የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ዋናው » Sat Apr 28, 2007 2:33 pm

ጌታ wrote:ዋኒቾ ለካ በጤናህ እንዲህ አሪፍ ልጅ አልሆንክም?

እንደሻው ዛሬ ታዋቂ ሳይሆን የቴዎድሮስ ታደሰን ዘፈን ሰፈር ውስጥ መዝፈን ይወድ ነበር:: አሁን የራሱ ዌብሳይት ከፍቶ ምናምን ለንደን ነኝ ያለሁት ሲል አንብቤያለሁ:: ይመቸው::

የከፍተኛ 5 ቀበሌ 18 ኪነትንስ ታስታውሰዋለህ? በአንድ ወቅት ጥሩ ይንቀሳቀሱ ነበር:: (ይህ ፍንዴክሶቹን እነ ጦምኔውን አይመለከትም)


ጌታ
ባንድ አየር አብሮ የማደጉ ሚስጥር ነፍስ ማነበቡ አይቀርም መቼም አዲስከተሜኛ አየሁብህ ልበል:: ደስ ይላል::
ታዲያ ጨዋታዉን እናምጣዋ የ18ቱን ኪነት በዝና አውቀው ነበር ስለኩሪ ከዛ የምፍለቋን ጉዳይ ግን አልደረስኩበት ይሆን እንጃ.....
18ቀበሌ የአደሬ ሠፈር ጥቂቶችን ባንድ ወቅት ውሃ ለማጣጣት እንገናኝ ነበር ...እነምስራቅ ሸረፋ እነ ሠዒድ.....

ጦምሽ እስቲ በነካ እጅህ ስለሠፈር ትኵስ ወሬ አምጣ ...ለምሳሌ ባለጌው ፎቅ ለምን ባለጌ ስለመባሉ አይነት ለውጦች ካሉ...

ቋንጥሽ____ ስለአብነቷ ቂጥ እኔንጃ ምን በ11 ሠዓት ላይ ከአዲስከተማ ቁልቁል ሚተመውን ቂጥ አይተህ ጥንግርግር ትል የለ እንዴ ነው ብዙም ሳያምርባቸው ነው የወጣከው ቅቅቅ በነገራችን ላይ እዚ አሉ የአብነት እንስቶች በጣም ቆነጃጅት ናቸው::

እስቲ መጣው ደግሞ ለጭውውታችን ከመነን ባሮ ጅን ይዤ እየተጨዋወታቹ


ዋናው___________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ቶድ » Fri May 04, 2007 5:52 pm

መጥቻለሁ:
እኔም የአዲስ ከተማ ልጅ ነኝ::ስለአዲሱ አስፋልት አስተያየት የሰጠኸው ....ከሱ የተሻለ አስፋልት የት ሰፈር ሆነህ ነው? እኛ ሠፈር ከሆንክ ይህ አስፋልት አሁንም ሁሌም እሱ ብቻ ነው አዲስ አስፋልት ያለው:: ሌላ ልታሰራልን ካሰብክ ስሙን እንቀይረዋለን ግን ብንቀይረውስ ማን ብለህ ልትሠየመው ይሆን ???????????

በዚህ አጋጣሚ ጭዋታቹ ወደትውልድ መንደሬ በሀሳብ ወስዶኝ ነው የመጣሁት::
እመለሳለሁ.......

ቶድ::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ቶድ » Fri May 04, 2007 6:08 pm

ስለኩዋስ ብታነሱ አዲስ ከተማ ት/ቤት የቀበሌዎች ጨዋታ ላይ """ብርሀኔ ፑዛን""" አስታወሳችሁኝ......እባካችሁን የብረሀኔ ፑዛን ፉገራ ጣል ጣል አድርጉ::
ከቀልዶቹ መሀል:- ለበራሪ ኮከብ ሲጫወት......መሀመድ አሊን (የቢሄራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረውን) ጡንቻዉን ሰንጥቆት እየደማ እያለ መሀመድ ተናዶ << እንደዚህ አድርገህ ትተለትለኛለህ? ብላው እሺ ና ብላው!! ብሎ ሲለው ብረሀኔ ፑዛም እኔ የእስላም ስጋ አልበላም አለው::

እስቲ እናንተ ስትጨማምሩ እኔም እመለስበታለሁ::


ቶድ ነኝ::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ቶድ » Fri May 04, 2007 10:17 pm

ዛሬ የሰፈር ሰው ምነው ጠፋ???? ለኔ አስረክባችሁ እንዳልጠፋችሁ ነው!!!! አይ አለሙ ሜዳ ??? ያ ሜዳው ከመጥበቡ የተነሳ በረኞች የሚጨባበጡበት:: ታዴ ሸንካላውን የሚያስታውሰው ማነው?????? 21 ቀበሌዎችስ .......ሻፍትን የሚያውቀው ካለ......በላይ ንጋታ.... ግርማ አህያ ራስ.....ዘበርጋ ግሮሰሪ......መሀመድ የሱፍ (አደገኛ ኳስ ተጫዋች).......በዚህ ትንሽ ልበልና በኌላ ስለ ከፍተኛ 4...5...6...7...ይቅርታ ስለ ሁሉም ይቻላል .....................ቸር ይግጠመን
ቶ[/list]
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby እንቆጳፂዮን1 » Mon May 07, 2007 2:57 pm

ተመልሺያለው..........................................................................

በጣም ደስ ደስ ይምሉ የአዲስከተማ ትዝታሆች ነው ያስኮመኮማችሁኝ አቦ የዌናሞ ትዝታን ስታመጡ እኔም በህሳብ ችልጥ አልክኝ
ታዲያ ምነው ክዋስ ጨዋታ ብቻ አበዛቹ ....ያ የአብነቱ ተወዘዋዥ የቀለጠው መንደር ላይ ሚሰራው ታስታውሱታላቹ አዉን አይርላንድ ነው ያለው አዉን,,,
ጨዋታዉን አምጡት እንግዲ ቶድ አንተ የሰፈሩ አውራ ትመስላለህ አጫውተን ባክህ ዘበርጋ ግሮሠሪ ተልኬ እቁብ ልከፍል እሄድ ነበር እዛሰፈር መቅደስ ቂጦን ታውቃታለህ?
እንቆጳፂዮን1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 10
Joined: Wed Oct 11, 2006 7:05 pm

Postby ዋናው » Thu May 10, 2007 10:41 pm

ቶድ wrote: አይ አለሙ ሜዳ ??? ያ ሜዳው ከመጥበቡ የተነሳ በረኞች የሚጨባበጡበት::


በጣም ያሳቀችኝ አባባል ናት.....
ኸረ አዲስከተማዎች የት ጠፋቹ ....ተለጥጦ ኳስ-ሜዳ የደረሰው አዲስከተማ ...ዛሬ ምነው ጨላለመች? ...ቶድ ከአንተ ብዙ ብዙ
ትዝታ ዘ-አዲስከተማ እንደምንኮመኩም ተስፋ አለኝ

እስቲ ሌሎቹን ጠርቼ ልምጣማ


______________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ሀምሳለ » Wed May 16, 2007 4:49 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በሳቅ ገደልከኝ ቶድ አለሙ ሜዳ እኛ ሰናቀው በጣም ሰፊ ነበር :D ገፍተው ገፍተው አጠበቡት እሱንም :oops:

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ሳቅ ገደለኝ
ቆይ ከ ተካልኝ ከፍ ብሎ ያለው ሻይ ቤት ጌታን አየሁት ፓስቲ ግዛልኝ ልበለው መጣሁ ::

ሀምሳለ
ሀምሳለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 243
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
Location: America

Postby ቶድ » Thu May 17, 2007 3:06 pm

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን !!!!! ብቅ ብለናል!!!!!!!!!!!!!!
ሉህ !!!የ21 ልጅ ነኝ ... አለሙ ሜዳ የተጫወተ... አዲሱ አስፋልት...ወዘተ...ብለህ ምነው ጠፋህ???አይ አዲሱ አስባልት ''' ያ ጭቃ የሚያካፋበት መንገድ''' እሱ ይገርማል:: ዝናብ ባይዘንብ እንኳ እራሱ የመንገድ ቧንቧ የሚያፈነዳው:: እሱን መንገድ ለዘመናት ነው የታገስነው:: ደግሞ አዲሱ አስባልት???? አይገርምም!!! ወንድሜ ሉህ መችም ዘውድ እሸቴ ከተማርክ የራስህን በርጩማ ከቤት ይዘህ እየሄድክ .......እኔ አልወጣኝም.....እባክህ በትዝታ ተመለስና እንጨዋወት::
አምሳለ......እርድና ፊደሎችሽ ላይ ይታያሉ.....!! ከከፍተኛ 6 እነ ተካ ገለቱን.. ከከፍተኛ 5 እነቅድስት ቂጦን...ከከፍተኛ 4 እነካሳሁን ባሪያውን{ዳንሰኛውን...አየርላንድ ነው ያለው...}...እንዴት ነው??..ሰፈርሽ የት ነው?? ይቅርታ ትቼዋለሁ!!!ለጥያቄሽ መልስ...ከሳር ጠጅ ቤት በላይ ያለው ግሮሰሪ ''ኮንጎ ቤት ይባላል'':: የነግርማ አበበ{የባቡር ኳስ ተጫዋች የነበረው} ነው::የ10 ቀበሌ ልጅ ነው:; እህቱ መርከብ አበበ ትባላለች::የብሄራዊ ቡድን ቫሊቮል ተጫዋች ነበረች::
ወንድሜ ቋንጣ....... በጣም ነው የተመቸኸኝ.....ያንተ ጥያቄ አብነት ስለምትሠራው ቂጧ ትልቋ ሴትዮ ..መልሱ ፌዴራል ይፍታው ነበር:: ግን ስደት ባለሰው አይጨከንምና..እሷ ጡረታ ወጥታ...ልጅዋም እንደዛው.....አያሳዝንም.....ተስፋ ግን እንዳትቆርጥ!!! ቋንጥሽ ድፍረት ካልሆነብኝ...እድሜሽ ስንት ነው.... ብለህ አትጠይቅ ተብያለሁ ለካ...ቅቅቅቅቅ....እንጻጻፍ....አደራህን!!!!! አቦ አንት ይመችህ ቸር ይግጠመን::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ቶድ » Thu May 17, 2007 3:25 pm

ሐይ !!! ይቅርታ..... በድጋሚ መጣሁ......ሉህና አምሳለ ስለአለሙሜዳ ጀባ ልበላችሁ ብዬ ነው::የአለሙ ሜዳ ሰፈር ሰዎች በርበሬ ገዝተው አያውቁም ነገርግን ማንም አልጫ ሲበሉ አይቷቸው አያውቅም.....ለምንድንው??????መልሱ ......... የሜዳው ቀይ አፈር ወጡ ውስጥ ስለሚገባ ነው......የሚል ካለ የፈረደበት ነው::ያለሙ ሜዳ ጉልቤዎችን የረሳ ነው!!!!!!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ቶድ » Thu May 17, 2007 6:54 pm

እርማት!!!!!!!!!!!
የአለሙ ሜዳ ሰፈር ሰዎች በርበሬ አይገዙም ነገርግን የሚበሉት በርበሬ ነው::እንዴት ቢባል ቀዩ አዋራ እየቦነነ ወጥ ውስጥ ስለሚገባ ነው::.......ቁጠባ......ኑሮ በዘዴ......ወዘተ
ራስብሩ ........ሙያህን መጠየቅ አይቻልም እንጂ ቢቻል........
ወደጥያቄህ በቀጥታ.......ሳሙኤል ቀዲዳ በጣም ደህና ነው::መስቀል ቡናቤትን ሸጠውታል አሉ:: ዳሩ....መች እሱ ሆነና ጥያቄው........አላልኩም::እኔ ምን ወጣኝ እሺ!!!!!!
የእሱን እህት ልጆች አዜብና ቹቹን ታውቃቸው ነበር እንዴ???????????????
አይ የቹቹ ውበት.... እሸት ነበረች......:: ጥያቄህ በ+ኛ ተመለሰልህ??::ወንድሜ ይመችህ አቦ....ጠይቅ ይመለስልሀል
እዛ ቤት{መስቀል ቡና ቤት } አስቂኝ ገጠመኝ አለኝ...ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ:: መድረኩን ለቅቂያለሁ....ቻዎ!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ዋናው » Thu May 17, 2007 9:47 pm

ቶዳችን

እንዴት ነው ባክህ አዥጎደጎድከው'ኮ ትዝታ ዘ-አዲስ ከተማን በጣም ድንቅ ነው
የዛሠፈር የቀይ ወጥ ሚስጥር ግን ፍርፍር አድርጎ ነው ያሳቀኝ:: አቦ በጣም ጭዋታህ ለዛ አለው ምነው ታዲያ በዚህ ለዛህ ዋርካ ፍቅር ወይም ዋርካ ስነ-ፅሑፍ ጠፋህ?
ለማንኛውም አዲስከተማን በመስኮት ከዚሁ አጮልቀን ምናይበት አንተን ያስገኘን ዋርካንም አንተንም እናመሠግናለን::

ከብዙ ብዙ ማክበር ጋርዋናው________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ቶድ » Wed Jun 06, 2007 12:58 pm

አቦ የመርኬ ልጆች እንዲህ አይደብሩም !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ዋንቾ አንተ ባለህበት አምድ : አንተ በተወለድክበት ሰፈር መርኬ እንደዚህ በፍፁም ፈዘዝ ብላ አታውቅም !!!!!!!!!!!!!!
እንዴት ነው ሰፈር በትክክል እንጠያየቅ እንዴ ??????????
ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ለመንገድ.....................ስለ ቀበሌ 20......
በከ 5 ቀ 20 እና በከ6ቀ14 መሀከል የሚያልፍ በጣም ጥቁር ወንዝ አለ..........(....የሚያውቀው ሰው ካለ??????? ) .......አመተምህረቱን ባላስታውሰውም በእርግጠኝነት
ወቅቱ ግን እንግሊዝና አርጀንቲና በፎክላንድ ደሴት
የይገባኛል ጥያቄ የተዋጉበት ወቅት ነበር:: በዛን ወቅት ግን የወቅቱ የአለም መንግስታት ዋና ጸሀፊ በጣም አሳስቧቸው የነበረው ከባድ ጦርነት በ20 እና በ14 ቀበሌ መሀከል ተጋግሎ የነበረው .......የወንዝ ይገባሀል......ጦርነት ነበር:: በተደነቀው ውሳኔአቸውም መሰረት ወንዙ በ20ቀበሌ ተወስኖበታል:: 14 ቀበሌም ወንዙ አይገባኝም ብሎ ክስ በመክ
ፈቱ የኪሳራ ካሳ እንዲከፈለው ተወስኖለታል::..........................
....... አይገርማችሁም !!!!!!!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ሀሁ ለሉ » Thu Jun 07, 2007 3:16 pm

ዘገየው የአራዳ ልጆች አይደል ወረደ 5 ቀበ 20 ሰራተ,,,,,,,,,,,,,,,ሰፈር
ምነው ተራሳ የሚጋርም ሰፍር እኮ ነው እነዛ ..........................የሚገርሙ ሰወች ይኖሩ ነበር ...................ኦመዲላ የተማር አለ ? ተስፋ ኮከብ ...አዲስ ከተማ ከ1987-1991 ያትማራ ካለ .............ያራዳ ልጆች መፍለቂያ አዲስ ከተም
ሀሁ ለሉ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Sat Jan 13, 2007 10:33 am
Location: london

Postby ቶድ » Thu Jun 07, 2007 8:40 pm

ሰላምታ ለአንተ ይብዛ...ሀሁ ለሉ.... ስምህን ከየት ነው ያመጣኸው?????? እርግጠኛ ነኝ...ደራሲ...ወይም... የጋሽ ጸጋዬ ገ/መድህን አድናቂ ሳትሆን አትቀርም:: ኦሜዲላ... አ/ከተማ ት/ቤት...ቀበሌ 20( ሰራተኛ ሰፈር)....ወንድሜ ሙት እኔና አንት ብንጨዋወት እርግጠኛ ነኝ በደንብ እንደምንተዋወቅ.... ምነው ከላይ ከተጠቀሱት ቀበሌዎች 20 ቀበሌን ብቻ ጠቀስክ???...ከሆንክም መልክቴ እንደው ለጫወታ ብቻ ሆኖ ....እንድነሰባሰብ ብቻ ነው እንጂ... ለተረብ እንዳልሆነ ተረዳልኝ:: በመልክቴ ግን ምንም አስተያየት አለመስጠትህ ትንሽ ቅር ብሎኛል:: 20 ቀበሌ በጣም ደስ ከሚሉኝ ውስጥ.... ኳስ ተጫዋቾቹ....የስራ አክባሪነታቸው እና ህብረታቸው ነው:: ሀሁ ለሉ...መችም ፈርቼሽ ወይም ልሸነግልሽ እንዳልመሰለህ እርግጠኛ ነኝ:: መችም የኔ ነገር.....አንዳንዴ መተው ነው....ቀበሌ 20 አድርጌ ደመደምኩህ:: ያንተ መምጣት ሌሎቹን እንዲያሰባስብ እባክህ እንፃፃፍ......ከብዙ አክበሮት ጋር....
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ዋናው » Sun Jun 24, 2007 11:20 pm

ምነው ሠዉ ሁሉ አዲስከታምን ሚያህል ሠፈር ቶድ ላይ ብቻ ጥሎ ጠፋሳ?


__________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests