ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)" href="http://www.cyberethiopia.com/warka14/feed.php?f=2&t=23129" />

ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ወረኢሉ » Thu Sep 29, 2011 11:26 am


ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚወች እንኳን አደረሳጩ ለመስቀል በአል !!! እስኪ ትንሽ ለመዝናናት አንድግጥምለበል እነሆጀባብያለሁ ::


ፍቅር እሹሩሩ!!!


ከንፈሩን ስቀምሰው አልጠገብ ያለኝ
አንገቱን ሳሸተው ሽጭራሹን ባሰብኝ
ደረቱን ስዳብስ ልኔን እያራደው
የሴትነት ወጌን መቀነጠን ፈታው
አይቸው አልጠግብ ዓይኑ ያባብላል
እርቄውም አልሔድ ልቤ በሱ ቆርቧል

ለላም አያገኘዉ ሰውም አይንካብኝ
ሽሽግ ነው መውደዴ ያይን ራባለብኝ
እግሮቹን አይና እጆቹን አይና
ይሽፍታል ልቤ በፍቅሩ ገመና
ጨዋታውን ያየ ፍቅሩን የቀመስ
ያስታል መነኩሴ እንኳን ያፈረሰ

እንደኔ እቅፍ አርጎ ስሞ ለቀመሰው
የስጋ ምናኔ የመንፈስ ፈውስ ነው
የጨዋታው ለዛ ልብን ያማልላል
ያዙኝ ልቀቁኝ ሲልወኔው ያስረግዳል
ጓዳውም አይጠቅመው ሳሎኑም አይበቃው
መደቡም አልጋውም ለሱ ፈረሱ ነው

ቀኑ አልበቃ እያለው ሌሊት ይደግመኛል
እንደ እህል ውሀው እሱንያሰኘኛል
ጉንበስ ቀና ሲያስብል ልብን ያሸፍታል
እንኳን የሴት ወገብ የወንድ ትጥቅ ይፈታል
ፍቅሩ ታቦት ህፕንፕኝ ስርክ እያሰገደኝ
እንኳንስ ጨዋታው እንቅልፉም ናፈቀኝ

አፉም አይጠገብ ጭዋታው ለዛ አለው
ሲራመድ ያሳሳል የልብ መስታወት ነው
ያንጀት ፍቅፋቂ እሱ ነው ስስቴ
የሚያርበተብተኝ ጠፍቶሴትነቴ
አይቀምስ ሰራስር ጠበል አያስረጩት
በቀን በሌሊቱ ልብን የሚያሸብር
ምንድነው ሚሰጥሩ የህፃን ልጅ ፍቅር::


መልካም ንባብ

ወረኢሉ

ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Fri Oct 21, 2011 12:06 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ ሰላምታየ ይድረሳችሁ :- ሰላም ሶረኔ እንዴት ነሽ አለሽ ወይ ጠፋሽ በሰላም ነዉ? ፋጤ የጀመረችውን ሳትጨርስ ጠፋች የሷ ነገር እስኪ ቂመሀው ሲደራ ብቅ ትል ይሆናል ቅዥቢው እንዳለው በመርቃና ትጨርሰው ይሆናል::

እስኪ ካነበብኩት አንድ ልበላችሁ ሰለወሎ ታሪክ ፀሐፊው እንደጻፉት አስቀምጣለሁ :-

የወሎ እስልምና እውነተኛው ታሪክስ እንዲህ ነዉ:-

የእስላሞች መጀመሪያ ነብይና ንጉሥ የመሐመድን ልጁን የፋጢማ ባል አሊን አብደርህማን የሚባል ገደለው:: የሱ ልጅ ከፋጢማ የተወለደው ሐሰን ነግሦ ነበርና በኌላም የሚነግሱ የመሃመድ የፋጢማ የዓሊ ልጆች ናቸውና የአብድ ረህማን ልጆችና ወገኖች ሁሉ የዓሊን ደም ተበቅለው ይፈጁናል ሲሉ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከሸዋ በይፋት ተቀመጡ:: ይህም የሆነ በንጉሥ ድግና ሚካኤል ዘመን ነው::

ድግና ሚካኤል ከ656 እስከ682 ዓ.ም 26 ዓመት ነገሰ በሱ ዘመን ውስጥ እኒህ እስላሞች በስፋት ገቡ:: በዚያ ዘመን የነበሩ ተከታትለው የነገሱ ነገሥታትና መኳንንት ካህናትም በስፍናቸው ዝም ብለዋቸዋልና ብዙ ገንዘብ እየሰጡ በማታለል የነገሥታቱን የመኳንንቱን ልብ አብርደው እኒህ እስላሞች ቀስ ቀስ እያሉ በሸዋ ዳር ለዳር በልዩ አምባ ባርጎባ እስከ ወሎ አገር እያስተማሩ ሰው ሰራሽ ሃይማኖታቸውን ዘረጉና አስፉ:: ብዙ ያልተማረ ሕዝብን አሰለሙ::

ወሎም በነበረበት ከኒህ እስላሞች ጋራ ተገናኝቶ የእሰላምን ሃይማኖት መሰማት ጀመረ:: ከዚህም ቦሀላ ከኒህ እስላሞች ከሉ የሚባል ሽህ መጥቶ አስተማረውና ከወንድሞቹ ተለይቶ እሱ ካስለመም የእስላም ወገን እየበረታ ሄደ:: ባጼ ዓምደ ጽዮን ደክሞ የነበረ እንደ ገና እየተነሳ አስቸገረ: ሰለ ዚህም ወገነ ኦሮሞ ባንድ ወገን: እስላም: እየተነሳ ቢያስቸግራቸው ጋላን ብቻ ለማጥቃት እኒህ ከይፋትና ከወሎ እስላሞች ለመታረቅ ንጉሥና መኳንንቱ ካህናቱም ተሰብሰበው ባንድ ሆነው መከሩ መክረውም አልቀሩ ከእስላሞች ጋራ ታረቁ::

ዕርቃቸውም ለንጉሥ ሊታዘዙና ሊገብሩ በሃይማኖታቸው ሊኖሩ በየህዝባቸው በያገራቸው ሊሾሙ ባገራቸው ውስጥ ያለ ክርስቲያንን እንዳይበድሉ ቤተ ከርስቲያንም ሊጠብቁ እንጂ ላያቃጥሉ በዚህ ውል ክርስቲያኖች በወንጌል እስላሞች በቁርዓን ተማምለው ውል ሳያፈርሱ በፍቅር ሊኖሩ ታረቁ::

ሰለዚህ በይፋት ባርጎባ ባሉ እስላሞች አለቃ ወይም ገዥ ተብሎ ወላስማ ተብሎ ከወገናቸው ተሾመ:: ለወሎም ንጉሥ ሰጥቶት ከዋየት ወዲህ ያለን አገር ያዘና ግዛቱ ርስቱም አደረገ የዚያ አገር ሰም ጥንት ላኮ መልዛ ነበር:: ወሎ ከያዘው ወዲህ በሰሙ ወሎ ብሎ ተጠራ:: ይህ የሆነው በሺ363 ዓመተ ምህረት ነው::

ወሎም ገና በሕይወቱ ሳለ አገሩን ለ 7ቱ ልጆቹ አካፍሎ ሰጣቸው አገራቸውም በየስማቸው ተጠራ::

1- የሂመኖ ወረሂመኖ ተባለ
2- የቃሉ ወረቃሉ ተባለ ወረ ማለት አገር ወይም መንደር ማለት ነዉ
3- የአበይ አበይ ቤት
4- የዓሊ ዓሊ ቤት
5- የአምቦ ለገ አቦ
6- የሄዳ ለገ ሄዳ
7- የጎራ ለገ ጎራ ተባለ:: ለገ ወይም ለጋ ማለት መልካም ማለት ነዉ ሰለዚህም አገሩ በጥቅሉ ወሎ 7 ቤት ወሎ ይባላል::

የወሎ እዉነተኛ ታሪክ ይህ ነው የጋኔን ክታብ ተቀበለ አረርጌ ወርዶ የእስላም ክታብ ተማረ: ግራኝ ሲመጣ አብሮ መጣ ማለት ግን ፍጹም ሐስት እንደሆነ በታሪኩ አለመስማማትና በነገሩ ሁሉ ይታያል::

ወሎ ማነዉ ?
ከየት መጣ ?
ከትኛው ነገድ ነዉ ? እንዴት ወደ ላኮመልዛ ሄደ የሚለውን በሚቀጥለው እናያለም መልካም ነባብ ይሁንላችሁ::

>>>>> ታሪክን መዳሰስ <<<<<<<<< ይቀጥላል :.

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Sun Oct 23, 2011 12:14 am

ሰላም ለዚህ ቤት ታሪክን መዳሰስ የሚለዉን ከዚህ በታች ይቀጥላል:-

ሰለ ነገደ ኦሮሞ :-

ሰለ ነገደ ኦሮሞ የሚነገር ቁም ነገርና እውነት እውነተና ተረት የሆነ በየ አይነቱ ብዙ ልዩ ልዩ ታሪክ አለ __ አቶ አጽሜ በጻፉት የታሪክ መጽሐፍ ሰለ ኦሮሞ ሲናገር እንዲህ ይላል ኦሮሞ የሚሉት ህዝብ ካገሩ የወጣበት ምክያት እጅግ አይታወቅም:: ባለታሪኮች እነዚህ የጋላ ሕዝብ ከእስያ ፈልሰው ወደ ማድጋስካር እንደተሻገሩ : ከዚያም ፈልሰው ቦባሳ አጠገብ ከባህር ወደብ ተቀመጡ:: ቦባሳ ማለት ለከብትም ቢሆን መሰማሪያ ማለት ነው:: በጋለኛ:: ከዚያም ገናሌ የሚባለውን ጅረት ተከትለው ኢትዮጵያ ወጡ ይላል::

ካገራቸው ሲወጡ ግን ሁሉ ባንድ ጊዜ አልወጡም: የወደደ ወጣ ያልወደደ ቀረ እንጅ ይህ ኦሮሞ የተባለ ሕዝብ ከዚያ ተነሰቶ መጣና በባሌ ዳር ገላና በሚሉት ጅረት(ወንዝ) ዳርቻ ተቀመጠ:: ላሙንና ፍየሉን በጉን እያረባ እንደ ዘላን ሁኖ ኖረ::

ከመጣም ካፄ ልብነ ድንግል ስመ መንግሥታቸው ወናግ ሰገድ ከሳቸው መንግሥት በፊት 102 ዓመት ሁኖት ነበር:: ይህም አፄ ይስሐቅ በነገሡ በ 5 ዓመት በ6 ሺህ 904ዓ.ዓ በ1404 ዓ.ምህረት ነው የሚሉ አሉ:: እውነተኛው ግብ የጋሎች ወደ ኢትዮጵያ መውጣት በዛጎየ(መራ ተክለ ሃይማኖት ስመ መንግሥቱዛጎየ) መንግስት 10 አመት በ930 ዓ.ም ነው::

ፈረጆች ሰለ ኦሮሞ የጻፉት ታሪክ በራስ እውቀትና በመመርመር ነው:. እኛ ግን አዛዥ ጢኖ ዘጻፈውን ታሪክ አዝተን ነው ጋሎች ሲመጡ በጋላኔ ወንዝ (ጅረት) ወጥተው ሐሮ ውላቦ በሚባል አገር ገቡ:: በሐሮ ውላቦ ዋናተኛ በዋና የሚቆርጣትና የሚሻገራት ትንሽ ኩሬ ባሕር አለች:: ጋሎች አባታችንና ፍጥረታችን ከዚህ ውሃ ወጣ ይላሉ:. ሰለዚህም ኡማን ውላቦ ባቲ ይላሉ:. ይህም ከውላቦ ውሃ ፍጥረት ወጣ ማለት ነው:: ሰለዚህ ጋሎች ለውሃ ይሰግዳሉ:. ሰውም እንሰሳም ከዚያች ውሃ አይጠጣም:: ከልክል ነው:: ኦሮሞ ሁሉ ከዚያ ለውሃይቱ ይሰግዳል:. ከዚያም ስንጋና ብዙ ፍሪዳ ብግም ፍየለም ያርዳሉ::

በሐሮ ውላቡ ልዩ ልዩ ቛንቛ ያላቸው ጥቄት ህዝቦች አሉ ዶራስ ይባላሉ የጋላን ህዝብ ይመስላሉ ከሲዳሞ እስከ ውላቡ 4 ቀን ከውላቡ እስከ ቦረን 5 ቀን ያስኬዳል::

ጋሎች 2 ነገድ ናቸው : በርቱማና ቦረና ይባላሉ:.
በርቱማ 6 ልጆችን ወለደ:. እነርሳቸውም እኒህ ናቸው ::

1- ከረዩ
2- መረዋ
3- ኢቱ
4- አክቱ
5- ወረንሽ
6- ሁበና

የበረቱማ የበኩር ልጁ: ከረዩ 6 ልጆች ሀይለኞች ወለደ:. እነርሳቸውም:-

1- ሊበን
2- ትሎማ: ወሎ
3- ጁሌ
4- አቦ
5- ሉባ
6- ዐለስ ናቸው::

ወሎ ከ 7 ሴቶች 7 ወለደ
1- ሂበኖ
2- ዐበይ
3- አሊ
4- ቃሉ
5- አምቦ
6- ሂዳ
7- ጎራ ናቸው::

ከዚህ ሌላ ደግሞ ለወሎ በኮ ኖሊኢኑ የሚባሉ የልጆች አሉ የሚሉ አሉ ቦረና 11 ልጆች ወለደ::

1- ዳጨ
2- ጅሌ
3- ኮኖ
4- ቦቾ
5- አካኮ
6- ወቦ
7- ሉባ
8- ጭሌ
9- ሊቦን
10-ሆኮ ናቸው::

ከወሎ ልጆች 3ቱ ፊተኖች በወሎ ሰም ይጠራሉ 4ቱ በወርሰደቻ ሰም ይጠራሉ ይባላል::

መረዋ የበረቱማ ሁለተኛ ልጁ ወረያንን ወለደ
ወረድያም 3 ልጆችን ወለደ እነርሳቸውም:-

1- አና
2- ኡር
3- አበጢን ናቸው::

እኒህ የመረዋ ልጅች በሀይልና በብዛት ከሁሉ የበልጣሉ::

ይህም የጋላ ሕዝብ አረማዊ ሕዝብ ነውና እግዚአብሄርን አያውቅም:. እግዚያብሄር ለሙሴ ጽፎ ከሰጠው ካ10ቱ ቃላት ለጋላ የጐደለው መጀመሪያ ትእዛዝ ያንተ አምላክ እኔ ነኝ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ያለው ብቻ ዋና ነገሩ ነው:: ከባህርይ ህግ ጎዶሎነት የሚያስተምረው ሀዋሪያ ሰላጣ ሁሉን ይፈራልና ዛሩንም ወንዙንም ጋህሩንም ድንጊያውንም ስንበተ ጉዳ ቅዳሜን ስንበተ ጢና እያለ እንደ ክርስቲያን ያከብራል::

ሶስተኛው መንም ቢሆን በሀሰት ይምልም::
አራተጛው አባት እናቱን አክብሮ በእድሜ የበለጠውንም ባልጀራውን ያከብራል:: አለዚያ በጨፌ ማለት በሽንጎ ጉባኤ ይፈረድበታል::

አምስተኛ ነፍስ የገደለ በጉማ የንፍስ ዋጋ በመክፈል በጅግ ብዙ ገንዘብ ይቀጣል:: ደግሞ ነገሩ ታይቶ በአዩ በሉባ ተፈርዶበትም የሚሞትም አለ::

ሰድስተኛ ምንዝር በጨፌያቸው ወይም በችሎታቸው ከክርስቲያኖች ይልቅ እነሱ መልካም ይፈርዳሉ::

መልካም ነባብ ይሁንላችሁ::

>>>>> ታሪክን መዳሰስ ይቀጥላል <<<<<<

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ታሪክና ተረት ተረት...

Postby ቅዥቢው » Sun Oct 23, 2011 12:33 am

"የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ"ይሉ ነበር የኔታ አጥሬ::
ማነ ነሽ ወደ አሜሪካን ሃገር በሚስትነት ያስመጣሽ ያ ጎባጣ መላጣ ሾጣጣ ሽማግሌ ኦሮሞ ባልሽ ታሪክና ተረት ተረት እንደሚለያዩ አልነገረሽም እንዴ?የአለቃ ታዬን የተረት መጽሐፍ አንብበሽ ልብሽ ዉልቅ ብሏል ልበ ቢስ ጥፍጥፍ አምሳ ሳንቲም ፊት...
ስሚ እስልምና ታዬ እንደ ቃዠው ሳይሆን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን ቀይ ባህርና አካባቢውን አላለፈም::ቤተ-ኣምሓራ(ወሎ)ክርስትናንና እስልምናን ባጭር ጊዜ ልዩነት በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ነው የተቀበለችው::የማኽዙማይት ስርወ-መንግስትም የሸዋ እስላማዊ መንግሥትን የመሰረተው በዚሁ ክፍለ ዘመን የመጨረሻ ዓመታት ነበር::በነገራችን ላይ ሸዋ 'ሚለው ስያሜ ዓረብኛ 'ንጅ ኣምሓርኛ አይደለም::ታዬ እንደዘላበደው ሳይሆን ነገደ ኦሮሞ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በምድረ-ሐበሻ አልነበረም::ይህንንም ታዬ ራሱ በብዕሩ ዘግቦታል::
ላኮና መልዛ በዛሬው ወረሂመኖ ልዩ ስሙ ወሎ ተብሎ በሚጠራው የገጠር ቀበሌ ዉስጥ 'ሚገኙ ሁለት ኩታ ገጠም ቦታዎች ስያሜ ነው::
አንች ቆረቆንዳ ራስ የታዬን ቅዠት ታሪክ ብለሽ ዋርካችንን ከማቆሸሽሽ በፊት ራስሽን ቤተ-ኣምሓራ(ወሎ)ጓ-ምድር(ወረ-ኢሉና ወረ ሂመኖ)ጭቃ በረት(ቃሉ)ቤተ-ሰላም(ባቲ)ቤተ-ሳባ(ወረ-ባቦ)ገነት(ወልዲያ)ወይራ አምባ(ኮምቦልቻ)ኅሙሲት(ከሚሴ)ወዘተ ለምን በማን እንዴትና መቼ ተባሉ ብለሽ አዋቂዎችን ጠይቂ ጠያቂ ያሳጣሽና...
ለግንዛቤ ይሆንሽ ዘንድ በዘጠነኛውና አስረኛው ክፍለ ዘመን ሐበሽስታንን በጎበኙ ዓረብ ጸሐፍት የተጻፉ እንደ "አል-ታሪህ አል-ሐበሽያ"እና "ታሪህ አል-ኢስላም ፊ ቢላድ አል-ሐበሺያ"ን መስል የጉዞ ማስታወሻዎችን ፈልገሽ አስተርጉመሽ አንብቢ::ቢያንስ ስለ መልከአ ምድራዊ ስያሜዎች ጥሩ መረጃ ታገኛለሽ::የግራኝ ዜና መዋዕል ዘጋቢ(Chronicler of Gragn) ሸሐበዲን ቢን ዓብደል አዚዝ የጻፈውን "ፉቱህ አል-ሐበሺያ"ን ብታነቢ ታዬ ምን ያክል እንደ ቃዥ ትረጃለሽ::
በተረፈ 'ሚከተሉትን መጽሓፍት እንድታነቢ ፈርጀብሻለሁ...
Alvarez, Francisco The Prester John of the Indies translated by C.F. Beckingham and G.W.B. Huntingford Cambridge: Hakluyt Society, 1961.
Anfray,Francis.Les anciens ethiopiens. Paris: Armand Colin, 1991.
Beckingham,C.F. & Huntingford,G.W.B. Some Records of Ethiopia 1593-1646 Being Extracts from the History of High Ethiopia or Abassia by Manoel de Almeida Together With Bahrey's History of the Galla.London:Hakluyt Society,1961.
Lobo, Father Jerome. A Voyage to Abyssinia. Translated by Samuel Johnson. London: Elliot and Kay, 1789.
Lockhart, Donald M.trans. The Itinerário of Jerónimo Lobo. London: Hakluyt Society, 1984.
Ludolphus,Hio,New History of Ethiopia.London:Samuel Smith,1684.
Whiteway, Richard Stephen. The Portuguese expedition to Abyssinia in 1541-1543 as narrated by Castanhoso.London:Hakluyt Society,1902.
ወደ ቤንጋዚ እየተጓዝኩ ነው የቀረ ስድብ ካለ ከቤንጋዚ መልስ አዘንብብሻለሁ...
ፕሮፌሰር ዶ/ር ቅዥቢው ዘ-ብሔረ ኣምሓራ
ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:57 pm

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Sun Oct 23, 2011 9:58 am

ሰላም ቀዥቢው አመስግናለሁ ሰለሁሉ እንዳነባቸዉ የጻፉልኝን መጸሀፍ እስኪ ርሶ መለስ ብለዉ ያንብቡት እኔረስዋ ካሉት ቦታ ሳይሆን የአባ ባርይ ድርሰቶች በፕሮፌሰር ጌታቸው ሐይሌ በጻፉት መጸሀፍ ላይ ነዉ ያነበብኩት :: መሳደብው ግን የርስዎን ማነነት ይገልፃል በርቱ::
ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ታሪክና ተረተረት...

Postby ቅዥቢው » Sun Oct 23, 2011 4:25 pm

አንች ረገምሽኝ እንዴ?በጧቱ ከመኪና አደጋ ለትንሽ ነው የተረፍኩት::
የጋሼ ጌታቸውን መጽሐፍ ማንበብሽን በመስማቴ ተደስቻለሁ::መጽሐፉ ገበያ ላይ ሲውል አሜሪካን አገር ነበርኩ::ፊርማው ያረፈበትን ኮፒ ወዲያው ነበር አፈፍ ያደርግኩት::ምን ያደርጋል ብዙም ሳልቆይ ለደህነንት አስጊ ግለሰብ ብለው አሜሪካኖች እጅና እግሬን እንደ ደላንታ በግ ጥፍር አርገው አስረው ከአትላንታ ወደ ሊብያ ሚሱራታ ወረወሩኝ::በወቅቱ በሊብያ ፓስፖርት ነበርና 'ምንቀሳቀሰው::
ለማንኛውም የጋሼ ጌታቸውን መጽሐፍ በደምብ አንብቢው::አስተውለሽ ከሆነ አንች ዋራካ ላይ ያሰፈርሻቸውን የመጽሐፉን ክፍሎች ከአለቃ ታዬ መጽሐፍ ላይ የተወሰዱ መሆናቸው በግልጽ ተቀምጧል::ለመጽሐፉ እንደ መግቢያ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት የጻፉትን ደግመሽ አንብቢው::"ኦሮሞ ወይስ ኦሮሞ" 'ሚለውን ክፍል ዋርካ ላይ ዱቅ ብታደርጊው ታሪክ አስተማርሽ ብቻ ሳይሆን ታሪክ ሰራሽ ያሰኝሻል::በነካካ እጅሽ የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን "ታሪክና ተረተረት" 'ምትለዋን ጦማር ፈልገሽ አንብቢ::
በይ አፉ በይኝ እኔ የቅሬያችን አባል የነበረ ሙዓመር አል-ቓዛፊ የተሰኘ ደግ ሰው ሞተ ብለው አርድተውኝ ለቅሶ ልደርስ ወደ ሊብያ እየተጓዝኩ ነው ስመለስ በሰፊው እንገናኛለን...
ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:57 pm

Postby guest11 » Sun Oct 23, 2011 9:07 pm

[img]
guest11
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 27
Joined: Mon Sep 12, 2011 9:59 am

ታሪክን መዳሰስ

Postby ወረኢሉ » Sun Oct 23, 2011 10:47 pm

ሰላም ቅዥቢው እንኳን እግዚያብሄር ከአደጋ አዳነህ እኔ እንኳን እርግማን አላውቅም መባረክ ከሚያውቁበት መድር ሰለተወለድኩ አመስገንኩህ እንጅ ለላ መንም አላልኩም ለሰጠህኝ አስተያየት አሁን አመሰግናለሁ ያልከኝንም ለማስቀመጥ እሞክራለሁ:: እንዳልከዉ ፕሮፌሰር ጌታቸውም ያሰፈሩት ከ አለቃ ታየ ትልቁ መጸሀፍ ወስደዉ ነዉ እነም ከመጨረሻ ያለዉን ያስቀደምኩት ሰለ ወሎ የሚያወራ ነገር ሰላነበብኩ እዉነታው ምን ያህል ነዉ የሚል ጥያቄ ሰለፈጠረብኝ ነዉ:: ይሄው በጻፌ ካንተ ብዙ ነገር አገኝሁ እንዲሁም ሌሎችም የሚሉት ያነበብቱ ይኖራል ብየ ነዉ እዉነታው ይሄ ነው ወይም አይደለም የሚል ድምዳሜ ይዥ አይደለም ::

በል ከለቅሶው ሰትመለስ እንዴ እንደነበር ታወራናለህ እኛም ያው የሀዘኑን መቀመጫ መከዳዋን አነጣጥፈን ዙርባ ጋሌሳውን አዘጋጅተን እንጠብቃለን ሀዘኑን ቀሊል ያደርግልህ ላንተና ለመሰሎቻችሁ:: አፉ ብያለሁ መልካም ጊዜ ይሁንልህ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ታሪክን መዳሰስ

Postby ወረኢሉ » Tue Oct 25, 2011 11:27 pm

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ ሰላምታዬ ይደረሳችሁ::

ካለፈዉ የሚከጥል:-

እነዚህም የበርቱማና የቦረን ልጆች የጋላ ነገድ ሁሉ ከህጻነነት ጅምሮ እስከሽምግልና እንደ ክህነት ያለ መዓርጋቸው ገዳ ይባላል:: ገዳ ማለት እንደ ክህንነት ያለ ሹመት ሥልጣንም ነው:: ይኸውም ሥልጣናቸው እንደ ዘመናቸው ቁጥር ለ8 ለ8 ዓመት ይከፈላል:. ገዳ ይሉታል::

በ8 ዓመት የሚከፍሉትም በ5 ሉቦች ስም እንደተጠራ 5 ናቸው በ8 በ8 ዓመት አንድ ሉባ ተሽሮ ሌላው ሉባ ሲሾም እንደ ሌላው ህዝብ ንጉሥ ባላባትም ጌታች የለባቸውም እስከ 8 ዓመት ለሉባ ይታዘዛሉ ከ8 ዓመት ቦሀላ ሌላ ይሾማል የዚያ ጊዜ ለየነገዳቸው ነገሩ እንደኛ ይመሰላል:: እኛ ዓመት በእየ ወንጌላዊ ሰም 1- ማቴዎስ: 2-ማርቆስ 3-ሉቃስ: 4-ዮሀንስ: ለ4 ዓመታት ሰም እንደምንሰጣቸው እነሱም በ8 ዓመት እንድ ስም ይስጣሉ 40ውን ዘመን በ5 አርበኞች ሰም ይጠራሉ 40ውን ዘመን ሲጨርስ ተገዝሮ ሉባ ይሆናል::

ይህም 40ው ዘመን ከ5 የሚከፍል ያ5 አርበኛች ስም የሚጠራበት እኒህ ናቸው መጀመሪያው ገዳ ቢርመርጂ ነው ሁለተኛው ሆረታ ወይም ሚልባህ ሶስተኛው ምንችሌ ወይም ሙደና አራተኛው ዱሎ:አምስተኛው ሮበሊ ይባላሉ:: እነዚህ የጋላ ህዝብ ሥራት አባ ዱሎች በ40 በ40 ዘመን ይመላለሳሉ:: የጋላ ታላቁ ሕግ ይህ ነው::-------------

--------------------------------------------------
ጋሎች በሴት ቅናትና መጋደል ይቅር ብለው ህግ የሰሩበት ምክንያት:-

በወሎ በፊት ገና ሳያስልሙ አንድ ጅግና ጎበዝ ባገራቸው ነበረ: መልካም ቆንጆ ምሽት ነበረችው:: አንድ የጨዋ ልጅ መልከ መልካም ገና ከሴት ያልደረስ ጐበዝ በጎረቤት ነበረ:. የዚህ ጅግና ምሽት በዚህ ጐበዝ ፍቅር ተነድፉ ነፍስ አልቀረባትም ዘወትርም ለምኝታ ትመኘው ነበረች:: ከዕለታት አንድ ቀን በተመቸ ቦታ አገኘችው ፈቃድዋንም ለመፈጸም ያዘችው በጋላ ሥርዓት ያልገደል ሰው ከሴት አይደርስም ነበረ ይልቁንም ከጉልማሳ ምሽት ምንም አይቀርብም ነበረ::

ሰለዚህ እንዲህ አላት የተደረገ ነገር ሳይሰማ አይቀርምና እኔም ገና መራየን አላወጣሁምና ይህ ነገር ቢሰማ አንች ትነወሪያለሽ ባልሽንም ታስነውሪያለሽ ሰልዚህ አሁን አይሆንም በኍላ ግን ከዘመቻ ገድዬ በተመለስሁ ጊዜ በግልጥ ወዳጅ አደርግሻለሁ የጅግና የገሌ ምሽት ሆነሽ አሁን ከኔ መራዬን ካላወጣሁ ልጅ ጋራ ብትገኝ በኌላ ላንች ታላቅ ሃፍረትና ነውር ይሆንብሻል አላት::

እሷ ግን አንድ ጊዜ በክፉ ፍትወት ተነድፋ በሱ ፍቅር እሳት ልብዋ ተቃጥሏልና ይህማ ምን ችግሮህ እኔ አንዱን ልጄን በችሥጢር በንዲህ ያለ ስፍራ እስድልሀልሀለሁ እሱን ግደልና ሰልበህ እያዘፈንህ ና አለችው:: እሱ ገን አዬ ብትጠይኝ ነው እንጂ ይህስ መውደድም አይደለ የዚያን ጀግና ጐበዝ ልጅ ገድዬ በኌላ የትደረገ ነገር ሳይሰማ አይቀርምና ቢሰማ ይገለኛል እንኳን እኔን ከነዘር አዛኍርቴ ያጠፋኛል አላት:: እሷም ግድ የለህም ይህን ነገር ከኔና ካንተ በስትቀር ሌላ ማን ያውቀዋልና ብለህ ትጠራጠራለህና ትፈራለህ አለችው::

መልካም ነባብ : ታሪክን መዳሰስ ይቀጥላል::

<<<<<<<< ታሪክን መዳሰስ >>>>>>>

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

የተረሳ

Postby ወረኢሉ » Wed Aug 29, 2012 11:19 am

ሰላም ለዚህ ቤት !

የተረሳ ቤት የሚገርም ነዉ ሰዉ ሁሉ ጠፍቶ እስኪ ላጸዳዳዉ እና እመለሳለሁ ቁልፉ አለመጥፋቱ ነዉ ዋናዉ ነገር::

ወረኢሉ
ከጠፋችበት ተመልሳ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Re: የተረሳ

Postby ሳምራውው33 » Wed Sep 05, 2012 6:22 pm

ወረኢሉ wrote:ሰላም ለዚህ ቤት !

የተረሳ ቤት የሚገርም ነዉ ሰዉ ሁሉ ጠፍቶ እስኪ ላጸዳዳዉ እና እመለሳለሁ ቁልፉ አለመጥፋቱ ነዉ ዋናዉ ነገር::

ወረኢሉ
ከጠፋችበት ተመልሳ


ከዚህ በፊት ተጋብዛ ትሁን አትሁን አላውቅም ግን ለማንኛውም ይቺን ዘፈን ጀባ ብዬአልሁኝ ::

http://www.youtube.com/watch?v=2CupakYRQDg

እንደው ባጋጣሚ ወረኢሉ ሄጄ
ያቺን ሳዱላ ልጅ ባጋጣሚ አይቼ.....

ይሄንንም ዘፈን በጣም ነው የምወደው ግጥሙ ጠፋብኝ አንተ ጨርስልኝ ከቻልክ..
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

እንቁጣጣሽ

Postby ወረኢሉ » Fri Sep 07, 2012 11:12 pm

ሰላም ለቤቱ ታዳሚዎች በሙሉ እንደምን አላችሁ እንኳን ለ እንቁጣጣሽ አደረሳችሁ !!!

ሳምራውው እንኳን ደህና መጣህ ወደ ወሎ ገራገሩ ቤት አሪሂቡ ብለናል በጣም አመስግናለሁ ሰለጋበዝከን የባህል ሙዚቃ ጨርሽው ያልከኝን ገጥም በሌላ ጊዜ እሞክራለሁ :: ለዛሬ ገን አንድ ሰለ እንቁጣጣሽ ብየ ልውጣ:-

እንቁ - ለጣጣሽ !!

አንችማ ምን ተዳሽ: እኔው ልባክንልሽ
እኔው ልብ ገንልሽ: እኔው ልክሰርልሽ
አንችማ ምን ተዳሽ: ብዙ ነው አመልሽ
አይጣል ነው ፀባይሽ: የእጅ መንሻ ምስሽ::

አንችማ ምን ተዳሽ .:
ዘመን አያልቅብሽ: አያረጅ ጉልበትሽ:
አይነጥፍ ውበትሽ: አይደበዝዝ መልክሽ:
ስንት ተስፋ አጭረሽ: ስንት ወዳጅ አፍርተሽ
ስንቱን ነፍስ አጣፍተሽ: እንዲያም ሲል አቋድስሽ

አንችማ ምን ተዳሽ: ለጥቁሩም ቀን አለሽ:
ለነጩም ቀን አለሽ: ይግባኝ ስሚም የለሽ
ራስሽን ያነገስሽ: መብትሽን ያስከበርሽ
እኔው ነኝ ካዳሚሽ: እኔው ነኝ አረዳሽ::

ኑግ ልለጥልጥልሽ: ተልባ ልውቀጥልሽ
ቄጠማው ይጎዝጎዝ: ከሴም ይጣልልሽ
ቂጣውም ይጎዝጎዝ: ከሴም ይጣልልሽ
ቂጣውም ይጋገር :. ቡናም ይፈላልሽ
እኔው ልማፀንሽ: እኔው ላቆላምጥሽ
"" ያለ"" እኔ ማን አለሽ::

ፌጦ ነው ማርከሻሽ: ቂምሽን ማስረሻሽ
አምናን ላትደግሚብኝ: ዛሬ ልማፀንሽ
የዓመት መቀበያሽ: እንቁ ነው ለጣጣሽ::

www.youtube.com/watch?v=PA7H26ZCW5w

መልካም ነባባ መልካም እንቁጣጣሽ ይሁንላችሁ ለመላው ኢትዮጵያዊ ወገኖቸ ሁሉ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ወረኢሉ » Fri Nov 30, 2012 9:16 pm

ሰላም ወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች አማን ነዉ እንዴት ከረማችሁ ቤታችንን እስኪ ልጎብኘው ብየ ብቅ ብያለሁ:-

ዛሬ ለቅምሻ ያህል ልበል ብየ ነዉ የባህሪ አጥኒዎች እንደፃፉት::

ይሄን ያውቁ ነበር የራስዎን ባህሪ ፈልገው ያግኙ:-

ሰው በአጠቃላይ ከ አስተዳደጋዊ ና ፆታዊ ባህሪ ዉጭ በ ተፈጥሮ አራት(4) መሰረታዊ ባህሪዎች አሏቸው: ይህም ዘር ቋንቋ የትምህርት ደረጃ የማይለይ ነዉ:: እነዚህ ባህሪዎች የራሳቸው የሆነ ጠንካራ ባህሪ አላቸው ደካማም ባህሪ አላቸዉ በተለይ በትዳር አብሮ ሲኖሩና በጓደኝነት ዉስጥ ይገለጣሉ::

እነዚህ ተፈጥሯዊ ባህሪዎች:-

1- ሳንኩዊን

2- ሜሌኮሊ

3- ኮለሪክ

4- ፈለግ መቲክ

1- ሳንኩዊን ባህሪ ያላቸዉ ሰዎች ጥሩ ወይም ጠንካራ ጎናቸው:-

ባላቸው ነገር ይረካሉ : ሩህ ሩህ ናቸው : አዳዲስ ነገርን የማወቅ ጉጉት አላቸዉ : አዳዲስ እቅድን ያቅዳሉ ያሰቡት ወይም ያቀድት ይሳካላቸዋል::

ጥሩ ያልሆነ ወይም ደካማ ጎናቸዉ:-

ለውሳኔ ይቸኩላሉ ወይም ለማድረግ ችኩሎች ናቸው : የጀመሩትን አይጨርሱም አንድ ነገር ጀምረዉ እንደገና ሌላ አዲስ ይጀምራሉ መጨረስ አይችሉም::

2- ሜሌኮሊ የሚባለዉ ባህሪ ያላቸው:-

ጥሩ ወይ ጠንካራ ባህሪያቸዉ:-

አዳዲስ ነገሮችን ያፈልቃሉ : አቅማቸዉን ያውቃሉ ባላቸው ለክ ነዉ የሚኖሩት ወጭ የሚያወጡት ባቅማቸው ነዉ : የሌላውን አያዩም : ጥሩ ጓደኛ መሆን ይችላሉ::

ጥሩ ያለሆነ ወይም ደካማ ጎናቸዉ:-

ጥቅም ተኮር ናቸው : ሁሉን ነገር ለራሴ ባይ ናቸዉ እራሳቸውን የሚያስቀድሙ ናቸዉ : ሁሉን ነገር የሚያደርጉት በጥቅም ነዉ የሆነ ነገር ሰትጠየቋቸው ለኔ ምን ታደርግልኛለህ ባይ ናቸው: ተለዋዋጭ ባህሪ አላቸዉ አሁን ሰቀው ከሆነ ወዲያው ሊያኮርፉ ይችላሉ ::

3- ኮለሪክ የሚባለዉ ባህሪ ያላቸዉ:-

ጥሩ ወይ ጠንካራ ጎናቸዉ:-

በራሳቸዉ ይተማመናሉ : ባላቸዉ አያፍሩም : በፈለገዉ ቻሌንጅ ዉስጥ ተጋፍተዉ ይሄዳሉ: ከሌላው ማነስ አይፈልጉም : በችግርም በደስታም ውስጥ አልፈዉ መሄድ ይችላሉ : ለአላማቸዉ ሌላዉን ማስተባበር ችሎታ አላቸው የማሳመን ችሎታ አልቸው : ተደማጭ ናቸዉ ሲናገሩ ይሰማሉ ያደምጣሉ . : ተስፋ መቁረጥ አያውቁም : መልካም ነገር ብቻ ነው የሚታያቸው : ክፉ ነገር ማየት አይችሉም ::

ጥሩ ያልሆነ ወይም ደካማ ጎናቸው:-

ይቆጣሉ ተቆጭ ናቸው : ያቀዱትን ካላሳኩ አያርፉም ያሰቡት ነገር ካልተከናወነ: ጥፋታቸዉን አያምኑም አጠፋሁ አይሉም አይቀበሉም : አሽሙረኞች ናቸው የጎንዮሽ ነግግር ነዉ የሚናገሩት : ግልፅ አይናገሩም በጎን ነዉ የሚናገሩት : ሰውን አያምኑም : አይፀፀቱም ::

4- ፈለግ መቲክ የሚባል ባህሪ ያላቸዉ:-

ጥሩ ወይም ጠንካራ ጎናቸው:-

ቀልደኞች ናቸዉ ያስቃሉ ያዝናናሉ : ጥሩ መክር መስጠት ይችላሉ ጥሩ አማካሪዎች ናቸው . ፍሬማ ሥራ ይሰራሉ : መስሎ ማደር ይችላሉ : ለወዳጃቸው ታማኞች ናቸዉ በጫና ጊዜ በውጥረት ጊዜ በጣም ጥሩ ሰራ መስራት ይችላሉ ያላቸውን ሀይል አውጥተው::

ጥሩ ያልሆነ ወይም ደካማ ጎናቸዉ:-

ለነሱ ከሚመስላቸው ውጭ ለዘብተኛ ናቸው : ታቅዶ የቀረበላቸውን ሁሉ ካላመኑበት አይቀበሉም : በሰው ቀላጅ ናቸው ቀልዳቸው ሰውን ይጎዳል ልክ ያለፈ ቀልድ ይቀልዳሉ ለነሱ ያስቃቸዋል ግን ሰውን ይጎዳሉ ::

የነዚህ ባህሪዎች ልዩነታቸዉ ውበት ነዉ በተለይ የምታገቡትን ሰዉ ባህሪ በጣም ለይቶ ማውቅ በጣም ይጠቅማል የምታውቁትን ይጨምሩ ካነበብኩት ነዉ መልካም ነባብ ይሁንላችሁ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby እሪኩም » Sun Dec 15, 2013 10:04 am

ሠላም
አለን
Image
መሸፈት ያለ ነው ይጠየቅ ልብሽ :
ሥንድድ እና ድንብል አሸን ክታብሽ ::

http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=23129
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests