ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)" href="http://www.cyberethiopia.com/warka14/feed.php?f=2&t=23129" />

ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ሰላም

Postby ሜሔታቤል » Fri Oct 01, 2010 7:40 pm

ሰላም ያገር ልጆች እንደምን አላችሁ!

አማን ነዉ እንዴት ነዉ ወረኢሉ መቸም አንች እያለሽ ይሄቤት ሁሌ እንደደመቀ ነዉ ሰለ ሀገራችን የምታቀርቢያቸው ትምህርት የሚሰጡ ጽሁፎች በጣም አሪፍ ነዉ በርችልኝ::

መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ እመለሳለሁ ቸኮየ ነዉ :.

ሜሔታቤል
እዉነት መናገር ካልቻልክ
ቢያንሰ ዉሸት አትናገር !
ሜሔታቤል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sun Feb 22, 2009 9:35 pm
Location: Ethiopia

ሰላም

Postby ጃሪ » Tue Oct 12, 2010 5:10 pm

ሰላም አማን ነዉ ወይ የዚህቤት ወዳጆቼ እንደምን ከረማችሁ ! ወረኢሉ እንደምን አለሽ ያገር ልጅ ሰለ ወረኢሉ የምታስነብቢን የሚገርም ነዉ በርች እየተከታተልኩ ነዉ ::

በሙዚቃ ሠረገላ
ነፍሴ ጋልባ
ልጅነቴን ጠርታ
ጉርምስናዬን አስታውሳ
ልቤን አተራምሳ::

ዓይኗን ጨፈን አደረገች
እጆቿን ዘረጋችና ጡቶችሽን ዳስስች
ዘንፋላ ጸጉርሽን ለበሰች
በከንፈሯ ከንፈርሽን ዳሰሰች
ቁምነገርና ለዛሽን ካን ጎሌ ጓዳ ቀስቅሳ
አጓዘችኝ ብዙ ዓመታት የጊዜን ድንብር ጥላ ላንድ አንድ አፍታ::

አየሽው ብንለያይም አልተለያየን
ብንራራቅም አልባከን
ለቅፅበታም ቢሆን ከልቤ ውስጥ ተገናኘን
ብልጥጭታውና ቅፀበቱ
ምን ቢያጥር ህይወቱ
ኮረኩረን
አስታወሰን
የቀን የወሩን የዓመቱ
በድንገታዊ ምፅዓቱ::

አየሽው ተለያይተንም አልቀረን
የማንረሳው ብዙ አለና
በትዝታ ተገናኘን::

የ ቅ ፅ በ ት ት ዝ ታ !!

መልካም ቆይታ ::

ጃሪ
ከፍል ውሃ
ባቄላ ምርቱ እንጅ አያምርም ክምሩ :
ይምጣ የወሎ ልጅ ከነምንሽሩ ::
Image
እናት ሃገሬን ኢትዮጵያን እወዳለሁ::
ጃሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Fri Jul 11, 2008 10:17 pm
Location: wollo

ሰላም

Postby ወረኢሉ » Tue Oct 19, 2010 8:22 pm

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ ሰላምታየ ይድረሳችሁ በያላችሁበት !!
ሰላም ጃሪ እንደምን አለህ ብቅ ብለህ ሰላየሁህ ደስ ብሎናል አትጥፋ::

አንድ እንቆቅልሽ ልበላችሁ !

እንቆቅልህ እንቆቅልሽ !
ምናዉቅልህ- ምን አውቅልሽ
ብታውቅልኝ -ብታውቂልኝ
ባታጠብቁት ብትፈቱልኝ
እንቆቅልሽ እስኪ ስሙኝ::

እንቆቅልሽ የናውቅልሽ
እንቆቅልሽ የናውቅልህ
የከክልኝ ልከክልህ
እንቆቅልሽ የሚወዷት
ሁሉ ይኔ የሚላት
ሁሉ የሚወዳት የሚፈራት
በስሟ ሚገዘት የሚምልላት
እንቆቅልሽ እረ ማናት??

በውበቷ የደመቀች የገነነች
ሰንቱን ጀግና እንዳላርበተበተች
እንደተወደደች ደግሞ እንደተገፋች
እንደተሽጠች እንደተለወጠች
እንቆቅልሽ እስቲ ማነች ?????

እንቆቅልሹን የሚፈታ ሽልማት አለዉ ቅቅቅቅቅቅ::

መልካም ንባብ ይሁንላችሁ ::


ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ሰላም

Postby ወረኢሉ » Sat Dec 04, 2010 12:41 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት እንደምን አላችሁ ቤታችን ጠፍታ በመከራ አገኘሁት የሚፈልጋት ጠፋ ማለት ነዉ ለነገሩ እኔም ጠፍቼ የለም ለማንኛው አትጥፉ ካላችሁ ብቅ በሉ ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ጣዕም » Wed Dec 15, 2010 4:39 am

ሰላም ወገኖች, በዚህ ፎረም ላይ በተከታታይ የሚቀርቡትን መጣጥፎች በማንበብ ብዙ ቁምነገሮችን አግኝቸበታለሁ:: ለተወሰነ ጊዜ በመቋረጡ አዝኘ ነበር አሁን ብቅ በማለታችሁ ደስ ብሎኛል:: ቀጥሉበት በርቱ
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

ሰላም

Postby ወረኢሉ » Fri Dec 17, 2010 10:24 am

ሰላም ጣዕምየ እንደምን አለህ ሰላም ነዉ ወይ የጠፋ ሰዉ እዉነትህን ነው ቤታችን የሚጽፍ የለም እኔም ሰሞኑን ሰራ ሰለበዛብኝ ወደዚህ ብቅ አላልኩም ነበር ለዛ ነዉ እስኪ ጊዜ ሲኖር አንዳንድ እንላለን አንተ አትጥፋ ያለንን ሰቀባበል ነዉ ደስ የሚለው የአንድ ሰዉ ብቻ ከሆነ ይሰለቻል ቅቅቅቅቅቅ ::
መልካም ጊዜ ይሁንልህ ::
ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby አደቆርሳ » Fri Dec 17, 2010 8:10 pm

ቸር ያሰማን ነው የሚባለው የጠፋ ሰው ሲገኝ ....
ባለፈው ሰሞን ይህቺን ቤት ፍለጋ ስማስን ቆይቼ ሳይሳካልኝ ነው የተመለስኩት::
ወዳጃችን ወረኢሉ ስምሽን በማየቴ ደስ ብሎኝ ለሰላምታ ነው ብቅ ያልኩት
የግጥምና የዜማ መፍለቂያ የተሰኘችው ወሎ ትክክል ስለመሆኑ በግብር እያየንባት ያለች ቤት እንዳትቀዘቅዝ አደራም ጭምር ለማለት ነው::
በተረፈ ቸር ያቆየን ወዳጅሽ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 976
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

መልካም ገና

Postby እሪኩም » Mon Jan 03, 2011 5:33 pm

ሠላም ለቤቱ!

እንዴምናችሁ?
መልካም ገና ለሁሉም!

ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ እሕቶች፣
ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ ወንድሞች፣
ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያላችሁ እሕቶች፣
ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያላችሁ ወንድሞች፤
Image
ሠላም፣ ፍቅር እና ጤና እግዛብሔር ይስጣችሁ፣
ሠላም፣ ፍቅር እና ጤና አላሕ ይስጣችሁ፣
ልዩነት አጥፉና አንድ ይሁን ልባችሁ፣
የፊታችን ገናም በር ይክፈትላችሁ፣
ሠብሠብ በሉና ይመር ጨዋታችሁ፣
ተንኰል እና ሤራን ያምዘግዝግላችሁ።

ፍቅር ጀባ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ


Image
መሸፈት ያለ ነው ይጠየቅ ልብሽ :
ሥንድድ እና ድንብል አሸን ክታብሽ ::

http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=23129
እሪኩም
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 853
Joined: Fri Apr 01, 2005 1:20 am
Location: ወሎ

ሰላም

Postby ወረኢሉ » Sat Jan 15, 2011 9:42 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች እንደምን አላችሁ አማን ነዉ እሪኩሜ አሜን አሜን ብለናል አመስግናለሁ ደህናነህ ከረጅም ጊዜ ቦሀላ ሰላየሁህ ደስ ብሎኛል እቤታችን ይልመድብህ መጥፋት ጥሩ አይደለም እኔም ሰሞኑን ገብቸ አላውቅም አልተመቼኝ ነበር ዛሬ ሰገባ ነዉ ያየሁት ይቅርታ ::

መልካም ጊዜ ::


ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ሰላም

Postby ወረኢሉ » Fri Mar 04, 2011 12:36 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት እንደምን አላቻሁ ቤታችን ጠፍታ በመከራ ነዉ ያገኘሗት ፈላጊ አጥታ ነው ቅቅቅቅቅ እስኪ መልካም እኔው ፈልጌ ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ባለሱቅ » Fri Mar 04, 2011 4:55 am

ወየውውውውውው
ሞት ይርሳኝ
አንቺ ልጅ አለሽ ወይ በህይወት

ገባሽ ሲሉ ሰማሁ... እውነት ነው እንዴ
የት ብለሽ እንዳትጠይቂኝ ብቻ?

ገባሽ አሉ... ተጠቃለሽ?
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ውረጂብኝ እንግዲህ

ጠፍተሻል እኛም ቤት[
በይ ቶሎ ቡናሽን ይዘሽ ብቅ በይ.... ተነጥፏልና

ቺርስ በወልኛ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Mon Mar 07, 2011 9:33 pm

ሰላም ባለሱቅ አለህ እንዴ ይሄን ቤት እኮ የረሳህው መስሎኝ ነበር ዋርካላይ ሰም ካላየህ ሰዉ አታስታዉስም አሉ የሚገርም ነዉ ደህናነህ ገን ? ደግሞ ገባሽ መናም የምትለዉ የት ይሆን የገባሁት? መቼም አያልቅብህም ቅቅቅቅቅ ለማንኛውም አመስግናለሁ ::

ቡና ካልተፈላ አይንህ እንደማይገለጥ አዉቃለሁ በል እስኪ ጊዜ ሳገኝ ብቅ እላለሁ ሁሉንም ሰላም በለልኝ ::

መልካም ጊዘ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Mon Apr 04, 2011 10:59 pm

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ በያላችሁበት ሰላምታየ ይድረሳችሁ:: ቤታችንን ልጎብኛት ብየ ነዉ ሰው ሁሉ ሰለጠፋ:-

"" ሰው - የጅን -----""

የቀላው ቢጠቁር - ወዛም ቢገረጣ
ያጣውም አግኝቶ - ባለፀጋም ቢያጣ
ወርሐው ቀጥ ቢል - እውር ቢቀናጣ
ኮበሌው በስለት - በዱአ ባይመጣ
በካር ባገር ጠፍቶ- ሽበላ ቢታጣ
ሽሬታው ተወዶ - ገበያ ባይወጣ
ሐያት ብቻ ደህና - ሰው የጁን አያጣ::

------------ "" -----------------


"" ፈረሴን ጫኑልኝ ያንን ቀይ ቦራ
መከራም ደስታ ነዉ ከኢትዮጵያ ጋራ ""

ያገሬ ሰው ተናገረና ሰለመከራ እንዲህ አለ ደግሞ

አሁን ምን ያረጋል - የጊዜ ደሳሳ
አሮጌ ቤት አይደል - በባላ አይነሳ!

በድጋይ ቢመታኝ መታሁት በኩበት
ስፍራ ለሌለዉ ሰው ምን ያደርጋል ጉልበት!


"" የግጥም ቃና ""

እኛ መች አወቅነዉ የነፃነት ታጋይ ስይጣን እንደሆነ
አሻፈረኝ ብሎ ከዚህ በኛው ዓለም መጥቶ እንደመነነ !

""እርጅና ""

እንኳን ድሮ ሳምን - እንኳንም ተሳምን
ምን በፋራ ቢሆን ከንፈር እየሳትን ጥርስን እያጋጨን
ያለሃሳብ ስመን ያላሳብ ተሰመን ብናረጅ አይቆጨን::

መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ባለሱቅ » Tue Apr 05, 2011 4:57 am

እረ በተሰቀለው
ይሄ ቤት በህይወት አለ እንዴ
በቀደም መልስ ምናምን ልፅፍ ብፈልግ ባስፈልግ አጥቼ.. ዛሬ ሳየው
እንዴ ይህች ልጅ በእጇ ይዛው ነው እንዴ ምትዞረው ብዬ ግርምምም ሲለኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ደሞ ብለሽ ብለሽ.... እኛ ላይ ግጥም መግጠም ጀመርሽ
እንኳን ድሮ ሳምን - እንኳንም ተሳምን
ምን በፋራ ቢሆን ከንፈር እየሳትን ጥርስን እያጋጨን
ያለሃሳብ ስመን ያላሳብ ተሰመን ብናረጅ አይቆጨን ::

ወይ ጉድድድድድድድድድ
እኔ ገና ተስሜም ስሜም አልጠገብኩም....
ራስብሩ ምን ይልሽ ይሆን ይህንን ስድብ አይቶ
ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ላጋጫቹ እንጂ

እንደምን አለሽ ወረኢሉ

በቅድሚያ በወደም አስበሽ ደውለሽ ጤንነቴን ስለጠየቅሽን ላመሰግንሽ እወዳለሁ
አምላክ አሳቢ ይስጥሽ

ባለፈው ለካስ ጤይቀሽን ነበር... በአላህ ዛሬ ነው ያየሁት
ደግሞ ገባሽ ምናም የምትለዉ የት ይሆን የገባሁት ?

እንዴ የት እንደገባሽ,ም አታውቂም ማለት ነው?
ሱቅ ነዋ!
ሱቅ ውስጥ ጥልቅ
ከባንኮኒው ስር ንጥፍ
ገንዘብ ምናምን ብርብር
ያልተነቃብሽ መስሎሻ;ል
ሞኝሽን ብዪ ... በግጥም

በነገራችን ላይ አሪፍ ግጥም እንደሆነች ልነግርሽ እወዳለሁ... የዛሬዋ ግጥም ወርቅ ናት...
ራስብሩ እንዳያነባት ግን.... አደራሽን

ሰላም ዋይ... በተረፈ
ባለሱቅ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1288
Joined: Mon Sep 27, 2004 6:20 am
Location: ethiopia

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Sun Apr 10, 2011 10:40 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች እንደምን አላችሁ ! ባለሱቅየ እንደምን አለህ እንዴት ነዉ አንተ ያንን ሀገር አለቅም ብለሀል መሬት ስትርገፈገፍ አብረህ መርገፍገፍ የወደድክ ትመስላለህ እንግዲህ እግዚያብሄር ይጠብቅህ ምን ማድረግ ይቻላል:: ደግሞ ከራስ ብሩ ጋር ልታጣላኝ ነዉ እንደዚህ የምትለዉ ቅናት ይመስልብሀል: ደግሞ እሱቅም አልገባሁ የትም አልሄድኩም ባለሁበት ነዉ ያለሁት አንተን ሳልነግርማ የትም አልገባም ቅቅቅቅቅ ::

ለማንኛዉም አትጥፋ ይልመድብህ ባይሆን ቡና እናፈላልሀለን ጫት ስትቅም :: እስኪ አንድ ብየ ልዉጣ ብየነዉ ሰገባ አንተን አየሁህ በግጥም ላልከዉ በሚቀጥለዉ እጽፋለሁ መልስህን :.


"" የቀን እንጅ ""

መለሎ ነዉ ያልኩት - አጥሮ አግኝቼዋለሁ
ቀይ ነዉ ያልኩትም - ጠቁሮ አይቼዋለሁ
እድሜ ዘልዛላ ነዉ - ብዙ ታዝቤአለሁ::

ወፍራም የመሰለኝ - ኮስምኖብኝ ታይቷል
ምሁር ነዉ ያልኩትም - ከፊደል እርቋል::

ባለፀጋም ያልኩት - ደህይቶ አየሁት
ኩሩ ነዉ ያልኩትም - ተዋርዶ አገኘሁት::

አገር አለዉ ያልኩት- ምጻተኛ ሆኗል
ዘርና ሰልጣንም - ፋሽኑ አልቆበታል::

ከእንግዲህስ ይብቃኝ - አንደበቴን ልግታው
ጊዜ የጣለውን - ጊዜ እስኪያነሳው
ወትሮም የቀን እንጅ- የሰው ጀግና የለው::

መልካም ሰንበት ይሁንላችሁ ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests