የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Jun 02, 2010 7:51 pm

3ኛ ግሥ

ለግዕዝ ቋንቋ : መሠረት የሆነው
ግሥ /Vocavulary : መሠረቶቹ :
ከዚህ የሚከተሉት : ስምንት አስራው /አርእስት :

...ግዕዝ__ትርጉም_ 2ኛ ትርጉም________ልዩ ባህርይ
1. ቀተለ... ገደለ............................ (በግዕዝ ጀምሮ ግዕዝ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
2. ቀደሰ....አመሰገነ...... ለየ ......... በግዕዝ ጀምሮ ግዕዝ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ መሀሉ ጠብቆ የሚነገር)
3. ባረከ.... አመሰገነ.... ባረከ......... በራብዕ ጀምሮ ግዕዝ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
4. ገብረ....አደረገ........ ሠራ ........ በግዕዝ ጀምሮ ሳድስ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
5. አእመረ...አወቀ.....አሳወቀ.......
6. ሴመ.....ሾመ .............................. በሐምስ ጀምሮ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
7. ብህለ....አለ ................................ በሳድስ ጀምሮ ሳድስ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
8. ቆመ....ቆመ ................................ በሳብዕ ጀምሮ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)

ሲሆኑ :

ሌሎች : ግሦች በሙሉ በነዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው ::

ግሥ ማለት : በሃላፊ ጊዜ የሚጀምር ሆኖ : ከዛም እየተራባ ወይም እየተባዛ የሚገሠሥ ወይም የሚተነተን የትምሕርት ዓይነት ነው ::

ለምሳሌ

ግዕዝ ______አማርኛ _________ የጊዜ መለያ
ቀተለ :........... ገደለ :.................. (የሃላፊ ጊዜ - Past)
ይቀትል :........ ይገድላል :.......... (ትንቢት - future)
ይቅትል :....... ይገድል ዘንድ ..... (ዘንድ አንቀጽ ...)
ይቅትል :....... ይግደል :............... (ትእዛዝ command)

ቀቲል : ቀቲሎት ...... መግደል ........... ንዑስ አንቀጽ (በኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት መሰረት : መጀመሪያው ይህ (ዘር - ስም ) ነው )

ቀታሊ :............. የገደለ :.................... ነጠላ ለወንድ (man)
ቀታልያን :......... የገደሉ :................... የብዙ ወንዶች (plural)
ቀታሊት :.......... የገደለች :................. ነጠላ ለሴት (female)
ቀታልያት :......... የገደሉ :................... ለብዙ ሴቶች (plural)

ቅቱል :.............. የገደለ :................. ውስጠዘ (በውስጠ ታዋቂነት ዘ : ያለበት ማለት ነው ::
ቅቱላን :............. የገደሉ :................ ለብዙ ወንዶች
ቅትልት :............ የደለች :................ ለሴት
ቅቱላት :............ የገደሉ :................ ለሴቶች (ብዙ )

ቀትል :.................. ግድያ -ጦርነት :............ ዘር -ስም -ባለቤት
ቀትላት :................ ግድያዎች - ጦርነቶች ... (ብዙ )
ቅትለት :................ መግደል -መገደል :........ ሳቢ - ዘር (ቀትል -ዘር ከሚለው ጋር የሚመሳሰል ለማለት ይመስላል )
ቅትለታት :............. >> :...................... (ብዙ )

መቅትል :............... መግደያ : (ለመሳሪያው ) :.. መስም ውስጠ ዘ (በውስጡ የ : ዘ : ባህርይ ያለው ::
መቅትላን :............... መግደያዎች :............. (ብዙ )
መቅትልት ............... መግደያ ...................... ለሴት
መቅትላት ................... >> ...................... (ብዙ -ለሴቶች )

ምቅታል :................... መግደያ (ለቦታ ) .......... ምዕላድ
ምቅታላን .................. >> ........... ለብዙ

ቀተለት (ተ -አይጠብቅም ) :.. የገደሉ :................ መድበል :: (መድበል የሚለው : የአንድ ግሥ አወራረድ መጨረሻው : ነው )

ከዚህ በላይ : ለመግለጽ የሞከርሁት : የግሥን ምንነት ለመግለጽ ያህል ነው ::
ግሥ ሲባል : ጠቅለል ባለ ሁኔታ ይህን ሲመስል :
ሁሉም ግሦች : በዚህ ዓይነት የየራሳቸው አካሄድን ይከተላሉ ::

ይቆየን

ስብሐት ለእግዚአብሔር
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Fri Jun 04, 2010 3:19 am, edited 9 times in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby እንሰት » Wed Jun 02, 2010 11:46 pm

ዘ ተዋሕዶ wrote:የግዕዝ ቁጥር {አኅዝ} እንዴት እንደሚጻፍ አልቻልሁበትም
የምታውቁ ካላችሁ እስኪ ባካችሁ ጠቁሙኝ

1 - አሐዱ

2 - ክልኤቱ {ል} ይዋጣል

10 - ዐሠርቱ

ሰሙኑ {ሙ} አይጠብቅም

11 - አሥሩ ወ-አሐዱ እያለ እስከ 19 {አሥሩ ወተሱዑ} ይቀጥላል

20 - ዕሥራ : ዕሥራ ወአሐዱ {ዕሥራ ወተሱዑ} እያለ ይቀጥላል
100 : ምዕት {ዕ} ድምጹ አይወጣም
አሐዱ ምዕት : እያለ እስከ ተስዓቱ ምዕት {900} ይቀጥላል

101 : አሐዱ ምዕት ወ-አሐዱ እያለ እስከ ዐሠርቱ ምዕት - 1,000 ይቀጥላል ::

ዐሰርቱ ምዕት - አንድ ሺህ - 1,000

ዕሥራ ምዕት - ሁለት ሺህ -2,000
ዕልፍ - አሥር ሺህ - 10,000 :: ዕልፍ ሲል {ል} አይጠብቅም

ክልኤቱ ዕልፍ - ሃያ ሺህ - 20,000: ሰለስቱ ዕልፍ - ሰላሳ ሺህ.... እያለ ይቀጥላል

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ይቆየን

ይደረስ ለዘ ተዋህዶ ለፈጣኑ መልስህ እ/ር ይስጥልኝ::
እነዚህ በተራ ቁጥር 1-2 የዘረዘርኩዋቸው ጥምሮች ዝምድናቸው ምንድን ነው በግእዝ አቆጣጠር?

(1) 2,20, 200, 2000,

(2) 10,20
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዘ ተዋሕዶ » Fri Jun 04, 2010 11:10 pm

መራህያን ወይም ተውላጠ ሥም (pronoun) የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው ::

የሩቅ ነጠላ
ውእቱ ........... እሱ (ዝንቱ .... ይህ)
ይእቲ .......... እሷ (ዛቲ ......... ያች)

የሩቅ ብዙ
እሙንቱ ....... እነሱ ለወንዶች (ውእቶሙ)
እማንቱ ......... እነሱ -ለሴቶች (ውእቶን)

የቅርብ ነጠላ
አንተ ........... አንተ
አንቲ ........... አንቺ

የቅርብ ብዙ
አንትሙ ............... እናንተ (ለወንዶች)
አንትን ................. እናንተ (ለሴቶ)

የቅርብ-ነባቢ(ነባብያን)
አነ ................... እኔ
ንህነ ................ እኛ

ይቀጥላል
Last edited by ዘ ተዋሕዶ on Sat Jun 05, 2010 11:53 pm, edited 2 times in total.
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

ግዕዝ

Postby ኦሣማ ቦምብላደ » Sat Jun 05, 2010 3:01 am

ጤና ይስጥልኝ!
ከወራት በኍላ ወደ ዋርካ ብቅ ብል አንድ "የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ቤት" የተሰኘ ድንቅ ቤት አየሁ::በር ሳላንኳኳ ዘው አልኩ::መልካም ጅምር ነው::ይህ ጥንታዊ ቋንቋችንና መለያችን በተለያዩ ምክኒያቶች ከ12ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ እየተዳከመ መምጣቱ እውን ነው::ያጋጠሟቸውን ችግሮች ተጋፍጠው ቅድመ ዓያቶቻችን ግዕዝን እዚህ አድርሰውታል::ግዕዝ አሁን ያለበት ሁኔታ አሳዛኝና አሳሳቢ ነው::የግዕዝ ብቸኛ ጠባቂ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ቋንቋውን ከነሙሉ ግርማ ሞገሱ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ መቻሏ አጠያያቂ ሆኗል የሚሉ ወገኖች አሉ::የሚያቀርቡት ምክኒያትም የሀይማኖት መምሕራንን የግዕዝ ቋንቋ ችሎታ ክህሎት ማነስን ነው::እኔ ሙስሊም ሐበሻ ነኝ::ይህን የብዙሃን ፍራችም እጋራለሁ::ግዕዝ ከቤተክርስቲያን ወደ አደባባይ መውጣት አለበት::ይህን ለማድረግም:-
1ኛ.በዚህ ክፍል በግል ተነሳሽነት የግዕዝ ቋንቋን የሚያስተምሩ ዜጎች(Geez online) የሚል የመርጃ መረብ(website) ከፍተው የግዕዝ ቋንቋ ክህሎታቸውን ለብዙሃን የሚያዳርሱበት ሁኔታ እንዲመቻች ጥረት ማድረግ...
2ኛ.የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ተቋም ለዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ላይ የጣለውን ስውር ማዕቀብ አንስቶ ግዕዝ እንደ ሌሎች ቋንቋዎች ትኩረት ተሰጥቶት የግዕዝ ቋንቋ ጥናት አካዳሚ እንዲቋቋም ጥሪ ማድረግ
3.በኣምሓራና ትግራይ ክልል በሚገኙ ት/ቤቶች ግዕዝ እነደ አንድ የትምሕርት ዘርፍ እንዲሰጥና በነዚሁ ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የ/ት ተቋማት የግዕዝ ቋንቋ ትምሕርት ክፍለቶች(Departments)እንዲከፈቱ ሃሳብ ማቅረብ ይኖርብናል!
እኔ በዓረቡ ዓለም ስዞር ያጋጠሙኝን ሳባዊና ግዕዝ ነክ ገጠመኞች እንዲሁም የዓረብኛና የግዕዝን ጽኑ ትስስር የሚያሳዩ መረጃዎችን ጊዜ ሲፈቅድ ይዤ ብቅ እላለሁ!
ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ያላችሁን ለወረወራችሁ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ!
ሁሉም የሚያውቀውን ከማካፈል አይቦዝን!
በርቱ!!!
ሸህ ኦሣማ ቦምብ ላደን
ኦሣማ ቦምብላደ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 145
Joined: Thu May 21, 2009 2:54 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Sun Jun 06, 2010 12:21 am

ባለቤትነትን የሚያመለክቱ (possessives)

እንተ እና : የሚባሉትን : እያቀያየሩ መጠቀም ይቻላል

እንተ - እና - ዘ

እንቲአሁ ---- ዚአሁ -------- የሱ
እንቲአሆሙ- ዚአሆሙ ---- የነሱ (ለወንዶች)
እንቲአሃ ----- ዚአሃ --------- የሷ
እንቲአሆን -- ዚአሆን ------ የነሱ (ለሴቶች)

እንቲአከ ------ ዚአከ ------- ያንተ
እንቲአክሙ-- ዚአክሙ ---- የናንተ (ለወንዶች)
እንቲአኪ ----- ዚአኪ ------- ያንቺ
እንቲአክን ---- ዚአክን ------ የናንተ (ለሴቶች)

እንቲአየ ---- ዚአየ --------- የኔ
እንቲአነ ----- ዚአነ --------- የኛ

በተጨማሪም እለ የሚለውን : በሚከተለው መልኩ መጠቀም ይቻላል ::

እሊአሁ --------- የሱ የሆኑ
እሊአሆሙ ------ የነሱ የሆኑ
እሊአሃ ---------- የእሷ የሆኑ
እሊአሆን -------- የነሱ የሆኑ

እሊአከ ---------- ያንተ የሆኑ
እሊአክሙ ------- የናንተ የሆኑ
እሊአኪ ---------- ያንቺ የሆኑ
እሊአክን --------- የናንተ የሆኑ

እሊአየ ----------- የእኔ የሆኑ
እሊአነ ----------- የእኛ የሆኑ

ይቀጥላል
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Tue Jun 22, 2010 4:31 am

ባለፈው በሁለተኛ ተራ ቁጥር እንዳየነው

ነባር
እንደ እንደ መደበኛው ግሥ/አንቀጽ : የሚረባ/የሚተነተን እንዳልሆነ መግለጻችን ይታወሳል ::

ይሁን እንጅ : ምድባቸው ከነባር የሆኑና የግሥ አመል/አካሄድ ያላቸው (ነባር አናቅጽ) የሚባሉ አሉ :

እነሱም

ውእቱ ======= ነው
ይእቲ ======= ናት

እነዚህ : ነባር አናቅጽ : ረዳት ግሥ ማለትም ግሥን የሚወክሉ/የሚያስሩ ::

በተለይ ውእቱ : ነው በሚለው ብቻ ሳይወሰን በሚከተለው መልኩ በመራህያን እየገባ አገልግሎት ላይ ይውላል ::

ዝንቱ ===== ውእቱ ===== እሱ/ይህ ነው
አንተ ===== ውእቱ ===== አንተ ነህ
አንቲ ===== ውእቱ ===== አንቺ ነሽ
አንትሙ === ውእቱ ===== እናንተ ናችሁ
አንትን ==== ውእቱ ===== እናንተ ናችሁ
አነ ====== ውእቱ ===== እኔ ነኝ
ንህነ ===== ውእቱ ===== እኛ ነን

ውእቶሙ === እነሱ === ወይም እነሱ ናቸው (ለወንዶች)
ውእቶን ==== እነሱ === ወይም እነሱ ናቸው (ለሴቶች)

እነዚህ ከላይ የተገለጡት ሁለቱ

ነባር አናቅጽ/ግሥም : ባለቤትም ሆነው ያገለግላሉ[/u] ::
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ወርቅነሸ » Fri Jun 25, 2010 8:01 am

ዘ ተዋሕዶ wrote:3ኛ ግሥ

ለግዕዝ ቋንቋ : መሠረት የሆነው
ግሥ /Vocavulary : መሠረቶቹ :
ከዚህ የሚከተሉት : ስምንት አስራው /አርእስት :

...ግዕዝ__ትርጉም_ 2ኛ ትርጉም________ልዩ ባህርይ
1. ቀተለ... ገደለ............................ (በግዕዝ ጀምሮ ግዕዝ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
2. ቀደሰ....አመሰገነ...... ለየ ......... በግዕዝ ጀምሮ ግዕዝ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ መሀሉ ጠብቆ የሚነገር)
3. ባረከ.... አመሰገነ.... ባረከ......... በራብዕ ጀምሮ ግዕዝ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
4. ገብረ....አደረገ........ ሠራ ........ በግዕዝ ጀምሮ ሳድስ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
5. አእመረ...አወቀ.....አሳወቀ.......
6. ሴመ.....ሾመ .............................. በሐምስ ጀምሮ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
7. ብህለ....አለ ................................ በሳድስ ጀምሮ ሳድስ አስከትሎ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)
8. ቆመ....ቆመ ................................ በሳብዕ ጀምሮ በግዕዝ የሚጨርስ ላልቶ የሚነገር)

ሲሆኑ :

ሌሎች : ግሦች በሙሉ በነዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው ::

ግሥ ማለት : በሃላፊ ጊዜ የሚጀምር ሆኖ : ከዛም እየተራባ ወይም እየተባዛ የሚገሠሥ ወይም የሚተነተን የትምሕርት ዓይነት ነው ::

ለምሳሌ

ግዕዝ ______አማርኛ _________ የጊዜ መለያ
ቀተለ :........... ገደለ :.................. (የሃላፊ ጊዜ - Past)
ይቀትል :........ ይገድላል :.......... (ትንቢት - future)
ይቅትል :....... ይገድል ዘንድ ..... (ዘንድ አንቀጽ ...)
ይቅትል :....... ይግደል :............... (ትእዛዝ command)

ቀቲል : ቀቲሎት ...... መግደል ........... ንዑስ አንቀጽ (በኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት መሰረት : መጀመሪያው ይህ (ዘር - ስም ) ነው )

ቀታሊ :............. የገደለ :.................... ነጠላ ለወንድ (man)
ቀታልያን :......... የገደሉ :................... የብዙ ወንዶች (plural)
ቀታሊት :.......... የገደለች :................. ነጠላ ለሴት (female)
ቀታልያት :......... የገደሉ :................... ለብዙ ሴቶች (plural)

ቅቱል :.............. የገደለ :................. ውስጠዘ (በውስጠ ታዋቂነት ዘ : ያለበት ማለት ነው ::
ቅቱላን :............. የገደሉ :................ ለብዙ ወንዶች
ቅትልት :............ የደለች :................ ለሴት
ቅቱላት :............ የገደሉ :................ ለሴቶች (ብዙ )

ቀትል :.................. ግድያ -ጦርነት :............ ዘር -ስም -ባለቤት
ቀትላት :................ ግድያዎች - ጦርነቶች ... (ብዙ )
ቅትለት :................ መግደል -መገደል :........ ሳቢ - ዘር (ቀትል -ዘር ከሚለው ጋር የሚመሳሰል ለማለት ይመስላል )
ቅትለታት :............. >> :...................... (ብዙ )

መቅትል :............... መግደያ : (ለመሳሪያው ) :.. መስም ውስጠ ዘ (በውስጡ የ : ዘ : ባህርይ ያለው ::
መቅትላን :............... መግደያዎች :............. (ብዙ )
መቅትልት ............... መግደያ ...................... ለሴት
መቅትላት ................... >> ...................... (ብዙ -ለሴቶች )

ምቅታል :................... መግደያ (ለቦታ ) .......... ምዕላድ
ምቅታላን .................. >> ........... ለብዙ

ቀተለት (ተ -አይጠብቅም ) :.. የገደሉ :................ መድበል :: (መድበል የሚለው : የአንድ ግሥ አወራረድ መጨረሻው : ነው )

ከዚህ በላይ : ለመግለጽ የሞከርሁት : የግሥን ምንነት ለመግለጽ ያህል ነው ::
ግሥ ሲባል : ጠቅለል ባለ ሁኔታ ይህን ሲመስል :
ሁሉም ግሦች : በዚህ ዓይነት የየራሳቸው አካሄድን ይከተላሉ ::

ይቆየን

ስብሐት ለእግዚአብሔር

አቶ ዘ ተዋሕዶ ግዕዝ ከመቅተል ሌላ ትምህርት የለውም እንዴ... እኛ እናስተምረው ትምህርቱ ቀተለ ደመረ ዘለቀ አበደ ስለመ ብለን አስተርምረነዋል :lol: :lol:

ጀሚላ ከችርችል ጎዳና
ወርቅነሸ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 467
Joined: Tue Oct 06, 2009 12:20 pm

Postby ዘ ተዋሕዶ » Sat Jul 10, 2010 5:06 am

ለሶስተኛ መደብ (ለነጠላና ለብዙ ፆታዎች ) የሚያገለግሉ

ለነጠላ ወንድ
. ዝንቱ :
. ዝክቱ : ይህ : እሱ
. ዝ ይህ

ለብዙ ወንዶች
. እሙንቱ
. እሉ
. እሎንቱ
. እልክቱ : እነሱ : (እነሱ )

ለነጠላ ሴት (ፆታ)
. ዛቲ
. ዛ : ያች

ለብዙ ሴቶች
. እማንቱ
. እላ
. እላንንቱ
. እልኩ
. እንትኩ : እነዚህ : እነዛ : (እነሱ)

ከላይ እንደገለጽነው

"ውእቱ " ማለት : "ነው " : ማለት ሲሆን
በአሥሩም መደቦች ያገለግላል :

ነገር ግን :
. ለሩቅ ሴት
. ለሩቅ ወንዶች ና
. ለሩቅ ሴቶች ሲሆን : የተለየ ጸባይ አለው ::

ለምሳሌ

1, ለሩቅ ነጠላ ሴት

ዛቲ : ይህች (ያች ) : ናት : ለሚለው :
የሩቅ ሴት : ውእቱ በማለት ፋንታ :
ዛቲ : ይእቲ : ይህች ናት ይላል ::

2ኛ , ለሩቅ ወንዶች

እሙንቱ
. እሉ
. እሎንቱ
. እልክቱ : ለሚሉት : ውእቱ : ሳይሆን :
ውእቶሙ (ናቸው ) ይሆናል ::

3ኛ , ለሩቅ ሴቶች

. እማንቱ
. እላ
. እላንንቱ
. እልኩ
. እንትኩ :: ለሚለውም : ውእቱ ሳይሆን :

ውእቶን : (ናቸው ) ይላል ::

ስለዚህ

""ውእቱ "" : ከአሥሩ መደቦች ውስጥ

1. ለሩቅ ወንዶች
2. ለሩቅ ሴት እና
3. ለሩቅ ሴቶች : እንደማያገለግል : በጥንቃቄ ማስተዋሉ ጥሩ ነው ::

ይቀጥላል ::
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jul 24, 2010 3:05 pm

ሰላም ዘተዋሕዶ:-

ማስቸገር ባይሆንብኝ የዚህን ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰደ ጥቅስ ትክክለኛ ትርጉም ብትነግረኝ::

''አንተ ቀጥቀጥከ አርእስቲሁ ለከይሲ ወሀብኮሙ ሲሳዬሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ::''

ጥቅሱ ላይ ስህተት ካለም እግረመንገድህን እርማት ብትሰጥበት በቅድሚያ አመሰግናለሁ::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby እንሰት » Sun Jul 25, 2010 8:30 am

ሰላም መምሕራችን
ሶስት ቃላት ፍቺዎቻቸው አስቸግረውኝ ብቅ አልኩ

1. ሆድ በግእዝ እንግዳ ነው ወይስ ሌላ ቃል አለው?

2. ሰጠ በግእዝ መጠወ ነው ወይስ መጠወተ?

3. አወቀ በግእዝ አእመረ ነው ወይስ ለበወ:: ሁለቱም ከሆነ ልዩነታቸው ምን ላይ ነው?

በቅድሚያ አመስግናለሁ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ለተ...

Postby ዋኖስ » Mon Jul 26, 2010 8:13 pm

በቅድሚድሚያ የተጠያቂን እድል ላለመጋፋት ስል ጥቂቶቹን ልሞክር!

አእመረ- አወቀ= ትጉሃን አእመሩ መጻሕፍት እንዲል

ዖቀ=አወቀ- ኦ አኃዉየ ዑቁ ኢያስሕቱክሙ ባዕዳን- እንዲሉ

ለበወ- ልብ-አደረገ: አስተዋለ እንደማለት

አወፈየ= ሰጠ- እግዚእነ አወፈየ መራኁተ ለጴጥሮስ- እንደማለት

ጸገወ= ሰጠ- ጸገወኒ ጸጋ እግዚእየ- እንደማለት

መጠወ= ሰጠ- መጠወ አብ ወልዶ ዋሕደ ለሞት እንዲሉ

ቀሪዉን ለተጠያቂ....

ከመልካም አክብሮት ጋ

ዳሞት ከዳሞትእንሰት wrote:ሰላም መምሕራችን
ሶስት ቃላት ፍቺዎቻቸው አስቸግረውኝ ብቅ አልኩ

1. ሆድ በግእዝ እንግዳ ነው ወይስ ሌላ ቃል አለው?

2. ሰጠ በግእዝ መጠወ ነው ወይስ መጠወተ?

3. አወቀ በግእዝ አእመረ ነው ወይስ ለበወ:: ሁለቱም ከሆነ ልዩነታቸው ምን ላይ ነው?

በቅድሚያ አመስግናለሁ::
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዘ ተዋሕዶ » Wed Jul 28, 2010 5:57 am

መልሱን :
በመወያያ መድረኩ ላይ አቅርቤዋለሁ
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

Re: ለተ...

Postby እንሰት » Wed Jul 28, 2010 2:54 pm

እጅ ነስቻለሁ
ዋኖስ wrote:በቅድሚድሚያ የተጠያቂን እድል ላለመጋፋት ስል ጥቂቶቹን ልሞክር!

አእመረ- አወቀ= ትጉሃን አእመሩ መጻሕፍት እንዲል

ዖቀ=አወቀ- ኦ አኃዉየ ዑቁ ኢያስሕቱክሙ ባዕዳን- እንዲሉ

ለበወ- ልብ-አደረገ: አስተዋለ እንደማለት

አወፈየ= ሰጠ- እግዚእነ አወፈየ መራኁተ ለጴጥሮስ- እንደማለት

ጸገወ= ሰጠ- ጸገወኒ ጸጋ እግዚእየ- እንደማለት

መጠወ= ሰጠ- መጠወ አብ ወልዶ ዋሕደ ለሞት እንዲሉ

ቀሪዉን ለተጠያቂ....

ከመልካም አክብሮት ጋ

ዳሞት ከዳሞትእንሰት wrote:ሰላም መምሕራችን
ሶስት ቃላት ፍቺዎቻቸው አስቸግረውኝ ብቅ አልኩ

1. ሆድ በግእዝ እንግዳ ነው ወይስ ሌላ ቃል አለው?

2. ሰጠ በግእዝ መጠወ ነው ወይስ መጠወተ?

3. አወቀ በግእዝ አእመረ ነው ወይስ ለበወ:: ሁለቱም ከሆነ ልዩነታቸው ምን ላይ ነው?

በቅድሚያ አመስግናለሁ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Jul 31, 2010 8:50 pm

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ዘተዋሕዶ:-

ማስቸገር ባይሆንብኝ የዚህን ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰደ ጥቅስ ትክክለኛ ትርጉም ብትነግረኝ::

''አንተ ቀጥቀጥከ አርእስቲሁ ለከይሲ ወሀብኮሙ ሲሳዬሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ::''

ጥቅሱ ላይ ስህተት ካለም እግረመንገድህን እርማት ብትሰጥበት በቅድሚያ አመሰግናለሁ::

ምነው በዘመድ ነው እንዴ እዚህ ቤት መልስ የሚሰጠው?
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘ ተዋሕዶ » Mon Aug 02, 2010 4:33 am

ዘርዐይ ደረስ wrote:
ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ዘተዋሕዶ:-

ማስቸገር ባይሆንብኝ የዚህን ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰደ ጥቅስ ትክክለኛ ትርጉም ብትነግረኝ::

''አንተ ቀጥቀጥከ አርእስቲሁ ለከይሲ ወሀብኮሙ ሲሳዬሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ::''

ጥቅሱ ላይ ስህተት ካለም እግረመንገድህን እርማት ብትሰጥበት በቅድሚያ አመሰግናለሁ::

ምነው በዘመድ ነው እንዴ እዚህ ቤት መልስ የሚሰጠው?

መልሱን በመወያያው አምድ ይመልከቱ
ዘ ተዋሕዶ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 186
Joined: Wed Aug 23, 2006 9:18 pm

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest