መልካም ዜና ለክርስትያኖች!!!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

መልካም ዜና ለክርስትያኖች!!!

Postby ግሸንማርያም » Fri Oct 21, 2005 3:44 am

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
በመጀመሪያ የማክብር ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ::

ታላቁ መምህር መምህር ዘበነ ለማ በDnver colorado የአሁኑ ቅዳሜ ከሰአት, እሁድ ጠዋት, እና እሁድ ከሰአት በDenver Colorado መዳኒያለም ቤተ ክርስትያን ታላቅ የወንጌል ትምህርት ስላዘጋጀ በቦታው ላይ ተገኝታችሁ የእግዚአብሔርን ቃል እንድትማሩ በእግዚአብሔር ስም እጋብዛለሁ::

ትምህርቱ የሚሰጥበትም ቦታ መድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው:: እናንተ እንክዋን ለመሄድ ባትችሉ ወይም ከቦታው የራቃችሁ ቢሆን እንክዋን በስልክ እየደወላችሁ Denver Colorado የሚገኙትን ዘመዶቻችሁን በስልክ እየደውላችሁ ንገሩዋቸው::

የእግዚአብሔር ቸርነት የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳንን የጻድቃንን ሰማእታት ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን::

ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ::
ግሸንማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 366
Joined: Mon Aug 15, 2005 8:11 pm
Location: ethiopia

Postby NATHRATHE » Sun Oct 23, 2005 8:10 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

የእግዚያብሔር መልካም ፈቃድ ሆኖ መምህር ዘበነ በ Denver CO መድኃኒያለም ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ቅዳሜ እለት እና ዛሬ ጠዋት ከቅሳሴ በዋላ የተዘጋጀውን ጉባዬ ተከታትያለሁ::

በትላንትናው እለት ቁጥሩ ከ300 መቶ በላይ የሚሆን የ Denver እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ቃለ እግዚያብሔርን ለመስማት የተገኙ ሲሆን መምህር ዘበነም ቃለ እግዚያብሔርን በሚገባ ለምህመናኑ አስተምራል::ዛሬም ከ3:00 PM Mountain time ጀምሮ ቃለ ወንጌልን ለምመናኑ ያስተምራል::በዛሬው እለት ያብዛዣው ምህመናን እረፍት የሚሆኑበት ስለሆነ ከትላንትናው ከእጥፍ በላይ ምህመናን ሊገኙ እንደሚችሉ የደብሩ ሰንበት ተማሪዎች ከተመኩሮአቸው አንፃር ገምተዋል::እኔም ጉባዬውን ተካፍዬ ሂደቱን በመጠኑ ለመግለጽ እሞክራለሁ::

ይቆየን::
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests