ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)" href="http://www.cyberethiopia.com/warka14/feed.php?f=2&t=23129" />

ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)

Postby ወረኢሉ » Tue Jul 03, 2007 11:43 pm

ሰላም ወንድም እና እህቶች!



የዘር አምባጓሮ የኃይማኖት ንትርክ ወሎ መች ለመደ:
ሥሙ ምስክር ነው ፋጤ ገብረማርያም ሙህዬ ከበደ::



ወሎ - ላኮመልዛ - የአሥራ ሁለት አውራጃዎች (ዋግ - ላስታ - ራያ ቆቦ - የጁ - አምባሰል - ዴሴ ዙሪያ - አውሳ - ቃሉ - ቦረና - ወረኢሉ - ዋድላ ደላንታ እና ወረሂመኖ) ባለቤት ፣ የሙዚቃ ቅኝቶች (ባቲ - አንች ሆዬ አምባሰል እና ትዝታ) ምንጭ ፣ የታሪካዊ ቦታዎች (ውጫሌ መቅደላ ላል ይበላ ጊሼን ወዘተ) ሥፍራ ፣ የሙያ እና የቀለም ትምህርት ቤቶች (ወ/ሮ ስሂን ወልዲያ ወዘተ) ፣ የሙዚቃ የጀግኖች ባለሙያዎች እና ምሁራን መፍለቂያ ፣ እስላም እና ክርስቲያኑ ፣ ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት እና በእኩልነት የሚኖሩበት አገር ነው:: በጥቅሉ ወሎ ገራገሩ ማለት ይቀላል::


አማርኛው የእኔ ትግርኛው የእኔ:
አፋርኛው የእኔ ኦሮሞኛው የእኔ:
አገውኛው የእኔ አርጎብኛው የእኔ:
ጋፋትኛው የእኔ ቆንጆዎች የእኔ:
ክርስትናው የእኔ እስልምናው የእኔ:
ያም እኔ ያም እኔ ያገር ልጅ ወገኔ:
በጣም ያኮራኛል ንፁህ ኢትዮጵያዊ ወሎዬ መሆኔ::



የወሎን ህዝብ በትምህርት በግብርና በጤና በባህል ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብ እና በመሳሰሉት አብይ አንኳር መስኮች ማሳደግ እና ማዳበር የሁላችንም ጥረት ይሆናል:: ሁላችንም በመተባበር ለዚህ ቀና ዓላማ ግብ መድረስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት እንችላለን:: ሥለዚህ በዚህ ዐምድ እና መድረክ ቅን ሃሳቦችን መሠንዘር እንችላለን::

በተጨማሪ ፓልቶክ ውስጥ WOLLO GERAGERU (ወሎ ገራገሩ) በሚለው ክፍል ውስጥ ቅዳሜ እና እሁድ ከ21:00 CET ጀምሮ መወያዬት ለብቁ ውሳኔ እና ተግባር ጥርጊያ መንገድ መክፈት ይቻላል:: ፓልቶኩ እንደ አመችነቱ በየቀኑ ይከፈታል::

ብሩህ ለሆነ ዓላማ አብረን እንነሳ


ስኂን ትጣራለች!!

Image

የሰው አስኳል የሰው እንብርት:
የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት::

ስንት አርግዘሽ ስንት ወለድሽ:
ስንት ዘርተሽ ስንት አበቀልሽ:
ስንት አትርፈሽ ስንት ገደልሽ:
ስንት አጥፍተሽ ስንት ታደግሽ :?:

ስኂን ስኅኗ መቅረዛዊት:
ያንቺ ውላጅ ያንቺ ቁራጭ:
ያንቺ ፍላጭ ያንቺ ቅዳጅ::

በምድረ አለሙ ተናኝቶ:
ድንቅ ውሎ ዋለ ጎምርቶ:
ይበል ይበል ተሰኝቶ::

አዎ ስኂን ስኂኗ መቅረዛዊት:
የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት::

Image

ዝንተ ዓለም ህያው ነው ግብረ ተመክሮሽ:
እንኳን ቅርስ ነው ምግባረ ውሎሽ::

አንችስ ህያው ነሽ:
ማነው ሞትሽ ያለሽ?

ስኂን ስኂኗ መቅረዛዊት
የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት::

1985

ሕብረት ኃይል ነው::
እህታችሁ ወረኢሉ ከወሎ ገራገሩ
Last edited by ወረኢሉ on Fri Oct 03, 2008 3:06 am, edited 11 times in total.
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Re: ሥኂን

Postby ወልዲያ » Wed Jul 04, 2007 8:22 am

ሠላም ወረኢሉ!

ከወረኢሉ

ሠላም ለሥኂን ተማሪዎች እንደምን ከረማችሁ::
ሥኂን ትጣራለች!!

Image
የሠው አሥኳል የሠው እንብርት:
የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት
ሥንት አርግዘሽ ሥንት ወለድሽ?
ሥንት ዘርተሽ ሥንት አበቀልች?
ሥንት አትርፈሽ ሥንት ገደልሽ?
ሥንት አጥፍተሽ ሥንት ታደግሽ?
ሥኂን ስኅኗ መቅረዛዊት:
ያንቺ ውላጅ ያንቺ ቁራጭ:
ያንቺ ፍላጭ ያንቺ ቅዳጅ:
በምድረ አለሙ ተናኝቶ:
ድንቅ ውሎ ዋለ ጎምርቶ:
ይበል ይበል ተሠኝቶ:
አዎ ሥኂን ሥኂኗ መቅረዛዊት
የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት:
ዝንተ አለም ህያው ነው ግብረ ተመክሮሽ
እንኳን ቅርሥ ነው ምግባረ ውሎሽ
አንችስ ህያው ነሽ
ማነው ሞትሽ ያለሽ?
ሥኂን ስኂኗ መቅረዛዊት
የእውቀት ጮራ ፋና ወጊት::

1985


ይህ ነው ቁም ነገሩ አብረን ለመሥራት:
ይህ ነው ቁም ነገሩ አብረን ለማምረት:
ይህ ነው ቁም ነገሩ አብረን ለመተቻቸት:
ይህ ነው ቁም ነገሩ አብረን ለማውራት:
እስቲ ብቅ ብለን አብረን እንጨዋዎት::


ትምህርት የእውቀት ብልጭታ ነው
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ፋጤ » Wed Jul 02, 2008 12:48 pm

ሰላም ለዚህ ቤት አማ ነው:.


ለመግለጽ አልዳዳም ------ ክብርሽን ዘርዝሬ:
ላንች ያለኝ ሰሜት -------በቅጡ አብጠርጥሬ::
ብቻ ባልችል ብዙ ------ በጣም ክሽን ቃላት:
----- የልቤን ለማውሳት:
እንዲያው በደፈናው ስሂን የብዙ እናት::

-----------ብልሽም አልረካሁ
-----------አሁንም ቃል አጣሁ::

ጥንትም አውቅሽ ነበር - - - ያኔ ዶሮ ገና:
ፀሐፍት በብዕር ከሽነው ሲያቀረቡት
- -- - - - ያንችን ምጡቅ ዝና
የያኔው ዝናሽ ሳይነጥፍ- - - ፈካሽ እንደገና:
ለብዙሀን ምሳሌ ሆንሽ ሆኖ ተግባርሽ ገናና::

ከቶ ስንት ይሆኑ--- ያንችን ጡት የጠቡ:
ሰምሽን በማሰጠራት---- ሀገር የገነቡ:
አይደል ሙያ ብቻ ---- በቴክኒኩም ጐራ
ፍሬሽ በርካታ ነው -----በቀለሙም ተራ::

ብዙሀን ሲመኙ ----ቀለም ሊቀስሙብሽ:
------------ በውቀት ሲካኑብሽ:
------------ እኔም ገባሁብሽ::

አየሁት ዘልቄ ----- ቃኘሁት ውስጥሽን:
ምቹውን ጓዳሽን::

ተገነዘብኩ እኔም በከንቱ እንዳልነበር:
የነዚያ የመፀሐፍት ሙገሳ የስሂንን ክሸና:
የውቀት መአድሽን ተጋርተዋል እና::

ብመሰክርልሽ ታሪክሽን ባወሳ:
ስምሽን ባነሳ:
ቅንጣትም አረካሁ:
አሁንም ቃል አጣሁ::
ተማሪ መምህር ጋር--- ገሀድ ተወያይቶ:
- - - - - - በግልጽ ተግባብቶ:
በፍቅር ተኖረብሽ ------ ቅራኔ ተረስቶ::

መቼም የግድ ሆኖ የአብሮ ነትሽን ሰሜት:
------------መቀጠል ባልችልም:
የውቀት ማዕድሽን ---መቋደስ ባቆምም
የዘላለሜ ንሽ ስሂን አረሳሽም::

አቦ አትጥፉ በአላህ ብቅ በሉ::


ፋጤ
ከስሂን በር
Last edited by ፋጤ on Thu Apr 30, 2009 1:44 am, edited 1 time in total.
Image
አሰደሳችና ጠቃሚ ይሆናል ለምትለው
ነገር ሁሉ በይሉኝታ አትለፈው !!
ፋጤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 107
Joined: Mon Aug 20, 2007 9:25 pm
Location: WolloW

Postby ከንቲባ » Wed Jul 02, 2008 1:57 pm

እዛኛው ቤት ስድብ የሚችል ነገረኛ ሰው ገብቶባችሁ ሸሻችሁ አይደል ? ተጋደሉ እንጂ ::
እሱን አባሩት እናንተ አትሽሹ ::
forward for the desicive fight !
ከንቲባ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 113
Joined: Tue Jun 17, 2008 10:37 pm
Location: Austria

በስሂን ይገለጣል

Postby ወልዲያ » Tue Jul 08, 2008 5:48 pm

ሠላም ለቤቱ!


በስሂን ይገለጣል

Image

ከንቲባ አይተሃል ሁሉን ተረድተሃል:
እንስራ ባልን ወቅት ሰውን ይረብሻል:
በሆነ ባልሆነው ሬቱን ይቀባል:
ምንም ችግር የለም እውነቱ ይወጣል:
ጊዜውን ጠብቆ በስሂን ይገለጣል::

ወረኢሉ አለሸ ወይ ብቅ በይ በጊዜ:
አስጎበኝሻለሁ ወንዙ ነው ተከዜ::



ለትምህርት ዕድገት በአንድነት እንነሳ
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ወረኢሉ » Tue Jul 08, 2008 7:17 pm

ሰላም ለሰሂን ቤት ሰላም ብለናል ፋጤ መልካም አድርገሻል ቤቱን ፈልገሽ ይህን ማምጣትሽ ጥሩ ነው::

ሰላም ከንቲባ እንኳን ደህና መጣህ መልካም አስተያየት ነው በርታልን: እኛ ምን እናድርግ ብለህ ነው መሸሽን መርጠናል ዋርካ ሰፊ ነው ምንችግር አለ በለህ ነው:. በል ይልመድብ አሪሂቡ ብለናል::



ወረኢሉ
ከስሂን ግቢ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ወረኢሉ » Tue Jul 08, 2008 7:29 pm

ሰላም ወልዲያ አለህ እንዴ መልካም ነው ይሄው ብቅ ብያለሁ ለመሆኑ የጃማ ጦስኝ የት ጠፋች ያ ባለሱቅ ሲያሽኮረምም ነብር ይዟት ጃፓን ገባ እንዴ?? መጠርጠር ነው ቅቅቅቅቅ::

እስኪ እነዛን የሚያ ዝናኑ ቀልዶችህንና ግጥምህን አስነብበን በሰፊው በነጻ መድርክ ከልካይ በሌለበት.....::

ሰውማ - ሰው አለ
ሜዳው ሁሉ ሰው ነው::
ሰው መች ላይን ጠፍቶ
ልብ እንጂ ያዘነው:.
ግፊያው አሰጨንቆት
በሰልፍ ስልችቶ

አንድም - የሚራመድ
አንድም - የሚስተውል
አንድም - የሚሰማ
አንድም - የሚናገር
አንድም - የሚረዳ
አንድም - የሚነቅፍ
አንድም - የሚደግፍ
የሚመስለው አጥቶ::

መልካም ጊዜ ይሁንላችህ አትጥፉ በርቱ::



ወረኢሉ
ከሰሂን ግቢ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ባንቺው መጀን

Postby ወልዲያ » Tue Jul 08, 2008 9:21 pm

ሠላም ወረኢሉ እና ታዳሚዎች!



የጃማ ጦስኟ የእኔ ባለቤት:
ማርዬ ሂዳለች ልታስተምር ትምህርት::

Image

ማርዬ ቤታችን ላሙና እየሰራች:
ለጤና የሚበጅ ጦስኝ ሻይ አገኘች::

ቦረና ተሻግራ ሳይንት ከለላ:
ታሪክ ለመዳሰስ አረፈች መቅደላ::

ባቲ እና ከሚሴ - ኮምቦልቻ እና ዴሴ:
አሽኩቲ ፈለገች ናትራ ዳማ ከሴ::

ኩታበርን አልፋ ደረሰች ጊሼን:
አብረንደፍ አበትን አየች ውጫሌን::

ሓይቅ ተሁለደሬ ወረባቦ ገብታ:
ወሎ ገራገሩ የፍቅር ጠብታ::

Image

ባለፈው ሳምንት ደብዳቤ ጦስኝ ልካልኝ:
ግቢያችንን ሳየው በጣም ማረከኝ:
መጓዜ አይቀርም እሷን አሰኘኝ::

ባለሱቅ ቢደክም ቢያሽኮረምማት:
ላያገኛት ነገር በከንቱ ልፋት::---:-)

ፋጤ የጃሪዋን ባለሱቅ ወድዶ:
ሆጤ ጠለፈና አሻገራት ዳውዶ::

ባንቺው መጀን (ደርብ ዘነበ)
http://www.youtube.com/watch?v=ytO8scHnxQ8

>>>>>>>>>>>>>>> ይቀጥላል


አብሽር ወሎ
ወልዲያ - የጁ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Postby ባለሱቅ » Tue Jul 08, 2008 11:14 pm

ሰላም ሰላም ያገር ልጆች

ጥሩ ጅምር ነው ወረኢሉ

ሰላም ባለበት እድገት አለ

ሰላም ፈጥራቹ ያሰባችሁትን አድርጉ

ጌታ ከናንተ ጋር ይሁን

ሰላም ለሁላቹም
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ስሂን

Postby ወረኢሉ » Wed Jul 09, 2008 12:20 pm

ሰላም ስሂኖች

ባለሱቅ አመሰግናለሁ:: አትጥፋ:: ፋጤን ዬት አደረስካት?


ባለሱቅ wrote:ሰላም ሰላም ያገር ልጆች

ጥሩ ጅምር ነው ወረኢሉ

ሰላም ባለበት እድገት አለ

ሰላም ፈጥራቹ ያሰባችሁትን አድርጉ

ጌታ ከናንተ ጋር ይሁን

ሰላም ለሁላቹም


ስሂን

በዚያን ሰሞን:
ሬዲዮኔን አጉል ጠባይ ተጠናውቷት:
ቀንም ማታም
ነጋ ጠባም
ስብሰባ የስብሰባ ጥሪ
እያለች ስትልጎመጎም
አንድ ወሬ ጠቅ አረገኝ
ካሳብ ጉዞ አናጠበኝ::

ሰማህ አንተን እኮነው ትሰማለህ?
ስትለኝ
ግራ ገብቶኝ
አዋ ምነው ስላት
የእውቀት ማዕድ ያበላህ
ለቁምነገር ያበቃችህ
ት/ቤትህ ጠራችህ
ሰትለኝ
ባነንኩ
ብዙ አሰብኩ
ብዙም ቦታ ተብከነከንኩ::

ቢጨንቀኝ ት/ቤት? የማን?
የማን ት/ቤት የኔ?
አዎ ያንተ:
ዝነኛዋ
እኮ የቷ?

ወይዘሮ ስኂን ናታ የጥንቷ


እና

ሂድ ስማት
ለጥሪዋ ድረስላት
የምትልህን አድምጣት
ወግ ይድረሳት::

ስትለኝ

የቆየው ናፍቆቴ ህይወት ዘርቶ
በህሊናየ ዘልቆ ገብቶ
ሳላወላውል መጣሁኝ::
የተባለውን የታለመውን
የታሰበውን ሰማሁኝ::

እና

ለምወዳት ለማፈቅራት
ለዕውቀት እናት
ልድረስላት አልኩኝ::
አጠፋሁኝ?
ግን ሰው
ለሚወደው
ለሚያፈቅረው
ለኔ ላለው
ምኑን ይሆን የሚሰጠው?
ገንዘቡን?
ለቂያማ ቀን ያኖረውን?
መጦሪያ ማደሪያውን?
ለነገ ያለውን?
ወይስ ጌጡን?
የአንገት ሀብሉን?
መዋቢያ ማማሪያውን?
ነው ቀለበቱን?
የቃል ኪዳን መሰረቱን?
ለካስ ስው ለሚወደው
የሚያደርገው የሚያረካው
ሲጨንቀው ሲጠበው
ከጉኑ ቆሞ አይዞህ ሲልው
ያኔ ነው ናፍቆት ፍቅሩን የሚገልፀው
ውለታውን የሚከፍለው::

እና ጐበዝ ስኂን

እኛ ቆመን ሽህ ሚሊዮን ትሁን

ስኂን

ኮሌጅም ዩኒቨርሲቲም ትሁን
ትመር ትድመቅ
ታብራ ትርቀቅ

ስኂን

እልፍ ትሁን
እየኖረ የሚያኖራት
ከብሮ የሚያስከብራት
ታውቆ የሚያሳውቃት
ስኂን ስኂን የሚያሰኛት
ዘር ይብዛላት::

ከቀድሞ የወ/ሮ ስኂንተማሪዎች
በተሥፋዬ ማሞ የተዘጋጀ ሥነግጥም


በሉ አንጠፋፋ ቸር ይግጠመን
ከወሎ ገራገሩ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

እጃችንን እንጣል

Postby ወልዲያ » Wed Jul 09, 2008 1:27 pm

ሠላም ለሁሉም!



ከሀ ሁ አልፌ ሀ ግዕዝ ሁካኢብ:
መልዕክተ ዮሓንስ ወንጌሉ ሲነበብ:
ዳዊት እና ጊሼን ማርዬ አይጠገብ::

ትምህርትን ለመማር ችግሮች ነበሩ:
ያው እንደ አቅምቲ ጠፋፋ ነገሩ::

በእኔ የደረሰው በሌሎች እንዳይደርስ:
ምነው ከልባችን ሥህንን የማንዳስ::

ሥራ ቢበዛብን ችግር አያቃልል:
አንዳንድ ጊዜ ተነስተን ገንቢ ቃል ብንጥል:
ህብረት አንድነት ነው እንዴት ያስደስታል::

ዛሬን ለማሸነፍ ዛሬ ካልተነሳን:
ለነገ ካለፈ ለእኛም አይበጀን:
በሉ ነቃ ነቃ ኩራትን ጣጥለን::

Image

የጥቁር ሰሌዳው ቀለሙ ጠፋፍቷል:
ጠመኔው እንዳይጽፍ በጣሙን ዶምዱሟል:
ወንበር ጠረንጴዛው ደስኩ ተሰባብሯል:
ግድግዳው ሲወድቅ ኮርኒሱ ፈራርሷል:
ቤተ መጻህፍቱ እንዳልነበር ሁኗል:
ቲዎሪ ብቻ ነው ተግባረ እድ ቀርቷል:
መዝናኛ ክበቦች በጣም ይፈለጋል:
እስቲ ብድግ ብለን እጃችንን እንጣል::

Image
የወረኢሉን ቡና ናፍቆኛል - አብረን ለመጠጣት - እንሰባሰባ

አብሽር ወሎ

መልካም አብዶዬ
ወልዲያ
ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ቡና ጠጡ

Postby ወረኢሉ » Wed Jul 09, 2008 1:37 pm

ሰላም ስኂኖች ቡናውን ለመጠጣት አሪሂቡ ብለናል ለቡናማ ማን ብሎን.......:-)

ቡና ጠጡ

በጣሙን ሲማርክ ወለል ጨፌ ለብሶ:
ለምለም አርንጓዴ እሳር ተነስንሶ::

ጎርቤት ቤተስብ ሁሉ ይጠራና:
መቁያ ላይ ሲፈስ ታጥቦ ጥሬ ቡና::

ቤቱ ሰው ሲሞላ ሲታይ ሽር ጉድ:
ሢቆላ ቡና ሲንጣጣ ፈንድሻው:
አብሮ ተጓዥ ህይወት የአገር ትዝታው::

ከእጅ ሲወጣነው የሚታወቅ ጣዕሙ:
እንደምን ዎላችሁ ሲል አልፎ ሂያጅ ሁሉ:
ቡና እየፈላነው ኑ አሪሂቡ ይላሉ::

በደስታ ይገባና አቦል ቡና ቀምሶ:
መርቆ ይወጣል ፈገግታ ተላብሶ::

ትንሽ ቅሬታም ቢኖረው ጎረቤት:
ቶሎ ይፈታዋል ቡና በመጣጣት::

ሰው ተፈቃቅዶ ሳይለየው ጎረቤት:
የሚኖሩባትን ባህለ ክብርት:
ቆሞ እየሄደ እያሉ ማጣት:
እንዴት ይናፍቃል ቆይቶ ሲያዩት:
በውጭ ሲኮስስ ዛሬ ይህ ህይወት:
እንዴው ይቅር እንጅ ቡና መጠራራት:
እንደምን ይሆናል ባህልን መዘንጋት::

ሲታመሙ መጠይቅ መካፈል በደስታው:
ምክርን መለገስ አቅም በፈቀደው:
በቀና ከሆነ ይበልጣል ከቡናው::


በሉ ቸር ይግጠመን
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ጆሮ ዳባ

Postby ወልዲያ » Wed Jul 09, 2008 1:43 pm

ሠላም ወረኢሉ!

ቡና ለመጠጣት ብቅ እላለሁ ብዬ:
ኮረዳ አይቼ - እየተከተልኩኝ - ገባሁኝ ጎብዬ:
መመለሴ አይቀርም አምባሰል ማርዬ::

አቦል ጀባ - ጤና ጀባ - እያልን ቡና እንዳልጠጣን:
አብረን ተነጋግረን ችግር እንዳልፈታን:
ምነው ጆሮ ዳባ እኛ እንላለን::
Image
ኃይቅ ዳር ነው ቤቴ አሣ አበላሻለሁ:
ወደ አበት እንውጣ ማር አቀምስሻለሁ:
አንቀጽ 17 ውጫሌ እሮቢት እኔ አሳይሻለሁ:
ጊሼን ማርያም እንሂድ ቅኔ አስቃኝሻለሁ:
ጃማ ሥንዴ በዝቶ ወረኢሉ እላለሁ::


ፍቅር የአንድነት ምልክት ነው
ወልዲያ - የጁ



ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

ወሎ ገራገሩ

Postby ወረኢሉ » Wed Jul 09, 2008 2:03 pm

ሰላም ወልዲያ ምን ይደረግ ቆንጆ ሀገር ገብተህ ነው ኮረዳ ተከትለህ የሄድከው:-

መጣች የወሎ ስጅ እንዳረግ ተመዛ:
ሳይበሉ የሚጠግብ ትዝታዎን ይዛ::


ተብሎ የለ ትዝታ እንዳይሆን ይዞህ የተጓዘው ምን ይደረግ ሀገራችን በጉብሎች ማራኪ ናት የቆንጆ ሳቅ ፈገግታ የሚስነቅባት የጥንቷ ላኮመልዛ የዛሬዋ ወሎ ጥንቅሽና ሽንኮራ ደጋሊትና ዘንጋዳ የሚቆርጥባት ገብስናስንዴ የሚፍስባት ማኛ ስርገኛ የሚታጨድባት የሚወቃባት የባቄላ የምስር እሽት የሚፈልፈልባት ብርቱካንና መንደሪን የሚበቅልባት ዘይቶን ከሎሚ የሚያፈራባት ትርጎና ሙዝ የሚገመጥባት ጥንቅሽና ሽንኮራ የሚመጠጥባት ፓፓያ ለውዝ ማንጎና ጥጥ የሚለቀምባት አሣ የሚረባባት ከመሆኗም ሌላ::

ከገበሬው ጋራ ምርቱ እንዲያ ሲያምር:
የጎበዞች ሀገር ወሎ እንዴት ይቅር::


ተብሎ የተዜመላት ናት::

ወሎ በሎጋ ሀይቅ ደሴቷ በጃሪ ፍልውሀዋ በደንቆሮ ዋሻ በግሽን ማሪያም አጣብቂኝነቷ በግማደ መስቀሉ መቀመጫነቷ በላሊበላ ፍልፍል ህንጻዋ በታሪካዊ ሥራዋና ቅርሳቅርሷ ዕውቅና ሲኖራት በንግግር ዘየዋ በህዝቧ የዋህነት በሌማት እንጅራ በፎሌ ጠላ በአንኮላ ወትት ለጋሽነቷም ትታወቃልች:: ወሎ ገብሱ በሚስኝው ህዝቧ ጭምር ብዙ ትዝታ አለ እረ ስንቱ አሪሂቡ ብላ መጋበዝንም መተባብርንም የሚያውቅ ህዝብ ያተርፈች ናት::

በናቷም ባባቷም ወረሂመኖ ናት:
እንደ በልጅግ ጥይት ትመታለች አናት::

አረጎ አፋፉ ላይ ያገኘናት ልጅ:
በጅ አትንኩኝ አለች በከንፈር ነው እንጅ::

ባቄላ ምርቱ እንጅ አያምርም ክምሩ:
ይምጣ የወሎ ልጅ ከነምንሽሩ::


የተባለላት ናት::

ጎበዝና ጎበዝንም ዱላ ማናሳት ታቅበታለች:: በጅግና ሞት በኔና ባንች ሞት አዘካሪ ኧኽይ ወለሌዋም::

ተው ስደድልኝ የጅህን ሎሚ
በሽተኛ ነኝ ልቤን ታማሚ::

ለሎሚው ነው ውይ ለምቧዩ ፍሬ:
ስው ለወደደው ይስጣል በሬ::


ትልዋለች::

ወንዱም :-

አቧራ በሚያምስ ልብን በሚያፈርስ ድልቂያ

አይዘለዘልም ይጅብ ኩላሊት:
እስቲ አንክስ አንድ ጊዜ የፊት የሗሊት::

በጊቱን ጅብ በላት እረኛው ወስልቶ:
ዘልቆ ለወሎ ልጅ የሚነግር ጠፍቶ::

የመዋጣ ዱላ አልፎ አልፎ ጅንፎ አለው:
እንዲያውም ተንኮልን እየመቱበት ነው::

ማማው ደብረታቦር ደጋሊቱ የጁ:
ወንጭፋ አጠረና ወፎች እህል ፈጁ::

አንወሻሽና እውነት እንናገር:
አይደለም ወይ ወሎ የነስኂን ሀገር::


በል ወልድያ ብዙ አስባልከኝ የወሎ ትዝታ መች ያልቃል በ ብዙ ቦታ ያስገባል እንኳን ጎብየ::

በሌላ ትዝታ እስከምንገናኝ መልካም ቆይታ::


ከወሎ ገራገሩ
ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ትዝታ

Postby ወልዲያ » Wed Jul 09, 2008 5:36 pm

ሠላም ወረኢሉ!


ትዝታ

Image

ወሎን አስቃኘሽኝ ጊሸን ላል-ይበላ:
ቴዎድሮስ ዬት አል ታላቋ መቅደላ::

የጎብዬ ጉብል ልቤን ወስዳ ወስዳ:
አስቀምጠዋለች በክብር ከጓዳ::

አንቺ ሓበሻ ልጅ ነይ እና አጫውችኝ:
ሁሉም ነገር ያምራል እንቢ አሻፈረኝ::

**************************
የወንዜ ቡቃያ [ፀሃይ ደበበ]
http://www.youtube.com/watch?v=y7PmXKaubs4
እኔ እና የጎብዬዋ ኮረዳ ስንጨፍር----:-)
**************************

መርጦ አፋፉ ላይ ውድበን ውድበን:
መቻሬ አምባቸው ሙጋድ ጥላሁን:
ቲንፋዝ መሰለ እንዬው ተሻግረን:
ኧረ ስንቱ ስንቱ ጠፋ ደረጃችን:
ሜጤሮ እንጓዝ ሙሉ ጌታችን::

ልቤ ሾልካ ልትሄድ ዱብ ዱብ አለች:
አማራ ሳይንት ላይ ደርሳ ሰፈረች::

አቀበቱን ልውጣ እኔ አይደክመኝም:
አንቺም ተከተዪኝ አላማጣ ኮረም::

ወይራው ጠጅ ቤት መጣብኝ ትዝታ:
ጦሳ ዳውዶ ብዬ እንደዚህ ስረታ:
መቼ የረሳኛል ዋድላ እና ደላንታ::


አምባሰል ባቲ አንቺ ሆዬ ትዝታ
ወልዲያ - የጁ

ወልዲያ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 679
Joined: Tue Apr 17, 2007 11:55 am
Location: የጁ - ወሎ

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 2 guests