ዋርካችን ኑሪ(ግጥም)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ዋርካችን ኑሪ(ግጥም)

Postby ኣክሱምማርያም » Fri Dec 02, 2005 5:00 pm

ዋርካችን

ውሎ ማደሪያ
የኛ መደበርያ
የሰነፎች ስብስብ ብትሆንም
ዋርካን መጠበቅ ለክፉ አይሰጥም።

ይህች የኛ ዋርካ
የፍቅር የፖለቲካ
የፉንጋዎች የሰልካካ
የብስል ወይም የጥሬ
አታጣራ ተራ ወሬ

ዋርካ ነሽና የወሬ ቤት
ወሬ ቀድተሽ ወሬ ማጠጣት
እንካ ሰላንቲያ መግጠሚያ
ዋርካ የኛ መዋያ
የውሽት መነሃሪያ
የኛ ዋርካ
ድድ ማስጫችን
ብጉር ማፍረጫችን
ዋርካችን ኑሪ የውሸታሞች ጎራ
ጥላሽ አይለየን እኛም ባንቺ እንኩራ
እንጠብቅሻለን እስኪገኝ ስራ።
አንቺም ከልይን ከጠላት ሴራ
እንወድሻለን አለብን አደራ::
ኣክሱምማርያም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Fri Dec 02, 2005 3:50 pm

Postby ደደቡ » Fri Dec 02, 2005 8:44 pm

ደስ የሚል ግጥም ነው ግን ዲጎኔ ቢያገኘው ምን ያህል ባሳመረው ነበር?ዲጎኔ ወንድሜ እባክህ እንታረቅና ይህችን ዋርካ ከጥላቻ ወደ ፍቅር እንቀይራት::የተለያየ አመለካከት ሊኖረን ይችላል ግን በሰላም መኖር የሚከለክልን ነገር የለም::
እባክህን ልዩነታችንን በወጉ እንያዝና በምንስማማባቸው ነገሮች እንድንወያይ እየጋበዝኩህ ነው::ባለፈው ስላስቀየምኩህ ይቅርታ::ጠልቼህ ሳይሆን አምልጦኝ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ::እነግሸንም ተቀይረዋል::እነአክሱምማርያም ለእውነት ለመቆም እንደቆረጡ እየሰማን ነው::ስለዚህ አንተንና እኔንም የሚያነታርከን ነገር የለም::ካንተ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ጋር እንጅ::
ስለዚህ ዲጎኔ ሞረቴው እባክህን ዋርካችንን የሚወደድ ቦታ በማድረግ እንድትተባበረኝ በትህትና እጠይቃለሁ::
WITH ALL RESPECT.
Live and let's live.
አገሬ ኢትዮጵያ ማንም አይደፍርሽ
ወታደሮችሽ ሁሉም ከትግራይ ናቸው
ደደቡ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 47
Joined: Fri Oct 22, 2004 9:22 pm
Location: ethiopia

ለዳጎኒ ::

Postby አክሱምማርያም » Fri Dec 02, 2005 8:53 pm

በስመ ስላሴ አሜን ::

አይ ጎደኒ ማመሲያ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም :: ሲሉ አልሰማክም ?

ዲጎኒ በሚልው አሳፋሪ ስም ሰው ሁሉ ስለጠላክ አሁን ለመወደድ ወደ ክርስትያን ስም ጠጋጠጋ ማለት ጀምርክ ::

በጣም ያስታውቅብካል :: ያሳፍራልም :: ጴንጤ ብሆን ኖሮ በአንት አፍር ነበር ::

በራሴም በጣም እንድኮራ አድርገከኛል:: ለምን ብትል: በእውነተኛው የብእር ስምህ ዋጋህን ሰለሰጠንህ አህን ደግሞ እንደ እስስት መልክህን ትቀያይራለህ:: እኔግን ብሞት የአንተን ብእር ስም አልጠቀምም:: ለምን? በራስ መተማመን ስላለኝ: ስለ እውነት ስለምመስክር የማወራው ስለማያልቅብኝና ክርስትያን ስለሆንኩኝ:: አንተ ግን የሞትክ ደንባራ መናፍቅ ነህ:: ነፈዝ :lol:
አክሱምማርያም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 359
Joined: Tue Sep 13, 2005 4:04 am
Location: ethiopia

Postby ዲጎኔ » Mon Jun 24, 2013 4:36 am

ሰላም ለሁላችን በያልንበቱ
እንደጥንቱ እስመላለምህረቱ
ብዙ ምስጋና ይድረስ ለባለቤቱ
ለሰራዊት ጌታ በኩለንተና ብርቱ
እስትንፋስ ሰጥቶ ላደረገን ታቦቱ
የመንፈሱ ማደሪያ በቅዱስ ጥምቀቱ
ደግሞም አድናቆት ለዋርካ አስተዳደር
ይህን ሳይት ሲከፍቱ ላደረጉት ትብብር
ሁሉ ያሻውን እንዲጸፍ የልቡን ሳያስቀር
እና ዛሬ የጥንት ዋርካ ፖስቶች ስቃኝ
የወዳጄ ማሳሰቢያ ወደጫፍ ላይ ሳገኝ
ይህን መድብል እንዳቅሚቲ ገጠምኩኝ
ምስጋና ለሚገባው ምስጋናን ከተብኩኝ
በጦቢያው ባህላችን የተከበረ
በሰለጠኑት ዘንድ ይፋ የተዘከረ
ምስጋና ይቅረብ ወገን ለተባበረ

ደደቡ wrote:ደስ የሚል ግጥም ነው ግን ዲጎኔ ቢያገኘው ምን ያህል ባሳመረው ነበር?ዲጎኔ ወንድሜ እባክህ እንታረቅና ይህችን ዋርካ ከጥላቻ ወደ ፍቅር እንቀይራት::የተለያየ አመለካከት ሊኖረን ይችላል ግን በሰላም መኖር የሚከለክልን ነገር የለም::
እባክህን ልዩነታችንን በወጉ እንያዝና በምንስማማባቸው ነገሮች እንድንወያይ እየጋበዝኩህ ነው::ባለፈው ስላስቀየምኩህ ይቅርታ::ጠልቼህ ሳይሆን አምልጦኝ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ::እነግሸንም ተቀይረዋል::እነአክሱምማርያም ለእውነት ለመቆም እንደቆረጡ እየሰማን ነው::ስለዚህ አንተንና እኔንም የሚያነታርከን ነገር የለም::ካንተ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ጋር እንጅ::
ስለዚህ ዲጎኔ ሞረቴው እባክህን ዋርካችንን የሚወደድ ቦታ በማድረግ እንድትተባበረኝ በትህትና እጠይቃለሁ::
WITH ALL RESPECT.
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Mon Jun 24, 2013 7:45 am

በለው በለው...ትኩስ ድንች የሚባል የግጥም ቤት ቢኖር ይችን የወንድሜን ዲጎኔ አታሞ.. ( ..ቦርጭ አላት ለዛ ነው አታሞ ያልኴት) :D ግጥም እዛ ውስጥ ክላሲፋይ ባደርግናት ነበር:: ወገን ደደቡ እንታረቅ ብሎ ለወገን ዲጎኔ ያቀረበው ጥሪ ይሄ ወገን እወነተኛ የግዚአብሄር ሰው መሆኑንና መንፈስ ቅዱስ የቀረበው ሰው መሆኑን አመላካች ነው:: ወንድምህ 70 * 70 ጊዜ ቢበድልህም ይቅር በለው..ይላል ..ይሁን እንጂ ወገን ደደቡ ""እቺን ግጥም ዲጎኔ ቢያገኘው ምን ያህል ያሳምረው ነበር"" ያለውን ሳነብ ይሄ ሰውዬ በጣም አስቂኝና ቀልደኛም እንደሆነ ማወቅ አስችሎኛል:: አለማወቅ ጸጋ ነው ድፍረት ይሰጣል..ወንድሜም እውነት መስሎት
ገጠምኩኝ..
ከተብኩኝ...
ታቦቱ..
ጥምቀቱ..
ስባቱ ..ዱለቱ..
እያለ በሳድስ ቤት ረፈረፈው::
ሰላም አምሹ ኢቪሪ ባዲ... እኛ-ጋ ምሽት ነው:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7943
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests