የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ዋናው » Wed May 07, 2008 1:41 am

ጦሜክስ.... ቆቁ.... ዲጎ.... ያባቱ.... ቶድ.... ባቲ.... ሁሉንም ኬፍ ገጭቺያለው ያዱገነት ወግ እንዴት ነው? እስቲ ገና ዛሬ መግባቴ ነው ዋርካ::ሠላም ልላቹ ነው የገባዉት ሠሞናቱን በሰፊው እንገናኛለን::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ያባቱልጅ » Wed May 07, 2008 11:42 pm

ዮሀንስ
እሱን አታንሳው..ሰፈራችን ምስቅልቅሉ ወቶዋል አሉኝ...እኔ የተመለስኩት እንግዲህ Feb ላይ ነበር. አሁን መነገድ ሊሰሩ በለው ነው አሉ ከድልድይ የጀመሩ ሳላይሽ (ማዞሪያ) ይዞ አብነት, ከዛም ወደ ተክልይ ነው አሉ የሚዘልቀው....የሚገርመው የኢትዮጵያ ህዝብ መች መንገድ ቸገረው እና....ደጉን ያምጣ አሉ ጋሽ አቤ
የሚደበረው በተለይ ባለሱቆቹን ሲያስነሱዋቸው የሰጥዋቸው ተቀያሬ ቦታ OR ገንዘብ የለም. ቤቱ የግል ከሆነ ብቻ የሆነች ገንዘብ ተሰጣለች...አስቡት የትኛው ቤት ነው የግል

እስቴ ሁሉም ሆኖ ጤና ይሁኑ ...በያሉበት
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ቶድ » Fri May 30, 2008 2:50 am

ኧረ እባካችሁ የግድ የጎሳዬን ወገን ተሰብሰቡ የሚለውን ዘፈን መርኬ ተሰብሰቡ እያልን ካልዘፈንን አንሰባሰብም ማለት ነው?
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ዋናው » Mon Jun 02, 2008 10:49 pm

ሠላም ቶድ ....

በጣም ሚገርምህ ሁሉም እንዳንተ ከ 13 ቀናትና ከዛ በላይ የተረሣዉን ታላቁን ቤታችንን እያስታወሠ ወደዚች ሣሎን ጎትቶ ሲያመጣ ለትዝታም ይሁን ለጫወታ አንድ ሁለት ሚለው የለም:: ብቻ ኸረ አንጠፋፋ ብሎ ዘለላ ሠላምታዎችን ጭሮ ላጥ ይላል ልክ ሽቄ ዛሩ እንደቆመለት የመርኬ ልጅ :wink: ...... ምነው ጨዋታ ጠፋብን እንዴ ጎበዝ?
አንድ ጊዜ ምን ሆነ መሠለህ ጃፋርን መቼም ታውቀዋለህ የመጀመሪያው የሠፈራችን የዲቪ ባለዕድል ነው: አንዲት ያዲስከተማ ቺክ ተሟሙቶ ፊክስ ያደርግና ይጋብዛታል ጃፋር ያው ታውቀዋለህ እንኳን ከቺክ ጋር ካዋቂ ጋር ሲያወራ ሚያልበው ልጅ ነው... እናም ለርሷ ማንጎ ጁስ ለርሱ ሻይ በሎሚ አዝዞ ዓይን ዓይኗን እያየ ሚያወራው ይጠፋል ''ተጫወት'' ትላለች እየቆየች: እሱም ዓይኑን እየሠበረ ''ተጫወቺ'' ይላታል በኌላ ቆይቶ ቆይቶ መሀላቸው ያለውን ፀጥታ ለማባረር የተላከች ምትመስል ዝንብ ልጅቷ እጅ ላይ ስታርፍ ... እሽሽሽ ብላ ስታባር ያያትና ወሬ ያገኘ መስሎት ''ዝምብ ትወጂያለሽ?'' ብሎ ጠየቃት''ምነው ቆሻሻ እመስላለው?'' ብላ ጁሱን ደፍታበት ሄደች:: በወቅቱ ጃፋር ይሄ ነገር በኔ አልተከሠተም ብሎ ሲያስተባብል ሠሚ ቢያጣም ከረጅም ጊዜ በኌላ ግን ነገሯን በጆክ መልክ ሠማናት: እስካሁን የጃፋር ታሪክ ተስፋፍታ ነው ብለው ሚያምኑ አዲስ ከተማዊያን አሉ:: እንደነ ባቲ....ቅቅቅ

እቺን ዕውነተኛ ቀልድ ያነሣዋት ወግ ከጠፋብን እንዲያው ምናምኑን እንተፈንቶውንም እያወራን ቢሆን ሠፈራችንን እናስታውስ ብዬ ነው:: እንደዝንቧም ባይሆን

እስቲ በል ዛሩ የቆመ የመርኬ ዓይነት ባይሆንም ነገ ቀጫጫ ሽቀላ አለችብኝ በዚሁ ላምልጥ
መልካሙን ሁሉ ላዲስከተማዊያን
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ዮሀንስ ተክለ » Mon Jun 09, 2008 12:13 pm

ውድ አዲስ ከቴዎች እንደምን ከረማችሁ!!!
በዚህ ሰመር ወደ አዱ ገነት ለመብረር በዝግጀት ላይ ነኝ ካሁኑ ከሰባተኛ እስከ ማዞሪያ ,መርኬ,ኡጅራ ቤት,ሲኒማ ራስ ሁሉንም አይቸ ሰመለስ በሰፊው አወራችሀለሁ ምናልባት ሰላምታ ላደርስላችሁ የምትፈልጉት ካለ አሳውቁኝ
ወይ አዲስ ከተማ ወይ ሰፈሬ ሆይ
አገርም እንደ ሰው ይናፍቃል ወይ!!!ጨምሩበት
ዮሀንስ ተክለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Wed Dec 12, 2007 2:01 pm

Postby ዲጎኔ » Mon Jun 09, 2008 2:03 pm

ሰላም ለሁላችን
ውድ ዮሀንስ ተክለ
መልካም ጉዞ እመኝልሀለሁ::ያን ሰፈራችንን በደንብ ቃኝተህ ወቅታዊ ዘገባ አቅርብልን በተለይ ሰባተኛ እንዴት ነው? ሲኒማ አድሲ ከተማንስ ለምን ረሳህው ስንት ገብቶ ይሆን በሽልንግ የምናይበት ቤት ነበር:YMCA ምን ያህል ተሻሽሏል?አሁንም የቀበሌ ነው:: ሻሚታ ሰፈሩስ አሁንም ደርቷል?
አክባሪህ ዲጎኔ ሞረቴው ከጌጃ ሰፈር አዲስ ከተማ ማዶ
ዮሀንስ ተክለ wrote:ውድ አዲስ ከቴዎች እንደምን ከረማችሁ!!!
በዚህ ሰመር ወደ አዱ ገነት ለመብረር በዝግጀት ላይ ነኝ ካሁኑ ከሰባተኛ እስከ ማዞሪያ ,መርኬ,ኡጅራ ቤት,ሲኒማ ራስ ሁሉንም አይቸ ሰመለስ በሰፊው አወራችሀለሁ ምናልባት ሰላምታ ላደርስላችሁ የምትፈልጉት ካለ አሳውቁኝ
ወይ አዲስ ከተማ ወይ ሰፈሬ ሆይ
አገርም እንደ ሰው ይናፍቃል ወይ!!!ጨምሩበት
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ለሰፈሬ ምርጦች

Postby ቶድ » Wed Jun 11, 2008 10:57 pm

የከበረ ሰላምታ ለተጠፋፋነው ለውድ የመርኬ ልጆች!! ኧረ እንዴት ናችሁ ባያሌው??????? ውድ ዮሀንስ ተክለ እባክህ ከተቻለህ መርካቶን ሳምልኝ!! ያ ያሳደገንና ያስተማረን መርካቶ የፈለጉ እንደፈለጉ ሸነሸኑት የሚለውን ወሬ እንደሰማሁ በጣም ነው ያዘንኩት:: ቢሆንም ድሮስ መርኬ መች ለራስዋ ሆና ታውቃልችና ነው??????? ለፍታ ለሰው ደክማ ለሰው. ነበር......... ቢሆንም እስካሁን ግን ብዙ ሰው ያመሰግናት ነበር ............. ያሁኑ ግን ከፋ!!!!!!! ከተገለገለባትም በኌላ እያፈራረሳት ነው ሲባል በጣም ከማዘን በስተቀር ምን አቅም አለኝ???????????አይዟችሁ እግዚአብሔር ያውቃል:: አቦ ምነው ብሶት አበዛሁ ጎበዝ??????እስኪ ሰለሰፈራችን አንድ ታዋቂ ሌባ ላጫውታችሁ:: ስሙን ሳልናገር....... ከመስጊድ በጣም የሚበረክት ውድ ጫማ ይሰርቅና........ 5 ዓመት ሙሉ አደረገው:: ጫማው ምንም አልሆነም ........ ማሰሪያ ብቻ ነው የሚበጠሰው:: ማሰሪያ በተበጠሰ ቁጥር አዲስ እየገዛ ይቀይርለታል:: ታዲያ የሰፈር ልጆች ሲተርቡት............ አንተ የጫማ ማሰሪያ ብቻ የምትቀይርለት.....ቡታጋዝ ነው ወይስ ጫማ ብለው የተረቡት በጣም አልረሳውም::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ቶድ » Wed Jun 18, 2008 4:43 am

ኧረ የመርኬ ልጆች ያለ!!!!!!!!!! ጎበዝ ፃፍ ፃፍ አርጉ እንጂ!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Re: ለሰፈሬ ምርጦች

Postby ዋናው » Fri Jun 20, 2008 11:21 pm

ቶድ wrote: ... ከመስጊድ በጣም የሚበረክት ውድ ጫማ ይሰርቅና........ 5 ዓመት ሙሉ አደረገው:: ጫማው ምንም አልሆነም ........ ማሰሪያ ብቻ ነው የሚበጠሰው:: ማሰሪያ በተበጠሰ ቁጥር አዲስ እየገዛ ይቀይርለታል:: ታዲያ የሰፈር ልጆች ሲተርቡት............ አንተ የጫማ ማሰሪያ ብቻ የምትቀይርለት.....ቡታጋዝ ነው ወይስ ጫማ ብለው የተረቡት በጣም አልረሳውም::

እቺ ተረብ ግድል ነው ያደረገችኝ ቶድ
የመርኬ ሠው ድህነቱን ለራሱ ኢንተርቴይን እያደረገ ሚኖር ህዝብ ነው::
ባለፈው የሠፈር ልጆች የላኩልኝ ቪዲዮ ዘግይቶ ደረሰኝ:: ሳየው በጣም ነው ፍርስ ያልኩት: ለቅበላ ተሰባስበው ጾም መያዣን ሲያከብሩ ነው:: ለባልፈው ዑዳዴ ጾም ታዲያ ምን ብለው ሴሌብሬት እያደረጉ እንደነበር ታውቃለህ ይሄ የመጨረሻ ሕጋዊ ጾማችን ነው ምክኒያቱም ካሁን በኌላ ኑሮው ስለናረ የግዱ ጾም የግላችን ይሆናል እያሉ መቼም ችግር እንደቃመ ሠው ዓይኖቹን አፍጥጦ ቢመጣም የመርኬ ልጅ ሆዱ እንዳይጮኽ ሚጎርሰው አያጣም ከሱም አልፎ ለሱሱ ሚሆን የኢሻራን ጫት በአፉ እያደረገ ነው ስለችግር በሬዲዮ ሚሠማው: ኸረ ለዘላለሙም ችግር አይያቸው አቦ::
አሁን አሁን መርኬ ላይ ትላልቅ የኩርቱ ፌስታሎች ገበያ አጥተዋሉ ይባላል:: ምክኒያቱም ገበያተኛው ምንም ቢሽምት ከስሷ ላስቲክ አያልፍምና ነው:: ጋሼ ላድርስልዎት ሚባል ዕቃ ሚይዝም ጠፍቷል ግን ግርግሩ አሁንም አለ ሠው መኖር አለበት ሲኖር ደግሞ ቢያንስም መሸመቱ ግድ ነው::
እኔ ምለው እቺ የሠፈር አምዳችን በአገርቤት መብራት ነው'ንዴ ምትሠራው? ሠው ሁሉ ጠፋፋ ኸረ ጎበዝ እንጠያየቅ::

ዋናው ነኝ ከአዲስከቴ (የኢትዮጵያ እምብርት)
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ለሰፈሬ ምርጦች

Postby ዋናው » Fri Jun 20, 2008 11:25 pm

ዮሐንስ ተክለ እንደጻፈው

ውድ አዲስ ከቴዎች እንደምን ከረማችሁ !!!
በዚህ ሰመር ወደ አዱ ገነት ለመብረር በዝግጀት ላይ ነኝ ካሁኑ ከሰባተኛ እስከ ማዞሪያ ,መርኬ ,ኡጅራ ቤት ,ሲኒማ ራስ ሁሉንም አይቸ ሰመለስ በሰፊው አወራችሀለሁ ምናልባት ሰላምታ ላደርስላችሁ የምትፈልጉት ካለ አሳውቁኝ
ወይ አዲስ ከተማ ወይ ሰፈሬ ሆይ
አገርም እንደ ሰው ይናፍቃል ወይ !!!ጨምሩበት
ሳልልክህ ሄድክ'ንዴ?
Last edited by ዋናው on Sat Jun 21, 2008 3:03 am, edited 2 times in total.
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ባለከዘራ » Sat Jun 21, 2008 1:00 am

ሠላም: አድስ: ከቲዎች: እንዋናው: ቶድ: የምታወሩት: ሁሉ: እንግዳ: ሆነብኝ: ምናልባት: there might be a generation gap: መርኪን: የለቀኩት: በ1976: በእትዮጵያ: HIGH SCHOOL ሆኚ: የወጥኣሁት: የምታወሩት: ከሲለሽI: ባሪያወና: ከሙሉገታ: ወጨፎ: በስተቀር: ላወቅ: አልቻልኩም: ደሮ: merkato: አካባቢ: ያልገባኡበት: ቦታ: የለም: typical የአዲስ: ከተማ: ልጅ: ነበርኩ:: ዋናው: ክሰለሽI: ለላ: የምታውቀው: ሰው: አለህ:ዎዪ: I mean auto garage ፊትለፊት? Auto genera general tag# was 55555, it was red sport ባለፈው: ላዪ:ሰላነሳህው:
nuro kalut telaja yimokal
ባለከዘራ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Wed Apr 23, 2008 2:13 am

Postby ቶድ » Sun Jun 22, 2008 4:14 pm

ለውድ ባለከዘራ!!!!!!!! እንኳን ወደዚህ ዓምድ በሰላም መጣህ:: በተጨማሪም ስለ ጄኔሬሽን ጋፕ ላቀረብከው ጥያቄ......... አንተ ማንነትህን ሰፈርህን ቅያስህን ወይንም ስልምታውቀው ሰው ጫወታ አምጣና ....... ብዙ ዝርዝር ነገሮች ይቀርቡልሀል:: 1976???????? አሁን በቅርብ ጊዜ እኮ ነው የወጣኸው:: 24 ዓመት ብቻ እኮ ናት ጎበዝ:: ስለነ ሙሉጌታ ወጨፎና ስለስልሺ ባሪያው እያውክ....... ስለ ሳሚ ጋላክሲ (አውቶ ጄኔራል ጋራጅ) እያወራህ......... የምን ጋፕ ነው የምትለው............ እስኪ ከአንተ ትዝታዎች ጀምርልንና....... ከዛ የኛን መልስ ታየዋለህ:: እዚህ ዓምድ ውስጥ ሉሲ የተሰረገችበትን ቦታ መምራት የሚችሉ አንጋፋ ፀሐፊያን ያሉበት ክፍል እና ስለ መርኬ ያለምንም ማጋነን ከታላቋ ንግስት ከጣይቱ ብጡል ዘመን ጀምሮ ያለውን በዝርዝር ያወጉሀል:: ቅቅቅቅቅቅቅቅ................... ቸር ይግጠመን::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ባለከዘራ » Wed Jun 25, 2008 4:18 am

ወንደም: ቶድ: በጣም: ነው: ያሳክቀኝ:: አመስግናለሁ::
nuro kalut telaja yimokal
ባለከዘራ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 82
Joined: Wed Apr 23, 2008 2:13 am

Postby አቡኑ » Thu Jun 26, 2008 6:52 pm

ቶድ wrote:ለውድ ባለከዘራ!!!!!!!! እንኳን ወደዚህ ዓምድ በሰላም መጣህ:: በተጨማሪም ስለ ጄኔሬሽን ጋፕ ላቀረብከው ጥያቄ......... አንተ ማንነትህን ሰፈርህን ቅያስህን ወይንም ስልምታውቀው ሰው ጫወታ አምጣና ....... ብዙ ዝርዝር ነገሮች ይቀርቡልሀል:: 1976???????? አሁን በቅርብ ጊዜ እኮ ነው የወጣኸው:: 24 ዓመት ብቻ እኮ ናት ጎበዝ:: ስለነ ሙሉጌታ ወጨፎና ስለስልሺ ባሪያው እያውክ....... ስለ ሳሚ ጋላክሲ (አውቶ ጄኔራል ጋራጅ) እያወራህ......... የምን ጋፕ ነው የምትለው............ እስኪ ከአንተ ትዝታዎች ጀምርልንና....... ከዛ የኛን መልስ ታየዋለህ:: እዚህ ዓምድ ውስጥ ሉሲ የተሰረገችበትን ቦታ መምራት የሚችሉ አንጋፋ ፀሐፊያን ያሉበት ክፍል እና ስለ መርኬ ያለምንም ማጋነን ከታላቋ ንግስት ከጣይቱ ብጡል ዘመን ጀምሮ ያለውን በዝርዝር ያወጉሀል:: ቅቅቅቅቅቅቅቅ................... ቸር ይግጠመን::

ወድ ባለ ከዘራ በኔ ግምት የጄነሬሽን ጋፕ የምትለው ነገር እንክዋን ያለ አይመስለኝል እኔ ለምሳለ አዲስ ከቴን የማውቃት ከትውልድ ዘመኔ ከ 50 ዎቹ በኢትዮጵያ ጀምሮ ነው ለምሳሌ ምን ብትለኝ
ድሮ ከተማርኩበት አቶ ዘውዴ እሸቴ ት/ቤት ማለት ከወስኔ ጠጀ ቤት በታች ሲሆን ትንሽ ትንሽ ትዝ የሚለኝ ደሞ ወደ ደሮው ቃጫ ፋብሪካ የሚሄደው መንገድ ሳይሰራ በመንገዱ ዳር አናጋው ት/ቤት የሚባል እንደነበረና እኔ እራሴ የመጀመሪያው የባልቻ አባነፍሶ ተማሪ ስሆን ያን ጊዜ አቶ ሀጎስጢኖስ የሚባሉ አስተማሪ እንደነበሩን ቲቸር ታየ,አበበች,አቶ ከበደ እጅ ሰራ አስተማሪ በሰንሰል የሚገርፉን ይህን ሁሉ አስታውሳለሁ

ታድያ ምኑ ነው የጀነሬሽን ጋፕ የምትለው ምናልባትም አወቅህ ይሆናል
አቡኑ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 907
Joined: Tue Oct 11, 2005 7:42 pm
Location: Mars

Postby ቶድ » Fri Jul 11, 2008 10:38 am

መርካቶ በሰላም ነው የተጠፋፋነው????????????
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests