የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት

Postby ዘ ተዋሕዶ » Thu Oct 16, 2008 11:59 am

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

ውድ ወገኖች እንደምን አላችሁ ?

በዚህ ርዕስ ሥር : ለመግባቢያነት ያህል ግዕዝ ቋንቋ እንማማራለን

ለጊዜው ቀለል ባለ መንገድ እንጀምረውና ሁኔታውን እያየንም በጋራ እንዲሰፋ እናደርጋለን

ትምሕርቱ በቋንቋው ላይ ብቻ ያተኮረ ስለሆነ : ሌሎች አርዕስቶችን አያስተናግድም ::

የግዕዝ ቋንቋን ስናጠና በቅድሚያ ማወቅ ያለብን ፊደላቱን ነው ::

ከ ሀ እስከ ፐ ያሉት ፊደላት : ሁሉም የግዕዝ አይደሉም ::
ይህም ማለት {የሰው እና የቦታ ስሞች ካልሆኑ በቀር } በግሥ አረባብም ሆነ በዐረፍተ ነገር አመሰራረት ላይ የማይገኙ ማለት ነው

የግዕዝ ያልሆኑት ፊደላትም የሚከተሉት ናቸው

1. ሸ ሹ .......
2. ቸ ቹ ......
3. ኘ ኙ ......
4. ኸ ኹ .....
5. ዠ ዡ .....
6. ጀ ጁ .......
7. ጨ ጩ .....: ናቸው ::

ሌሎች ግን ሁሉ {ኰ - ጐ - ቈ - ኈ } የሚባሉትን ጨምሮ የግዕዝ ፊደላት ናቸው ::

ለዛሬው ከላይ በመግቢያዬ ላይ የጠቀስሁትን የግዕዝ ሐረግ {ዐረፍተ ነገር } ላብራራ

በ -ስመ አብ ወ -ወልድ ወ -መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ


{በ} የሚለው ቃል በዚህ ንባብ ትርጉሙ አይለውጥም ያው {በ} ነው ::

{ስመ} - የሚለው ቃል : ሰመየ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም : ስም አወጣ - ሰየመ ማለት ነው : {ስም} ::

{አብ} - ተአበወ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አባት ሆነ ማለት ነው :: {አባት}

{ወልድ} - ወለደ {ለ : አይጠብቅም } ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ወለደ {ለ : ይጠብቃል } :: {ልጅ}

{መንፈስ} - ነፍሰ : ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ነፈሰ ማለት ነው :: {ረቂቅ}

{ቅዱስ} - ቀደሰ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም {በዚህ ቃል ብቻ } አመሰገነ : አከበረ ማለት ነው :: {ክቡር : ምስጉን}

{አሐዱ} - አሐደ : ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም አንድ አደረገ ማለት ነው :: {አንድ}

{አምላክ} - መለከ ካለው ግሥ የተገኘ ሲሆን : ትርጉሙም ገዛ ማለት ነው : {ገዥ}

{ወ }. ወልድ ወ .መንፈስ ቅዱስ {ወ የሚለው በዚህ ዐረፍተ ነገር ብቻ } {እና } ተብሎ ይፈታል ::

{የመጀመሪያው የግዕዙ ቃል} ሲሆን {የመጨረሻው ደግሞ የአማርኛ ቀጥተኛ ትርጉሙ} ነው ::

ጠቅለል ያለ ትርጉሙ

በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ
ወይም
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማለት ነው ::

ስለ አቀራረቡ ማኛውንም ዓይነት አስተያየትም ሆነ ጥያቄ በደስታ እቀበላለሁ ::

በሚቀጥለው ትምሕርታችን
{የግዕዝ} ፊደላት ለግዕዝ ቋንቋ ያላቸውን መሰረትነት እንማማራለን

ስብሐት ለእግዚአብሔር - ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
አሜን

ይቆየን
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Thu Oct 23, 2008 9:19 am, edited 3 times in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Thu Oct 16, 2008 12:05 pm

ሀ - ግዕዝ -------------------------- {1ኛ }
ሁ - ካዕብ ------------------------- {2ኛ }
ሂ - ሳልስ -------------------------- {3ኛ }
ሃ - ራብዕ -------------------------- {4ኛ }
ሄ - ሐምስ {ም } አይጠብቅም -- {5ኛ }
ህ - ሳድስ {ድ } አይጠብቅም -- {6ኛ }
ሆ - ሳብዕ {ዕ } ይዋጣል -------- {7ኛ } .....
እያለ እስከ ፐ ይቀጥላል

{ኰ - ጐ - ቈ - ኈ } የሚባሉት ፊደላት ግን ሆሄያቸው እንደ ሌሎቹ ፊደላት ሰባት {ሀ -ሆ } ሳይሆን አምስት ብቻ ነው ::

ኰ - ግዕዝ
ኲ - ሳልስ
ኳ - ራብዕ
ኴ - ሐምስ
ኵ - ሳድስ እያለ ይቀጥላል

የነዚህን {ልዩ } ፊደላት የድምጽ አወጣጣቸውን በጽሑፍ ማስቀመጥ ያስቸግራል :
ምናልባት : የግዕዝ ፊደል {በቄስ ትምሕርት ቤት } በደንብ የተማሩ ሰዎች በአካባቢያችሁ ካሉ በመጠየቅ የበለጠ መረዳቱ ብትችሉ ጥሩ ነው ::

ማሳሰቢያ

አማርኛ : የሥነ ጽሁፍ ቋንቋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ {ቋንቋዎች } እየተቀላቀሉ ስለሄዱ
የግዕዝ ያልሆኑ {ሽ -ቸ -ኘ -ኸ -ጀ -ጨ } ፊደላትም {እንደ ግዕዝ ፊደል ሁሉ } : ግዕዝ - ካዕብ ............ሳብዕ } እየተባሉ ይዘምታሉ ::

በቀጣይ ደግሞ ስለ ግዕዝ ቁጥሮች እንማራለን

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ይቆየን
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Thu Oct 16, 2008 4:08 pm

የግዕዝ ቁጥር {አኅዝ} እንዴት እንደሚጻፍ አልቻልሁበትም
የምታውቁ ካላችሁ እስኪ ባካችሁ ጠቁሙኝ

እስከ ዚያው ግን የእንግሊዝኛውን {ዐረብኛውን} አኃዝ እየተጠቀምሁ አነባበቡን ብቻ ልቀጥል

1 - አሐዱ

2 - ክልኤቱ {ል} ይዋጣል

3 - ሰለስቱ

4 - አርባዕቱ

5 - ሐመስቱ

6 - ሰደስቱ

7 - ሰብዓቱ

8 - ሰመንቱ

9 - ተስዓቱ

10 - ዐሠርቱ

በሌላ አባባል {የቀንን ቁጥር ለመግለጽ ሲፈለግ}

አሚሩ

ሰኑዩ

ሰሉሱ

ረብዑ {ብ} አይጠብቅም

ሐሙሱ

ሰዱሱ

ሰብዑ

ሰሙኑ {ሙ} አይጠብቅም

ተሱዑ {ሱ} አይጠብቅም

አሥሩ {ሥ} አይጠብቅም {""ወ"" የሚለው የግዕዝ ቃል and} የሚለውን የእንግሊዝኛ ትርጉም ይተካል

11 - አሥሩ ወ-አሐዱ እያለ እስከ 19 {አሥሩ ወተሱዑ} ይቀጥላል

20 - ዕሥራ : ዕሥራ ወአሐዱ {ዕሥራ ወተሱዑ} እያለ ይቀጥላል

30 - ሰላሳ : ሰላሳ ወአሐዱ {ሰላሳ ወተሱዑ}እያለ ይዘልቃል

40 - አርብዓ : አርብዓ ወ-አሐዱ {አርብዓ ወተሱዑ} እያለ ይቀጥላል

50 ኅምሳ : ኅምሳ ወ-አሐዱ {ኅምሳ ወ-ተሱዑ} እያለ ይቀጥላል

60 - ስሳ : ስሳ ወአሐዱ {ስሳ ወ-ተሱዑ} እያለ ይቀጥላል

70 - ሰብዓ : ሰብዓ ወአሐዱ {ሰብዓ ወተሱዑ}እያለ ይቀጥላል

80 - ሰማንያ : ሰማንያ ወ-አሐዱ {ሰማንያ ወተሱዑ} እያለ ይቀጥላል

90 ተስዓ {ዓ} ይዋጣል : ተስዓ ወአሐዱ {ተስዓ ወተሱዑ} እያለ ይቀጥላል

100 : ምዕት {ዕ} ድምጹ አይወጣም
አሐዱ ምዕት : እያለ እስከ ተስዓቱ ምዕት {900} ይቀጥላል

101 : አሐዱ ምዕት ወ-አሐዱ እያለ እስከ ዐሠርቱ ምዕት - 1,000 ይቀጥላል ::

ዐሰርቱ ምዕት - አንድ ሺህ - 1,000

ዕሥራ ምዕት - ሁለት ሺህ -2,000

ሰላሳ ምዕት - ሶስት ሺህ - 3,000

አርብዓ ምዕት - አራት ሺህ - 4,000

ኅምሳ ምዕት - አምስት ሽህ - 5,000

ስሳ ምዕት - ስድስት ሺህ - 6000

ሰብዓ ምዕት - ሰባት ሺህ - 7,000

ሰማንያ ምዕት - ስምንት ሺህ - 8,000

ተስዓ ምዕት - ዘጠኝ ሺህ - 9,000

ዕልፍ - አሥር ሺህ - 10,000 :: ዕልፍ ሲል {ል} አይጠብቅም

ክልኤቱ ዕልፍ - ሃያ ሺህ - 20,000: ሰለስቱ ዕልፍ - ሰላሳ ሺህ.... እያለ ይቀጥላል

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ይቆየን
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Wed Jun 02, 2010 10:44 pm, edited 1 time in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ጎርዶ » Sat Oct 18, 2008 5:23 am

ቋንቋ መማር ጥሩ ነው ልመንትፍሽ ማለት በግዕዝኛ ምን ማለት ነው ? ?
ጎርዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 230
Joined: Tue Dec 14, 2004 6:57 am
Location: spain

Postby ብርኃናዊት » Mon Oct 20, 2008 4:57 pm

:arrow:
Last edited by ብርኃናዊት on Mon Oct 20, 2008 7:35 pm, edited 1 time in total.
ብርኃናዊት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3302
Joined: Sat Oct 27, 2007 3:57 am

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Oct 22, 2008 9:10 pm

ውድ ወገኖች እንደምን አላችሁ ?

የግዕዙን ቁጥር አጻጻፍ እስካገኝ ሌላውን ልቀጥል
አጻጻፉን እንዳገኘሁ
ወደ ቁጥሩ {አኅዙ} እመለስበታለሁ
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

የግዕዝ ቋንቋ መግቢያ

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Oct 22, 2008 9:27 pm

ለግዕዝ ቋንቋ ዋናው መሰረት የግዕዝ ፊደላት ሲሆኑ እነሱንም ከነስያሜያቸው {ከግዕዝ እስከ ሳብዕ ያሉትን) ጠንቅቆ ማወቅ የግድ ይላል ::

ይህን ከተረዳን : ወደ ዋናው ግዕዝ ቋንቋ ለመግባት ቁልፉን አገኘነው ማለት ነው ::

ከግዕዝ እስከ ሳብዕ የቆጠርናቸው የፊደላት ስያሜዎች ጥቅማቸውን በሚቀጥለው የትምሕርታችን ክፍል እናየዋለን ::

ስለ ግዕዝ ቋንቋ ስናጠና ቋንቋውን ብቻ ሳይሆን አነባበቡንም ጭምር ነው ::

የግዕዝ ቋንቋ ሲነገር {ከፍና ዝቅ ተደርጎ የሚነገር} የራሱ የሆኑ የአነጋገር (ዜማ) ስልቶች አሉት ::

የነዚህ ስልቶች ስያሜያቸው

1. ተነሽ
2. ተጣይ
3. ሰያፍ
4. ወዳቂ ይባላሉ ::

አጠቃቀማቸው
1. ተነሽ {የሚነሳ. ከፍ ባለ ድምጽ የሚነገር ማለት ነው}
2. ተጣይ {ዝቅ ባለ ድምጽ የሚነገር ማለት ነው }
3. ሰያፍ {የተነሽ አይነት ባሕርይ ያለው ከፍ ባለ ድምጽ የሚነገር ማለት ነው}
4. ወዳቂ {እንደ ተጣይ አይነት ባሕርይ ያለውና ዝቅ ባለ ድምጽ የሚነበብ ማለት ነው ::
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Wed Jun 02, 2010 10:48 pm, edited 1 time in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Oct 22, 2008 10:00 pm

ሀ ግዕዝ
ሁ ካዕብ
ሂ ሳልስ
ሃ ራብዕ
ሄ ሐምስ
ህ ሳድስ
ሆ ሳብዕ
እያልን እስከ ፐ የቆጠርናቸው ስያሜዎች
ተነሽ
ተጣይ
ሰያፍ
ወዳቂ በሚሉት ውስጥ እየገቡ የሚያገለግሉበት ሁኔታ በሚክተለው መንገድ ቀርቧልና ረጋ ብለው በማስተዋል ይከታተሉት ::

ተነሽ : በግዕዝ. በካዕብ. በሳልስ. በሳብዕ. እነዚህ የመጨረሻ ፊደላቸው የሆኑ ቃላት ሁሉ ተነሽ ይባላሉ :: ተነሽ : ሐምስና በሳድስን አይጠቀምም ::

ምሳሌ
በግዕዝ : ቀደሰ
በካዕብ : ቀደሱ
በሳልስ : ተቀደሲ
በራብዕ : ተቀደሳ
በሳብዕ : ቀደስዎ ይላል :
የዚህ ቃል አነጋገር በሙሉ : ከፍ ባለ ድምጽ ይነገራል ::

ተጣይ : በሳድስ ብቻ ይነገራል :
ምሳሌ ማርያም : ሚካኤል : ቃል : ምሕርት የመሳሰሉና ዝቅ ባለ ድምጽ የሚነገሩ ሁሉ የመጨረሻ ፊደላቸው ሳድስ ከሆነ ተጣይ ይባላል ::

ሰያፍ : ከፍ ባለ ድምጽ ሆኖ በሳድስ ብቻ ይነገራል : ይህም የተጣይ ተቃራኒ ማለት ነው ::

ምሳሌ : ይቄድስ : የሐውር : ገብርኤል : ወዘተ : የመሳሰሉና ከፍ ባለ ድምጽ የሚነገሩ ሁሉ የመጨረሻ ፊደላቸው ሳድስ ከሆነ ሰያፍ ይባላል ::

ወዳቂ በግዕዝ. በካዕብ. በሳልስ. በሐምስ : በሳብዕ. ይነገራል ::
ምሳሌ : አሐተ : አሐዱ : አሐቲ : ሉያ : ሃሌ : ሀሎ : የመሳሰሉና ዝቅ ባለ ድምጽ የሚነገሩ ሁሉ የመጨረሻ ፊደላቸው የነዚህ ስያሜዎች ከሆነ ወዳቂ ይባላል ::

መጨረሻው ሳድስ የሆነ በሙሉ የተጣይ መሆኑን ከላይ አይተናል : እዚህ ላይ ለየት ባለ ሁናቴ ልብ የምንለው አንድ ነገር አለ :
: የምትለው ቃል ተጣይ መሆን ሲገባት : ለብቻዋ ተለይታ ወዳቂ ናት ::

ይህ እንግዲህ የቋንቋው ህግ ነው ::
ከ : ዝ : በቀር ሌሎች መጨረሻቸው ሳድስ የሆኑ ቃላት ሁሉ ተጣይ ናቸው :
ዝ : ግን መደቧ ከወዳቂ ጋር ነው ::

: ማለት : የአማርኛ ትርጉሙ ይህ ማለት ነው ::
የሌሎችንም ትርጉም በሌላ ጊዜ አቀርባለሁ

ማሳሰቢያ
በዛሬው ትምሕርታችን የተማርናቸውን : ድምጻቸውን በጽሑፍ ብቻ ሙሉ ለሙሉ ማስረዳት ስለሚያስቸግር : አነባበቡን በተመለከተ ግዕዝ የሚያውቁ ሰዎች ስታገኙ ቀረብ እያላችሁ ለመረዳት መሞከሩ ብልህነት ነው ::

ስብሐት ለእግዚአብሔር - ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን

ይቆየን
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Mon Oct 27, 2008 4:42 pm

ሰላም ወገኖች እንደምን አላችሁ ?

የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት እንዴት ነው ?

እስካሁን ድረስ 3 የትምሕርት ዓይነቶችን ተምረናል

1. የግዕዝ ፊደላትን ከአማርኛው ለይተን ከግዕዝ እስከ ሳብዕ ያለውን ስያሜያቸውን : ተምረናል :

2. የግዕዝ ቁጥሮችን : ሙሉ በሙሉ ባናጠናቅቃቸውም መሰረታዊ የሆኑትን ቁጥሮችና አነባበባቸውን ጭምር ለማየት ሞክረናል

3. ተነሽ : ተጣይ : ሰያፍ : ወዳቂ :: የሚባሉት ከፊደላትና ከግዕዝ ቋንቋ ጋር ያለቸውን ቀዳሚነት እና ማዕከላዊነት ተረድተናል ::

ከላይ የገለጽኋቸውን ነጥቦች : ምን ያህል እንደተገነዘባችኋቸው ለማወቅ እንዲያስችለኝ
በመወያያው መድረክ ጥያቄዎች (የሙከራ ፈተና) አቀርባለሁና ጎራ ብላችሁ ሞክሩ ::

ከፈተናው በኋላ ትምሕርቱን እንቀጥላለን
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Mon Nov 03, 2008 11:32 pm

ወገኖች እንደምን ሰንብታችኋል ::

ለዛሬው ትምሕርታችን

ተነሽ : ተጣይ : ሰያፍ : ወዳቂ ::

የሚባሉትን ዘርዘር አድርገን ለማየት እንሞክራለን ::

የእነዚህ ነጥቦች : ዋና ጥቅማቸው :

1ኛ : ግዕዝ ቋንቋ : ክቋንቋነቱ በተጨማሪ : የራሱ የሆነ የአነባበብ ስርዓት አለው ::

ይህ የንባብ ሥርዓትም
ተነሽ : ተጣይ : ወዳቂ : ሰያፍ : በሚባሉ አራት መለያ ነጥቦች ይገልጻል ::

በተነሽ[b] የተመደቡት : [b]ግዕዝ : ካዕብ : ሳልስ : ራብዕና ሳብዕ[b] : እነዚህ ሆሄያት/ፊደላት መጨረሻቸው የሆኑ ቃላት ሲሆኑ : የሁሉም ድምጻቸው ከፍ ባለ ቃል የሚነገሩ ናቸው ::

[b]በሰያፍ
የሚመደበውም : የመጨረሻ ፊደሉ/ሆሄው [/b]ሳድስ ብቻ ሲሆን : ይህም ድምጽ እንደ ተነሽ ከፍ ባለ ቃል ነው የሚነገረው ::

በተጣይ የሚመደብ : የመጨረሻ ፊደሉ/ሆሄው ሳድስ ብቻ ሲሆን : በሰያፍ ተቃራኒ ዝቅ ባለ ድምጽ ይነገራል ::

በወዳቂ የሚመደቡትም : የመጨረሻፊደላቸው/ሆሄያቸው ግዕዝ : ካዕብ ; ሳልስ : ራብዕ : ሐምስ : ሳብዕ ሲሆኑ : ሳድስ በሙሉ የተጣይ ሲሆን : ብቻ ተለይቶ ምድቡ የወዳቂ ነው ::

ከመጀመሪያው በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽሁት : አነባበቡን በጽሑፍ (ሙሉ በሙሉ) መግለጽ ያስቸግራል :::

ስለሆነም : የበለጠ ለመረዳት ቋንቋውን በደንብ የተማሩ ሰዎች በካባቢያችሁ ካሉ : እንዴት እንደሚነበብና ስለ ድምጽ አወጣጡም መረዳቱ የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል ::

ስብሐት ወክብር ለእግዚአብሔር
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን


አሜን

ይቆየን
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Tue Nov 04, 2008 11:50 am

ሰላም ወገኖች
እንደምን አላችሁ ?

ቀደም ሲል የግዕዝ ያልሆኑ ፊደላትን ስጽፍ ሁሉንም አላስቀመጥሁም ነበርና እስኪ አሁን ማስተካከያ ለማድረግ ልሞክር ::

ሸ :
ቨ :
ቸ :
ኘ :
ኧ :
ኸ :
ዠ :
ጀ :
ጨ :

የሚጻፈው ሺፍትንና P ን ተጭነን ነው ::

ከሚባሉት በቀር

ሌሎች


ሟ........... በሙሉ : የግዕዝ ፊደሎች አይደሉም ::

የቦታና የሰው ወይም የዕቃ ስም ካልሆነና በግዕዝ ቋንቋ ስም የሌለው ከሆነ : በየትኛውም የአማርኛ ፊደል በተጻፈበት ሁኔታ እንዳለ ሆኖ : በግዕዝ ጽሑፍ ውስጥ ሊገኛ ይችላል :;
ከዛ ውጭ ግን : በቋንቋው ሥርዓት ወይም አረባብ ውስጥ አይገባም ::

ይቆየን
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Wed Jun 02, 2010 10:35 pm, edited 1 time in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Nov 05, 2008 6:15 pm

ውድ ወገኖች እንደምን አላችሁ ?

የግዕዝ ቋንቋ : በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል ::

1ኛ አገባብ/ሰዋስው - grammar
2ኛ ነባር - noun
3ኛ ግሥ - verb, ናቸው ::

1ኛ
አገባብ ማለት በእንግሊዝኛው Grammar ጋር ይመሳሰላል ወይም ተቀራራቢነት አለው ::
አገባቦች ከግሥ ወይም ከስም በፊትና በኋላ እየገቡ ትርጉም የሚሰጡና አረፍተ ነገሩ እንዳይቆም (ግሡ እንዳያስር) የሚያደርጉ ናቸው ::

ለምሳሌ

[b]አብርሐም ወጽአ እምብሔሩ

አብርሐምን ከሀገሩ ወጣ ያለውን

አብርሐም ድኅረ ወጽአ እምብሔሩ ሖረ ምድረ ከነዓን
አብርሐም ከሀገሩ ከወጣ በኋላ ወደ ከነዓነ ምድር ሄደ

ድኅረ : የሚለው አገባብ : ወጽአ የሚለውን ግሥ እንዳያስር አደረገው :
ወይም አረፍተ ነገሩን (ከወጣ ኋላ በማሰኘት) አስረዘመው ማለት ነው ::


አገባብ
1. ንዑስ አገባብና
2. ዓቢይ አገባብ :
3. ደቂቅ አገባብ : ተብሎ በሶስት ይከፈላል ::

1ኛ ዓቢይ አገባብ
እስመ-አምጣነ-- እና
አኮኑ --------- እና
በእንተ -------- ስለ
በይነ ---------- ስለ
እንበይነ ------- ስለ
ህየንተ --------- ስለ
ተውላጠ ------- ስለ - ለውጥ
ፍዳ-ብቅል------- ስለ - ምትክ
ኅበ- መንግለ -- ወደ
ወ(እ)ደ -------
እንዘ ---------- እየ
መጠነ-አቅመ---
ከመ-ሕገ ------- እንደ
በዘ ------------ በየ
እምዘ ---------- ዘንድ
አርዓያ-አምሳለ--- እንደ (አምሳል)
እመ ----------- ቢ ...................... ይቀጥላል ::

ይቆየን :

ስብሐት ለእግዚአብሔር
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Tue Nov 01, 2011 5:49 pm, edited 5 times in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Sat Nov 15, 2008 7:21 am

2ኛ ነባር noun

ነባር ማለት : እንደ ስሙ ሁሉ የማይንቀሳቀስ ማለት ሲሆን : እንደ ግሥ ዓይነት አወራረድ የማይከተልና የማይተነተን : የቦታ : የሰውና የሌሎችም ፍጥረታት ስም እና የተለያዩ አገባቦች : እንዲሁም የማይራቡ ግሶች ስብስብ ነው ::

መጨረሻውን ከግዕዝ እስከ ሳብዕ ባሉ ሆህያት (ፊደሎች) እያደረገ የሚገኝ ነው ::

ምሳሌ

. የሰው ስም (የፈጣሪን : የማንኛውም ሰውና መላእክትንም ስም ያካትታል)

. የቦታ ስም (የየትኛውንም አገር ባህር የብስ : አካባቢ : መንደር : ተራራ :በሙሉን ያጠቃልላል)

. የነገሮችች ስም : (የዕፅዋት : የእንስሳት : ማንኛውም የመገልገያ አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን ሁሉ ስሞች ይገልጻል)

ይቆየን

ስብሐት ለእግዚአብሔር
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Tue Nov 01, 2011 5:52 pm, edited 5 times in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Tue Dec 23, 2008 1:31 am

ይቀጥላል
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Wed Jun 02, 2010 11:20 pm, edited 2 times in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ናጁ. » Sat Jan 31, 2009 3:02 am

ዘ ተዋሕዶ wrote:3ኛ አገባብ

አገባብ ማለት በእንግሊዝኛው Grammar ጋር ይመሳሰላል ወይም ተቀራራቢነት አለው ::
አገባቦች ከግሥ ወይም ከስም በፊትና በኋላ እየገቡ ትርጉም የሚሰጡ ናቸው ::

አገባብ
1. ንዑስ አገባብና
2. ዓቢይ አገባብ :
3. ደቂቅ አገባብ : ተብሎ በሶስት ይከፈላል ::

1ኛ ዓቢይ አገባብ
እስመ-አምጣነ-- እና
አኮኑ --------- እና
በእንተ -------- ስለ
በይነ ---------- ስለ
እንበይነ ------- ስለ
ህየንተ --------- ስለ
ተውላጠ ------- ስለ - ለውጥ
ፍዳ-ብቅል------- ስለ - ምትክ
ኅበ- መንግለ -- ወደ
ወ(እ)ደ -------
እንዘ ---------- እየ
መጠነ-አቅመ---
ከመ-ሕገ ------- እንደ
በዘ ------------ በየ
እምዘ ---------- ዘንድ
አርዓያ-አምሳለ--- እንደ (አምሳል)
እመ ----------- ቢ ...................... ይቀጥላል ::

ይቆየን :

ስብሐት ለእግዚአብሔር
ናጁ.
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 374
Joined: Wed Aug 23, 2006 5:30 am

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests