ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)" href="http://www.cyberethiopia.com/warka14/feed.php?f=2&t=23129" />

ወሎ ገራገሩ (WOLLO GERAGERU)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ሳይታማ-1 » Thu Apr 21, 2011 7:18 pm

መልካም የትንሳኤ በአል ....እጆት አይንተፍ.....
Menor deg new!
ሳይታማ-1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Tue Sep 23, 2008 9:00 am

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Thu Apr 21, 2011 11:25 pm

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ከርስቶስ የስቅለት መታስቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ሳይታማ ሰላም እንደምን አለህ እንኳን በሰላም ወደ ወሎገራገሩ ቤት መጣህ አርሂቡ ብለናል ይመችህ ይልመድብህ አብሽር ወዳጄ እጆችም አይነጥፉም ጊዜ እያጣን ነዉ::

እስኪ እንደኔ የታዘበ ካለ ብየ ነዉ ይሄን ሀሳብ ያነሳሁት ወይም በዚህ ዙሪያ ላይ አንባቢዎች ምን ትላላችሁ በቅርብ ወደ ኢትዮጵያ ሄጀ ካየሁት ነገሮች መካክል አንድ ነገር አስደነቀኝ ደግሞም አሳዘነኝ ይሄንኑ ጉዳይ እንደኔ ያታዘበ አንድ ወዳጄ ዛሬ አንስቶ በጣም አዝኖ ወይ ሀገሬ እና የሀገሬ ተማሪ ብሎ አጫወተኝ ለካ እኔ ብቻ አይደለሁ ? በየ ከተሞቻችን ብዙ ጽሁፎች ይለጠፋሉ የሚያስቁ የሚያሳዝኑ እንዲሁም ማስጠንቀቂያ ወይም ምክር የያዙ ይሄኛው ግን ለየት አለብኝ ለኔ "" ተከፍሎን የመመረቂያ ጽሑፍ እንጽፋለን የሚል ነበር ያነበብኩት እኔ የተረዳሁት ተማሪዉ ጽሁፉን አዘጋጅቶ በኮፒውተር(በታይፕ) ለመጻፍ መስሎኝ ነበር ለካስ ዛሬ ወዳጄ ሲነግረኝ የኢትዮጵያ የተማሪ ጥራት የት እንደደረሰ እና እንዴት እንደገሽበ ወይም እየተበላሽ እንደመጣ በጣም አዘንኩ ተማሪዎች እንደምንም ብለዉ በኩረጃም ሆነ በሌላ መንገድ ለመመረቅ ሲደርሱ ያዉ የመምረቂያ ወረቀት ማቅረብና መዘጋጀት ሰላለባቸው ሰነፍ ወይም ኮራጅ ከየት አምጥቶ ያቀርባል በገንዘብ እዉቀት ገዝተዉ በሰው ሰራ ብዙዎች እንደሚጠቀሙ እና እንደሚመረቁ ሲነግረኝ ለካ በየቡታዉ የተለጠፈው ማስታወቂ መሆኑ ገባኝ የሚገርም ነዉ በሀገራችን ለካ "" የእውቀትም ሙስና"" ይፈቀዳል ማለት ነዉ:: ከየት ወዴት እየሄድን ይሆን ??? ይህ ሁሉ በምድራችን ላይ የሥነ ምግባር መጥፋት ነዉ:: ይህንንስ አድርጎ የሚመረቀው ተማሪ መጨረሻው ምን ይሆን ?? ማንን እያታለለ ነዉ ?? ህሊናውን ወዴት መሸሸ ይችላል?? ነዉ ወይስ ተመረቀ ለመባል?? ሰዉ የስነምግባር ልቀት (Ethical Intelligence) ቢኖረው ኖሮ ይህን ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም ህሊናው አይፈቅድም ነበር::
እስኪ የምታነቡ ይህን ጽሁፍ የምትታዘቡትን አስቀምጡ እኔ የሀገሬ ወጣት ተማሪ ወዴት እንዴት እየሆነ ነው እላለሁ?? በመጨረሻም ሰለ ሥነ ምግባር እና ሞራል እሴቶች ታዋቂው የሕንድ መሪ ማህተመ ጋንዲ ያስቀመጧቸውን ሰባት አባባሎች ካነበብኩ ያገኘሁትን ብየ ልጨርሰ:-

- ፓለቲካ ያለ መርህ (Politics without Principle)
- ደስታ ያለ ህሊና (Pleasure without Conscience)
- እዉቀት ያለ ባህርይ (Knowledge without Chracter)
- ንግድ ያለ ግብረገብ (Commerce without morality)
- ሀብት ያለ ሥራ (Wealth without Work)
- ሳንይስ ያለ ስበአዊነት (Science without humanity) እና
- አምልኮ ያለ መሥዋዕትነት (Worship without Sacrifce)ፈጽሞ እርባና የላቸዉም::

መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ መልካም ንባብ ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby ራስብሩ » Sat Apr 23, 2011 9:42 pm

ሠላም ለወሎ ገራገሩ ጤና ይስጥልኝ !
እዚህ ቤት አልፎ አልፎ ቁምነገሮችን ለመቅሰም ብቅ እላለሁ እንጂ እጄን ሳላነሳ ቆየት ብያለሁ :
መልካም የፋሲካ በዓል ለመላው የወሎ ገራገሩ ታዳሚዎች እና ለቤቱ እንግዶች ሁሉ እመኛለሁ !

ራስብሩ
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/6554 ... s_Biru.jpg
ራስብሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 785
Joined: Thu Aug 25, 2005 6:49 pm

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Sat Apr 23, 2011 10:54 pm

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች እንኳን ለጌታችን ለመዳሂኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ :: ራስ ብሩ እንደምን አለህ ወዳጀ እንኳን አብሮ አደርሰን በጣም አመስግናለሁ ከረጅም ጊዜ ቦሀላ ወደዚህ ቤት ብቅ ሰላልክ በጣም ደስ ብሎኛል ይልመድብህ ለቤተሰብ ሁሉ መልካም የፋሲካ በአል ይሁንላችሁ::

http://www.youtube.com/watch?v=s7KcicFq ... re=related

መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

Postby anferara » Sun Apr 24, 2011 10:22 am

ለወሎ ገራገሩ ታዳሚዎች

እንክዋን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!

መልካም በዓል ለሁላችሁም:::
anferara
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 445
Joined: Wed Sep 27, 2006 5:06 pm

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Tue Apr 26, 2011 11:03 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች!
አፈራራየ እንኳን አብሮ አደረሰን እንደምን አለህ እንኳን ደስ ያለህ----ሴራ በገነተልዑል ቤተመንግሥት ክፍል ሁለት-- ወደ ህትመት ክፍል መግባቱን ሰማሁ በጣም ደስ ይላል በጉጉት ስጠብቀዉ ነበር የድካምህን ዉጤ እዚህ ላይ ሰለደረስ በድጋሜ እንኳን ደስ ያለህ አንባቢዎችም እንደዚሁ በርታ ለማንበብ እንጠብቃለን ራስ ብሩ መቼም የመጀመሪያውን እንደሚያደርስል እርግጠኛ ነኝ ቅቅቅቅ::

መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ሰላም

Postby ጃሪ » Sun May 22, 2011 10:30 pm

ሰላም ያገር ልጆች ይህ ቤት ጠፍቶኝ በመከራ አገኝሁት ለመሆኑ ወረኢሉ የት ሄዳ ነዉ ? በይ ወደ ቤትሽ ተመለሽ በሉልኝ እኔም እመለሳለሁ :.

ጃሪ
ባቄላ ምርቱ እንጅ አያምርም ክምሩ :
ይምጣ የወሎ ልጅ ከነምንሽሩ ::
Image
እናት ሃገሬን ኢትዮጵያን እወዳለሁ::
ጃሪ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Fri Jul 11, 2008 10:17 pm
Location: wollo

ወሎ

Postby ወረኢሉ » Wed May 25, 2011 12:08 am

ሰላም ለወሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በሙሉ!
አማን ነዉ ጃሪ ሰላም አለህ እንዴ በሰላም ነዉ ጠፋህ እኔ ሰሞኑን አልተመቸኝም ነበር ለዛ ነዉ እስኪ ጊዜ ሲኖር ብቅ እላለሁ ካነበብኩት አንድ ልበልና ልዉጣ::

ኑሮና ጨረቃ !

ኑሮና ጨረቃ ምን --- አንድ አረጋችሁ
በብዛት ጎላችሁ ----በጥቂት ሞልታሁ
አንዳንዴም ጠፍታችሁ--ተስፋ አስቆርጣችሁ
ህልም አጨልማችሁ --- መድረሻ ነስታችሁ
ዳግም ለሰው እልክ ትወለዳላችሁ--ታንሰራራላችሁ

የሰው ልጅ ቢብሰው ---- የሰው ልጅ ቢከፋው
መኖርን ይመርጣል ----- አንድ ቀን ይሆናል

ይላል ::

ጨረቃና ኑሮ ---- ያምላክ ጥበብ ናችሁ
ጥቂት አልብሳችሁ-ብዙሀኑን ገላ ለብርድ የሰጣችሁ
ልትምሉ ማትችሉ -- ከፍ ቢያደርጓችሁ

ዝቅ ቢያደርጓችሁ

ግና ደስ የሚለው ምጥን አስማታችሁ
ለረዥም አመታት ያልተስለቻችሁ
የቻለም ይመልስ ከሁለት አንዳችሁ
ትቀጥሉ ይሆን በዚሁ አቋመችሁ::


መልካም ንባብ ይሁንላችሁ::

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ወሎ

Postby ፋጤ » Wed Jun 01, 2011 12:37 am

ሰላም ያገሬ ልጆች ወይኔ ይሄ ቤት ናፈቀኝ በስንት ጊዜ ነዉ የገባሁት የሚገርም ነዉ ወረኢሉ እንዲሁም ሌሎቻችሁ አማን ነወይ? የሆነ ያነበብኩትን ላካፍላችሁ:-

ቦታዉ ደ/ወሎ ጢጣ !!

ወታደሮቹ አጎንብሰው በፍጥነት እየሮጡ ካገኙት ቁጥቋጦ ስር ይወሽቃሉ እድለ ቢሶቹ ካሰቡት ሳይደርሱ ከየት እንደተተኮሰ በማያውቁት ጥይት ተመተዉ ከመሀል ይቀራሉ.....

ለጉድ የሚወርደው ዝናብ ከተኩሱ እሩምታና ከቦንቡ ፍንዳታ ጋር ቅዝቃዜው ይነዝራል T-50 ና T-55 ከባድ ብረት ለበስ ታንኮች ባለ መቶ ና መቶ አስርሚ.ሜ ቀልሐቸውን እንደ ተሽከሙ እርሻወቹን እየመረመሩ በፍጥነት አለፉ ::

አንድ የተጣደፈ ወታደር ግራ እግሩን እየጎተተ ፈንጠር ብላ ከተቀመጠችው የሳር ጎጆ ቀረበና በሩን በሀይል ይደበድብ ጀመር ከተወሰነ ሰከንድ በኌላ "" ማ ... ማነው? የሚል ድምፅ በፍርሃትና በቆራጥነት ተጥቅልሎ ከትንሿ ጎጆ ሹልክ አለ ::

ባካችሁ ... እርዱኝ ? ክፍኛ ቆሰያለሁ አለ ወታደሩ ገበሬው እየፈራ በሩን ቀስ ብሎ ከፈተው የቆሰለው ወታደር በፍጥነት ገባና በሩን ጥርቅም አድርጎ ዘጋው:: .......... በቅጡ ከፈገገዉ የወይራ ፍም ትንሽ ራቅብላ አንዲት ወጣት መንታልጆችን አቅፋ ታጠባለች :: .... የቆሰለዉን እግሩን እየጎተተ እሳቱ አጠገብ ያለዉ መደብ ላይ ተቀመጠና ገበሬውን እንዲረዳው ተማፀነ::

...."" የወታደር ተማፃኝ እንዴት ያናድዳል ::""

በሞቀ ውሀና በንጽህ ጨርቅ የቆሰለውን እግሩን ገበሬው ቀስ እያለ ያጥብለት ጀመር:: ባለ 7.5 ሚ.ሚ የክላሽ ጥይት ነች አለ ወታደሩ የቁሰሉን ክፍተት በሙያና በልምዱ ለክቶ ወታደሩ መፍጠን እንዳለበት ያውቃል የተወሰኑ ወታደሮች ሊያጠቁት እየተከተሉት እንደሆነም እንደዚያው.....

ገበሬው በንፁህ ጨርቅ የግራ ባቱን አጥብቆ አሰረለት::

ይቀጥላል እመለሳለሁ >>>>>>>>>>>>

ፋጤ
Image
አሰደሳችና ጠቃሚ ይሆናል ለምትለው
ነገር ሁሉ በይሉኝታ አትለፈው !!
ፋጤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 107
Joined: Mon Aug 20, 2007 9:25 pm
Location: WolloW

Postby ኮሎኔል » Mon Jun 06, 2011 10:53 pm

ሠላም ለወሎ ገራገሩ
ያመለጡኝን ነበብ ነበብ አረኩና የፋጤን የተጀመረ ደብዳቤ
ለመጨረስ ጎጆ ውስጥ ቀረሁ::
እከታተለዋለሁ አመጣጤ ግን ዋናው ለሰላምታ ነው
ደህና ሁኑልኝ
አክባሪያችሁ ኮሎኔል ነኝ
Ethiopia
ኮሎኔል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Fri Apr 07, 2006 7:19 pm
Location: zimbabwe

ወሎ

Postby ፋጤ » Tue Jun 07, 2011 10:40 pm

ሰላም ያገሬ ልጆች እንደምን አላችሁ የጀምርኩትን እንኳን ሳልጨረሰው ጠፋሁ እዉነት ነዉ ኮሎኔል ሰላም ነዉ እንኳን በሰላም መጣህ ከርጅም ጊዜ ቦሀላ ሰላየሁህ ደስ ብሎኛል:: እስኪ ወደ ጀምርኩት ልመለስ :-

"" ይቅርታ አድርግልኝና ያደፈ ጋቢ : አሮጌ ሱሪ የምቀይርህ የገበሬ ጫማ ልትስጠኝ ትችላለህ ? "" ወታደሩ በትህትና ጠየቀ :: ብዙ የማያወራዉ ገበሬ ያለዉን በሙሉ አቀረበለትና ራቅ አለዉ::

የገብሬው ታላቅ ወንድም በደረግ ወታደሮች ኢሃፓ ነህ ተብሎ በግፍ ተረሽኗል ከወንድሙ ሞት በኌላ ወታደር የሚባል ነገር ይጠየፋል :: አሁንም ተቸግሮ ከቤቱ የመጣውን ወታደር ፈጣርየን አላስቀይምም ብሎ እንጅ በሞፈር ጭንቅላቱን መቶ ቢገድለው የወንድሙን ደም እንዳፈሰ ይቆጥረው ነበር::

"" ውለታህን አንድ ቀን እንደምመልስ ተስፋአደርጋለሁ "እከዚያ ይችን ራሽያ ማካሮቭ እንደማስታወሻ ትሁንህ ""
ብሎ ከሁለቱ ሽጉጦች ከፍ ያለዉን ሰጠውና እርዳታ ካልተነፈገባት ጎጆ ወጥቶ ዘወር ወዳለው ጫካ እያነከሰ ተሰወረ::

ወታደሩ ከተሰወረ ከሩብ ሰአት ቦኌላ ሁለት ወታደሮች አጭር ቁንጣ የለበሱ ፀጉራቸውን በጣም ያሳደጉ የመጀመሪያውን ወታደር ዱካ እየተከተሉ እዛቸው ጎጆ ቀረቡ:: "ኳ ኳ ኳኳ .. በሩ ጠበቅ ተደርጎ ሲቆረቆር ጠንከር ያለ መልክት እንዳለው ግልጽ ነበር:: ገበሬውም ማንነታቸውን ከዉስጥ እያጣራ በሩን ከፈተና " አቤት" አለ ለሰሰ ብሎ ወታደር ሲያይ በዝምታ ጭልጥ ቢል ምርጫው የሆነዉ ገበሬ ::

እዚጅ ጎጆ ውስጥ አንድ የሚያነክስ ወታደር መጥቶ ነበር? አለ ከሁለቱ ወታድሮች የተበሳጨና የመግደል ፍላጎቱ በእጅጉ የተነሳሳበት የሚመስለው:: " የምን ወታደር ? እረ ወታደርም የለብንም " አለ ገበሬው እየተቀጠቀጠ :. ይታይሀል ይህ ዱካ ከተራራው ጫፍ ጀምረን ነዉ የተከተልነዉ . . . . . . . ወይ ደብቀህዋል አልያም እንዲያመልጥ ረድተህዋል:: እዉነቱን ተናገር አይኔ እያየ ነዉ ወንድሜንና ጓደኞቼን በቦንብ ሰጋቸዉን የቦጫጨቀው ለመሆኑ ወንድም ምን ማለት እደሆነ የጓደኝነትን ሚስጥር ታውቃለህ ? ንገረን ጊዜ የለንም . . . . . . ወታደሩ የመጨረሻ በሚመስል ትእግስቱ ለመነው:: እረ ማሩኝ ? ካላችሁም ግቡና ፈትሹ እኔ አራስ ሚስቴን እየርዳሁ ነዉ ከኔና ከባለቤቴ ውጭ ማንም የለንም ማንም አልመጣብን ብሎ የዱካውን ነገር አስተባበለ::
ና ውጣ....... አለና የተበሳጨው ወታደር ትንሿን ጎጆ ሊበረብር ገባ ይሄኛው ወታደር ይህ ሁሉ ሲሆን ምንም ልተነፈሰም ብቻ ግን ዘወር ዘወር እያለ አካባቢውን ይቃኛል መልኩም የየዋሆች አይነት ነዉ::

ሲበዛ የተበሳጨው ወታደር እንዲህ አለ :::::

ይቀጥላል <<<<<<<

ፋጤ
Image
አሰደሳችና ጠቃሚ ይሆናል ለምትለው
ነገር ሁሉ በይሉኝታ አትለፈው !!
ፋጤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 107
Joined: Mon Aug 20, 2007 9:25 pm
Location: WolloW

ወሎ

Postby ፋጤ » Fri Aug 05, 2011 3:29 pm

ካለፈዉ የቀጠለ <<<<<<<>>>> ምራ ከኛ ጋር ትሄዳለህ እዚያም በደምብ ትጠየቃለህ አለ ለጓደኛው በንዝላልነት ተቀምጣ የተገኘችውን ማካሮቭ ሽጉጥ እያሳየው :: ኧረ ባካችሁ እንደት ነዉ አራስ ባለቤቴን ብቻዋን ጥያት የምሄደው? ገበሬው እንደማልቀስ ቃጣው ወታደሩም በያዘዉ መሳሪይ በስደፋ ጀርባውን ሲነጥለው........ አላዘነ::
ኧረ ሰለ ፈጠራችሁ ተውልኝ ለምን ባልሰራው ታስቃዩታላችሁ? እኔንስ ለማን ትቶ ነዉ የሚሄደው? እህት እናት የላችሁም ? አለች ጉዷን ያላወቀችው ሚስት መንታወቿን እንዳቀፈች ከጎጆዋ እየወጣች ወደ ወታደሮቹ እየቀረበች:: አይዞሽ ሙኑም አይዶኦሩስበት ለጡያቄ ቡቻ ነዉ የሚፈለግ አሁን ይሞሎሳል አለ ሳይናገር የቆየው ወታደር በሚችለዉ ትንሽ አማረኛ ለማስረዳት እየሞከረ:: ዉብ ስራ ቢመሽም እመለሳለሁ ግቢ የዛሬው ብርድ ይጠዘጥዛል ...... አለገበሬው ራሱን አርጋግቶ ባለቤቱ እንድትረጋጋ የማባበያ ሰሟን እየጠራ::

ቁልቁል እያዳፋ ሲወሰድት ሚስት አለቀሰች አትከተላቸዉ ነገር........ ዝናቡ ማካፋት ጀምሯል ሰማዩም እንደ ጠቆረ ነዉ አራሷም የሆነ ነገር ይቀፋት ጀመሯል ::::::

""ኪው ይተረገመች ጥይት ከየት እንደተ ተኮስች የማታስታውቀው የአራሲቷን ግምባር ለሁለት ከፈለችው ልጆቿን ለቃ በጀርባዋ ተዘረጋች:: እርይ ጨረር ...........ሁለቱ ጨቅላወች ..... በዚያ ቀፋፊ ምችት እናታቸው ጥላቸው መሄድ እንደሌለባት ብጩኸታቸው ሊያሳምናት ሞከሩ ብዙ ደከሙ ጣሩ.......ግን አልተሳካም ሞት እኮ ነው እንደተለመደው ድል አረገ::

በትንሿ ጊጆ ውስጥ እርድዳታ ተደርጊለት የሄደው ወታደር በወታደር ቤት ታርኩ የገጠሙትን ብዙ ነገሮች ያሰፈረበትን የግል ማስታወሻ ደብተሩን ጥያለሁ በማለት የሚስኪኑን ገበረ ጎጆ ለሁለተኛ ጊዜ ጎበኘ"".......አራሷ ሞታለች ልጆቹ ዝናብ እየመታቸው በተንጋለለችው ጉያ በተለያየ አቅጣጫ ተሽጉጠው ይንጫረራሉ::

እሬሳውን እጊጆው መለሰ አንደኛውን ህንፃን አባብሎ አንቅልፍ ሲወሰደው ከእሳቱ እራቅ ካለ መደብ ላይ አስተኛውና ወደ ሁለተኛው ፊቱን አዞረ ....... አልተኛ አለ የናቱ ሞት ከክኖት ነዉ መስል ማልቀስ ብቻ .....ይዞት ወደ ውጭ ወጣ እንዳለ ባሏን በብስጭት የውሰደባት ወታደሩን እመጫቷን ሊጠብቅ ና ሊያስታምም ሲገሰግስ ተመለከ አዉቆታል ሲያሳድዱት ከነበሩት ወታደሮች መሀል አንዱ ነዉ::

የሰማይ እምባ እየወረደ ነዉ ተኩሱም ቆሟል ወታደሩም ልጁን እንዳቀፈ ወደጫካው ሽመቀ እድፍጦ ጠበቀ ልጁም ዝም ተሰኝቷል በመጋሰገስ ላይ የነበረዉ ወታደር ትንሿ ጎጆ ደረሰ መሳሪያውን ጥሎ እንዲንበረከክ እያነከሰና ወደፊት እየተጠጋው ተዛዝ አስተላለፈ አጭር ቁንጣ የለብሰው ወታደር ባማንከሱ ሳቢያ አውቆታል በፍጥነትም ለመተኮስ መሳሪያ የያዘበት እጁን ልጅ ወዳቀፈው ወታደር ሲዘረጋ ተቀደመ ተዝለፍልፎም ወደቀ በወደቀበትም ሆኖ መተኮስ ጀመረ ልጅ ያቀፈው ወታድርም እግሬ አዉጭኝ ብሎ እያነከስ ልጁን እንዳቀፈ ተምዘገዘገ ...... ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ::

*******************

መንታውቹ ወላጆቻቸውን አጡ ውንድማ ማቾቼ ተለያዩ::

****************
ይቀጥላል <<<<<<<<<<


ፋጤ
Image
አሰደሳችና ጠቃሚ ይሆናል ለምትለው
ነገር ሁሉ በይሉኝታ አትለፈው !!
ፋጤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 107
Joined: Mon Aug 20, 2007 9:25 pm
Location: WolloW

መገን ምርቃና...

Postby ቅዥቢው » Sat Aug 06, 2011 4:25 pm

...እሬሳውን እጊጆው መለሰ አንደኛውን ህንፃን አባብሎ አንቅልፍ ሲወሰደው ከእሳቱ እራቅ ካለ መደብ ላይ አስተኛውና ወደ ሁለተኛው ፊቱን አዞረ ....... አልተኛ አለ የናቱ ሞት ከክኖት ነዉ መስል ማልቀስ ብቻ .....ይዞት ወደ ውጭ ወጣ እንዳለ ባሏን በብስጭት የውሰደባት ወታደሩን እመጫቷን ሊጠብቅ ና ሊያስታምም ሲገሰግስ ተመለከ አዉቆታል ሲያሳድዱት ከነበሩት ወታደሮች መሀል አንዱ ነዉ ...የሰማይ እምባ እየወረደ ነዉ ተኩሱም ቆሟል ወታደሩም ልጁን እንዳቀፈ ወደጫካው ሽመቀ እድፍጦ ጠበቀ ልጁም ዝም ተሰኝቷል በመጋሰገስ ላይ የነበረዉ ወታደር ትንሿ ጎጆ ደረሰ መሳሪያውን ጥሎ እንዲንበረከክ እያነከሰና ወደፊት እየተጠጋው ተዛዝ አስተላለፈ አጭር ቁንጣ የለብሰው ወታደር ባማንከሱ ሳቢያ አውቆታል በፍጥነትም ለመተኮስ መሳሪያ የያዘበት እጁን ልጅ ወዳቀፈው ወታደር ሲዘረጋ ተቀደመ ተዝለፍልፎም ወደቀ በወደቀበትም ሆኖ መተኮስ ጀመረ ልጅ ያቀፈው ወታድርም እግሬ አዉጭኝ ብሎ እያነከስ ልጁን እንዳቀፈ ተምዘገዘገ ...... ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ::"
ፋጥዋ በኔ ሞት ስንት ዙርባ ጋሌሳ ጫት ቅመሽ ነው እንዲህ የተተረተርሽው አቦ?አጃኢብ ነው ዋርካ 'ማታሳየን ጉድ የለም...ፋጥውይ ለማንኛውም የዚህን ምርቃና ወለድ ቀደዳ ፍጻሜ ለማንበብ በጉጉት እየጠበቅኩ ስለሆነ የገራዶም ይሁን የአምባሰል ጫት ቃም ቃም አድርጊና ተተርተሪልን...
ቅዥቢው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:57 pm

ወሎ ገራገሩ

Postby ወረኢሉ » Sun Sep 11, 2011 2:09 pm

ሰላም የውሎ ገራገሩ ቤት ታዳሚዎች በመሉ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ የሰላም: የደስታ: የፍቅር ይሁንላችሁ !!!

ወረኢሉ
ወረኢሉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 382
Joined: Wed Feb 21, 2007 1:52 pm
Location: ማርዬ - አምባሰል

ሰላም

Postby ሶረኔ » Mon Sep 12, 2011 6:42 pm

እንኳን ለአዲስ አመት አደረሳችሁ !

የዚህ ቤት በጣም ነዉ የምወደው አሁን ግን ሰውሁሉ ጠፍቷል በሰላም ነዉ እረ ሰለሀገራችን አስነብቡን ቤቱ እንዳማረበት ይቆይ :: እስኪ ለአዲስ አመት ስጦታ:-

እነም አንተ እኮ ነኝ:-

ገጽታህን ሳየው መልኬ የሚመሰለኝ
ክንድህ ሲዘረጋ እጄን የሚነካኝ
ቁመናህን ሳየው ልኬን ያስታወስኝ
ቁርጥ አንተን መሳይ እኔም አንተ እኮ ነኝ::

እኔ አንተን አንተ ስል አንተ አንተ እምትለኝ
እንከን የለሽ ፍጥረት አምሳያህ እኔ ነኝ
ራስክን ስትፈልግ ሁሌ እምትዳስሰኝ
እግረኛ ቆራቢህ አብሮ አደግ እኔ ነኝ::

ሰታዝን አዝኜ ስትስቅ የፈካሁኝ
በሰደት በውርደት ከጎንህ የቆምኩኝ
ኪዳኑን ጠባቂ በቃልህ የኖርኩኝ
እውነተኛ ወዳጁ አካልህ እኔ ነኝ::

ታሪኬ ታሪክህ ስምህ ስሜ ያልኩኝ
ለፈቃድህ ኑሬ ሞትህ የገነዘኝ
ማንም ያላወቀኝ አንተም ቁብ ያላልከኝ
አብሮ አደግ ጓደኛህ ጥላህም እኔ ነኝ::

መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ!!!!

ሶረኔ (ከደኖች መካከል)
• ሶረኔ፥ – ሶረኔ፥ –
• ንፋስ፥ – አወዛውዞ፥ –
• የጣለሽ፥ – ወደ፥ – እኔ
ሶረኔ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Mon Sep 12, 2011 6:24 pm
Location: Wollo

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests