የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ባቲ » Fri May 28, 2010 8:21 pm

የአዲስከቴ ልጆች ሰላም ነው? አማን ናቹ ?
ዋንቾ በቅርቡ ሀገር ቤት ሄዶ የነበረ ጓደኛዬ ብዙው ነገር መፈራረሱን መነቃቀሉን መቆፋፈሩን ሲነግረኝ ለልማት መሆኑን ሳውቅ ግን ልቤ ማዘኑን አልተወም:: ጎዝጉዘን የቃምንባቸው ቦታዎች መንገድ አናት ላይ መንገድ ሊንጣለልባቸው ጥድፊያው ለጉድ ነው አለኝ:: ........የትዝታዎቻችን መስተናገጃ ስፍራስ ታስቦበት ይሆን? ይታሰብበት:: ባይሆን አንዱን ትልቅ ግቢ ታሪካዊ ቤት ተብሎ እንደቆመ ይቅርና ገብተን እንደድሮው ሲያምረን ሲያምረን እንቃምበት:: ለልጅና ልጅልጆቻችንም ወደፊት እንዲህ ነበር ድሮ በኛ ዘመን እያለን በሙሉ ልብ ለመጎራት እንዲያመቸን:: ምን ትላለህ?
ድሎት ምቾት ጭሰት ለሁላችን!
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ያባቱልጅ » Mon May 31, 2010 6:40 pm

ባቲ wrote:የአዲስከቴ ልጆች ሰላም ነው? አማን ናቹ ?
ዋንቾ በቅርቡ ሀገር ቤት ሄዶ የነበረ ጓደኛዬ ብዙው ነገር መፈራረሱን መነቃቀሉን መቆፋፈሩን ሲነግረኝ ለልማት መሆኑን ሳውቅ ግን ልቤ ማዘኑን አልተወም:: ጎዝጉዘን የቃምንባቸው ቦታዎች መንገድ አናት ላይ መንገድ ሊንጣለልባቸው ጥድፊያው ለጉድ ነው አለኝ:: ........የትዝታዎቻችን መስተናገጃ ስፍራስ ታስቦበት ይሆን? ይታሰብበት:: ባይሆን አንዱን ትልቅ ግቢ ታሪካዊ ቤት ተብሎ እንደቆመ ይቅርና ገብተን እንደድሮው ሲያምረን ሲያምረን እንቃምበት:: ለልጅና ልጅልጆቻችንም ወደፊት እንዲህ ነበር ድሮ በኛ ዘመን እያለን በሙሉ ልብ ለመጎራት እንዲያመቸን:: ምን ትላለህ?
ድሎት ምቾት ጭሰት ለሁላችን!

ባቲ የጻፍኩትን ዋርካ በላብኝ :evil: :evil:

በቃ የህችን ፎቶ ካላያችሁት እንድታዩ ያክል ነው

http://www.flickr.com/photos/dannyhabesha/

ሰላም
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ዲጎኔ » Fri Jun 11, 2010 5:53 am

ሰላም ለአዲስ ከቴዎችና ወዳጆቻቸው ሁሉ
ውድ ዋናው እዚያች ብሩክ ሰፈር መሄድህ ብቻ ታድለሀል ሌላው ቢቀር ከልብ ለልብ ያለአንዳች የዘርና የሀይማኖት ልዩነት ያደግንባት ሰፈር ናትና::በል እንግዲህ በነካ እጅህ ወደታች ወረድ በልና ጋሽ እንዳለ ስጋ ቤት ሁለት ጎድን በፊደል ሰራዊት የሉካንዳ ቤት ልጆች አስተማሪያቸው ስም ብላልኝ::ከዚያ ልደትዬ ጎን እትዬ ተዋበች በህይወት ካለች እነደዚሁ የፊደል ሰራዊት አስተማሪሽ ልኮኛል ብለህ ድንቅ ምንቸት አብሿን ንጭልኝ!ከዚያ ወደግራ ዞር ብለህ ሳባጠጅ ፋብሪካ ብርዝ ካለ ለእኔ ደርዘን ላክ አንተ እንደምርጫህ በመጀመሪያው የአረንቻታ ፋብሪካ አባቴ ስም ተጎንጭልኝ::
መጨረሻ በመስጅድ አልፈህ በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አለፍ ብሎ ካለው ግዛው ክትፎ ቤት አርካፉኔ ብለህ አሰነካልኝ::

ዋናው wrote:ዛሬም እዚህ የትውልድ ሰፈሬ ነበርኩ ግን ማንም የለም... ብሌን ገብቼ አንድ ማሕበራዊ አዘዝኩኝ ማጎረሰው ሰው አልነበረም... ግማሹን በልቼ መስቀል አንድ ከረባት አዘዝኩኝ እዛም ማንም የለም ....
አሁን ብሌን ገብቼ ድራፍት እየጠጣው ነው:: ማንም ማውቀው ሰው የለም ኸረ ሠዎች ሁሉ የት ሄዱ?
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ቶድ » Tue Aug 03, 2010 12:22 am

ምነው ሸዋ አለ ያገሬ ሰው!!!! ምነው ምነው ጎበዝ አልበዛም እንዴ???? ብዙ ተጠፋፋን እሳ!!!!!

ስለ መርካቶ አምላክ ስትሉ ኧረ ብቅ ብቅ በሉ!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ጦርነዶ » Sat Aug 14, 2010 9:38 pm

ሰላም ለሁላችሁም ለአዲስ ከተማ ልጆች

ሙሉጌታ ወጨፎን የማስታውሰው የማትሪክን ውጤት 3.6 ወይም 3.8 ማምጣቱ ነበር :: ድንቅ ጆክ ተናጋሪ ነው አንድ ሁለቴ ለቅሶ ቤት አግኝቸው ነበረ :: ፈጠራው የሚደነቅ ፍጡር ነው :: መጨረሻው ምን እንደሆነ አላውቅም አንድ ጊዘ ግን የደከመ መስሎ አይቸዋለው ::
መነን ሆቴል አሪፍ ቺኮች ነበሩበት ::

7ኛን ያልጎበኘ የአዲስ ከተማ ልጅ ገዳም ገብቶዋል ::
12 ቀበለ መዝናኛ የአለም ዋንጫን የምናይባት ነበረች ወይ ጊዜ:: ቅጣው ጠጅ ቤት: ከፋ ሆቴል ጨረቃ ሆቴል
ጅቡቲ ሆቴል ከማስታውሳቸው ጥቂቶቹ ናቸው ::

የታቲ ገየትን አስታወሳችሁኝ

በታቲ ገየት ሰዎች ሳምንቱን ሙሉ ብረት ሲሰሩ ይቆያሉ ልጆቹም አብረው ነው የሚሰሩት:: ሌበር ኦርጋናይዘሽን ምናምን ብሎ ነገር የለም :; ልጅ ተወልዶ ምግብ መብላት
ከጀመረ መስራት አለበት ::

ታዲያ ልጆቹ ሳምቱን ሙሉ አይታጠቡም ከመቆሸሻቸው ብዛት ማን የማ ልጅ መሆኑ አይታወቅም ::

ልጆቹ የሚታጠቡት በሳምንቱ መጨረሻ ነውና በትልቁ በርሜል ውሀ ተሞልቶ ሳሙና ይጨመርበትና ልጆቹን ጉርዱ በርሜል ውስጥ እያስገቡ ያወጡዋቸዋል:: ታጠቡ ማለት ነው አሁን ፊታቸው በጉልህ ይታያል:: ሳምንቱን በሙሉ ፊታቸው በጥላሽት ተሸፍኖ ነበረና ::
ተራው የደረሰው አጣቢ እያንዳንዱን ልጅ እያወጣ ልጆቻቸውን ለሚጠባበቁ ወላጆች እያሳየ " ዚ ባይ የማኒ :?:" እያለ ይጠይቃል ወላጅም "የዲትን" ትላለች :: ብዙ አስቂኝ ቀዶች አሉባቸው ስለታቲ ገየት ሌሎችን በሌላ ጊዜ ይዤ አቀርባለው::

ላሁኑ ፈያ ሁኑ
love Ethiopia
ጦርነዶ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Fri May 28, 2010 9:40 pm

Postby ቶድ » Wed Sep 22, 2010 11:29 am

ጦርነዶ!!!! አቦ ፉገራ ....... ይመችህ አቦ!!!!! በሳቅ ነው የገደልከኝ:: አንተ እጅግ በጣም ውስጥ አዋቂ (የ20 ቀበሌ) ነህና እባክህን ተጨማሪ ፉገራዎችን ብታዥጎደጉዳቸው ግሩም ነው::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ቶድ » Fri Oct 15, 2010 10:35 pm

አቦ መርኬዎች????? ምንድነው ነገሩ????? የተወሰኑ ቤቶች በመንገድ ስራው ምክንያት ቢፈርሱ ...... አዲስ ከተማ በጠቅላላ ፈረሰ ማለት ነው እንዴ?????? እባካችሁ ተመለሱና ሰፈራችንን ሞቅ ሞቅ እናድርጋት!!!!!!!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ጦርነዶ » Wed Nov 10, 2010 6:39 am

ሰርላም ብያለው የት አካባቢ ነው የፈረሰው የውልጫቶ ጫት ቤት ፈረሰ እንዳትለኝና እርሜን እንዳላወጣ ::

ብቅ ብቅ በሉ የታቲ ገየቶች ካላችሁ በይበልጥ......

አቦ በጫት ናፍቆት ከመቃጠል ብየ የዘንባባ ቅጠል ልጀምር ነው ::

የት ፈርሶ ይሆን .... :?:
love Ethiopia
ጦርነዶ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Fri May 28, 2010 9:40 pm

Postby ዲጎኔ » Mon Nov 15, 2010 5:30 am

ሰላም
እንዲህ ከለጋነቱ ጀምሮ ስራ ከለመደ ማህበረሰብ በመውጣቴ ደስተኛ ነኝ::ዛሬም የማንም ሸክም ሳልሆን ቤተሰቤንና እራሴን እንዳስተዳድር ላበቃኝ ጌታ ምስጋና ይሁን!
ዲጎኔ ሞረቴው ከሸክላ ተራ ጥበበኞቹ ሰፈር

ጦርነዶ wrote:ሰላም ለሁላችሁም ለአዲስ ከተማ ልጆች

ሙሉጌታ ወጨፎን የማስታውሰው የማትሪክን ውጤት 3.6 ወይም 3.8 ማምጣቱ ነበር :: ድንቅ ጆክ ተናጋሪ ነው አንድ ሁለቴ ለቅሶ ቤት አግኝቸው ነበረ :: ፈጠራው የሚደነቅ ፍጡር ነው :: መጨረሻው ምን እንደሆነ አላውቅም አንድ ጊዘ ግን የደከመ መስሎ አይቸዋለው ::
መነን ሆቴል አሪፍ ቺኮች ነበሩበት ::

7ኛን ያልጎበኘ የአዲስ ከተማ ልጅ ገዳም ገብቶዋል ::
12 ቀበለ መዝናኛ የአለም ዋንጫን የምናይባት ነበረች ወይ ጊዜ:: ቅጣው ጠጅ ቤት: ከፋ ሆቴል ጨረቃ ሆቴል
ጅቡቲ ሆቴል ከማስታውሳቸው ጥቂቶቹ ናቸው ::

የታቲ ገየትን አስታወሳችሁኝ

በታቲ ገየት ሰዎች ሳምንቱን ሙሉ ብረት ሲሰሩ ይቆያሉ ልጆቹም አብረው ነው የሚሰሩት:: ሌበር ኦርጋናይዘሽን ምናምን ብሎ ነገር የለም :; ልጅ ተወልዶ ምግብ መብላት
ከጀመረ መስራት አለበት ::

ታዲያ ልጆቹ ሳምቱን ሙሉ አይታጠቡም ከመቆሸሻቸው ብዛት ማን የማ ልጅ መሆኑ አይታወቅም ::

ልጆቹ የሚታጠቡት በሳምንቱ መጨረሻ ነውና በትልቁ በርሜል ውሀ ተሞልቶ ሳሙና ይጨመርበትና ልጆቹን ጉርዱ በርሜል ውስጥ እያስገቡ ያወጡዋቸዋል:: ታጠቡ ማለት ነው አሁን ፊታቸው በጉልህ ይታያል:: ሳምንቱን በሙሉ ፊታቸው በጥላሽት ተሸፍኖ ነበረና ::
ተራው የደረሰው አጣቢ እያንዳንዱን ልጅ እያወጣ ልጆቻቸውን ለሚጠባበቁ ወላጆች እያሳየ " ዚ ባይ የማኒ :?:" እያለ ይጠይቃል ወላጅም "የዲትን" ትላለች :: ብዙ አስቂኝ ቀዶች አሉባቸው ስለታቲ ገየት ሌሎችን በሌላ ጊዜ ይዤ አቀርባለው::

ላሁኑ ፈያ ሁኑ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ጦርነዶ » Fri Apr 29, 2011 1:16 am

ጎበዝ ተጠፋፋን ኪጋሊስ እንዴት አድሮ ይሆን :?:

ዘመዶቻችን የባንክራብሲ ሎየር ለመፈለግ ቡታጀራ ገቡ አሉ
እድሜ ለጸሀዩ ወያኔ መንግስት ::
love Ethiopia
ጦርነዶ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Fri May 28, 2010 9:40 pm

Postby ቶድ » Sat Jul 23, 2011 11:18 am

እውነት ትክክለኞቹ የመርኬ ልጆች ነን እዚህ ቤት የምንሰበሰበው????? እኔጃ አያጠራጥርም ጎበዝ???????

እባካችሁ የአዲስ ከቴ ልጆች .... ብቅ ብቅ በሉ!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

መርኬ

Postby ቶድ » Mon Dec 19, 2011 3:20 pm

መልካም ለፈረንጆቹ ገና በዐልና አዲስ አመት!!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

ወይ ጌታ!

Postby ቶድ » Mon Jun 25, 2012 11:00 pm

መርኬ ገጽ 21 ገባ???????
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Re: የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Postby ቶድ » Thu Dec 29, 2016 3:00 pm

ሰላም ሰላም ሰላም ለዚህ ቤት ብለናል!!!!!! መርኬዎች ሁሉ ሰላም ነው???????? ከች ብለናል!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Re: የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Postby አርሴማ123 » Fri Oct 27, 2017 4:40 pm

ፋይናሊ!! የአዲስ ከቴ/የመርኬ ልጆች ዋርካ ለይ ተገናኘን!!
ስሜ፣ ገጀራው
ወረዳ ፣ ሰባት
ቀበሌ፣ 31 ( ከአዲሱ ሚካኤል ቸርች ጀርባ)ቀ
የተማርኩት ከ 2 እስከ 8 የካቲት 23!!
ጦመኔው አንቺም እዛው እንደተማርሽ ነግረሽናል እስኪ ትዝታዎችሽን ልቀቂብን? ቲቸር ምንዳን ታውቂዋለሽ? ተክሌንስ? አቦ እሱን ሰውዬ ስፈራው በዛ እርዝመቱ ለይ ጥቁርነቱ ተጨምሮበት የሆነ የኬንያ ማራቶን ሯጭ ነው የሚመስለኝ ቢሮ እየወሰደ ስንት ጊዜ ለጥልጦኛል መሰለሽ! አቦ ሰብሰብ በሉና እናፍካው
አርሴማ123
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sun Sep 11, 2016 1:07 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests