውም ጠላቶችህን በማሸነፍ ድል ታገኛለህ ብለው ትንቢት ነገሩት :: ቡራኬም ሰጡት ጸሎትም አደረጉለት::በሚሸኙት ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱ ህንጻ የተፈጸመ ቢሆንም ስዕሉ ገና ያልተሳለ በመሆኑ ንጉሡ እንዲረዱኝ አመልክትልኝ አሉት:: መልእክቱን እንዳይረሳው ማሳሰቢያ ትሆነው ዘንድ የሚጠጡባትን { ቅምጫና{ቅል} ሰጡት :: እርሱም ወደ ጎንደር ሄደ ከንጉሱም ደርሶ ጠላቶቹን በማሸነፍ ድል አግኝቶ ከንጉሡም ተሸልሞ የራሱን ጉዳይም ፈጽሞ የአባታችንን መልዕክት ረስቶ ወደ ሐገሩ ሲመለስ መገጭ ከሚባል ወንዝ ደረሰ ወንዙንም እሻገራለሁ ሲል ፈረሱ ተኛበት ወታደሮቹም የተኛውን ፈረስ ለማስነሳት ቢደበድቡትም ሊነሳላቸው አልቻለም{ እንደ በልአም አህያ እንደማለት ነው} ዘኁ 22- 28 } ይህም የሆነው የአባታችንን የአባ ዩሐንስ ክብር ይገለጽ ዘንድ ነው:;በዚያን ጊዜ ሀገረ ገዥው ወኃ ጠምቶት ስለነበረ ወታደሮቹ ውኃ እንዲያመጡለት አእዘዛቸው :: እነርሱም በቅምጫና { በቅል} ቀድተው ቢሰጡት መልዕክቱ ትዝ አለው በዚህን ጊዜ የተኛው ፈረስ ቢነካው ተነስቶ ወደጎንደር ጉዞውን ቀጠለ :: ሀገረ ገዥውም ተመልሶ ጎንደር ከንጉሡ ደረሰና አባታችን የነገሩትን ሁሉ አስረድቶ መልዕክቱን ለንጉሡ አደረሰ ንጉሱም ትንቢቱንና መልእክቱን ሰምተው አደነቁ '' ለስዕል ማስፈጸሚያ የሚበቃ ገንዘብ ለአባታችን እንዲያደርስ ለሀገረ ገዥው ሰጥተው ሲሸኙት በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ የምትተዳደርበት መሬት አይተህ ከልለህ ስጣቸው ብለው ደጃዝማችን አዘዙ :: እርሱም የንጉሱን ትዕዛዝ በማክበር የተላከላቸውን ገንዘብ ለአባታችን ሰጥቶ አባታችን የፈቀዱትን ቦታ ለገዳሟ መተዳደርያ እንዲሆን ሰጥቷቸዋል::
አባ ፋኑኤል]
ከዚህም በዃላ የብጹ አባታችን ጊዜ ዕረፍታቸው እንደ ደረሰ በጸጋ እግዚአብሔር ስለአወቁት ደቀመዛሙርታቸውን አባ ፋኑኤልን አስቀርበው በእኔ ምትክ ገዳሟን አስተዳድር ልኡል እግዚአብሔር ስለፈቀደልህ የገዳሟን ሥርዓት ጠብቀህ የቤተክርስቲያኗን ስዕል እንድታስፈጽም መንፈሳዊ አደራ ሰጥቸሀለሁ አሏቸው:: አባ ፋኑኤልም በተቀበሉት መንፈሳዊ አደራ መሰረት የገዳሟን ሥርዓት ጠብቀው የቤተክርስቲያኗን ስዕል አስፈጽመው አባታችንም የመላኩን የቅዱስ ኡራኤልን ስም ለማዘከር { ለማስታወስ}ገዳሟን ኡራ ኪደነ ምሕረት በማለት ሰይመዋል:: የቤተክርስቲያኑ ስዕል በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት እርዳታ በ18 97 ዓ ም እንደታደሰ ይነገራል:: የአባታችን እረፍትም ጥቅምት 22ቀን በእየአመቱ ይታሰባል:: ገዳሙንና ቤተክርስቲያኗን በመጎብኘት በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ነገሥታት እና መኮንት የመታሰቢያ ስጦታ ሰጥተዋል:: ለአብነት ያህል::
> አጼ አድያም ሰገድ እያሱ በ16ኛው መቶ ክፍለዘመን አንድ የወርቅ ካባና ሁሉት እያንዳዳቸው 12 አጽቅ ያላቸው ከብርና ከውርቅ የተሰሩ ተቃመ ማህቶት ::

> አጼ ዮሐንስ በ16 29 ዓ ም አንድ የብር ዘውድ ::

> አጼ ተክለ ጊዮርጊስም በ17 72 ዓ ም አንድ የብር ከለቻ::

> አጼ ቴዎድሮስ በ1847 ዓ ም አንድ የብር ዘውድ ::

> አጼ ዮሐንስ በ1885 ዓ ም አንድ የወርቅ ቅብ መጾረ መስቀል::

> ንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን አባለቤታቸው ወይዘሮ ላቀች መኮንን በ1888 ዓ ም አንድ የብር ዘውድ ::

> በትለያዩ ጳጳሳት , መነኮሳት እና ካህናት የተበረከቱ ጥንታዊ የብራና መጽሐፍት በቤተክርስቲያኗ ይገኛሉ::
የአባቶቻችን በረከት ይደርብን አሜን ተፈጸመ::

ደብረ ዲማ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

Postby ትትና » Tue Oct 18, 2005 7:17 pm

ወንድማችን ደብረ ዲማ ቃለ ህይወትን ያሰማልን:: ከአባታችን በረከት ይክፈልህ!!!

ትትና
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby NATHRATHE » Wed Oct 19, 2005 6:10 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ወንድማችን ደብረ ዲማ ቃለ ህይወት ያሰማልን::እውነት በጣም ጥሩ የሆነ መንፈሳዊ ትምህርት ነው::

ይቆየን::
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

እግዚአብሔር ሁሉን በጥበቡ አዘጋጀ::

Postby ደብረ ዲማ » Wed Oct 19, 2005 7:28 am

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን :; ሰላም ወድ ክርስቲያን ወገኖቼ { ወድ ቢኖ እንኩዋን አተም በሰላም ቆየህኝ አሜን


ውድ ትህትና ጥያቄስን አረሳሁትም የጀመርሁትን ለመጨረስ ብየ እንጂ::

ነገሩ እንዲህ ነው በወንጌል አምነህ ህገ ኦሪትን ብትንቅ አትጥጠቀምም አንድም { በፍርድ ወንበር ተቀምጠህ ለተበዳዩ ሳይሆን ለበዳዩ ብትፈርድ } ወንጌልን ከህገ ኦሪት ህገ ኦሪትን ከውንጌል እንደለየህ ይቆጠራል አንድም { አይሁድ አማጽያን በወንጌል ስለማያምኑ } ቢመጸውቱ [ ቢጾሙ [ ቡጸልዩ በመድህነ አለም ክርስቶስ አላመኑምና እዳ ፍዳ አለባቸው ለማለት ነው ብዙ ማለት ይቻላል :; ይቆየን ደብረ ዲማ::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

Postby ምሪ » Wed Oct 19, 2005 6:22 pm

ወንድማችን ደብረዲማ ቃለ ህይወትን ይሰማህ ብዙ ነገርን እያስተማርከን ነው እንደ ትትና እኔም መልሱን ስጠባበቅ ነበር እግዚያብሔር ይስጥልን
ምሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 89
Joined: Sat Aug 21, 2004 10:23 am
Location: united states

Postby ትትና » Mon Oct 24, 2005 5:14 am

ቃለህይወትን ያሰማልኝ ወንድማችን ደብረዲማ!!!

ስለቅዱሳን ገድል ሲነገረን በህይወት ከመዛላችን ብርታትና ጥንካሬን እናገኛለን:: የዛሬን አያድርገውና ወደዚህ ሀገር እንደመጣሁ ብዙ ወንድሞቼ የቤተክርስቲያን ልጆች ደብዳቤ ሲጽፉልኝ የቅዱሳንን ገድል እየጨመሩ ያስነብቡኝ ነበር:: እኔም ታዲያ ውስጤ ደስ ሲለው ብርታትን ሳገኝ ይታወቀኛል:: ዛሬ ታዲያ እሩጫው የህይወት ውጣውረዱ አገራችን ደሞ የፖስታውም መላኪያ መናር እንደበፊቱ ቶሎ ቶሎ እንዲጽፉ አላደረጋቸውም ቢሆንም አልፎ አልፎ የሚልኩልኝ እንደስንቅ ትሆነኛለች::

እባክህ አንተም በተቻለህ ሁሉ የምታውቀውን ንገረን::

እህትህ
ትትና
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

መንፈሳዊ ምግብ ከማር ይስሀቅ.. ለትህትና::

Postby ደብረ ዲማ » Mon Oct 24, 2005 5:57 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
በልቼ ጠጥቼ አይቼ ሰምቼ ንጽሕ ጠብቄ ከሴት እርቄ መኖር ይቻለኛል አትበል::

>>> ተፈትነህ እራስህን የማይለወጥ ሁኖ እስክታገኘው ድረስ { በአርምሞ ኑር}
> ሰውነትህን እንዲህ ፈትነው::
> በስራው ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ገንዘብ አድርግ::
> አጋንትን ድል ትነሳ ዘንድ::
> ልቡናህ ዝንጉ አይሁን :: ተዘክሮተ እግዚአብሔርን አትተው::
> በእኔ ሀይል ስራ እሰራልሉ አትበል::
> የባህርየ ድካምነት እንዳንጋዳ ሁና አሰናክላ እንዳትጥልህ::
> እንጋዳ ሁና በጣለጭ ጊዜ ድካምህን ታውቀዋለህ::
> አዋቂ ነኝ አትበል::
> አዋቂነኝ በማለትህ ሰይጣን በትቢት እንዳይገባብህ :: {አንድ ምሳሌ ልጨምር ዛሬ በርካታ መናፍቃን እየወደቁ ያሉት በትቢት መሆኑን አንዘንጋ} ምክነያቱም የአምላክ እናቱን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን ሳያከብሩ { ጌታ ኢየሱስ } አዳኝ ነው ብለው ሲዘበዝቡ ማየት ምን ያህል ውርደት ይሆን???
> በምትናገረው ነገር ገራገር ሁን::
> ሸካራ ነገር ተናግረህ ተዋርዶ እንዳያገኝህ { ውሽት}ወውነትን ለአንደበትህ አስተምረው::
> የለዘበ የለዘበ ነገር ተናገር ::
ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግነው የተፈጠርህው እርሱን ለማመስገን ነው እና::
ደብረ ዲማ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶቀዳማዊት::
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ይሁን አሜን::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

Postby ትትና » Wed Oct 26, 2005 9:24 am

ስለምክርህ እግዚአብሄር ይስጥልኝ!!!
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests