ቤተክርስትያንና የገንዘብ ፍቅር

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ቤተክርስትያንና የገንዘብ ፍቅር

Postby ፎግር » Sun Oct 23, 2005 2:55 pm

ትላንት ትላንት የኦርቶዶክስ ቄሶች በገንዘብ ሲታሙ እንስማ ነበር: እውነትም ነበር ነውም:: እኔ ራሴ የነፍስ አባት ተብዬው ዶሮና ጠጅ እንዲሁም ቲፕ ቢጤ ሳይዘጋጅ መጥቶ ውህ አይረጭም ነበር:: ከዛም ጢም ብሎ ከጠገበ በሁዋላ የአብርሀም ቤት...ማናምን እያለ ገንዘቡን ይዞ ይሄዳል:: ለዚህና ለመሳሰሉት እውነቶች ምንም ማስራጃ አልፈልግም:: ነገር ግን የሚደንቀው እውነተኛዋ የክርስቶስ ቤ/ክ ውስጥ ያሉ አገልጋዩች ምነው እንዲህ በገንዘብ ፍቅር ተነደፉ? ያየሁትን ላካፍላችሁ:: የዛሬ 3 አመት ነበር ኢትዩጵያ እያለሁ አንድ ቤ/ክ የአባልነት ፎርም ስሞላ ጥያቄው ያለማጋነን >20 ነበር:: ታዲያ ከሞላሁ በሁዋላ ለፓስተሩ ስሰጠው ከዛሁሉ ጥያቄ ለእ/ር አስራት/መባ በወር/በሳምንት ስንት ትሰጣለህ የሚለውን ወዲያው ሲያይ ምንም አልሞላሁም ነበርና ባዶ ሆኖ አየው:: ከዚያም ምንም አትሰጥም እንዴ አለኝ? እኔም አይ እኔ ተማሪ ነኝ ቤተሰቦቼ ለትራንስፓርትና ለአንዳንድ ነገር ከሚሰጡኝ በቀር ሌላ ምንጭ የለኝም ቢሆንም አንዳንዴ መባ እሰጣለሁ አልኩት:: አምላክ ያውቃል ለሌሎቹ የሚሰጠውን የፍቅር ሰላምታ ሲነፍግኝ አየሁት:: ከሁሉ የገረመኝ ስንቴ ትጸልያለህ/ መ/ቅዱስ ታነባለህ....የሚሉ ጥያቄዋች ተዘለው ገንዘብ ጋር መሮጡ ነበር:: ሌላው እዚህ አሜሪካ ውስጥ የሆነውን ልናገር:: የበአል ፕሮግራም ነበር እዚያ ላይ ፓስተራ ምን አለች መሰላችሁ የናት የአባት ያያቶች ሳይቀር እዳ መክፈል አለብን ስትል እኔ ደነገጥኩ;; የገንዘብ ማለት እንደነበር ገብቶናል ምክንያቱም ስለገንዘብ ነበር የሚወራውና;; ታዲያ እንዴት ነው ይህ እዳ የሚከፈለው ለሚለው ጥያቄ የነበረው መልስ ምን መሰላችሁ 90% ከምናገኘው ለቤ/ክ በመሰጠት ነው ብላ አረፈችው:: አምላክ ያሳያችሁ እዳችን ተሳረ ጌታ ነጻ አወጣን እያልን በምንናገርበት አንደበት እንዲህ አይነት አሳፋሪ ነገር ስንናገር ያስደንቃል:: ሀይማኖተኛ ካልሆንን በቀር ይህ እውነት(የገንዘብ ፍቅር) በብዙ ቤ/ክች እየተደረገ ያለ ልምምድ ነው:: ሰውን ገንዘብ አምጡ እያሉ ከቤ/ክ ማራቅ:: ብዙ ክርስትያን ማለት እችላለሁ በጣም መሮታል:: የአምላክን ፍቅር ፍለጋ ቤ/ክ ሲሄድ የመድረክ ቀማኞች ከጌታ ቤት ያስወጣሉ:: ፍርዱን ለጌታ እንተወው:: እነዚህ ፓስተሮች ግን እውንተኞቹን አይወክሉም እንደነ ቢሊግርሀም አይነቶች ውድ የጌታ ልጆች ከገንዘብ ይልቅ አምላክን መርጠው ስንት ፍሬ አፍርተዋል:: ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልምና::
love
ፎግር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Sun Feb 20, 2005 12:18 am
Location: united states

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests