በዶ/ር ማርቲን ሉተር ላይየሀሰት ውንጀላ ጸሀፊ በአሜሪካ የአስርቱ ትእዛዛት አስወጋጅ መሪ ነው

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

በዶ/ር ማርቲን ሉተር ላይየሀሰት ውንጀላ ጸሀፊ በአሜሪካ የአስርቱ ትእዛዛት አስወጋጅ መሪ ነው

Postby ዲጎኔ » Wed Oct 19, 2005 4:26 am

የክርስቶስ ሰላም ይብዛልን::
በአንዱ ኢትዮጵያዊ የዋርካ ተሳታፊ ሰሞኑን በታላቁ የስነ-መለኮት አስተማሪ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ላይ የሀሰት አሉባልታ ምንጭ ሆኖ የቀረበው
Norma E Cunningham የተባለው ሰው በአሜሪካን ሀገር የህዝቡን ስነምግባር ለዘመናት ጠብቆ የያዘውን የክርስትና እምነት ለማጥፋት ከተደረጁት ቡድኖች አንዱ የሆነው የአስርቱ ትእዛዛት አስወጋጅ ግብረ-ሀይል መሪ መሆኑ ተረጋግጧል::

እነዚህን የጸረ-ክርስትና እንቅስቃሴ መሪዎች ለኢትዮጵያ ጥንታዊ ክርስትና ተቆርቆአሪ ነኝ በማለት ይመጻደቅ ከነበረ ሰው መቅረቡ ምን ያህል በስምና በወግ ክርስትና ባይ በግብር ግን የረቀቀ ጸረ ክርስትና መረብ እንደሚዘረጋ መድረኩን በማየት ሁሉም የኢትዮጵያ ክርስቲያን እንዲገነዘበው በትህትና አቀርባለሁ::

Norma E Cunningham
Freedom from Religion-ffrf

በተረፍ ክርስቲያኖች ሁሉአንዳችን ሌላችንን ሳንዘልፍ በመከባበር እንድንማማርና በአሜሪካም ሆነ በአለም ላይ ባለችው አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ በሀይማኖትና በነጻነት ሽፋን የተነሳውን የአውሬውን ረቂቅ መንፈስ በጾም በጸሎት እንድንዋጋ አሳስባለሁ:

"ውጊያችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና"(ኤፌ6:12)
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ማርቲን ሉተር "አይሁዶችና ውሸቶቻቸው" የሚል መጽሐፍ አልጻፈም ነው የምትለው

Postby Acts 8:26-39 » Wed Oct 19, 2005 4:59 am

ዲጎኒ
ሉተርን በተለያዩ ምክንያቶች የሚቃወሙ ሊኖሩ ይችላሉ:: እኛ ያነሳነው ነጥብ ግን ሉተር የጻፈው መጽሐፍንና ይህም በአዶልፍ ሂትለር የመተግበሩ ጉዳይ ነው::
ማርቲን ሉተር ""The Jews and their lies"" "አይሁዶችና ውሸቶቻቸው" የሚል መጽሐፍ አልጻፈም የምትል ከሆነ ማንም ሰው ኦንላየን
http://www.humanitas-international.org/ ... r-jews.htm
ሊያንብበው ይችላል:: የተጠረዘ መጽሐፍ የሚፈልግ ካለ (Hard copy) በተለይ ውጭ የሚገኝ ሰው ማንኛውም ቤትመጻህፍት ሄዶ ሊያነብበው ይችላል::
ይህንን ሐሰት የምትል ከሆነ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር ቅረብና ሁላችንም እንመልከተው::
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ደጋግሜ ጠቅሻለሁኮ እንኩአን ሉተር ቅዱስ ጳውሎስም በብስጭት ክፉ ተናግሯል

Postby ዲጎኔ » Wed Oct 19, 2005 5:11 am

ምነው የሀገር ልጅ ስንቴ ልናገር እንኩዋን የቀድሞው መነኩሴ ማርቲን ሉተር ሀውርያው ቅዱስ ጳውሎስም በገሪሳዊያንና በተቃዋሚዎች ሲበሳጩ ክፉ ቢናገሩም አይን ቢያሳውሩም እኛ ይህንን እንዳንጠቀምና እንዳንናገር በሌሎች ብዙ ክፍሎች እነዚሁ ሀዋርያ እንደመከሩን ቀናውን የምህረቱን ነገር ብቻ እንሰብካለን::

ግን አንተ ብለህ ብለህ ይህንን የአሜሪካ ክርስቲያኖችን የሚያስለቅሰውን የእግዚአብሄር ስም ከአደባባይ እንዲፋቅ ቆርጦ የተነሳውን ከሀዲ ገና ለገና ማርቲን ሉተርን የሚነቅፍ በመጻፉ ታቀርባለህ?አበስኩ ገበርኩ መሀረነ ክርስቶስ:ምነው ከዮዲት ጉዲት ጀምሮ እስከ ግራኝ አህመድና መንግስቱ ሀይለማርያም ድረስ ክርስትናን ሊያጠፉ የተነሱትን አሁን በክርስቲያኖች መካከል ላለ መለስተኛ ልዩነት ታቀርበዋለህ?አዎ እንደ ሀገራችን ጽንፈኛ አመለካከት ልዩነታችን መለስተኛ አይደለም እንደምትለኝ አውቃለሁ ግን ሉተርን ዱሮ ገዝታ ካባረረችው ካቶሊክ ጋር ግን ስነ-መለኮታዊ ውይይት ስለቀጠለ እንደዚህ አይነቱን ጸረ-ክርስትና ከሀዲ አብረን መፋለም እንጂ አንዳችን አንዳችንን ለመንቀፍ ባንጠቅሰው ደህና ነው:ዛሬ ሉተርን በነቀፈበት ነገ ደግሞ ቅዱስ አባታችንን አቡነ ሰላማ/አትናቴዎስን ሲቀጥል እኔ ዋቢ አላደርገውም ለአንተ ና ለአንት ብቻ ግን እተውልሀለሁ::

የክርስቶስማስተዋል መንፈስ በዋርካ ላይ ይፍሰስ:አሜን
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Wed Oct 19, 2005 6:03 am

ዲጎኒ
ሰዉ ራሱ አንብቦ ማገናዘብና መፍረድ ይችላል የሚል እምነት አለን:: እኛ እራሱ ማርቲን ሉተር የጻፈውን መጽሐፍ ከነ ስሙና ምንጩ አቅርብናል:: የዋርካ ታዳሚ ይህንን መጽሐፍ ጊዜ ወስዶ አንብቦ የየብኩሉ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል:: አስቀድሞ ለማከላከል መሞከሩ ግን ፈርንጅ እንደሚለው የሰውን ኢንተሊጀንስ መስደብ ነው::
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ሊከተለኝ የሚወድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ እንደሚለው ቃል እስኪ የየራሳችሁን መስቀል አሳውቁን

Postby መስቀሉ » Thu Oct 20, 2005 4:39 pm

በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምአንድ አምላክ

"በሁአላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ" ወንጌለ ማርቆስ 8-34
እናንተ ሰዎች ሁላችሁም መቀሉን ለመሸከም የምትወዱ አትመስሉም መስቀሉንም ሳይሸከሙ ክርስትና የለም ::ይህ መስቀል ደግሞ በወርቅና ብርማ ቀለም ያማረው ሳይሆን ስለክርስቶስ የሚደርስባችሁ መከራና መገፋት ሲሆን ሁሉም መስቀሉን አሽቅንጥሮ ለመጣል ሲውተረተር ይታያል ያለፉት የክርስቶስ ቤተሰቦች ላለፉበት የመስቀል ገድል ስንሰማ እምነታችን ይነቃቃል ትምህርትና ተግሳጽም እናገኛለን የእናንተን መስቀል የማስወገድ ምልልስ እንሰማ ግን እናፍራለን::

በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በአለም ዙርያ ዛሬ ስንቶቹ የክርስቶስን መስቀል በመሽከም የሚሰጡትምስክርነትን ብትሰሙ ኖሮ ገና ድሮ ንስሀ ገብታችሁ ይህንን እንካሰላምታችሁን ባቆማችሁ ነበር
መስቀሉ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 675
Joined: Sat Sep 24, 2005 2:08 am
Location: ethiopia

ወዳጄ ልቤ መስቀሉ ስለምክርህ እያመሰገንኩ መስቀሉን ሳላውቅ ገፍቼ ከሆነ እራሴን እፈትሻለሁ

Postby ዲጎኔ » Fri Oct 21, 2005 1:45 am

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወዳጄ ልቤ መስቀሉ ስለሰጥህው ምክር ዝቅ ብዬ እጅ እየነሳሁ ተቀብዬ አውቄ ሳይሆን በዚህ ምልልስ መስቀሉን ገፍቼ እንዳይሆን እራሴን እንደምፈትሽ አረጋግጣለሁ::

አክባሪህ ዲጎኔ ከተግሳጽና ምክር አለቃ ጎርፉ ግቢ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests