የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን በመንቀፈ { መስቅሉ]ለጻፈውመልስ[ ለጸራዊ}

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን በመንቀፈ { መስቅሉ]ለጻፈውመልስ[ ለጸራዊ}

Postby ደብረ ዲማ » Wed Oct 26, 2005 8:19 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
ይድረስ ለመስቅሉ { ፀራዊ}

ፀራዊ} ማለት ጠላት { ተቃዋሚ } ተከራካሪ ማለት ነው::
ሰይጣን ማለትም { እንደ አለፈው በል} / ሉቃ 10 18/ ሠይጣን ከመባሉም ሌላ ብዙ መጠርያ ስምች አሉት እነዚህም , ዲያብሎስ .. ዘንዶ .እባብ . ዜቡል ሐሰተኛ ነቢይ/ ማቴ 12, 24./ 2 ቆሮ 15.. ራዕ 12, 9, 20, 2/ 10ከነዚህም በተጨማሪ ሳጥናኤል . ጋኔን የአየሩ ጅን . ተልከስካሽ >ወዘተ በመባል ይጠራል
በእባብ አድሮ በአዳምና በሄዋን ሞተስ ጋና ሞተ ነፍስን ያመጣ ሰይጣን ነው በቃኤል አድሮ የእናቱን ልጅ አቤልን ያስገደለ ሰይጣን ነው:: በመምለኬ ጣኦት በምናሴ አድሮ የሕገ እግዚአብሔርን ጠባቂና አስጠባቂ የሆነውን ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስን በኩላብ አሰቅሎ በመጋዝ አስተርትሮ ያስገደለ ሰይጣን ነው :: በእስራኤል አድሮ ዓይነ ልቡናቸውን አሳውሮ አጭልሞ ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ የተቀደሰውን ኤርምያስን በድንጋይ አስቀጥቅጦ ያስገደለ ሰይጣን ነው:: በሄሮድስ አድሮ የኢየሱስ ክርስቶስን መንገድ ጠራጊ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ያስገደለ ሰይጣን ነው::
በአጠቃላ ከጥንት ጀምሮ ክፉ ሰዎችን በመሣርያነት ተጠቅሞ መንፈሳዊያን ሰዎችን የሚያስገድል :: ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን የሚያሰድብ ይኽው ሰጣን ነው ::
መድሃኒታችን አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰይጣን ከመጀመርያ ነፍሰ ገዳይ ነበር ሲል; - ነፍሰ ገዳይነቱን ገለፀ እንጂ የመግደያ መሳርያውና የአገዳደል ስልቱን አልገለጸም:; ሰይጣን ነፍስ ሲገድል ከብረት የተሰራ ሰይፍ ጎራዴ _ ጦር ሌላም መሳርያ ይዞ አይታይም::
ሰይጣንራሱ ረቂቅ ነው:: መሳርያውም እረቂቅ ነው:: የሰይጣን መሳርያ ሰዎችን ማነሳሳት ነው:: የሰዎችን አእምሮ አጨልሞ በጎ አመለካከታቸውን ከውስጣቸው በማጥፋት እቅድስ ቤተክርስቲያንን : ጻድቃንን መላእክትን/ ሰማዕታትን / ወዘተ ማሰደብና ማዋረድ የእለት እለት ተገባሩ ነው ::ነፍስ መግደል ኃጢያት እንዳልሆነ አድርጎ ማሳየትና ገዳዩ ሰውን ስለገደለ በእረፍት እንደሚኖር የሚያገኘውም ልዩነገር እንዳለ ማስጎምጀት የሰይጣን የመግደያ መሳርያው ነው :: ክቡር መስቀሉ የተባሉት ፀሐፊም የሚጥፉት መጣጥፋቸው ከላይ ለመረጃ ያህል ከአቀረብነው የመነጭ ክፉ መንፈስ ስለሆን እንላለን የእግዚአብሔር ስም ይገስፅህ አሜን:: ከቅድስት ቤተክርስቲያንን ከውድ ልጆቿ ተወገድ:: አሜን
አጋንት ሰይጣን ምግባሩ በእግዚአብሔር የሚያምኑን ክርስቲያኖች ተቀዋሚ በመሆን ከፈጣሪ የተሰጣቸውን ሕግ ሥርዓት እንዳይፈፅሙ ማድረግና ወድክፋት መንገድ መምራት : በዓለም ላይ መከራና ስቃይ እንዲበዛ ማድረግ የሰይጣን ትልቁ ስራው ነው :: ለዚህም ነው በሰዎች ልቡናአድሮ ሐዋርያዊት{ አለማቀፋዊት } ኦርቶዶክስ ተዋህዶን } የሚያስወቅስና የሚያሰድብ} የአምላካችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ነኝ የሚል ከአፉ ክፉ አይወጣም ሰይጣንን ሊቋቋመው ይችላል:: ስለዚህም በሐዲስ ኪዳን እንዲህ ተብሎ ተጥፏል:: ሰይጣንን ተቋቋሙት ከእናንተም የሸሸ ዘንድ ለእግዚአብሔር ተገዙ ይላል:: / ያዕ, 4. 7 :: በብሉይ ኪዳንም መጽ,, እዮብ, ያስተምረና:: ከክርስቶስ ልደት በፊት ዶያብሎስ ብዙ ስልጣን ነበረው ሰወችን ያሳስትና ያሰቃይ ነበር ::
የሰይጣን ስራ በዚህ ብቻ አያበቃም:: መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝቡን ሲያስተምር ትምህርቱን እንዳይሰሙ / እንዳይቀበሉ / በሰዎች መንፈስ አድሮ ይቃወም ሁከትም ያስነሳ ነበር:: ዛሬም እንደ ነመስቀሉ ያሉ / ፀራዊ / እያስነሳ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ያሰድባል::
ሰይጣን ሰዎችን ለክፉ ነገር ከዳረጋቸው በዃላ በሶኦል አብረውት እንዲኖሩ ማድረግ ነው ;;
እግዚአብሔር አምላክ ከዚህ ይጠብቀን ከክፉ ሰይጣን ስራ ይታደገን አሜን::

ደብረ ዲማ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቀዳማዊት::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

ጸረ-መስቀል የሆነውን የመስቀሉ ቃል ይገልጠዋል

Postby መስቀሉ » Wed Oct 26, 2005 2:36 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ

ለደብረ ዲማ

የእኔ የመጽሀፍ ቅኝት ወይስ የአንተ ፍሬከርስኪ ግዝት ማናቸው ጸረ-መስቀል እንደሆነ የሚለየው ያው ቀራኒዮ መስቀል ላይ የተገለጸልን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ይሆናል:አንተን ግን አሁንም ጌታመስቀል ላይ እንዳለ የምታደርገው/የምትጽፈውን የማታውቅ ስለሆነ ይቅር ይበልህ እልሀለሁ::
እስኪ አሁን የተከፈተውን ርእስ በአሳማኝ ምላሽ መመከት ሲያቅትህ እዚህ ሌላ አምድ መክፈትህ የፈሪ ሽሽት እንጂ ሌላ ምን ይሉታል!

አንተ መጽሀፉን ከጻፉት የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ፈጽሞ የማትሻል ዶ/ር ዲበኩሉ በመጽሀፉ ላይ እንደጠቀሱት በጎ መማማሪያ ሂስ የሚጽፉ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን ከሚያሳድዱት ጎራ ስለሆንክ የትም ሄደህ የተለመደ ከንቱ ግዝትህን ብትዘከዝክ ማንም እንደማይፈራህ ይልቁንም በገባህበት ገብተን ድንቁርናህን እንደምናጋልጥ እወቀው::
መስቀሉ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 675
Joined: Sat Sep 24, 2005 2:08 am
Location: ethiopia

Re: ጸረ-መስቀል የሆነውን የመስቀሉ ቃል ይገልጠዋል

Postby NATHRATHE » Wed Oct 26, 2005 3:17 pm

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ወንድም ደብረ ዲማ ሰሞኑን መናፍቃንን አፍ የመዝጋት ስራ በእግዚያብሔር ቸርነት ተሳክታል::ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ድሮ ሌት ተቀን ሲጭሩ የነበሩ መናፍቃን ሁላ አሁን የት እንደደረሱ አይታወቅም::የአሁኖቹ ደግሞ ከመጀመሪያዎቹ የማይሻሉ አላማቸውን የማያውቁ ---- ሰይጣን ነው መሰለኝ የተጸናወታቸው ወይ Protestant ነን ብለው የሚመስላቸውን አልተቀላቀሉ ወይም ክርስቶስ በደሙ የመሰረታትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስርዐትና ትምህርት በሚገባ ተምረው እንደእግዚያብሔር ቃል አልኖሩ እንዲሁ በባዶ ሜዳ የሚዳክሩ ወላዋዮች ናቸው::እነዚህ ከስድብና ከመንደር ተራ ወሬ የዘለለ ቁም ነገር ስለማይናገሩ እኔ እነሱ የምከፍቱት ርዕስ ስር ሄጄ አላነብም እዚህ እኛ የከፈትነው አምድ ስር መተው የለመዱትን ውሸት ካልቀባጠሩ መልስ አልሰጣቸውም::ስለሆነም ከእነሱ ጋር በመዳረቅ በከንቱ ጊዜአችንን ከምናጠፋ እግዚያብሔር ያቀበለንን የምናውቀውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለዚህ ብንጽፍ እርስ በርስ ስለምንማማርና ያልተረዱ ወገኖችንም እውነትን ወደማወቅ ስለምናመጣቸው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ብንጽፍ::በነገራችን ላይ ሰሞኑን የምትጽፋቸውን ጽሁፎች በጣም አስተማሪና በሳል ናቸው::በዚሁ እንድትበረታ የእግዚያብሔር ቸርነት የድንግል አማላጅነት አይለይህ::
መስቀሉ wrote:በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ

ለደብረ ዲማ

የእኔ የመጽሀፍ ቅኝት ወይስ የአንተ ፍሬከርስኪ ግዝት ማናቸው ጸረ-መስቀል እንደሆነ የሚለየው ያው ቀራኒዮ መስቀል ላይ የተገለጸልን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ይሆናል:አንተን ግን አሁንም ጌታመስቀል ላይ እንዳለ የምታደርገው/የምትጽፈውን የማታውቅ ስለሆነ ይቅር ይበልህ እልሀለሁ::
እስኪ አሁን የተከፈተውን ርእስ በአሳማኝ ምላሽ መመከት ሲያቅትህ እዚህ ሌላ አምድ መክፈትህ የፈሪ ሽሽት እንጂ ሌላ ምን ይሉታል!

አንተ መጽሀፉን ከጻፉት የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ፈጽሞ የማትሻል ዶ/ር ዲበኩሉ በመጽሀፉ ላይ እንደጠቀሱት በጎ መማማሪያ ሂስ የሚጽፉ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን ከሚያሳድዱት ጎራ ስለሆንክ የትም ሄደህ የተለመደ ከንቱ ግዝትህን ብትዘከዝክ ማንም እንደማይፈራህ ይልቁንም በገባህበት ገብተን ድንቁርናህን እንደምናጋልጥ እወቀው::


የመናፍቅ ፉከራ መሆኑ ነው::አይደለም ከቤተ ክርስቲያን በዚህ ዋርካ ላይ ስንቱን መናፍቅ ድምጥማጡን በእግዚያብሔር ቃል እንዳጠፋነው ዋርካን እንደዛ የመናፍቃን መጨፈሪያ እንደነበረች ከዚህ በፊት የተከታተለ ያውቀዋል::እስቲ ልብና ይስጣችሁ::

ይቆየን::
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

ለመስቀሉ ከደብረ ዲማ::

Postby ደብረ ዲማ » Thu Oct 27, 2005 7:32 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::

ወዳጀ ሆይ አንተ ስለኔ ድንቁርና ለማውቅ ከምትደክም እና ጊዜህን ከምታቃጥል እኔ እነግርሃለሁ አትድከም ::
እድሜ 30 ፈሪ ሲሆን
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን / ምእመናት / አላዋቂ ድንቆሮ ዃላቅር ስሆን ሐጢያቴም በቁጥር አይለካም :: በደፈናው ጭንጋፍ ኢትዮጵያዊ ስሆን ሐገሬንና ኦርቶዶክስ ሃይማኖቴን በጣም አድርጌ እወዳለሁ እስከሞት ::
አለማዎቅ ደግሞ ሐጢያት አይደለም :: የማያውቁትን መዘላበድ ግን ሞትም ጭምር እንጂ :: ቸር ንሰንብት:: ደብረ ዲማ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ::
ደብረ ዲማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 142
Joined: Thu Mar 17, 2005 9:10 pm
Location: united states

ስንቱ ብዝረራ? በበቃኝ? በነጥብ? በሞት? ተለየ

Postby ዘላለማዊ » Fri Oct 28, 2005 12:19 am

ይህቺ ደግሞ የምትደንቅ ቱማታ ነች:-

የመናፍቅ ፉከራ መሆኑ ነው ::አይደለም ከቤተ ክርስቲያን በዚህ ዋርካ ላይ ስንቱን መናፍቅ ድምጥማጡን በእግዚያብሔር ቃል እንዳጠፋነው ዋርካን እንደዛ የመናፍቃን መጨፈሪያ እንደነበረች ከዚህ በፊት የተከታተለ ያውቀዋል ::እስቲ ልብና ይስጣችሁ

NATHRATHE:- ስንቶቹን በዝረራ, በበቃኝ, በነጥብ, በሞት, እጅ በመስጠትና ዋርካ ለምኔ እንዳስባልክ አስነበብከን; እናመሰግናለን:: ግን እኮ ይህ እንደ ፖለቲከኛ ደረት የሚያስነፋ አይመስለኝም; ያዙኝ ልቀቁኝም የሚያሰኝ አይደለም::

አዎ የኦርቶዶክስ ትምህርት ሰዎችን አሽንፎልህ ሊሆን ይችላል; ወይም ዘለፋዎችህ ሰዎችን ከመጻፍ አስደንብረው ሊሆንም ይችላል:: አለበለዚያም ከአፋችሁ ከንቱ ንግግር አይሰማ የሚለው የመጽሐፉ ቃል ልብና አእምሯቸውን የገዘላቸው በመሆኑ በከንቱ ቃላት መንፈሳቸውን ላለማበላሸት ጥለው የሸሹም ሊኖሩ ይችላሉ - ያንተኑ ቃል ተከትዬ እንጂ የማውቀው የለኝም:: ሆኖም ግን የክታብ ኃይማኖት, የመናፍስት ጠሪ ትምህርት, የሙታን ሳቢ መንፈስ ቅዱስን የአንድ አምላክ ቃል አሸንፈ ማለት አለመሆኑን ተገንዘብልኝ::

ልብ ግዛና መለስ ብለህ ጽሁፎችህን ለኔ ብለህ ሳይሆን እውን መጽሐፍ ቅዱሱን አንብበህ የምታውቅ ሰው ከሆንክ ባነበብከው ቃል መዝነው? ለነገሩ ለፍጥረታዊ ሰው ክቡር የሆነውን ሰው መግደልም ጽድቅ ነውና ላታስተውለው ትችላለህ:: ልብ በል ይህ ንግግርህ እንኳንስ ክርስትና የኢትዮጵያዊ ጠረን የለውም:: ዓላማህ ማሸነፍና መሸነፍ ሳይሆን እውነትን በፍቅር መመስከር ቢሆን ሁላችንም እንጠቀማለን::

ትምክህትህ ይህ በመሆኑ በጣም አዝናለሁ:: ዋርካ ላይ የመጣነውና መንጽሐፍ ቅዱስን የሚያህል የከበረ ቃል መነጋገር የጀመርነው ሰዎችን ለማባረር ሳይሆን ወደ እውነት ለመምራት መስሎኝ ነበር; ይህንንም አምናለሁ:: አንተ ግን አስደንብሮ ማባረርን ከስኬት ከቆጠርከው ምን አይነት መንፈስ ይዘህ እዚህ ስፍራ ላይ እንዳለህ ለማስተዋል አይቸግርም::

የሰላም አምላክ በጎ ህሊናን እንዲሰጥህ ልመናዬና ጸሎቴ ነው::
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
ዘላለማዊ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Mon Aug 16, 2004 12:03 pm
Location: ethiopia

ማሽነፍ አይደልም እውነትን መመስከር እንጂ

Postby አክሱምማርያም » Fri Oct 28, 2005 1:13 am

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱአምላክ አሜን::

ወንድማችን nathrathe እየመሰከረ ያለው ስለ እውነት (ሰለ እውነተኛው ክርስቶስ) እንጂ ስለ ማሽ ነፍ አይደለም:: እውነትን ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር በማጣቀስ አስተምሮናል ቃለ ህይወት ያስማልን:: እውነትን የያዘ ሁል ጊዜም አሽናፊ ነው:: እግዚአብሄር ይመስ ገን አሜን:: :lol: :lol:

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ ክህደትን ያጥፋልን አሜን::
አክሱምማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 359
Joined: Tue Sep 13, 2005 4:04 am
Location: ethiopia

Postby NATHRATHE » Fri Oct 28, 2005 6:22 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ሰላም ክርስቲያኖች

ዘላለማዊ ታችና እላይ የተጻፈው ሳታነብ ዝም ብለህ ለ ቁንጽል ነገር ይዘህ ትሮጣለህ::አንዱ ያንተ ቢጤ ፈረጠጥክ ላለው አይደለም በቤተ ክርስቲያን እዚህ ዋርካ ላይ እንኳን ስንቱ ተጠራጣሪዎች በሁለት ወገን ስለት ባለው በእግዚያብሔር ቃል ጥርጥራቸው ስላወቁት እንደሌላው ጊዜ ሲፈነጩ አይታዩም::ይህ በገሀዱ አለም ያለው እውነታ ነው::

ይቆየን::
NATHRATHE
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 236
Joined: Mon Apr 18, 2005 7:48 am
Location: united states

ወዳጄ እኔ የኦርቶዶክስ አማኝ አይደለሁም እኮ...!

Postby ዘላለማዊ » Fri Oct 28, 2005 3:42 pm

ሰላም ውድ ወገኖቼ::

NATHRATHE:- እኔ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታይ አይደለሁምና ነገርን አገላብጨ ሳላይ አሳብ መስጠትም ሆነ ወደ ድምዳሜ መምጣትን እጠነቀቃለሁ:: እሩቅ ሳትሄድ እዚሁ ገጽ ላይ ለወገናችን ደብረዲማ ይድረስ ባልከው ጽሁፍህ ውስጥ ያለውን ብቻ መጥቀሱ ዐላማህን በጣም ግልጥ አድርጎ ያሳየዋል:: ልጥቀሰው:-
ወንድም ደብረ ዲማ ሰሞኑን መናፍቃንን አፍ የመዝጋት ስራ በእግዚያብሔር ቸርነት ተሳክታል ::ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ድሮ ሌት ተቀን ሲጭሩ የነበሩ መናፍቃን ሁላ አሁን የት እንደደረሱ አይታወቅም ::የአሁኖቹ ደግሞ ከመጀመሪያዎቹ የማይሻሉ አላማቸውን የማያውቁ ---- ሰይጣን ነው መሰለኝ የተጸናወታቸው ወይ Protestant ነን ብለው የሚመስላቸውን አልተቀላቀሉ ወይም ክርስቶስ በደሙ የመሰረታትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስርዐትና ትምህርት በሚገባ ተምረው እንደእግዚያብሔር ቃል አልኖሩ እንዲሁ በባዶ ሜዳ የሚዳክሩ ወላዋዮች ናቸው ::እነዚህ ከስድብና ከመንደር ተራ ወሬ የዘለለ ቁም ነገር ስለማይናገሩ እኔ እነሱ የምከፍቱት ርዕስ ስር ሄጄ አላነብም እዚህ እኛ የከፈትነው አምድ ስር መተው የለመዱትን ውሸት ካልቀባጠሩ መልስ አልሰጣቸውም ::ስለሆነም ከእነሱ ጋር በመዳረቅ በከንቱ ጊዜአችንን ከምናጠፋ እግዚያብሔር ያቀበለንን የምናውቀውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለዚህ ብንጽፍ እርስ በርስ ስለምንማማርና ያልተረዱ ወገኖችንም እውነትን ወደማወቅ ስለምናመጣቸው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ብንጽፍ

ይህንን እኔ ነኝ እንዴ የጻፍኩት? ይህ ቃልህ የተናገርኩትን አሰት ያስብላልን? ወይስ ቅኔ እየዘረፍክልን / እየተቀኘህልን ይሆን? በበኩሌ አንድ ነገር አደንቃለሁ ቢያንስ በዚህ ሥፍራ መልስ ለመስጠት ስትል መጽሐፍ ቅዱሱን የማንበብ እድል ታገኝ ይሆናል ብዬ አስባለሁ:: ያነበብከው ቃል ሊያጽድቅህ ወይም ሊኮንንህ አይኖችህ እንዲያነቡት እግዚአብሔር መንገድን ስላመቻቸልህ በግሌ ትልቅ ነገር እንደሆነ አስባለሁ::

ፍርድ ለሰው ልጆች የተሰጠ ጉዳይ አይደለምና እርሱን ትተን ትምህርቱ ላይ ብናተኩር አስተዋይነት ነው ብዬ አምናለሁ:: በትምህርቱ ላይ አስተያየት መስጠት አንድ ነገር ነው በግለስብ ላይ ጣትን መጠንቆል ደግሞ ወንጀልም ኃጢአትም ነው; ከዚያም ባሻገር የክርስትና ምግባር አይደለም::

እውን የኦርቶዶክስ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን በዘለፋ ልትግተኝ አትችልም; በፍቅር ግን ብዙ ሥራ ይሰራል:- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም የተወልን አርአያ ፍቅር ነው:- "እኔ በልቤ የዋህ ትሁትም ነኝ" አይደልም ያለን በከበረ ቃሉ::

ወዳጄ ያገር ልጅ የዝረራ ፉከራውን ተወውና ቁምነገሩ ላይ አተኩር:: ቁምነገሩ የተሰቀለው ክርስቶስ ነው:: ስብከታችንም, ዜማችንም, ሽብሸባችናን መክበር መዋረዳችን ብቻውን በዙፋን የተቀመጠውን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚገልጥ ቢሆን እንዴት ያለ ቁምነገር መሰለህ::

ሰላም ይብዛልህ::[/quote]
በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና
መጽሐፈ መክብብ 7፡9
ዘላለማዊ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 825
Joined: Mon Aug 16, 2004 12:03 pm
Location: ethiopia


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests