የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ቶድ » Tue Jul 17, 2007 12:24 pm

ዋንቾ!!!!! አንተ ጉደኛ ልጅ::የስለሺ ቪዲዮ ቤት የፊተኞቹ 2 አግዳሚ ወንበሮች ይነሱና እነቶድ ነበሩ የሚሸከችኩት አልክ??::ቂቂቂቂቂቂ::በሳቅ ነው የገደልከኝ::ዋንቾ የረሳኸው ነገር ግን ስሌ ቪዲዮ ያሳይ የነበረው...18 ቀበሌ ድል በትግል አዳራሽ ውስጥ ሳይሆን እዛች ትንሿ ክፍሉ ውስጥ ነበር::ምክንያቱም በዛን ጊዜ የነበረው የወቅቱ ዳንስ ትንሽ ሰፋ ያለ ቦታ ይፈልግ ነበር::እንዴ!!! እነ ኦፔራዳንስ(ቴክኖ ትሮኒክስ),እነኤም.ሲ.ሀመር,ቦቢብራውን,ብላክ ቦክስ,.ስናፕስ. እና ሌሎችንም..እንዳልረሳሀቸው እርገጠኛ ነኝ::......እስኪ አሰልጣኛችንስ ማን ነበር???::በተለይ ብርቅና ድንቅ የሰፈራችን ዲጄዎች...እነመስፍን ታምሬ, ዘሌ ጽጌ,ስለሺና ኢብራሂም...ከዳንሳችን ጋር የሚጣጣም ዘፈን አመቻችተው ስለሚከፍቱልን....ዋውውውው ትዝታው ፈጽሞ በዕድሜው ሳያረጅ እኔ እንደማልፍ 100% እርግጠኛ ነኝ::
ዋንቾ!! እግረ መንገድህን ወደ መነን ስትሄድ እባክህ መነን ጋ ካለችው ልጅ ቆሎ.....ሱፍ በዛ አርጊበትና ብለህ ገዝተኽልኝ ና::ሂሳቡን ባልቻ ቡና ቤትህ ስመጣ እከፍልሀለሁ::
ውዶቹ...እነሀምሳል,ዲጎኔ,ጌታ,ባቱታ,ሀሁለሉና ሌሎቻችሁም የት ጠፋችሁ???
Last edited by ቶድ on Tue Jul 17, 2007 12:38 pm, edited 1 time in total.
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby ያባቱልጅ » Tue Jul 17, 2007 5:17 pm

አሁንስ እኔንም ነሸጣችሁኝ.....እስቲ ከአብነት ትንሽ ወረድ በሉ...ወደኮካ አካባቢ.....

ሰላም ዋሉልኝ

እመለሳልሁ
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ቶድ » Tue Jul 17, 2007 6:14 pm

ውድ ያባቱ ልጅ!!! እንኳን ደህና መጣህ!!!!.....ለመሆኑ ከክርስቶስ እና ከአዳም በስተቀር ያባቱ ልጅ ያልሆነ ማን አለና ነው ይህን የመሰል ስም ለብቻህ የጠቀለልከው::ብዙ ጥልቅ የሆነ የሀይማኖት ዕውቀት ስለሌለኝ ከተሳሳትኩም ይቅርታ ይደረግልኝና አምዱን ወደ ሀይማኖት እንዳንወስደው አደራ!!!!:: ለማንኛውም ፈጽሞ አንቃወምህምና......የከበረ ሰላምታ!!!
የአብነት ልጅ....ለዛውም የኮካኮላ....ግሩም ነው እባክህ!! ብዙ መጨዋወት እንችላለን ብዬ አስባለሁ::ለነገሩ የኮካ ልጆች ለሁለት ይከፈላሉ ብለው ያሟችኌል.....ያለው ማን ነበረ??::ለዛውም ጉዳዩን ሲያብራራልኝ....የተወሰኑትን የዛን ሰፈር ልጆች ስታወራ ሄልሜት ወይንም የጥንቱን የጦር ሰራዊት ኮፍያ(የብረቱን) ካላደረክ ፈረደብህ አለኝ::ቂቂቂቂቂቂቂ!!::እኔ ፈጽሞ የማላውቅ መስሎት!!:: ሌላኛዎቹን ደግሞ የተማሩና የአገር አደራ ተረክበው በየተሰማሩበት መስክ ግንባር ቀደም ተፋላሚ እንደሆኑ ሲነግረኝ በጣም ነው የተደሰትኩትና ወንድሜ አንተ ትዝታዎቹን ጀምርና እኛ ደግሞ .....እንከተላለን::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby batuta » Tue Jul 17, 2007 10:28 pm

ሰላም ለሁላጩ,hi ቶድ ሲሳይ ተሰማ አይደለሁም ግን ...
ለማንኛውም ሲሳይ ባለፈው ከጠቀስካቸው ሁሉ በእድመ አነስተኛ ነው. እንዲሁ አልኩ እንጂ እድሚ ቁጥር ነው ይባል የለ. ዋናው ሰው በዘመኑ ሰርቶ ማለፍ ነው[ቢቻል ጥሩ]
ኦ! የነ ነገር ለላ ዝብዝብ ውስጥ ገባሁ sorry ወንድም ለማንኛውም ወረው ካለህ አሁንም ይጫወት ይሆን? ከሆነ የት? እስኪ በዚያ ጥሩ አጻጻፍህ አንድ በል.
ሌላው ስለሺን በደንብ አውቀዋለሁ. አንተስ ገዛህኝ[አሊቶን]
ታውቀዋለህ? ሰላም ለሁ[/list]
batuta
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sun Jul 15, 2007 4:53 pm

Postby ቶድ » Thu Jul 19, 2007 11:19 am

የአዲስ ከቴው ውድ ባቱታ !!!"! እንዴት ከረምክ ጃል?????::አኪያሄድህ ትንሽ አስፈራኝ ልበል?? ሳንተዋወቅ እንዳልቀረን ገምቻለህ :: ዳሩ ባንተዋወቅም እንኳ.......የመርኬ ልጆች ይተዋወቁ አይደል እንዴ???::ስለሲሳይ ተሰማ ለጠይከኝ ጥያቄ በአሁን ሰአት የት እንደሚጫወት ባላውቅም ትንሽ ጊዜ ስጠኝና አጣርቼ አሳውቅሀለሁ!!!::ሲሳይ....ከታዋቂ ኳስ ተጫዋችነቱ ባሻገር በጣም አሪፍ ሙድ የነበረው ልጅና ፎጋሪ ሰው ነበር::ከፉገራዎቹ መሀል.......ቡና በሚጫወትበት ወቅት እናቱ ደሞዝ አይቆርጥልኝም ብለው ለስዩም አባተ(ለአሰልጣኙ) ስሞታ በማቅረባቸው....አሰልጣኙም እናቱ ስራ ቦታ እየመጡ ግማሽ ደሞዙን እንዲወስዱ ስለፈረደላቸው.....የቡና የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በቀን ሁለት ጊዜ ትሬሊንግ ሲያደርጉ ሲሳይ ተሰማ ግን አንዱን ብቻ ነበር የሚመጣው::በዚህ የተማረረው አሰልጣኝም ሲሳይን ጠርቶ ለምን እንደሆነ ሲጠይቀው ሲሳይ የመለሰውም መልስ...........አንደኛውን ትሬሊንግ እኩል ደሞዜን የምትካፈለው እናቴ መጥታ ትስራ አለ........ብለው ውሸታቸውን ያሙት ነበር ልበል???:: እንደዚህ በእውነት አደረገ ቢሉኝ እንኳ ለእናቱ ደሞዝ ላለመቁረጥ ፈልጎ ሳይሆን ትሬሊንግ ላለመስራት የስንፍና ምክንያት በማግኘቱ ይመስለኛል::.....ወደፊት ሌሎቹን ቀልዶቹን.........::ስለ ገዛኸኝ አሊቶ ለጠየከኝ ጥያቄ.....ገዜ ጓደኛዬ ነበር:: እጅግ በጣም ወርቅ ፀባይ የነበረው ልጅ ነበር::ጓደኝነታችን በእርግጥ በኳስ ጫወታ ዙሪያ የነበረ ቢሆንም...ፀባዩን ለመለየት የግድ ቀን በቀን አብረኸው መዋል አያስፈልግም::በአሁን ሰዓት በሳውዝ አፍሪካ ይኖራል::በለንደን የሚኖሩ የሳውዝ አፍሪካ ልጆች በሙሉ ስለሱ እጅግ በጣም ግሩም ነገር ያወሩለታል::አብረን እንብላና....... ችግርህን ልካፈል...... የግል ምልክቱ እንደሆኑ ሲነግሩኝ...ብዙም ባልገረምም በስደት አልም ላይ ሲኖር የሰው ልጅ ብዙ የባሀሪ ለውጥ ማምጣቱ አይቀሬ ነው ብዬ በማምንበት ሰአት የመርኬው ገዝዬ እንደዚህ አይነት የተመሰከረለት ወርቅ የሆነ ፀባይ ማሳየቱን...ጀባ ለወንድሜ ለባቱታና ለሚመለከትው ስል........ምናልባት ግን በብዕር ስም የምታናግረኝ አንተው ገዜ ከሆንክ....እኔም በበዕር ስሜ የማናግርኽ...........ቶቶቶቶድድድድ....ነኝ::ይመችህ....አቦ!! ን
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Postby batuta » Thu Jul 19, 2007 8:10 pm

ወንድም ቶድ እንደት ነህ ባያውሌው?I take my hat off !!! ስለ ሲሳይ ያልከው ያስቃል.ምን ያድርግ ትሬሊንጉ በጣም ያማርራል ሌላው እሱም ወጭው ብዙ ነበር. ቶድ ገዚ[አሊቶ] የመጨረሻ አሪፍ ልጅ ነው .እንደምታውቀው አሪፍነት የሚታደሉት ነው .ያ ሰፈር ብዙ አሪፍ ልጆች አሉበት በሁሉም መስክ . it's a wouderful place to grow up በል እንግዲህ ወንድም ቶድ ወሬ ይዤ እስከምመለስ ቸር ይግጠመን
ባቱታ
batuta
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sun Jul 15, 2007 4:53 pm

Postby batuta » Sat Jul 21, 2007 9:46 am

ወንድም ቶድ እንዴት ነህ?በድጋሚ እኔ ነኝ የዛረው እንኩዋን አመጣጤ ለየት ያለ ነው.ይህውም... ኢትዬጵያውያን በአውሮፓ የኹዋስ ጨዋታ [ልክ እንደ ሰሜን አሜሪካው]ያለ ባልሳሳት በዚህ ወር መጨረሻ ገደማ ይመስለኛል ያደርጋሉ የሚባል ነገር ሰማሁና እስኪ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን ካለ የት ይሆን የሚያደርጉት? አውሮፓ ከሆነ ያለኽው ልታውቅ ትችላለህ የሚል ግምት አለኝ. ሌላው እኔም በበረሀ ስሜ ቻው የምልህ ባቱታ ነኝ.ሰላም ሁን
batuta
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sun Jul 15, 2007 4:53 pm

Postby ሀምሳለ » Sat Jul 21, 2007 5:48 pm

ቶድ እና የአዲስ ከተማ ልጆች ሰላምምምምምምም

ያባቱ ልጂ የትኛው ኮካኮላ የድሮው ወይስ አዲሱ :D :D የድሮው ለካምቦዲያ ቀረብ ሲል አዲሱ ለጦር ሀይሎች ቀረብ ይላል አዲሱ ኮካ የማይረሳኝ በበሩ በኩል ሰታልፍ ቁልቁለት ነው ድልድይ አለ ከዛ ደግሞ ዳገት በጸሀይ ወደዳገቱ ወተህ ዝናብ ከዘነበ ወሀ ይሞላና መመለሻ የለህም :D :D አሁን ወይ ፎቅ ተሰርቶበት ይሆናል :D
ቶድ እስኪ ባቱታ የጠየቀህን (የጠየቀችህን ) ሰትመልስ እመለሳለሁ :D

አየለ ጂቦ ብለህ በሳቅቅቅቅቅቅቅ ነው የገደልከኝ በዝና ፈራው ነበር ግን ጂብ ይመስላል ለምን ጂቦ ተባለ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በጊዜ ግቡ አየለ ጂቦ አለ ክክክክክክክክክ ክክክክክክ
ሀምሳለ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 243
Joined: Fri Oct 13, 2006 8:43 pm
Location: America

Postby ዋናው » Sun Jul 22, 2007 3:43 pm

ሠላም ሠፈረ-አዲስከተማዊያን
አዲስ ከተማችን እዚህ ዋርካው ውስጥ ቡርቅቅ ብላ የትናየት ደረሠች....? ከላይ እስከ ኳስሜዳ...ከታች እስከ አዲሡ ኮካ....
ድንቅ ነው በአካልም እንዲ መስፋፋቷን እመኝላታለሁ: ቶድ ድንቅ ቪዥንህን ደጋግሜ ነው ማደንቀው::
ቶድ የሞላማሩን ሙሣ ማዴቦ ታውቀዋለህ ? በጣም የማደንቀው የሠፈራችን ሠው ነበር በነበረው ጠቅላላ እውቀት በቲቪና በረዲዮ የሚጠየቁትን የስልክ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ ይመልስ ነበር:: ባንድ ወቅት የአራትኪሎዋን ማርታ ደጀኔን ይፎካከራት እንደነበር አስታውሳለሁ...
ማን ያውቃል ራስህም ትሆናለህ?ቅቅቅቅቅ
ሌላው ከአዲስከተማ ደቡባዊ ክልል ሞላማሩ ሳልወጣ እዛው ካናል ሻይ ቤት አካባቢ አንዲት ሙኒክ ምትባል ወንዳወንድ ነበረች እኛ ሕፃናት ሆነን በዛ ስናልፍ ከጎረምሶች ጋር ቁማር ስትጫወት ስናይ እንደህንድ ፊልም ነበር የምናያት ቅቅቅ? ይሄኔ አሁን ብዙ ብዙ ሙኒኮች ተፈጥረው ይሆናል? ከሷ ቤት ሽቅብ ስትወጣ የአቶ ሻንቆዱሎን ቤት እንዳለፍክ የነበረው ቆርቆሮ ጊቢ ውስጥ ደግሞ አንዲት ራይማ ምትባል ቆንጆ ልጅ ነበርች (የውስማን እሕት) ዓይኗ ሠማያዊ ነበር የርሷን ውበት ለማየት ከልደታና ከተ/ሐይማኖት ሁሉ የሚመጡ ነበሩ እኔንኳን ያኔ
ለአቅመ-ማድነቅሳልደርስ በልጅ ልቤ ውበቷን ማየቱ ልክ ትምህርት እንደመፎረፍ ያስደስተኝ ነበር....አይ አዲስከቴ ...

እስቲ እንቅደድ እነሰባሰብና ...ለወጋችን ማጣፈጪያ ከብሌን ጃንቦ ድራፍት አስቀድቼላቹ ላምጣ?


ዋናው________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ጌታ » Tue Jul 24, 2007 3:15 am

ዋኒቾ እያንቦረቀቃቹ ሞላ ማሩ ከደረሳችሁማ ትንሽ ወደላይ ከፍ በሉና ተክልዬ በርበሬ ተራ እንሂዳ!! በፔፕሲ ፋብሪካ እና በተክልዬ መካከል ንጉስ ወልደጊዮርጊስ የሚባል ትምህርት ቤት አለ:: እርግጠኛ ነኝ ሁላችሁም አታውቁትም :lol: :lol: ባብዛኛው እዛ የሚማሩት የከፍተኛ 3 ቀበሌ አርባ ምናምን ልጆች ቢሆኑም ከሻውል ደማ አካባቢም ጭምር የሚሄዱ ብዙ ልጆች ነበሩ::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ያባቱልጅ » Tue Jul 24, 2007 8:59 pm

እናንተ ጨዋታችሁ እንዲት ይመቻል....

ቶድ ብሮ....ይሂውልህ ያሰፈር በተለይ ማዞሪያ አካባቢ እንዳልከው ሀልሜት ማድረግ ያስፈልገው ነበር:: ችግራቸው አይገባንም ነበር ግን በሆነ ወቅት የ35 እና የ36 ተመራጮች የቻሉትን አሰሩ ሌላውም እየሸመለገለ ሂደ መሰለኝ ቀነሰ::
ቴቸር አናጋው ትዝ ይላችሑዋል? አሁን ከፍትኛ 4 (ቢቸግር) ሆኖዋል::
ካሮት አጠባስ???? በናታህ ቶድ.....ልጆች በኛ ቤት ነበር የሚያልፉት ታዲያ ትልቁን ውሻችንን እይዝና የኮቴ እቀበል ነበር.
batuta እና አምሳለ የውሮፓው game holland ነው በ28 እና በ29 ጁላይ.
አምሳለ እስትይ አውጊን::
እመለሳለሁ
ሰላም ይብዛላችሁ
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ያባቱልጅ » Tue Jul 24, 2007 9:29 pm

ዋናው.... ድርፍቱ ብሌን ካለቀ ተካልኝ ድረስበት:: አለዛ ምንተስኖት ራት እየበላን እናውራለን.

ሄድኩ እንግዲህ....
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ቶድ » Thu Jul 26, 2007 7:59 pm

ሰሰሰሰሰሰላላላላላላምምምምምም!!!!!! ለአዲስ ከቴ ልጆች በሙሉ ይሁን በማለት መጪው የሀገራችን የ2000 ዓመት ለጠቅላላው የመርኬ ልጆች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት የብልጽግና የእድገት እንዲሁም የተመኛችሁትን በሙሉ ቸሩ እግዚአብሄር ያሳካላችሁ ዘንድ በቅድሚያ እመኝላችኍለሁ::

ውድ ያባቱ ልጅ.......በቅድሚያ ባቱታ ጠይቆኝ ለነበረው ጥያቄ መልሱን ስለመለስክልኝ በጣም ነው የማመሰግንህ:: ለነገሩ እኔ የኮቴ አልከፈልኩም እንጂ.....ብከፍል ኖሮ....ቅቅቅቅ......አሁን አለቅህም ነበር::በነገራችን ላይ ስለማዞሪያ ብታነሳ.........እኔ አንተ ወንድሜን በትዝታ አልጎዳም ብዬ ነው እንጂ......ካስፈለገ በትዝታ ባቡር እያንደረደርኩኝ ማዞሪያ ላይ ነበር የምጥልህ:: አንተም ደግሞ በመጠኑ የጫወታ ስስት አለብህ ልበል??? ኧረ ከማዞሪያ እኮ የሚጠቀሱ ስንት ጉልቤውች ....ኳስ ተጫዋቾች ....ቆነጃጅት.....ብቃት ያላቸው አራዳዎች....ኧረ ስንቱ.....:: ታዲያ አንተ ያማዞሪያ ልጅ ከሆንክ ምነው የአንድ ሁለቱን እንኳ ስም መጥቀስ ፈራህ????:: ለማንኛውም ካሳሁን ባሪያው....ታዋቂው አርቲስትና ዳንሰኛ በአሁኑ ሰዓት በአየር ላንድ እንደሚኖር ሰምቻለሁና ስለሱ የምታውቀው ካለ ትንሽ ጀባ በለን::ካላወክም.....ጠይቀን......በራችንን ካንኳኳህ......... ይከፈትልሀል::በነገራችን ላይ ካሳሁን ባሪያው ስል በስድብ መልኩ ያቀረብኩት ሳይሆን በሰፈር መታወቂያ ቅጥል ስሙ ማንሳቴ መሆኑን ይታወቅልኝ::በዚህም ንግግሬ የተከፋ ሰው ካለ የጠበቀ ይቅርታ እየጠይኩ....ቅጥል ስሙን ካልጠቀስኩኝ ብዙ ሰዎች ላያውቁት ይችላሉ በማለት ነው:: ውድ ያባቱ ልጅ........ብሌን ሆቴልን ስትጠቅስ የተሰማኝን ስሜት እንዳትጠይቀኝ:: መዋያዬ...አልፎ ተርፎም ማደሪያዬ ነበር:: ከብሌን ሆትል ሰራተኞች የምታስታውሱት ሰው ካለ ጀባ በሉን ወይንም ከትዝታዎቻችሁ::ተካልኝና ምንተስኖት ደግሞ......ዋውውውውው ....በተለይ የምንተስኖት ምግብ.......አሳውን ያዘዝክ እንደሆነ.....የዋኘበትን ውሀ ፈርገጥገጥ ብሎ.....ፊት ለፊትህ ተጋድሞ የመጣበት ትሪ ላይ ነው የሚያራግፈው::ቅቅቅቅቅቅ::ደግሞ ትልቅነቱ.........::

ወንድሜ ጌታ.....ሰላም ላንተ ይሁን::......ለመሆኑ ንጉስ ወ/ጊዮርጊስ ት/ቤትን ማናችሁም አታውቁትም ያልከን ለኒኩሊየር ቦንብ መስሪያ ወደ መሬት የተቆፈረ ጉርጓድ አስመሰልከው ልበል???? ገሊላ ት/ቤት እንኳ ይታወቃል እኮ ጌታው!!!!! ተክልዬ አካባቢ....በጣም ብዙ ጓደኞች ነበሩኝ:: ለመዝናናትም ቢሆን አክሱም ሆቴልና ንጉሴ ቤት ብዙ ጊዜ ብቅ ብቅ እል ነበር::እስኪ ስለዛ ሰፈር ጀባ በለን እና ጀባ እንበልህ::

ዋንቾ.......ምርጥ የሰፈሬ መመኪያ......ከሙሳ ማዴቦ ጋር መወዳደሬን ትንሽ ከበደኝ.......ከሱ ጋር እኮ የማዘጋጃ መዝገብ ቤት እንኳ አይወዳደርም::ስለ ሙኒካ ላነሳኸው ግን በጣም ነው ያሳከኝ::በተለይ ጫማ ጥፊዋ.....ለጉድ ነው::የሴት ጉልቤ በቃ እሷን ብቻ ነው ያየሁት ልበል???:: ደግሞ 3 አንበሶች ሻይ ቤት ዱቅ ብላ.....ከነ........ያው ጉልቤውቾ ማለቴ ነው....አቤት ስታስፈራ:: በነገራችን ላይ የአቶ ሻንቆዱሎን ስም ስታነሳ በዛ ቅያስ ይኖር የነበረውን ታዋቂ ሰው ወገኔ አሻግሬን (የቲቸር አሻግሬ ልጅ) አስታወስከኝና እኔም መልሼ አስታውሼሀለሁ:: አቤት የሞላማሩ መጠጡን ሳይሆን ጉልቤዎቹን ታስታውሳቸዋለህ:: ዛሬ ደግሞ ያለወትሮዬ ምነው ስለጉልቤ አበዛሁ???::ዳሩ ከሰፈር ትዝታዎች መሀል አንዱ ጉልበተኞች አይደሉ እንዴ.????......::

ከፍተኛ 6 ምነው ተበለጣችሁ ጃል??::አሁን ወቅቱ የማዞሪያ የሞላማሩና የተክልዬ ልጆች ነው ብላችሁ ነው እንዴ?????:: እስኪ ስለ እህል በረንዳ....መሳለሚያ.....አውቶቢስ ተራ....ሰባተኛ...አማኑኤል...ብሌን አካባቢ....ሞላማሩ......አብነት.....ካንቦዲያ......ማዞሪያ.....ጥሩ ጥሩ ጫወታ አምጡ........::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

Re: የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ

Postby ባቲ » Thu Jul 26, 2007 11:37 pm

እንቆጳፂዮን1 wrote:ባካቹ የአዲስ ክትማ ሰፈር ልጆች ካላቹ እዝ እንስባሰብ ፕሊዝ

ሰላም ለአዲስ ከቴ ልጆች
ስሜ:- ባቲ
አድራሻ:- ብሌን ና መስቀል ሆቴል
የኳስ መጫወቻ ቦታ:- አለሙ ሜዳ (26)
ዋና መዋኛ:- ሀገሬ ወዝና ና ዳክዬ ዋና
ት/ቤት:- እናት ኢትዮጵያ, ተስፋ ኮከብ, ኮልፌና አዲሱ(ከፍተኛ ሰባት)
የምወደው ቦታ:- አዳራሽ መርካቶ
የምወደው መዝናኛዬ:- ከቴ ሙቪ
ሻይ ቤት:- አቦ ሲታ ( አስራስምት አዳራሽ)
ጫት:- ኢሻራ ጫት (23), ምኞት ደግሞ የጠልፎ ናሽፍ
ምግብ: ከ21 ክበብ ጀርባ የማን እናት ነበሩ............የሳቸው ሽሮ በአይቤ
የማይረሱኝ ሰዎች:- ሻፍት ና መሉጌታ ወጨፎ 21 ቀበሌ
ወንድሙ 16ቀበሌ(?) ና ሌሎችም.................
ዋናው ቶክቻው አመሰግናለሁ:: ነበብ ነበብ አድርጌ ልጨርስና የምቸከችከው ይኖራል:: እስከዛው እንጀራ ትኩስ ሽሮ እስከአንገቱ የተደፋበት አይቤ ለእያንዳንድሽ ግብዣዬ ነው::
ባቲ
SaQ _Be _SaQ.....That's what I wish 4 all of Us
ስምየ ውዕቱ ክንዴ ባቲ
ባቲ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 942
Joined: Tue Jul 06, 2004 8:18 pm
Location: ethiopia

Postby ቶድ » Fri Jul 27, 2007 5:22 pm

ገቡ!!!!!ገቡ!!!!!ገቡ!!!!ገቡ!!!!!!!!

ወንድ ትሆን ሴት....ፆታህን ባላውቅም...........
...............ውበት ሲለካ ባቲነው ለካ........በማለት ለባለባቲ ስም .....እኔ ደግሞ ከወንድሜ ዋንቾ ባልቻ ቡ/ቤት ያላበው ባቲ ቢራ .....እንሆ ግብዣ.......::
............እንኳን ደህና መጣህ ባቲ:: የትኛው ባቲ.....እንደማልልህ እርግጣኛ ነህ::ደግሞ የምርጦቹ የወሎዎች ኦሪጅናል ባቲ ብትሆንም........እሰየው.....ግሩም ድንቅ ነበር:: ነገር ግን....የአዲስ ከቴው....ባቲማ....ዋውውውውውውውውውው!!!!!!!!!!

ሙሉጌታ ወጨፎን የሚያውቅ ሰው.......ዋውውው!! በጣም ነው ደስ ያለኝ::ያ እየበረረ የሚሄድን የሞላ ታክሲ አስቁሞ ስዓት ሥንት ነው ብሎ የሚጠይቀው....ቅቅቅቅቅቅቅቅ የሱ ልጅ ፉገራ በጣም ነው የሚመቸኝ::ደግሞ ሌላ ሰው ሰዓት ስንት ነው ብሎ ከጠየቀው....በፍጥነት እሩብ ጉዳይ ይላል...ሰዎቹም ለስንት ካሉት እሱን ደግሞ ከሌላ ሰው ጠይቅ የሚለው.....አቦ ይመቸኛል:: በል እንግዲህ ኮርኩረኝና ልኮርኩርህ:: የሙሌን ወንድምስ....አክሊሉ ወጨፎን ታውቀዋለህ ወይ???:: ሌላ ግን ወንድሙ ስትል...ወንድሙ አስግዶምን ማለትህ ነው??:: እሱን ከሆነ የዝነኛው የከፍተኛ 5 ኪነት አስተዋዋቂ ነበረ....በጣም የታወቀ ፎጋሪና...ግሩም እንግሊዘኛ ተናጋሪ....አልፎ ተርፎም እንግሊዘኛ ዘፋኝ ነበረ::

ወይ ጉድ.....ደግሞ ስለአዲስ ከተማ ሊቀመንበር ስለ ሻፍት .........አቦ ዘርዘር አርገውና ባቲህን ደጋግመው::ይመችህ ወዳጄ!!!!!!!! እኔም ብሆን የብሌንና የአለሙ ሜዳ ምልምል ነኝ::
ቶድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 100
Joined: Fri May 04, 2007 5:33 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests