የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ዲጎኔ » Tue Jun 26, 2007 5:13 pm

ሰላም ለሁሉ!
ውድ ዋናው እንኩዋን በሰላም ተመለስህ በመልካሙ ብእርህ እኔንም በምናቤ ወደሁዋላ መለስከኝ ያን ሰፈር በዛ ትውልድ ዘመን አውቀዋለሁ በተለይ ትቅደም የሚባለው ቡና ቤት ካምቦዲያ ሰፈር ...ወዘተ ግን የታሪክ ሀቅ ነው የሚለው መዝሙር የግርማ የቀበሌ 18 ይሆንን?
አክባሪህ ዲጎ ዘሞረቴው ከፈረሰኛ አጠገብ YMCA ጎን

ዋናው wrote:
ጌታ wrote:ዋኒቾ ለካ በጤናህ እንዲህ አሪፍ ልጅ አልሆንክም?

እንደሻው ዛሬ ታዋቂ ሳይሆን የቴዎድሮስ ታደሰን ዘፈን ሰፈር ውስጥ መዝፈን ይወድ ነበር:: አሁን የራሱ ዌብሳይት ከፍቶ ምናምን ለንደን ነኝ ያለሁት ሲል አንብቤያለሁ:: ይመቸው::የከፍተኛ 5 ቀበሌ 18 ኪነትንስ ታስታውሰዋለህ? በአንድ ወቅት ጥሩ ይንቀሳቀሱ ነበር:: (ይህ ፍንዴክሶቹን እነ ጦምኔውን አይመለከትም)


ጌታ
ባንድ አየር አብሮ የማደጉ ሚስጥር ነፍስ ማነበቡ አይቀርም መቼም አዲስከተሜኛ አየሁብህ ልበል:: ደስ ይላል::
ታዲያ ጨዋታዉን እናምጣዋ የ18ቱን ኪነት በዝና አውቀው ነበር ስለኩሪ ከዛ የምፍለቋን ጉዳይ ግን አልደረስኩበት ይሆን እንጃ.....
18ቀበሌ የአደሬ ሠፈር ጥቂቶችን ባንድ ወቅት ውሃ ለማጣጣት እንገናኝ ነበር ...እነምስራቅ ሸረፋ እነ ሠዒድ.....

ጦምሽ እስቲ በነካ እጅህ ስለሠፈር ትኵስ ወሬ አምጣ ...ለምሳሌ ባለጌው ፎቅ ለምን ባለጌ ስለመባሉ አይነት ለውጦች ካሉ...

ቋንጥሽ____ ስለአብነቷ ቂጥ እኔንጃ ምን በ11 ሠዓት ላይ ከአዲስከተማ ቁልቁል ሚተመውን ቂጥ አይተህ ጥንግርግር ትል የለ እንዴ ነው ብዙም ሳያምርባቸው ነው የወጣከው ቅቅቅ በነገራችን ላይ እዚ አሉ የአብነት እንስቶች በጣም ቆነጃጅት ናቸው::

እስቲ መጣው ደግሞ ለጭውውታችን ከመነን ባሮ ጅን ይዤ እየተጨዋወታቹ


ዋናው___________________________________________________________::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

ሰላምታ

Postby ቶድ » Fri Jun 29, 2007 1:07 pm

ዋንቾ ሰላም ላንተ ይብዛ:: ከአድናቂነቴ ባሻገር... አክባሪነቴ የላቀ ነው::...ተፎጋገርን እንዴ??...አልመሰለኝም!!!!!!!!!ስለ ኩሪ የ18 ቀበሌ ልጅ መጠራጠርህ ተገቢ ነው:: የ18 ወይም የከፍተኛ 5 ኪነት አባል አልነበረችም:: እሷ የገዳም ሰፈር አካባቢ ልጅ ነበረች:: ዋንቾ የህይወት አጋጣሚ ሆኖ ብዙ የጋራ ጓደኞች ነበሩን:: ስለ 18 ልጆች ስታነሳ ከምስራቅ ሸረፋና ከሰይድ ሌላ እነኢብራሂም(ዲጄው), እን ነቢል, እነኢብራሂም ቱሬ, እና ኳስ ተጫዋቹ ወይብን የመሳሰሉ ልጆች በተለይም ወደ 19 ቀበሌ ስትሄድ እን ቢቢዲ (ኤርሚ, ቴዲና ነቢል ከነወንድሟ.....እነሙራድ(የመኑ)..እነ ናስር ጭንቅሎና ኢብሮ....... ዳንስና ሙዳቸው በጣም ደስ ይል ነበር:: ምንያረጋል ስደት መጥፎ ነገር......ለጊዜው በአካል አለያየን:: 18,19,እና አሜሪካ ጊቢ የነበሩ አራዶች በጣም የጨረሱ ነበሩ::
ወንድማችን ዲጎኔ !!!!!!! አቦ የጫወታ ስስት አለብህ:: የካንቦዲያ ሰፈር ልጅ ሆነህ........አቦ ደስ አይልም........::እስኪ ስለ ካምቦዲያ ስለእናት ጓዳ ስለዋርካና ስለጥንቅሽ እንዲሁም ስለአብነት, ተካልኝና ዌናሞ ትንሽ አውጋን እኛም እናወጋሀለን:: ቸር ይግጠመን::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ሀምሳለ » Fri Jun 29, 2007 5:14 pm

ሰላምምምምምም የአዲስከተማ ልጆች

ዲጎኔ ካምቦዲያ አሁንም አለ :D ድሮ የጦፈ ሰፈር ነበር
ሰንቱ ሎጋ አይን ገለጠበት :D የዛሬን አያርገውና

14 ቀበሌ ለጆች ጎበዝ ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ

ሀሁ ለሉ ተስፋኮከብ ተማሪ እየተማረ ሰው ከላይ ሲያልፍ እግሩ ይታይ ነበር ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አሪፍ ት/ቤት
እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል ተረሳሽ ወይ አለ ዘፋኝ
አዲስ ከተማ የሚረሳ ሰፈር አይደለም

ሀም ሳ ለ
ሀምሳለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 243
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
Location: America

ቶድና ሀምሳለ መልካም ብላችሁዋል

Postby ዲጎኔ » Fri Jun 29, 2007 6:42 pm

ሰላም ለሁላችን
ውዶች ቶድና አምሳለ መልካም ብላችሁዋል!
እኔ መልካሙንም ክፉንም የልጅነት ጊዜዬን ካሳለፍኩባቸው ሰፈሮች አንዱ ጌጃ መርካቶ መዳረሻ ስለሆነ የማውቀውን ጠቀስቀስ አድርጌያለሁ::በተለይ ካምቦዲያ የሚል ስም የተሰጠው ሰፈር ከኢህአፓ ጊዜ በሁዋላ ሲሆን ከዛ በፊት YMCA ስፖርት ውድድር ለማየት ለመጫወት እሄድ የነበረ ሲሆን በክፉ የጉልምስና ዘመን እነትቅደምና አብነት ደግሞ መብነሽነሻዎቻችን ነበሩ ያኔ!ሻውል ደማ ት/ቤት የተማሪው ንቅናቄ ድራማ እያሳየን ቅስቀሳ የሚካሄድበት ሲሆን ሰፈሩ አሁንም ከገዥዎች ጋር ተጋፋጭ ሆኖ መቀጠሉን ባለፈው ታይቷል::ከሀገርቤት ልወጣ አካባቢ YMCA ሊመለስላቸው ነው የሚል ስለሰማሁ ደስ ብሎኝ ነበር የቀበሌ ዳንኪራ መርገጫ ሆኖ ወደአረቄ ከሚነዳ የስፖርትና የጤናማ ኪነጥበብ አምባ ቢሆን እመርጣለሁ::
ሌላ የምጠይቃችሁ"የታሪክ ሀቅ ነው" ያቀነቀነው የከፍተኛ 5/6 ነውን? የት ደርሶ ይሆን ዜማው አሁንም ይመጣብኛል ያ ትውልድን አስታውስበታለሁ!
በተረፈ ካምቦዲያ ሲሰየም ሲሰፋ እኔ ሰፈሩን ለቅቄያለሁና ውድ ቶድ ብዙ ዝርዝር የለኝም አንተ አውጋን!
ዲጎኔ ዘሞረቴው ከጌጃ ሰፈር ሜዳ መርካቶ መዳረሻው ላይ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዋናው » Sat Jun 30, 2007 9:45 pm

ቶድ የሠፈሬ አንበሣ
ስለነ ኤርሚ ቢቢዲ ብታነሣ ልቤ ሸፈተ ልበል....ዋው ያ ዘመን ተጨፈረ
በዛ ፓንክ :wink: በዛ ሠፊ ሱሪ ያኔማ እነ ቶድ የመድረክ ንጉስ ነበሩ እያሉ ሠዎች ሲያወሩ ሠማው ልበል እንጃ ጆሮዬ ይሆናል ቅቅቅ አዲስከተማ ስንቱን ጨፋሪ ስንቱን ዲጄ አፍርታለች አሁን የእሕል ውኃ ጉዳይ ብላ በታተነቻቸው እንጂ
እነሚብራስ ከመሣለሚያ እነአሚድ ከፒያሳ እነጥላሁን ስናፕ ከዶሮ ማነቂያ ለሙድ አዲስከተማን ይጋሯት ነበር ያኔ ዳንሱን አአዲስ ከተማ ተለማምደው ዊኬንድ ላይ ወደ ፓሪ ለመሄድ(ፓሪ ለመጫር....በዛዘመን አባባል)
ይልቅስ አንድ ሃሳብ ውስጤ አጫርክብኝ ስለጭፈራ ስታነሳ ...ሠሞኑን እንዲያሁም መጠጥ ቤቴ ቀዝቅዟል ዋርካ ፍቅር መጠጥ ቤቴ ሄጄ ይህንን ርዕስ ልፍጠርና ሠዉን ልሠብስበው እስቲ.....? ታዲያ ብቅ በል አንተ ምነው እሱን ቅምቀማ ቤት ጠላከው (ጴንጤ ሆንክ እንዴ?''

ቶድ እስከዛ በዚች ሙዚቃ በትዝታ ቆዝም
==> http://www.youtube.com/watch?v=N6blgjF6UkU[color=green]ዋናው
_______________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ሀምሳለ » Tue Jul 03, 2007 4:43 pm

ቶድ ዋናው ሰላም የከፍተኛ 5 ኪነቶች ሲባል ምን ትዝ አለኝ ሁሉም እየተመዘኑ የሚገቡ ይመሰል ቀጭኖች ነበሩ በዛላይ ቁመታቸው ረጃጀም ሁሉም ይመሳሰላሉ ያላቸው የሙዚቃ መሳርያ ማንም በዛ ሰአት የለውም ነበር :D አሁን አንድ የሚዚቃ መሳሪያ ተጫዋቻቸው እና ጭፋሪ የነበረችው ተጋብተው ዲሲ ይኖራሉ .

ዲጎኔ ወክማ ተቀይሮ እንደነበር አላቅም ነበር ግን የገለሰብ ነበር ? ለማነው የሚመለሰውስ ?
ሀምሳለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 243
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
Location: America

Postby ቶድ » Thu Jul 05, 2007 5:21 pm

አቦ ዋንቾ እባክህ ተወን.......በፈጠረህ!!!!!!!
በቃ በትዝታ እዛው ወሰድከኝ እኮ:: ዋናው : ስምን መላክ ያወጣዋል እንደሚሉት ስራህና ስምህ መጣጣማቸው ምስክር ነው:: ወደጠቆምከኝ ቡናቤትህ ነገ ጎራ እላለሁ::
ለዲጎኔ ዘሞረቴ!!!!!!!!!!!!!
ከሰላምታ በመቀጠል ከጽሁፍህ እንደተረዳሁት ታላቄ መሆንህን ነውና በማክበር ጀምሬ የማውቀውንና የሰማሁትን አጫውትሀለሁ:: ካምቦዲያ........ድሮ በናንተ ጊዜ እነአየለ ጅቦና መስፍን ታምነ ጉልቤ በነበሩበት ወቅት የፍቅር መናኸሪያ ነበረች ይባል ነበር:: በዛን ወቅት አስተናጋጅ የነበረ አሁንም የሚያስተናግድ ሰው እንደነገረኝ.....ድሮ በጥኃት ቡናቤቶቹን ሲያጸዱ ገንዘብ, ወርቅ, ሰዓትና ቦርሳ ያገኙ እንደነበረና አሁን ግን የድብድብ ሰፈር ከመሆኑ የተነሳ ጆሮ, ጥርስ, አይንና ቅንድብ ብቻ ከመሬት እንደሚገኝ ነገረኝ:: ዲጎኔ!! ፍቅርና እውነት ጽሁፍህ ላይ ይታያል:: በዛን ወቅት በሻውልደማ ት/ቤት የተማሪ ንቅናቄ ድራማ ሰታሳዩ .....በእርግጠኛነት የነበራችሁ ስሜት ታላቂቷን ኢትዮጵያን በህዝቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረተች ታላቅ ሀገር ማድረግ እንደነበረ ይሰማኝል:: ብዙ የተማረ ሀይል ያሰበውና የሞተለት አላማ ሳይሳካላቸው በትግል መውደቃቸው ቤቶቻችን ይቁጠረው:: አንተ እንዳልከውም የዛሰፈር ሰው አሁንም እየታገል ነው ላልከው አገራችን ገዢ እስካለ ድረስ ... ዲጎኔ...ትግል አይጠፋም:: ለሀገራችን ገዢ ሳይሆን አምላክ በፍቅር በሰላም አንድ አድርጎ የሚያስተዳድር አሰተዳዳሪ ይስጣት:: አደራ ፖለቲክኛ አይደለሁም:: አልፈራሁምም::
ሀምሣለ.....እስኪ ከ14 ቀበሌ ኳስ ተጫዋቾች ማንን ታስታውሻለሽ:: እነፈርዲ, ንጉሴ ጦጣ, መላኩ, ማሙሽ, ፓቼ, አጎ, አካሉ, ደሳለኝ(የፖሊሱ), ካሰዬ(ክራይ ቤት) ሾጤ, መለሰ በቀለና ሌሎችም ብዙ ብዙ...........የ14 ልጅ ከሆንሽ ከላይ በ14 ቀበሌና በ20 ቀበሌ የተጻፈውን ጦርነት ካላነበብሽው በድጋሚ ተመልከቺው::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ጌታ » Thu Jul 05, 2007 6:00 pm

ሀምሳለ wrote:ቶድ ዋናው ሰላም የከፍተኛ 5 ኪነቶች ሲባል ምን ትዝ አለኝ ሁሉም እየተመዘኑ የሚገቡ ይመሰል ቀጭኖች ነበሩ በዛላይ ቁመታቸው ረጃጀም ሁሉም ይመሳሰላሉ ያላቸው የሙዚቃ መሳርያ ማንም በዛ ሰአት የለውም ነበር :D አሁን አንድ የሚዚቃ መሳሪያ ተጫዋቻቸው እና ጭፋሪ የነበረችው ተጋብተው ዲሲ ይኖራሉ .


ሀምሳለ የከፍተኛ 5 ኪነት ስትይ ሊድ ጊታር ይጫወት የነበረውን ልጅ በጣም አውቀው ነበር:: በለጠ ይመስለኛል ስሙ:: እንዳውም ለሬዲዮም የበቃች ዘፈን ነበረችው አሉ::

እታለም..................መንደርሽ
መጥቼም እንዳልጠይቅሽ
ናፍቆቱን እንዴት ልወጣው
ጨነቀኝ ድምጽሽን ባጣው............................የሚል::

የአዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ሲከበር እዛ ነበር ያደርኩት:: ቢራ እነደውሃ መጫወቻ ሆኖ ፋራ ስለነበርኩ አልቀመስኩትም ነበር::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ቶድ » Thu Jul 05, 2007 10:23 pm

ወንድሜ ዲጎኔ.....ለአንተ ጥያቄ ስል ተመልሻለሁ::
ስለትቅደም ቡናቤት ለጠየከው አሁን እንደድሮው ታዋቂ አይደለም::በጣም ቀዝቅዟል::እርግጠኛ አይደለሁም እንጂ ሊዘጋ ነው ሲባል አስታውሳለሁ:: ስለአብነት ግን አትጠይቀኝ...እንደ ዋንቾ ቡናቤት(ለእድሳት ሳይዘጋው በፊት) በጣም ገበያ አለው:: በተለይ በእድሜ ትንሽ ገፋ ገፋ ያሉት ........ከ35 በላይ ማለቴ ነው: መሰባሰቢያ ነው:: ዲጎኔ እግረ መንገድህን ወንድሜ ቋንጥሽ ከዚህ በፊት ጠይቆ ስለነበረው አብነት ጸራ ስለነበረችው ቂጧ ትልቋ አስተናጋጅ የምታውቀው ካለ እባክህ ጀባ በለንና እሱም እርፍ ይበል::..........የታሪክ ሀቅ ነው የሚለውን ዘፈን የዘፈነው የከ6 ኪነት ዘፋኝ ግርማ ይባላል:: እጅግ በጣም ወኔ ቀስቃሽ ነበር:: ከ6 ኪነት እነ አለም ከበደን ያፈራ ቡድን ነው::
ሀምሳለ.........አይ ፉገራ...ቅቅቅቅቅቅቅ..እየተመዘኑ የሚገቡት ይመስል አልሽ.....በሳቅ ገደልሺኝ::ዲ.ሲ. ያሉት የከ5ኪነት ኪቦርዲስት ዳንኤል ወ/ገብሬልና ተወዛዋዧ ውባየሁ ይባላሉ:: ውቤ ሀገርፍቅርና ህዝብ ለህዝብ ታዋቂ ተወዛዋዥ ነበረች:: ዳኒ ደግሞ ሀገርፍቅር, ዋልያስ ባንድ,አክሱማይት ባንድ እና 5 የሚሆኑ ክላሲካል ሲዲዎች ያወጣ አርቲስት ነው::
ጌታ.....ወንድሜ እንዳልከው በለጠ የከ5 ሊድ ጊታሪስት ነበረ;; በ1979 አዲሳበባ 100ኛ አመቷን ስታከብር አንተ መጠጥ አልጠጣሁም ነው ያልከው??? ያኔ የድብድቡ ጊዜ ግማሽ ጠጥተህ የወረወርከው ጠርሙስ ይፋረድሀል:: ባልሳሳት ሼር ነበረ የምንጠጣውና አልረሳውም:: ከበድ አጃሞ, እንዳሻው ተስፋየ, ታደለ ሮባ, አበበ በርታ(ትወዛዋዥ), ውቢትና.......በጥቅላላ አሪፍ ነበሩ::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ሀምሳለ » Fri Jul 06, 2007 6:31 pm

ቶድ ዋውውውውውው በጣም ነው የገረመኝ የረሳሁትን ሰው ሁሉ አስታወስከኝ አሁን የጠቀስካቸው ሰዎች ሁሉ የት ደረሱ ግን ?አበበ ወዝዋዜ በጣም ጎበዝ ነበር ከበደ አንጃሞ ጉራጊኛ ሲዘፍን ጎበዝ ነበር እንዳሻው ተስፋዬ ከፍተኛ 4 ኪነት ወስጥ ድምጳዊ ዳዊት ተስፋዬ የሚባል ወንድም ነበረው ከቤቱ ነው መሰለኝ :D ታደለ ሮባ ሰሙን አቀዋለሁ ደምጳዊ ነበር ?ሀና ከኢትዮ ወጥታ ቆየች ባለችበት ሀገር ላይ ባህላዊ ዘግጅቶችን ታረጋለች ብለው ሰምቻለሁ
ዳንኤል ካሴቱ ነበረኝ ሰለ ከፍተኛ 4 እና 6 ኪነቶችስ የምታቀው ካለህ ጀባ ብትለን

ጌትሽዬ አሁን የረሳሁትን ሰው ሁሉ ነው እያስታወስኩ ያለሁት 100ኛው አመት ሲከበር :D :D ዋውውውውውውው ትዝታ ከተትከኝ

አዲሱ አዳራሽ ሲመረቀስ ትዝ አይላችሁም እስኪ ሰለሱ አንድ በሉኝ በጣም ቆንጆ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት :cry: :cry:


ሀም ሳ ለ
ሀምሳለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 243
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
Location: America

ሀምሳለ እንደጠቀሰችው

Postby ቶድ » Fri Jul 13, 2007 7:31 pm

[quote="ሀምሳለ"]ቶድ ዋውውውውውው በጣም ነው የገረመኝ የረሳሁትን ሰው ሁሉ አስታወስከኝ አሁን የጠቀስካቸው ሰዎች ሁሉ የት ደረሱ ግን ?አበበ ወዝዋዜ በጣም ጎበዝ ነበር ከበደ አንጃሞ ጉራጊኛ ሲዘፍን ጎበዝ ነበር እንዳሻው ተስፋዬ ከፍተኛ 4 ኪነት ወስጥ ድምጳዊ ዳዊት ተስፋዬ የሚባል ወንድም ነበረው ከቤቱ ነው መሰለኝ :D ታደለ ሮባ ሰሙን አቀዋለሁ ደምጳዊ ነበር ?
ሀይ አምሳልዬ ምርጥ የአ/ከተማ አራዳ...ድንቅ የውቢት ኢትዮጵያ ልጅ....ክብር ሰላምታዬ ይድረስሽ::ስለ ድንቅ ተወዛዋዡ አበበ በርታና ስለ ታዋቂው የጉራጊኛና የአማርኛ ዘፈን አቀንቃኝ ከበደ አርጃሞ ለጠየቅሽኝ ጥያቄ መሬት ይቅለላቸውና እኔ መርዶ ላረዳሽ አልፈልግምና ከሚያውቁ ሰው ጠይቀሽ ተረጂ::በስራቸው ግን አንቱ የተባሉና እነሱን ማጣት ሀዘኑ ለቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ለኢትዮጵያ በተለይም ለእኝ ለአ/ከተማ ልጆች ነው::ስለታደለ ሮባ ለጠየቅሽኝ ጥያቄ እሱ የበፊቱ የከ 5 እንግሊዘኝ ዘፋኝ.....የድሮው የአ/አበባ ግሩም ድንቅ ብሬክ ዳንስ ዳንሰኛና የአሁኖ........ላፎንቴን......ዘፋኝ ነው:: ይቅርታ የእነ ታደለ ሰፈር የ12 ቀበሌ ልጅ በዚህ በኩል ሲያልፍ ስላየሁ እሱን ላናግረው.........ተመልሼ ሌላ ነገር አጫውትሻለሁ::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ሀምሳለ » Fri Jul 13, 2007 10:29 pm

:cry: :cry: :cry: :cry: በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው አበበ የማይረሳኝ ያኔ ህዝብ ለህዝብ ሄዶ የመጣጊዜ በሳንቲም ቪድዮ እቤቱ ማሳየት ጀምሮ ነበር የመርኬለጅ :cry: ነብስ ይማር እኔ እንዴት አላደጉም ብዬ በጣም አስብ ነበር ለካስ :cry: የሚያሳዝን ነው :cry:

ቅቅቅቅቅቅቅቅ ታደለ ሮባን አውቀዋለሁ ጛደኞቹን አቃቸዋለሁ ግን 14 ቀበሌ ልጆች ናቸው :D እሱም እዛው ይመስለኝ ነበር.
ቶድ ትንሽ ቆየሁ መሰለኝ ከወጣሁ ሁሉነገር ትዝታ ሆኖብኛል ምንያህል ወደኃላ ወስደህ ሰንት ሰውን እንዳስታውስ አረከኝ መሰለህ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው :D
ሀምሳለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 243
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
Location: America

Postby batuta » Sun Jul 15, 2007 5:18 pm

በቅድሚያ ለሁላችሁም የከበረ ሰላምታ .በተለይ ቶድና ሀምሳለ
የጻፋችሁትን ሳይ እኔም እስኪ አንድ ልበል አልኩ. ቶድ ስለ 14 ቀበሌ ኹዋስ ተጫዋቾች መሀል የተወሰኑት ጋር የአንድ ዘመን ስንሆን እኔን በመዘንጋትህ ግን ትንሽ ቅር ተሰኝቻለሁ :ስቀልድ ነው... የተቀሩት ደግሞ የኛ ፈር ቀዳጆች ናቸው .እንግዲህ ትንሽ ጠለቅ ብዬ ባወራህ ደግሞ....
ለአጻጻፍህ አድናቂ ነኝ
ከአክብሮት ጋር ባቱታ
batuta
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sun Jul 15, 2007 4:53 pm

Postby ቶድ » Mon Jul 16, 2007 10:18 pm

ለውድ ሀምሳለና ባቱታ ....እንደምን አላችሁልኝ::በቃ ተጉዘው ከማይጨርሱትና....ተዝቆ ከማያልቀው ትዝታው.......ሁሉን ለጋሽ ሁሉን አልባሽ. ሁሉን አጉራሽ መርካቶ...... የ14 ቀበሌ ልጆች ብቻ ናቸው እንዴ የተማሩ የሚገኙበት እስኪባል ድረስ የሌላቀበሌ ልጆች ኧረ ምነው ጠፉ???????
ሀምሳልዬ ያንቺ ነገር ትንሽ ግራ እንዳያጋባኝ ፈራሁ ልበል::የአበበ በርታን ቪዲዮ ቤት እንዴት ነው???? ብዙ ጊዜ እኮ ባገራችን ሴት ልጅ የመንደር ቪዲዮ ቤት አትገባም:: ለመሆኑ የስለሺ ባሪያው ቪዲዮ ቤትስ ገብተሽ ነበረ ወይ?????በጣም የሚገርምሽ ግን ትዝታዎችሽ በጣም ሻርፕ በመሆናቸው አድናቆቴ በጣም ከፍ ያለ ነው!!!!! ቺርስስስስስስስስስስስስስስስ!!!!!!!!

ባቱታ.....ከ14 ታዋቂ ተጫዋቾች ውስጥ የረሳሁት ውድ ጓደኛዬን ሲሳይ ተሰማን ነውና.....ምናልባት አንተ ከሆንክ ጀባ በለኝና ጀባ እልሀለሁ:: ለማንኛውም እንኳን ወደ ትዝታ አምዳችን በሰላም መጣህ!!!!!!!
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ዋናው » Mon Jul 16, 2007 11:00 pm

ዕጥፍ ሠላምታ ለአዲስከቴዎች
ትዝታዎች ይነባበራሉ ነው ሚወራው ጎበዝ የአምሣለ የትላንት ዕይታ ምንኛ ዕትብቷን የቀበረችበት ስፍራ ውስጧ መኖሩን ይናገራል ::
ቶድ አንተን እንዲያው
ያዲስከቴ ማሕደር ብዬ ስም ባወጣልህ በምን እድሌ ?
የስለሺ ባሪያዉን ቪዲዮ ቤት ብታነሳው ውስጤን ሳግ ተናነቃት ገና አዲስ ሙዚቃ ወጥቶ ሠዉ ጋር በካሴት ሳይገባ ስሌ በቪዲዮ ካሤት አስሶ ያመጣ ነበር:: ቅቅቅ ግን ግን የቪዲዮው ትርዒት ካለቀ በኌላ የፊተኞቹ ሁለት አግዳሚ ወንበሮች ይነሡና እነ ቶድ ነበሩ ዳንሱን ለመለማመድ የሚሸከሽኩት::
እስቲ ተጫወቱ መጣው ከመነን ቀንዶ ገዝቼ


_________________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests